TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። ማርኬቲንግ 📞 0979333111 @TikvahEthMarketingBot መረጃና መልዕክት ፦ 0998999899 ​@tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna

Username
@tikvahethiopia
Category
News and media
Country
Ethiopia
Created
, 9 years
Subscribers1,623,514+1,849 in 6 days
Avg views per post, 7d213,980−15.2% vs prev 7d
ERR13.18%last 7 days

Subscribers, 30 days

Sep 22 – Sep 28+1,849 (+0.1%)

Show as table
DateSubscribers
Sep 22, 20261,621,665
Sep 23, 20261,622,007
Sep 24, 20261,622,577
Sep 25, 20261,622,983
Sep 26, 20261,623,420
Sep 27, 20261,623,359
Sep 28, 20261,623,514

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Sep 20, 2026256,217
Sep 21, 2026259,043
Sep 22, 2026288,180
Sep 23, 2026280,041
Sep 24, 2026227,950
Sep 25, 2026261,489
Sep 26, 2026226,092
Sep 27, 202688,330
Sep 28, 202637,868

Most viewed this month

  1. 01

    የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና ዝውውር በአንድ ወጥ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲፈጸም አቅጣጫ ሰጠ። ሚኒስቴሩ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በተመሳሳይ የአሠራር መርህ እንዲስተናገዱ በማስቀመጠው ሰርኩላር፣ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ሂደቶችን በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት ብቻ እንዲያከናውኑ አሳስቧል። 1. የተማሪዎች ቅበላ በሰርኩላሩ መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር በይፋ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች የምደባ መረጃና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ካጣሩ በኋላ በወቅቱ መቀበልና መመዝገብ አለባቸው። ዩኒቨርሲቲዎች ከሚኒስቴሩ ከተላለፈው የምደባ ውጤት ውጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ተማሪ መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደሌለባቸውም ተገልጿል። የመግቢያ ፈተና እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ተቋማትም ቅበላውን በተቀመጠው መስፈርትና ግልጽ በሆነ የውጤት አያያዝ ሥርዓት ማከናወን ይኖርባቸዋል። 2. የትምህርት መስክ ምደባ የትምህርት መስክ ምደባ ሲከናወን የሀገሪቱን የሰው ኃይል ፍላጎት፣ በኢኮኖሚ ሽግግሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መስኮች፣ የተማሪውን ውጤትና ምርጫ እንዲሁም የተቋሙን የቅበላ አቅም ታሳቢ እንዲደረግ ተደንግጓል። ምደባውም በግልጽ፣ ቀድሞ በሚታወቅና ለሁሉም ተማሪዎች በወጥነት በሚተገበር መስፈርት መፈጸም እንዳለበት ሰርኩላሩ ያስቀምጣል። በምደባው ወቅት ፦ - የተማሪው የመጀመሪያ ዓመት ወይም የዓመቱ አማካይ ውጤት፣ - የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት፣ - የተማሪው ምርጫ፣ - የትምህርት መስኩ የቅበላ አቅም፣ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ በተቋሙ የሚሰጥ የመግቢያ ፈተና ታሳቢ እንዲደረጉ ተገልጿል። ተቋሙ የትምህርት መስክ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ፣ የመጀመሪያ ዓመት አማካይ ውጤት 50 በመቶ፣ የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እና የመስክ መግቢያ ፈተና 30 በመቶ እንዲያዝ ተቀምጧል። መግቢያ ፈተና በማይሰጥበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ዓመት ለሚከናወን ምደባ የዓመቱ አማካይ ውጤት 70 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 30 በመቶ እንዲያዝ ተገልጿል። በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ለሚከናወን ምደባ ደግሞ የዓመቱ አማካይ ውጤት 80 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እንዲያዝ ተደንግጓል። በተጨማሪም ለሴት ተማሪዎች፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ለሌሎች ተገቢ የሆነ እዎንታዊ ድጋፍ በወጥነት እንዲተገበር ተመላክቷል። ለሴትና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በምደባ ወቅት በውጤታቸው ላይ 5 ነጥብ ተጨምሮ እንዲወዳደሩ የሚያደርግ አሠራርም ተቀምጧል። ዩኒቨርሲቲዎች ከተቀመጠው መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ ወይም በልዩ ትዕዛዝ የትምህርት መስክ ምደባን መቀየር እንደሌለባቸውም ሚኒስቴሩ አስቀምጧል። 3. የተማሪዎች ዝውውር ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ የሚደረግ የተማሪ ዝውውር የሚፈጸመው የላኪውና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። ዝውውሩ ከተፈጸመም በኋላ ትምህርት ሚኒስቴሩ በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት። የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስተር ከተማረ እና ከፕሮግራሙ ከ50 በመቶ በላይ ካልጨረሰ እንደሆነ ሰርኩላሩ ይገልጻል። ተማሪው የአካዳሚክ ጉድለት (F፣ NG ወይም I) የሌለበት፣ አማካይ ውጤቱ 2.00 እና ከዚያ በላይ የሆነ እና የዲሲፕሊን ጥፋት ያልፈጸመ መሆን አለበት። በደኅንነት ስጋት፣ በጤና ችግር ወይም በሌላ ተመሳሳይ ልዩ ሁኔታ የሚቀርብ የዝውውር ጥያቄም በሕጋዊና በተረጋገጠ ማስረጃ መደገፍ እንዳለበት ተገልጿል። በተጨማሪም ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር የሚፈቀድ ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር እንደማይፈቀድ ተቀምጧል። ዝውውር በአንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች መካከል፣ ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ወይም ከአንድ ፕሮግራም ወደ ሌላ ፕሮግራም ሊፈጸም እንደሚችልም ሰነዱ ያስቀምጣል። በተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሠራሽ አደጋ፣ በደኅንነት ችግር ወይም በሌላ ልዩ ሁኔታ ከመደበኛው የዝውውር አቅም በላይ የሆነ የቡድን ዝውውር የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ውሳኔ ከመፈጸም ይልቅ ጉዳዩን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲፈጽሙ ታዘዋል። 4. ቅሬታዎችና ግልጽነት ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች የሚቀርቡ የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ቅሬታዎችን የሚቀበል፣ የሚመረምርና በወቅቱ ምላሽ የሚሰጥ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት እንዲኖራቸው ተብሏል። የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ውሳኔዎችም በግልጽ መስፈርት፣ በተሟላ ማስረጃና በሰነድ የተደገፉ መሆን እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በመጨረሻም ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሰርኩላሩ ጋር የሚቃረን የተለየ አሠራር እንዳይከተሉ፣ በተማሪዎች ቅበላ፣ በትምህርት መስክ ምደባና በዝውውር ወቅት የተቀመጡትን መስፈርቶች በወጥነት እንዲፈጽሙ ተመላክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Photoalbum
    Views324K
    Forwards1.07K
    Reactions—
    Comments—
  2. 02
    Views318K
    Forwards1.15K
    Reactions—
    Comments—
  3. 03

    ‎" ግለሰቡ ' ተሰድቤያለሁ ሰው እገድላለሁ ፤ እኔም እራሴን አጠፋለሁ ' በሚል ' ቤተሰቦቼ የሚያለቅሱበትን የሀዘን መግለጫ ባነር ነው ያሰራሁት ' ነው ያለን " - የሰሜን ቤንች ፖሊስ አዛዥ ‎ ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሼኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዳ በተባለ አካባቢ የራሱን " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " የሚል የሐዘን መግለጫ ባነር በማሰራት፣ የተቀየመውን ሰው ገድሎ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሺካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ኢንስፔክተር ዘለቀ እንደገለፁት ድርጊቱን የፈጸመው አቶ ማሌች ሚቲኩ ገተራሻ የተባለ የ31 ዓመት አባወራ እና የሁለት ልጆች አባት ነው። አቶ ማልች ከተጣላው አካል ጋር በነበረው አለመግባባት ግለሰቡ " ሟርተኛ " ሲል ሰድቦኛል በሚል በትናንትናው ዕለት መስከረም 12/2019 ዓ/ም በቂም በቀል ተነሳስቶ ግለሰቡን ለመግደልና እራሱንም ለማጥፋት አቅዶ ለዚሁ እቅዱ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ የራሱን የሐዘን መግለጫ ባነር በቅድሚያ አሳትሞ በማምጣት በዕለቱ መጠጥ እየጠጣና በማስፈራሪያዎች ሲፎክር ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዙን ገልፀዋል። ‎ ‎ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ " ባነሩን ያዘጋጀሁት ቤተሰቦቼ እኔን እያሰቡ እንዲያለቅሱበት ነው " በሚል ለፖሊስ ቃሉን መስጠቱን ያነሱት ​የፖሊስ አዛዡ ድርጊቱ በአካባቢው አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን በሚዲያ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ‎ ‎​በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ በሕግ አሰራር መሠረት የሚኖረውን ቀጣይ አካሄድ ከሚመለከታቸው የሕግ አካላት ጋር እየተመረመረ ይገኛል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Photoalbum
    Views315K
    Forwards633
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    No text

    Photoalbum
    Views314K
    Forwards1.11K
    Reactions388
    Comments—
  5. 05

    No text

    Photoalbum
    Views313K
    Forwards18
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#108221Photoalbumedited

#Oromia #ሹመት ዶ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ። ዶ/ር ቶላ በሪሶ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነዋል። ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ ደግሞ የጤና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የጨፌ ስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ሹመትን አጽድቋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡- 1. አብዱረህማን አብደላ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 2. አቶ መስፍን መላኩ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 3. ዶ/ር ረሻድ ከማል - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 4. ዶ/ር መንግስቱ በቀለ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 5. አቶ አህመድ ኢድሪስ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 6. አቶ አህመድ ሃጂ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ይህ  የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ አዲስ በጸደቀው አዋጅ 267/2019 መሰረት ያደረገ ነው፡፡ 7. ዶ/ር ቶላ በሪሶ - የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ 8. አቶ ጉዮ ዋሪዮ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ 9. ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ- የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ ተስፋዬ ቱሉ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 11. ዶ/ር አብዲ ዩያ - የእቅድና ልማት ቢሮ ኃላፊ 12.  ዶ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ 13.  ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ- የጤና ቢሮ ኃላፊ 14.  አቶ ተሾመ ቦጋለ - የግብርና ቢሮ ኃላፊ 15.  ዶ/ር ነመራ ገበየሁ - የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ታረቀኝ ቡልልታ - የኢንተርፕራይዝና አንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 17. ዶ/ር አደሬ አሰፋ - የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 18. ወ/ሮ መሰረት አሰፋ - የመሬት ቢሮ ኃላፊ 19. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን - የሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ 20. አቶ ጥላሁን ወርቁ - የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ 21. ዶ/ር አያንቱ ጉተታ - የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 22. ወ/ሮ እልዳና ሱሌማን - የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 23. አቶ ቲጃኒ ናስር - የሰላም ቢሮ ኃላፊ 24. ወ/ሮ ሮዛ ቢያ - የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 25. ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ - የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ 26. ኢንጂነር ሃቢብ ቁምቢ - የመንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ 27. ኢንጂነር ማሪያ ጉታ - የውሃ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሹመዋል፡፡ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Open in Telegram
Views46,722−78%vs avg
Forwards68
Reactions—
Comments—
#108220Photoalbum
Views46,415−79%vs avg
Forwards68
Reactions—
Comments—
#108219Photoalbum
Views43,067−80%vs avg
Forwards68
Reactions485
Comments—
#108218Photo

#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በጥራትም:በብራንድም:በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ  የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ በፈለጉት ስክሬን መጠን ፣ ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን። ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፌት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://t.me/samcomptech

Open in Telegram
Views42,660−80%vs avg
Forwards0
Reactions21
Comments—
#108217Photo

ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በማስተርስ መርሃ ግብር ለመማር ፍላጎት ላላቹ በሙሉ ? 📚 ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሙሉ እውቅና ያለው ሲሆን፣ የዳግም ምዝገባውን በETA በተሳካ ሁኔታ ካለፉ ጥቂት ተቋማት መካከል አንዱ ነው። በ2019 ዓ.ም. የማስተርስ ትምህርታቸውን በሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ተመዝግበው ለሚማሩ ተማሪዎች:- ✈️ የውጭ ሀገር የምርምር ጉዞ ዕድሎች ይመቻቻሉ። 👨‍🏫 በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ፕሮፌሰሮች ትምህርት ይሰጣል። 🏫 በአዲስ አበባ 22 አካባቢ — ከካፒታል ሆቴል ጀርባ — ለመማር አመቺ በሆነ ካምፓስ ትምህርት ይሰጣል። 🎓 በሁለት ዓመት የትምህርት ቆይታ ውስጥ ሁለት ነፃ አጫጭር ስልጠናዎች በእውቅና ባላቸው ፕሮፌሰሮች ይሰጣሉ። 📌 ለበለጠ መረጃ፦ 🌐 www.marylandic.com📱 0935656939 / 0958310704

Open in Telegram
Views41,650−81%vs avg
Forwards0
Reactions35
Comments—
#108215Photoalbumedited

#NewsAlert አቶ ሽመልስ አብዲሳን በድጋሚ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሾሙ። የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን የ2019 ዓመት የመጀመሪያ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ በጉባዔው አቶ ሽመልስ አብዲሳን በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Open in Telegram
Views22,287−90%vs avg
Forwards12
Reactions—
Comments—
#108214Photoalbum
Views22,273−90%vs avg
Forwards13
Reactions587
Comments—
#108213File

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል። ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦ - ጀማሪ መምህር፣ - መለስተኛ መምህር፣ - መምህር፣ - ከፍተኛ መምህር፣ - ተባባሪ መሪ መምህር፣ - መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው። በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው። ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል። መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Open in Telegram
Views35,257−84%vs avg
Forwards170
Reactions258
Comments—
#108212Photoalbum

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል። በተጨማሪም፦ 👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር። 👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር። 👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር። 👉 ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር። የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል። በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል። ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል። የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Open in Telegram
Views32,191−85%vs avg
Forwards204
Reactions—
Comments—
#108211Photoalbum
Views31,190−86%vs avg
Forwards204
Reactions—
Comments—

All posts

Connections