TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። ማርኬቲንግ 📞 0979333111 @TikvahEthMarketingBot መረጃና መልዕክት ፦ 0998999899 ​@tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna

Юзернейм
@tikvahethiopia
Категория
Новости и СМИ
Страна
Эфиопия
Создан
, 9 лет
Подписчики1 623 514+1 849 за 6 дней
Просмотров на пост, 7 дн.226 625−11% к пред. 7 дн.
ERR13,96 %за 7 дней

Подписчики, 30 дней

22 сент. – 28 сент.+1 849 (+0,1%)

Показать таблицей
ДатаПодписчики
22 сент. 2026 г.1 621 665
23 сент. 2026 г.1 622 007
24 сент. 2026 г.1 622 577
25 сент. 2026 г.1 622 983
26 сент. 2026 г.1 623 420
27 сент. 2026 г.1 623 359
28 сент. 2026 г.1 623 514

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
20 сент. 2026 г.256 217
21 сент. 2026 г.259 043
22 сент. 2026 г.288 180
23 сент. 2026 г.280 041
24 сент. 2026 г.227 950
25 сент. 2026 г.269 391
26 сент. 2026 г.249 870
27 сент. 2026 г.188 451
28 сент. 2026 г.75 465

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና ዝውውር በአንድ ወጥ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት ባለው አሠራር እንዲፈጸም አቅጣጫ ሰጠ። ሚኒስቴሩ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በተመሳሳይ የአሠራር መርህ እንዲስተናገዱ በማስቀመጠው ሰርኩላር፣ ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ሂደቶችን በተቀመጡ መስፈርቶች መሠረት ብቻ እንዲያከናውኑ አሳስቧል። 1. የተማሪዎች ቅበላ በሰርኩላሩ መሠረት ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር በይፋ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች የምደባ መረጃና አስፈላጊ ማስረጃዎችን ካጣሩ በኋላ በወቅቱ መቀበልና መመዝገብ አለባቸው። ዩኒቨርሲቲዎች ከሚኒስቴሩ ከተላለፈው የምደባ ውጤት ውጭ በራሳቸው ተነሳሽነት ተማሪ መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደሌለባቸውም ተገልጿል። የመግቢያ ፈተና እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ተቋማትም ቅበላውን በተቀመጠው መስፈርትና ግልጽ በሆነ የውጤት አያያዝ ሥርዓት ማከናወን ይኖርባቸዋል። 2. የትምህርት መስክ ምደባ የትምህርት መስክ ምደባ ሲከናወን የሀገሪቱን የሰው ኃይል ፍላጎት፣ በኢኮኖሚ ሽግግሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መስኮች፣ የተማሪውን ውጤትና ምርጫ እንዲሁም የተቋሙን የቅበላ አቅም ታሳቢ እንዲደረግ ተደንግጓል። ምደባውም በግልጽ፣ ቀድሞ በሚታወቅና ለሁሉም ተማሪዎች በወጥነት በሚተገበር መስፈርት መፈጸም እንዳለበት ሰርኩላሩ ያስቀምጣል። በምደባው ወቅት ፦ - የተማሪው የመጀመሪያ ዓመት ወይም የዓመቱ አማካይ ውጤት፣ - የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት፣ - የተማሪው ምርጫ፣ - የትምህርት መስኩ የቅበላ አቅም፣ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ በተቋሙ የሚሰጥ የመግቢያ ፈተና ታሳቢ እንዲደረጉ ተገልጿል። ተቋሙ የትምህርት መስክ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ከሆነ፣ የመጀመሪያ ዓመት አማካይ ውጤት 50 በመቶ፣ የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እና የመስክ መግቢያ ፈተና 30 በመቶ እንዲያዝ ተቀምጧል። መግቢያ ፈተና በማይሰጥበት ጊዜ፣ በመጀመሪያው ዓመት ለሚከናወን ምደባ የዓመቱ አማካይ ውጤት 70 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 30 በመቶ እንዲያዝ ተገልጿል። በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ለሚከናወን ምደባ ደግሞ የዓመቱ አማካይ ውጤት 80 በመቶ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት 20 በመቶ እንዲያዝ ተደንግጓል። በተጨማሪም ለሴት ተማሪዎች፣ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ለሌሎች ተገቢ የሆነ እዎንታዊ ድጋፍ በወጥነት እንዲተገበር ተመላክቷል። ለሴትና ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በምደባ ወቅት በውጤታቸው ላይ 5 ነጥብ ተጨምሮ እንዲወዳደሩ የሚያደርግ አሠራርም ተቀምጧል። ዩኒቨርሲቲዎች ከተቀመጠው መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ ወይም በልዩ ትዕዛዝ የትምህርት መስክ ምደባን መቀየር እንደሌለባቸውም ሚኒስቴሩ አስቀምጧል። 3. የተማሪዎች ዝውውር ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ የሚደረግ የተማሪ ዝውውር የሚፈጸመው የላኪውና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። ዝውውሩ ከተፈጸመም በኋላ ትምህርት ሚኒስቴሩ በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት። የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስተር ከተማረ እና ከፕሮግራሙ ከ50 በመቶ በላይ ካልጨረሰ እንደሆነ ሰርኩላሩ ይገልጻል። ተማሪው የአካዳሚክ ጉድለት (F፣ NG ወይም I) የሌለበት፣ አማካይ ውጤቱ 2.00 እና ከዚያ በላይ የሆነ እና የዲሲፕሊን ጥፋት ያልፈጸመ መሆን አለበት። በደኅንነት ስጋት፣ በጤና ችግር ወይም በሌላ ተመሳሳይ ልዩ ሁኔታ የሚቀርብ የዝውውር ጥያቄም በሕጋዊና በተረጋገጠ ማስረጃ መደገፍ እንዳለበት ተገልጿል። በተጨማሪም ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር የሚፈቀድ ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር እንደማይፈቀድ ተቀምጧል። ዝውውር በአንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች መካከል፣ ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ወይም ከአንድ ፕሮግራም ወደ ሌላ ፕሮግራም ሊፈጸም እንደሚችልም ሰነዱ ያስቀምጣል። በተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሠራሽ አደጋ፣ በደኅንነት ችግር ወይም በሌላ ልዩ ሁኔታ ከመደበኛው የዝውውር አቅም በላይ የሆነ የቡድን ዝውውር የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ውሳኔ ከመፈጸም ይልቅ ጉዳዩን ለትምህርት ሚኒስቴር በማቅረብ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት እንዲፈጽሙ ታዘዋል። 4. ቅሬታዎችና ግልጽነት ዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች የሚቀርቡ የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ቅሬታዎችን የሚቀበል፣ የሚመረምርና በወቅቱ ምላሽ የሚሰጥ ግልጽ የአሠራር ሥርዓት እንዲኖራቸው ተብሏል። የቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባና የዝውውር ውሳኔዎችም በግልጽ መስፈርት፣ በተሟላ ማስረጃና በሰነድ የተደገፉ መሆን እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በመጨረሻም ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከሰርኩላሩ ጋር የሚቃረን የተለየ አሠራር እንዳይከተሉ፣ በተማሪዎች ቅበላ፣ በትምህርት መስክ ምደባና በዝውውር ወቅት የተቀመጡትን መስፈርቶች በወጥነት እንዲፈጽሙ ተመላክቷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Фотоальбом
    Просмотры324 тыс.
    Пересылки1,07 тыс.
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры318 тыс.
    Пересылки1,15 тыс.
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры315 тыс.
    Пересылки1,92 тыс.
    Реакции157
    Комментарии—
  4. 04

    ‎" ግለሰቡ ' ተሰድቤያለሁ ሰው እገድላለሁ ፤ እኔም እራሴን አጠፋለሁ ' በሚል ' ቤተሰቦቼ የሚያለቅሱበትን የሀዘን መግለጫ ባነር ነው ያሰራሁት ' ነው ያለን " - የሰሜን ቤንች ፖሊስ አዛዥ ‎ ‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሼኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዳ በተባለ አካባቢ የራሱን " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " የሚል የሐዘን መግለጫ ባነር በማሰራት፣ የተቀየመውን ሰው ገድሎ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሺካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎ኢንስፔክተር ዘለቀ እንደገለፁት ድርጊቱን የፈጸመው አቶ ማሌች ሚቲኩ ገተራሻ የተባለ የ31 ዓመት አባወራ እና የሁለት ልጆች አባት ነው። አቶ ማልች ከተጣላው አካል ጋር በነበረው አለመግባባት ግለሰቡ " ሟርተኛ " ሲል ሰድቦኛል በሚል በትናንትናው ዕለት መስከረም 12/2019 ዓ/ም በቂም በቀል ተነሳስቶ ግለሰቡን ለመግደልና እራሱንም ለማጥፋት አቅዶ ለዚሁ እቅዱ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ የራሱን የሐዘን መግለጫ ባነር በቅድሚያ አሳትሞ በማምጣት በዕለቱ መጠጥ እየጠጣና በማስፈራሪያዎች ሲፎክር ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዙን ገልፀዋል። ‎ ‎ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ " ባነሩን ያዘጋጀሁት ቤተሰቦቼ እኔን እያሰቡ እንዲያለቅሱበት ነው " በሚል ለፖሊስ ቃሉን መስጠቱን ያነሱት ​የፖሊስ አዛዡ ድርጊቱ በአካባቢው አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን በሚዲያ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ‎ ‎​በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ በሕግ አሰራር መሠረት የሚኖረውን ቀጣይ አካሄድ ከሚመለከታቸው የሕግ አካላት ጋር እየተመረመረ ይገኛል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

    Фотоальбом
    Просмотры315 тыс.
    Пересылки633
    Реакции—
    Комментарии—
  5. 05

    Без текста

    Фотоальбом
    Просмотры314 тыс.
    Пересылки1,11 тыс.
    Реакции388
    Комментарии—

Новые посты

#108238Фотоальбомизменён

የኦሮሚያ ክልል ስድስት ዞኖች ብቻ እንዲኖሩት የሚያደርግ አዲስ አደረጃጀት የተካተተበት አዋጅ በጨፌ ኦሮሚያ ጸደቀ። በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ላይ ዛሬ የጸደቀው አዋጅ፤ ለዞኖች " ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ማዕቀፍ እና የመወሰን ስልጣን የሰጠ ነው " ተብሏል። በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ " የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች፤ የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን " የወጣ እንደሆነ ተገልጿል። እስከ ዛሬ በስራ ላይ የቆየው የክልሉ አደረጃጀት፤ የኦሮሚያ ክልልን በ21 ዞኖች ያዋቀረ ነበር። አዲሱ አደረጃጀት ግን የኦሮሚያ ክልልን በአቅጣጫ ላይ በተመሰረቱ ዞኖች መልሶ የሚያዋቅር ይሆናል። በዚህ መሰረት አዳዲሶቹ ስድስት ዞኖች፤ ፦ - ምስራቅ፣ - ምዕራብ፣ - ማዕከላዊ፣ - ደቡብ፣ - ደቡብ ምዕራብ - ደቡብ ምስራቅ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። ይህን አደረጃጀት ስለያዘው አዋጅ ለጨፌ ኦሮሚያ አባላት ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ፤ የህግ ረቂቁ " በክልሉ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ሪፎርሞችን ለማስቀጠል " የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል። በኦሮሚያ የሚሰጡ አገልግሎቶች ወደ ታችኛው መዋቅር "እየወረዱ" መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጉዮ፤ የዞኖቹ አወቃቀር " ለአደረጃጀት፣ ቁጥጥር እና ክትትል የሚያመች " መሆኑን ተናግረዋል።  አዲሱ አዋጅ በስድስቱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ መስሪያ ቤቶችን ምንነት በግልጽ ያስቀመጠ መሆኑም ተገልጿል። " ለዞኖች ከፍተኛ የመወሰን ስልጣንን ይሰጣል" የተባለለት ይህ አዋጅ፤ የክልሉ መንግስት የሚገነባውን ስርዓት "በህግ የተጠናከረ እንዲሆን ያደርጋል " ተብሏል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድርገጽ ነው። www.EthiopiaInsider.com መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @Tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры45 303−80%к среднему
Пересылки35
Реакции—
Комментарии—
#108237Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры41 304−82%к среднему
Пересылки35
Реакции385
Комментарии—
#108236Фотоальбомизменён

" በተወሰደው ድንገተኛ እምርጃ ተቸግረናል " - የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ዜጎች ሰሞኑን ከተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም ለሊት ጀምሮ በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች በጅምላ ታግደዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ዜጎች ገንዘባቸውን አውጥተው መጠቀም፣ መገልገል አልቻሉም። በርካታ ዜጎችም እየተጉላሉ ይገኛሉ። መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ዜጎች፤  ምክንያቱ እንኳን ሳይነገር ለምን እንዲህ ያለው እርምጃ እንደተወሰደ እንዳልገባቸእ፣ በድንገተኛው እገዳ በጣም መቸገራቸውን ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበርም ችግር ገጥሟቸው እንደነበር ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በምን ምክንያት እገዳ እንደተጣለ ለህዝብ ወጥቶ ያስረዳ አንድም አካል የለም። አሁን ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ባንክ በአዲስ አበባ ያሉ ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሒሳብ ለማንቀሳቀስ ማመልከቻ እንዲያስገቡ እያደረገ ነው። ለደምበኞች መፍትሄ ለመስጠት በሚል 13 ቅርንጫፎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል። እነዚህም ፦ • አዲስ አበባ ቅርንጫፍ • አቃቂ • ተክለሃይማኖት • ንፋስ ስልክ • ሾቤ አያት • ስድስት ኪሎ • ሲኤምሲ (CMC) • ተፈራ ደግፌ • መሪ • ጠመንጃ ያዥ • ቴሌ መድኃኔዓለም • ጦር ኃይሎች ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጎ ነበር። በዚህም በርካታ በትግራይ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከፍተው የታገደባቸው ዜጎች ለማስለቀቅ ለበርካታ ሰዓታ ረጅም ሰልፍ ይዘው ታዝቧል። ከጥዋት ጀምረው የተሰለፉ በርካታ ዜጎችንም አግኝቷል። በተመለከትናቸው የባንኩ ቅርንጫፎች የሒሳብ ባለቤቶች (የሒሳቡ ሕጋዊ ወኪል) ወደ ተጠቀሱት ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ማንነታቸውን፣ ፊርማቸውንና አስፈላጊውን መረጃ ካረጋገጡ በኋላ የታገደውን ሒሳባቸውን ወደ አዲሶቹ ቅርንጫፎች የማዛወርና የማንቀሳቀስ ቅጽ እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል። ነገር ግን የሂሳብ ቁጥሮቹ መንቀሳቀስ የሚጀምሩት አስፈላጊውን የማረጋገጥ ስራ ከተሰራ በኋላ መሆኑ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደንበኞችን በማስተናገድ ላይ ከሚገኙት የንግድ ባንክ ሰራተኞች አንዱን አናግሯል። ይኸው ሰራተኛ " ተገልጋዮቹ  የፋይዳ መታወቂያቸውን ኮፒ በመያዝ በአካል ባመለከቱበት በ24 ሰዓታት ወስጥ የታገደው የባንክ ሂሳባቸው ይለቀቃል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን የባንክ ሒሳቦች እንደታገዱ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይሰራል። በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አፋር እንዲሁም አማራ ክልሎች ዳግም ባገረሸው ጦርነት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸው ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስረከም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры57 400−75%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108235Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры57 403−75%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108234Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры53 391−77%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108233Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры53 389−77%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108232Видеоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры52 386−77%к среднему
Пересылки69
Реакции347
Комментарии—
#108227Фотоальбомизменён

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተሾሙ። የከተማ እና መሰረተ ልማት ማኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ጫልቱ ቀደም ሲል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን ዶ/ር ረሻድ ከማልን ይተካሉ ። ዶ/ር ረሻድ ከማል ዛሬ ይፋ በተደረገው የኦሮሚያ ክልል የአስፈጻሚዎች አደረጃጀት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ተሹመዋል። ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ላለፉት አራት ዓመታት ገደማ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры39 494−83%к среднему
Пересылки68
Реакции—
Комментарии—
#108226Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры39 498−83%к среднему
Пересылки68
Реакции473
Комментарии—
#108225Фотоальбом

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል። @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры38 521−83%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи