Посты канала TIKVAH-ETHIOPIA

сначала новые

#108245Видеоальбомизменён

#Tickets የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዓመታት በኋል በደጋፊዎቹ ፊት ከሴኔጋል ጋር በባህር ዳር ስታዲየም በነገው ዕለት ጨዋታውን ያካሂዳል። የጨዋታው የመግቢያ ትኬት ሽያጭ በኦንላይን እንዲሁም በአካል እየተካሄደ ነው። ደጋፊዎች eff-tickets.com በመጠቀም ትኬታቸውን በኦንላይን መግዛት ይችላሉ ተብሏል። በአካል ደግሞ በአዝዋ ሆቴል በኩል በሚገኘው የመግቢያ በር በኩል መግዛት ይቻላል። የትኬቱ ዋጋ እንደደረጃው 500፣ 200 እና 100 ብር ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры14 663−93%к среднему
Пересылки10
Реакции—
Комментарии—
#108244Видеоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры14 662−93%к среднему
Пересылки0
Реакции142
Комментарии—
#108243Фото

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ግጭት ካለበት የትግራይ ክልል 161 ሰዎችን ወደ ሌላ ሥፍራ ማዘዋወሩን አስታውቋል። ዛሬ ሰኞ መስከረም 18/2019  ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ክልል ካስወጣቸው መካከል ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ - የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ሠራተኞች፣ - የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አባላት ይገኙበታል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ 161ዱን ሰዎች ከትግራይ ያዘዋወረው " ሁሉም የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ባቀረቡት ጥያቄ እና በሰጡት ይሁንታ መሠረት፣ የገለልተኛ ሚና በመወጣት " እንደሆነ መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры2 026−99%к среднему
Пересылки0
Реакции2
Комментарии—
#108242Фотоальбом

የሰውን እንቅስቃሴ እየተመለከቱ  ምራቅ እየተፉ " ልጠርግልህ " በማለት በተለምዶ " ትፍታ " የሚባለውን  የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ አንዳንድ ግለሰቦች ስላሉ በንብረታችሁ ላይ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል። ነገሩ እንዲህ ነው .... ተጠርጣሪዎቹ ፦ - አብዱልራዛቅ አገዢ፣ - ግዜያለሁ ተሻገር፣ - ይተያሁ ምንተስኖት እና አብዲ መሐመድ ይባላሉ። የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ/ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረደ 7 ልዩ ቦታው " ግዮን መድኃኒት ቤት " አካባቢ ከቀኑ 6:00 ሠዓት ገደማ ነው ። በዕለቱ አንድ የቻይና ዜጋ ከቸርችል ወደ መስቀል አደባባይ በእግራቸው እየተንቀሳቀሱ ነበር። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አብዱልራዛቅ አገዢ የተባለው ወደ ግለሰቡ ቀርቦ ምራቅ ይተፋበታል። በመቀጠልም " ቆይ ልጠርግልህ " በማለት ከለበሰው ጃኬት ውስጥ የዋጋ ግምቱ 360 ሺህ የሚያወጣ Iphone Pro Max 17 ሞባይል ይዞ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር የሠሌዳ ቁጥሩ ባልታወቀ ቪትስ ተሽከርካሪ ከአካባቢው ይሰወራሉ። የግል ተበዳይ የተፈጸመባቸውን ወንጀል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የለገሃር አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ያመለክታሉ። ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ክትትል አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ውስጥ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B83359 አ/አ በሆነ ቪትስ ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ሞባይሉን ለማስመለስ በተከናወነ የምርመራ ተግባር  አብዱልራዘቅ አገዢ ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ላይ በተደረገ ፍተሻ ንብረቱን በምሪት ማስመለስ ችሏል። ሰው ላይ ምራቅ በተመትፋትና " ልጥረግልህ/ልጥረግልሽ " በማለት የስርቆት ወንጀል የሚፈጽሙ ስላሉ ተጠንቀቁ። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры41 336−81%к среднему
Пересылки113
Реакции—
Комментарии—
#108241Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры41 286−82%к среднему
Пересылки113
Реакции568
Комментарии—
#108238Фотоальбомизменён

የኦሮሚያ ክልል ስድስት ዞኖች ብቻ እንዲኖሩት የሚያደርግ አዲስ አደረጃጀት የተካተተበት አዋጅ በጨፌ ኦሮሚያ ጸደቀ። በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ላይ ዛሬ የጸደቀው አዋጅ፤ ለዞኖች " ለመጀመሪያ ጊዜ የህግ ማዕቀፍ እና የመወሰን ስልጣን የሰጠ ነው " ተብሏል። በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ " የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች፤ የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን " የወጣ እንደሆነ ተገልጿል። እስከ ዛሬ በስራ ላይ የቆየው የክልሉ አደረጃጀት፤ የኦሮሚያ ክልልን በ21 ዞኖች ያዋቀረ ነበር። አዲሱ አደረጃጀት ግን የኦሮሚያ ክልልን በአቅጣጫ ላይ በተመሰረቱ ዞኖች መልሶ የሚያዋቅር ይሆናል። በዚህ መሰረት አዳዲሶቹ ስድስት ዞኖች፤ ፦ - ምስራቅ፣ - ምዕራብ፣ - ማዕከላዊ፣ - ደቡብ፣ - ደቡብ ምዕራብ - ደቡብ ምስራቅ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። ይህን አደረጃጀት ስለያዘው አዋጅ ለጨፌ ኦሮሚያ አባላት ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉዮ ዋሪዮ፤ የህግ ረቂቁ " በክልሉ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ሪፎርሞችን ለማስቀጠል " የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል። በኦሮሚያ የሚሰጡ አገልግሎቶች ወደ ታችኛው መዋቅር "እየወረዱ" መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጉዮ፤ የዞኖቹ አወቃቀር " ለአደረጃጀት፣ ቁጥጥር እና ክትትል የሚያመች " መሆኑን ተናግረዋል።  አዲሱ አዋጅ በስድስቱ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ መስሪያ ቤቶችን ምንነት በግልጽ ያስቀመጠ መሆኑም ተገልጿል። " ለዞኖች ከፍተኛ የመወሰን ስልጣንን ይሰጣል" የተባለለት ይህ አዋጅ፤ የክልሉ መንግስት የሚገነባውን ስርዓት "በህግ የተጠናከረ እንዲሆን ያደርጋል " ተብሏል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድርገጽ ነው። www.EthiopiaInsider.com መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @Tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры45 303−80%к среднему
Пересылки35
Реакции—
Комментарии—
#108237Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры41 304−82%к среднему
Пересылки35
Реакции385
Комментарии—
#108236Фотоальбомизменён

" በተወሰደው ድንገተኛ እምርጃ ተቸግረናል " - የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው ዜጎች ሰሞኑን ከተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም ለሊት ጀምሮ በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች በጅምላ ታግደዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ዜጎች ገንዘባቸውን አውጥተው መጠቀም፣ መገልገል አልቻሉም። በርካታ ዜጎችም እየተጉላሉ ይገኛሉ። መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ዜጎች፤  ምክንያቱ እንኳን ሳይነገር ለምን እንዲህ ያለው እርምጃ እንደተወሰደ እንዳልገባቸእ፣ በድንገተኛው እገዳ በጣም መቸገራቸውን ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበርም ችግር ገጥሟቸው እንደነበር ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በምን ምክንያት እገዳ እንደተጣለ ለህዝብ ወጥቶ ያስረዳ አንድም አካል የለም። አሁን ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ባንክ በአዲስ አበባ ያሉ ደንበኞቹ የታገደባቸውን ሒሳብ ለማንቀሳቀስ ማመልከቻ እንዲያስገቡ እያደረገ ነው። ለደምበኞች መፍትሄ ለመስጠት በሚል 13 ቅርንጫፎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል። እነዚህም ፦ • አዲስ አበባ ቅርንጫፍ • አቃቂ • ተክለሃይማኖት • ንፋስ ስልክ • ሾቤ አያት • ስድስት ኪሎ • ሲኤምሲ (CMC) • ተፈራ ደግፌ • መሪ • ጠመንጃ ያዥ • ቴሌ መድኃኔዓለም • ጦር ኃይሎች ናቸው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ተዘዋውሮ ምልከታ አድርጎ ነበር። በዚህም በርካታ በትግራይ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ከፍተው የታገደባቸው ዜጎች ለማስለቀቅ ለበርካታ ሰዓታ ረጅም ሰልፍ ይዘው ታዝቧል። ከጥዋት ጀምረው የተሰለፉ በርካታ ዜጎችንም አግኝቷል። በተመለከትናቸው የባንኩ ቅርንጫፎች የሒሳብ ባለቤቶች (የሒሳቡ ሕጋዊ ወኪል) ወደ ተጠቀሱት ቅርንጫፎች በአካል በመቅረብ ማንነታቸውን፣ ፊርማቸውንና አስፈላጊውን መረጃ ካረጋገጡ በኋላ የታገደውን ሒሳባቸውን ወደ አዲሶቹ ቅርንጫፎች የማዛወርና የማንቀሳቀስ ቅጽ እንዲሞሉ እየተደረገ ይገኛል። ነገር ግን የሂሳብ ቁጥሮቹ መንቀሳቀስ የሚጀምሩት አስፈላጊውን የማረጋገጥ ስራ ከተሰራ በኋላ መሆኑ ታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደንበኞችን በማስተናገድ ላይ ከሚገኙት የንግድ ባንክ ሰራተኞች አንዱን አናግሯል። ይኸው ሰራተኛ " ተገልጋዮቹ  የፋይዳ መታወቂያቸውን ኮፒ በመያዝ በአካል ባመለከቱበት በ24 ሰዓታት ወስጥ የታገደው የባንክ ሂሳባቸው ይለቀቃል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን የባንክ ሒሳቦች እንደታገዱ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይሰራል። በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አፋር እንዲሁም አማራ ክልሎች ዳግም ባገረሸው ጦርነት የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ወደ ትግራይ የሚደረጉ በረራዎች መቋረጣቸው ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስረከም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры57 400−74%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108235Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры57 403−74%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108234Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры53 391−76%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108233Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры53 389−76%к среднему
Пересылки69
Реакции—
Комментарии—
#108232Видеоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры52 386−77%к среднему
Пересылки69
Реакции347
Комментарии—
#108227Фотоальбомизменён

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተሾሙ። የከተማ እና መሰረተ ልማት ማኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ጫልቱ ቀደም ሲል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን ዶ/ር ረሻድ ከማልን ይተካሉ ። ዶ/ር ረሻድ ከማል ዛሬ ይፋ በተደረገው የኦሮሚያ ክልል የአስፈጻሚዎች አደረጃጀት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ተሹመዋል። ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ላለፉት አራት ዓመታት ገደማ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры39 494−82%к среднему
Пересылки68
Реакции—
Комментарии—
#108226Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры39 498−82%к среднему
Пересылки68
Реакции473
Комментарии—
#108225Фотоальбом

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ ተያይዘዋል። @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры38 521−83%к среднему
Пересылки0
Реакции—
Комментарии—
#108224Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры38 499−83%к среднему
Пересылки0
Реакции34
Комментарии—
#108223Фото

📣 𝐑𝐄𝐆𝐈𝐒𝐓𝐑𝐀𝐓𝐈𝐎𝐍 𝐍𝐎𝐖 𝐎𝐏𝐄𝐍!!! Jimma University has brought selected master’s programs right to the capital city, which are tailored to the demands of today's dynamic job market, and is now accepting applications.   𝙒𝙝𝙞𝙘𝙝 𝙥𝙧𝙤𝙜𝙧𝙖𝙢 𝙖𝙧𝙚 𝙮𝙤𝙪 𝙞𝙣𝙩𝙚𝙧𝙚𝙨𝙩𝙚𝙙 𝙞𝙣? 1. MSc in Data Science 2. MSc in Software Engineering 3. MA in Project Management and Finance 4. MBA in Business Administration 5. MA in Logistics and Supply Chain Management 6. MPH in General Public Health 7. MPH in Epidemiology 8. MSc in Health Monitoring and Evaluation 9. MSc in Health Economics   𝐑𝐞𝐚𝐝𝐲 𝐭𝐨 𝐉𝐨𝐢𝐧? Register via https://portal.ju.edu.et/announce/show/6   𝐅𝐨𝐫 𝐌𝐨𝐫𝐞 𝐈𝐧𝐟𝐨𝐫𝐦𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 📞 𝟎𝟗𝟕𝟖 𝟒𝟔𝟒𝟕𝟒𝟖 𝐨𝐫 𝟎𝟗𝟕𝟗 𝟒𝟔𝟒𝟕𝟒𝟖 📍 Kazanchis, Infront of Radisson Blu Hotel (the former HQ of Zemen Bank) 🔗 Telegram | TikTok   𝙀𝙖𝙧𝙣 𝙖 𝙅𝙞𝙢𝙢𝙖 𝙐𝙣𝙞𝙫𝙚𝙧𝙨𝙞𝙩𝙮 𝘿𝙚𝙜𝙧𝙚𝙚 𝙞𝙣 𝘼𝙙𝙙𝙞𝙨 𝘼𝙗𝙖𝙗𝙖!   #JimmaUniversity #PostgraduateProgram #MastersDegree #ApplyNow

Открыть в Telegram
Просмотры34 978−84%к среднему
Пересылки34
Реакции32
Комментарии—
#108221Фотоальбомизменён

#Oromia #ሹመት ዶ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ። ዶ/ር ቶላ በሪሶ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነዋል። ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ ደግሞ የጤና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የጨፌ ስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ሹመትን አጽድቋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡- 1. አብዱረህማን አብደላ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 2. አቶ መስፍን መላኩ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 3. ዶ/ር ረሻድ ከማል - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 4. ዶ/ር መንግስቱ በቀለ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 5. አቶ አህመድ ኢድሪስ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 6. አቶ አህመድ ሃጂ - የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ይህ  የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ አዲስ በጸደቀው አዋጅ 267/2019 መሰረት ያደረገ ነው፡፡ 7. ዶ/ር ቶላ በሪሶ - የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ 8. አቶ ጉዮ ዋሪዮ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ 9. ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ- የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ ተስፋዬ ቱሉ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 11. ዶ/ር አብዲ ዩያ - የእቅድና ልማት ቢሮ ኃላፊ 12.  ዶ/ር ቡልቶሳ ሂርኮ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ 13.  ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ- የጤና ቢሮ ኃላፊ 14.  አቶ ተሾመ ቦጋለ - የግብርና ቢሮ ኃላፊ 15.  ዶ/ር ነመራ ገበየሁ - የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ታረቀኝ ቡልልታ - የኢንተርፕራይዝና አንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 17. ዶ/ር አደሬ አሰፋ - የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 18. ወ/ሮ መሰረት አሰፋ - የመሬት ቢሮ ኃላፊ 19. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን - የሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ 20. አቶ ጥላሁን ወርቁ - የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ 21. ዶ/ር አያንቱ ጉተታ - የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 22. ወ/ሮ እልዳና ሱሌማን - የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 23. አቶ ቲጃኒ ናስር - የሰላም ቢሮ ኃላፊ 24. ወ/ሮ ሮዛ ቢያ - የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 25. ኢንጂነር ግርማ ረጋሳ - የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ 26. ኢንጂነር ሃቢብ ቁምቢ - የመንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ 27. ኢንጂነር ማሪያ ጉታ - የውሃ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሹመዋል፡፡ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры117 205−48%к среднему
Пересылки204
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч46 722
2 ч117 205
  1. Через 1 час46 722
  2. Всего сейчас117 205
#108220Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры117 908−47%к среднему
Пересылки204
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч46 415
2 ч117 908
  1. Через 1 час46 415
  2. Всего сейчас117 908
#108219Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры110 548−51%к среднему
Пересылки238
Реакции485
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч43 067
2 ч110 548
  1. Через 1 час43 067
  2. Всего сейчас110 548
#108218Фото

#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በጥራትም:በብራንድም:በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ  የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ በፈለጉት ስክሬን መጠን ፣ ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን። ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፌት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://t.me/samcomptech

Открыть в Telegram
Просмотры107 098−52%к среднему
Пересылки0
Реакции21
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч42 660
2 ч107 098
  1. Через 1 час42 660
  2. Всего сейчас107 098
#108217Фото

ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በማስተርስ መርሃ ግብር ለመማር ፍላጎት ላላቹ በሙሉ ? 📚 ሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ሙሉ እውቅና ያለው ሲሆን፣ የዳግም ምዝገባውን በETA በተሳካ ሁኔታ ካለፉ ጥቂት ተቋማት መካከል አንዱ ነው። በ2019 ዓ.ም. የማስተርስ ትምህርታቸውን በሜሪላንድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ተመዝግበው ለሚማሩ ተማሪዎች:- ✈️ የውጭ ሀገር የምርምር ጉዞ ዕድሎች ይመቻቻሉ። 👨‍🏫 በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ፕሮፌሰሮች ትምህርት ይሰጣል። 🏫 በአዲስ አበባ 22 አካባቢ — ከካፒታል ሆቴል ጀርባ — ለመማር አመቺ በሆነ ካምፓስ ትምህርት ይሰጣል። 🎓 በሁለት ዓመት የትምህርት ቆይታ ውስጥ ሁለት ነፃ አጫጭር ስልጠናዎች በእውቅና ባላቸው ፕሮፌሰሮች ይሰጣሉ። 📌 ለበለጠ መረጃ፦ 🌐 www.marylandic.com📱 0935656939 / 0958310704

Открыть в Telegram
Просмотры103 086−54%к среднему
Пересылки0
Реакции35
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч41 650
2 ч103 086
  1. Через 1 час41 650
  2. Всего сейчас103 086
#108215Фотоальбомизменён

#NewsAlert አቶ ሽመልስ አብዲሳን በድጋሚ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በጨፌ ኦሮሚያ ተሾሙ። የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን የ2019 ዓመት የመጀመሪያ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ በጉባዔው አቶ ሽመልስ አብዲሳን በድጋሚ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры165 484−26%к среднему
Пересылки118
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч22 287
5 ч165 484
  1. Через 6 часов165 484
  2. Всего сейчас165 484
#108214Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры160 941−28%к среднему
Пересылки154
Реакции587
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч22 273
5 ч160 941
  1. Через 6 часов160 941
  2. Всего сейчас160 941
#108213Файл

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል። ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦ - ጀማሪ መምህር፣ - መለስተኛ መምህር፣ - መምህር፣ - ከፍተኛ መምህር፣ - ተባባሪ መሪ መምህር፣ - መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው። በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው። ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል። መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры229 415+3%к среднему
Пересылки954
Реакции258
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч35 257
17 ч229 415
  1. Через 1 час35 257
  2. Через 24 часа229 415
  3. Всего сейчас229 415
#108212Фотоальбом

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል። በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል። በተጨማሪም፦ 👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር። 👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር። 👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር። 👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር። 👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር። 👉 ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር። የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል። በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል። ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል። የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры216 765−3%к среднему
Пересылки1 040
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч32 191
17 ч216 765
  1. Через 1 час32 191
  2. Через 24 часа216 765
  3. Всего сейчас216 765
#108211Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры221 257−1%к среднему
Пересылки1 029
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч31 190
17 ч221 257
  1. Через 1 час31 190
  2. Через 24 часа221 257
  3. Всего сейчас221 257
#108210Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры222 260−1%к среднему
Пересылки1 028
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч32 189
17 ч222 260
  1. Через 1 час32 189
  2. Через 24 часа222 260
  3. Всего сейчас222 260
#108209Фотоальбом

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры214 217−4%к среднему
Пересылки1 037
Реакции569
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч31 189
17 ч214 217
  1. Через 1 час31 189
  2. Через 24 часа214 217
  3. Всего сейчас214 217
#108208Фотоальбом

Bahir Dar - Senegal 🇸🇳 በአንጋፋው የቀድሞ አርሴናል ተጫዋች ፓትሪስ ቬይራ የሚመራው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ኢትዮጵያ፣ ባህር ዳር ከተማ ገብቷል። ቡድኑ ዛሬ ምሽት 3:20 ላይ ነው ውቢቷ ባሕር ዳር የገባው። ቡድኑ በደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ባህል የደመቀ አቀባበል ተደርጎለታል። የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ነገ ሰኞ 10:00 ሰዓት ጨዋታው በሚደረግበት ባሕር ዳር ስታዲየም ልምምዱን ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል። ቲክቫህ ስፖርት ባሕር ዳር መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Открыть в Telegram
Просмотры191 328−14%к среднему
Пересылки51
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч34 217
17 ч191 328
  1. Через 1 час34 217
  2. Через 24 часа191 328
  3. Всего сейчас191 328