ጦርነት ፣ ጭንቀት እና ተስፋ መቁረጥ ያላሸነፋቸው የቀላሚኖ ፍሬዎች ! የ9 ዓመት ጽናት 👏 ዶ/ር መብርሂት ግርማይ፣ ዶ/ር ኤደን ወርቅነህ እና ዶ/ር እመቤት በሪሁ ከ14 ዓመት በፊት ከመቐለ ፣ አክሱም እና አድዋ ተሰባስበው ቀላሚኖ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲገቡ ሕልማቸው አንድ ነበር ፤ ነጭ ጋውን ለብሶ ሕይወት ማዳን። በ2010 ዓ.ም. መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የሕክምና ትምህርታቸውን ሲጀምሩ፣ በስድስት ዓመት ተኩል ውስጥ "ዶክተር" ተብለው ለመጠራት ቀን ይቆጥሩ ነበር። ነገር ግን ዕጣ ፈንታ ሌላ ገጽ ገለጠ፤ በህይወታቸው ፍጹም ያልጠበቁት ሆነ። መጀመሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ ቀጥሎም 4ኛ ዓመት ተማሪ እያሉ የትግራይ ጦርነት ፈነዳ። ለሦስት ዓመታት የዩኒቨርሲቲው በር ተዘጋ። መብራት ፣ ኢንተርኔት እና ሰላም በጠፋበት ቦታ ስለ ህልም ሳይሆን ስለ መትረፍ ብቻ የሚታሰብበት ጊዜ መጣ። " ስድስት ዓመት የጠበቅነው 9 ዓመት መፍጀቱ ያማል " - ዶ/ር መብርሂት ግርማይ በጦርነቱ ወቅት በተለይ 2013 ዓ/ም እና 2014 ዓ/ም መብርሂት ስለ ነገ ሳይሆን " በሕይወት ስለመቆየት ብቻ " ታስብ ነበር። ኤደን ምንም እንኳን ወላጆቻቸው በክልሉ የተለያዩ ጦርነቶችን አሳልፈው የሚያውቁ ቢሆንም ለእነርሱ ጦርነት አዲስ እና ያልጠበቁት ተሞክሮ ነበር። በጦርነቱ ምክንያት እሷና ጓደኞቿ በከፍተኛ የሥነ-ልቦና እና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገቡ። " አንዱ አሸናፊ አንዱ ተሸናፊ ሆኖ የሚያልቅ ነበር የሚመስለን፤ ነገር ግን ሁኔታው ሲቆይ በሥነ ልቦና እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ነበረው። እኛ ያሰብነው እና የተገኘንበት ሁኔታ ለየቅል ነው " - ዶ/ር ኤደን ወርቅነህ ትምህርት ቆሟል፣ ጭንቀቱ ግን አልቆመም። ወደ አድዋ ቤተሰቦቿ የተመለሰችው እመቤት ጭንቀቱ ሊውጣት ሲል፣ ከቤት ተቀምጦ ከመጨነቅ ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠትና ታማሚዎችን ለመርዳት ተነሳች። ሦስቱም ጓደኛሞች ባሉበት ሆነው በመቐለ ፣ በአክሱም እና በአድዋ ለሆስፒታሎች ደብዳቤ ጽፈው በነጻ ማገልገል ጀመሩ። በትምህርት ቤቶች ለተጠለሉ ተፈናቃዮች የአልሚ ምግብ እጥረት ምርመራ እና የደም ግፊት ክትትል ሲያደርጉ፣ ያ ፈታኝ ጊዜ ትልቁ መምህራቸው ሆነ። በውስን እውቀታቸው የሰዎችን ሕይወት ሲታደጉ ማየታቸው፣ ነገ የተሻለ ሐኪም የመሆን ረሃባቸውን አቀጣጠለው። ኤደን ያንን የጦርነት ጫና "እንደ ትልቅ የመማሪያ ዕድል" ትመለከተዋለች። ይሁን እንጂ ፈተናው በጦርነቱ ማብቃት አላቆመም። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ትምህርት ቶሎ ባለመጀመሩ ተስፋ መቁረጥ ተጫጫናቸው። አብረዋቸው ከገቡት 110 ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ዕድሜያቸው እየገፋ በመሄዱና ለቤተሰብ ቀድሞ ለመድረስ ሲሉ ትምህርታቸውን አቋረጡ፤ ዘርፍም ቀየሩ። መብርሂትም ራሷ ተስፋ ቆርጣ ዘርፍ ለመቀየር አስባ ነበር። " 12ኛ ክፍል እያለሁ ሕክምና እማራለሁ ብዬ መወሰኔን የተጠራጠርኩበት ጊዜ ነበር " - ዶ/ር መብርሂት ግርማይ በመጨረሻ ግን የቤተሰብ እና የጓደኝነት ድጋፍ አሻገራቸው። ከዘጠኝ ዓመታት እልህ አስጨራሽ ጉዞ በኋላ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 ዓ.ም. በመቐለ ዩኒቨርሲቲ 17ኛ ዙር የሕክምና ምረቃ ላይ ሦስቱ ሴቶች ታሪክ ሠሩ፤ የኮሌጁን ከፍተኛ ውጤት በተከታታይ ጠቀለሉት ፦ 👉 ዶ/ር መብርሂት ግርማይ — 3.92 (የኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ተሸላሚ) 👉 ዶ/ር ኤደን ወርቅነህ — 3.90 👉 ዶ/ር እመቤት በሪሁ — 3.77 ጦርነት ብዙ ነገር ቢነጥቃቸውም ጽናታቸውን ግን መንጠቅ አልቻለም። ዛሬ ዶክተር መብርሂት በጤናው ዘርፍ አመራር ላይ፣ ዶክተር ኤደን እና ዶክተር እመቤት ደግሞ በሕክምና ምርምር ዘርፍ ተሰማርተው ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው ተነስተዋል። ምንጭ ቢቢሲ አማርኛ - የአቀራረብ ማሻሻያ ተደርጎበት ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የቀረበ። @tikvahethiopia
Open in TelegramPosts of TIKVAH-ETHIOPIA
ግብርና ሚኒስቴር የተሻሻሉ የቦር እና ካልሃሪ ሬድ ዝርያ ፍየሎችን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን ገለጸ። በመጀመሪያው ምዕራፍ የገቡት ፍየሎች 352 ሲሆኑ፣ የአሁኑን ጨምሮ በቀጣይ ምዕራፎች በአጠቃላይ 1700 ፍየሎች ይገባሉ ተብሏል። ወደ ሀገር ውስጥ የገቡት የቦር እና ካልሃሪ ሬድ ዝርያ ፍየሎች ፦ - በፈጣን ዕድገታቸው፣ - በትልቅ የሰውነት አቋማቸው፣ - በከፍተኛ የሥጋ ምርት አቅማቸው እና የአካባቢ ሁኔታን በመላመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ናቸው፡፡ ግብርና ሚኒስቴር " ዝርያዎቹ የሀገራችንን ነባር የፍየል ዝርያዎች የእድገት ፍጥነት፣ የሰውነት ቅርፅ እና የስጋ ምርታማነትን በሳይንሳዊ የዝርያ ማሻሻያ ስርዓት ለማሳደግ ትልቅ እድል ይፈጥራሉ " ብሏል። ፍየሎቹ በቀጣይ ከ21-30 ቀናት በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል በኳራንቲን (ለይቶ ማቆያ) ቦታ ጤንነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ዝርያዎችን ለሚያባዙ ለተመረጡ የግብርና ምርምር ማዕከላት እና ለሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚሰራጩ ይሆናል ተብሏል። የቦር እና ካልሃሪ ሬድ ፍየሎችን መጠቀም ከተመረጡ የሀገር ውስጥ የፍየል ዝርያዎች ጋር በማዳቀል ለስጋ ምርት የሚውሉ ፍየሎችን በብዛት ማርባትና ለገበያ ማቅረብ ያስችላል። Via Ministry of Agriculture ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 6 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegram#VIVA_SOFT የ "ቪቫ ሶፍት" (VIVA SOFT) ምርት ሕጋዊ ባለቤት የሆነው "ፒዩር ዉድ ፐልፕ ፔፐር ኤንድ ፓኬጂንግ" ድርጅታችን፤ የንግድ ምልክታችንን በመጠቀም ሕገ-ወጥ ምርቶችን ሲያመርትና ሲያከፋፍል በነበረው አካል ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰኑን እናሳውቃለን። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ RTD ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባለውለው ችሎት፤ የንግድ ምልክት በማስመሰል ሕገ-ወጥ ምርቶችን ሲያመርት የነበረውን አቶ ሰይድ መሀመድኑር ዑመር በሶስት ዓመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ተከሳሹ ቡራዩ እና ኮልፌ ቀራንዮ በሚገኙ መጋዘንና መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከደረጃ በታች የሆኑ ሶፍቶችን በሐሰተኛ ማሸጊያ ሲያመርት ተይዟል። ሕብረተሰቡ የንግድ ምልክታችንን በመጠቀም የሚደረጉ ማጭበርበሮችን እንዲጠነቀቅ እና ጥራቱን የጠበቀውን ኦሪጅናል የቪቫ ሶፍት ምርት ብቻ እንዲጠቀም እናሳስባለን። ፒዩር ዉድ ፐልፕ ፔፐር ኤንድ ፓኬጂንግ
Open in Telegram🏘 በሪል ስቴት አልሚዎች አማካኝነት ችግርና በደል የደረሰባቸው እና መፍትሔ በመሻት ወደ የአዲስ አበባ ከተማ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግልግል ተቋም አቤቱታ ያቀረቡ በርካታ የቤት ገዢዎች ጉዳይ፣ አልሚዎቹ ወደ ተቋሙ ቀርበው ያሉባቸውን ክፍተቶች በግልጽ ለማሳወቅና ለመተባበር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት እልባት ሳያገኝ እየቆየ መሆኑ ተገለጸ። ምክር ቤቱ ካለፈው ዓመት ጀምሮ 23 የክስ አቤቱታዎችን ከቤት ገዢዎች ቢቀበልም፣ በሪል ስቴት አልሚዎቹ ፈቃደኛ አለመሆን ሳቢያ በሰላማዊ ድርድር መፍታት የተቻለው አራቱን ጉዳዮች ብቻ ሲሆን፣ የአብዛኞቹ ቅሬታ አቅራቢ ቤት ገዢዎች ችግር ግን አሁንም መፍትሔ አላገኘም። የምክር ቤቱ የግልግል ተቋም ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወልደገብርኤል እንደገለጹት፣ ይህንን ችግር ታሳቢ በማድረግ ቤት ገዢውም ሆነ የሪል ስቴት አልሚው በሕግና በሥርዓት እንዲመሩና ያሉባቸውን ችግሮች እንዲፈቱ ወጥነት ያለው አሠራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል። #AhaduRadio ህዳር 6 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegramለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ. - 1 ሳምንት ብቻ ቀረው። ከመነሻው ይጀምሩ ፤ ሩጫዎን ይጨርሱ። የአለማችን ትልቁ 10 ኪ.ሜ ሩጫ የመሆን ህልማችንን በጋራ እውን እናድርገው። ህዳር 13 አይቀርም !!!! ሩጫዬ ቀለሜ!
Open in Telegram📢 REGISTRATION OPEN – AAU PROFESSIONAL TRAINING 🏛 College of N&CS | School of Information Science Training Areas 🔹 Cisco CCNA – 80 Hours 🔹 Cisco CyberOps (Security) – 40 Hours 🔹 Full Stack Web Development – 120 Hours Registration: Oct 30 – Nov 27 Classes Start: Nov 28, 2026 Schedule: Saturday & Sunday, 2:00–6:00 PM Mode: Online (Lectures, Labs & Exams) 💰 Fee Details: https://t.me/CiscoExams | https://t.me/AAU_DEVELOPER 📞 Contact: 0912 120 795 | 0945 039 478 | 0935 602 563 📍 Address: 4 Killo Campus, New Building, 2nd Floor, Room 10 🚀 Register Now either virtually or in-person and Upgrade Your Skills!
Open in Telegram👏 🇨🇳 ቻይና የሰራችው "CE-25A" የተባለ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን በአብራሪዎች የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በስኬት አደረገ። አውሮፕላኑ የተሰራው በቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (COMAC) እና CATL በተባለው የባትሪ ኩባንያ ትብብር ነው። 19 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን በሙከራው ወቅት ሁለት አብራሪዎችን እና አንድ መሐንዲስ ይዞ በአየር ላይ ለ16 ደቂቃ ያህል ቆይቷል። አውሮፕላኑ ለአጭር ርቀት የከተማ ለከተማ ጉዞዎች ተብሎ የተሰራ ነው። በአንድ ጊዜ የባትሪ ሙሌት እስከ 400 ኪሎ ሜትር መብረር ይችላል። ከዚህ ቀደም 19 ጊዜ ያለ አብራሪ ሙከራ አድርጎ ተሳክቶለታል። አሁን ላይ መንገደኞችን በመደበኛነት ማጓጓዝ እንዲጀምር የመንግስት ፈቃድ እየተጠባበቀ ይገኛል። ዥንዋ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 49,850 |
| 16 h | 165,871 |
| 30 h | 226,835 |
- After 1 hour49,850
- After 24 hours226,835
- Total to date226,835
" ከዚህ አሰቃቂ አደጋ እናት እና ልጅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ምንም ጨረፍታ ሳይነካቸው ተርፈዋል " - የቃጫ ቢራ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ • የሞቱ ሰዎች ቁጥር 8 ደርሷል። ትላንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መነሻውን ሆሳዕና ከተማ አድርጎ ወደ ሌሾ ማዞሪያ ሲጓዝ የነበረ የሠሌዳ ቁጥሩ "ኮድ 3 -24220 ደህ" የሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተሽከርካሪ በቃጫቢራ ወረዳ ሚኖ ቀበሌ "ታችኛው ዋዶሌ" ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ባጋጠመው የመገልበጥ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጾ ነበር። ዛሬ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ፍቅሬአብ አለሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አንድ ተጨማሪ ሰው ህይወቱ በማለፉ የሟቾች ቁጥር 8 መድረሱን ገልጸዋል። በአደጋው በቦታው የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ደግሞ ወደ ሕክምና ከተወሰዱ በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል። " ከዚህ አሰቃቂ አደጋ በሚያስደንቅ ሁኔታ እናትና ልጅ ምንም ጨረፍታ ጉዳት ሳያስተናግዱ ተርፈዋል " ያሉት አዛዡ ሕይወታቸው ካለፈው 8 መንገደኞች የ7 አስክሬን ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱንና አንደኛው መንገደኛ አስክሬን ግን እስካሁን መረጃ ስላልተገኘ ቤተሰብ በማፈላለግ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል። " አካባቢው በተደጋጋሚ አደጋ የሚከሰትበት ነው " ያሉት አዛዡ የዚህ አደጋ ትክክለኛው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንና ከባድ ገዳት የደረሰባቸው 2 መንገደኞች በከንባታ ሽንሽቾ እና ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 107,051 |
| 17 h | 187,552 |
| 31 h | 228,097 |
- After 24 hours187,552
- Total to date228,097
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 107,050 |
| 17 h | 187,312 |
| 31 h | 227,958 |
- After 24 hours187,312
- Total to date227,958
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 111,843 |
| 17 h | 177,614 |
| 31 h | 210,420 |
- After 24 hours177,614
- Total to date210,420
" የተሰረቀ ዕቃ በቅናሽ ዋጋ መግዛት ወይም ይዞ መገኘት እንደ ወንጀሉ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል " - የሕግ ባለሙያ አንዳንድ ሰዎች የተሰረቁ ስልኮች፣ ላፕቶፖችና ሌሎች ዕቃዎች በርካሽ ዋጋ የሚሸጡባቸውን ቦታዎች በማፈላለግ ሲገዙ ይስተዋላል። አንዳንዶች ምንጫቸውን ሳያውቁ ያገለገሉ ዕቃዎችን በርካሽ ስላገኟቸው ብቻ ከሰዎች ላይ ይገዛሉ ፤ ሌሎች ደግሞ እቃውን በትንሽ ብር ገዝተው አትርፈው ይሸጣሉ። ታዲያ አንድ ሰው " ዕቃው በቅናሽ ዋጋ ስለቀረበልኝ በቅን ልቦና ነው የገዛሁት ፤ የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " ቢል ከሕግ ተጠያቂነት ያመልጥ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑትን አቶ ጥጋቡ ደሳለኝን አነጋግሯል። የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት ምንድነው ? በአነስተኛ ዋጋ ስለተገኘ ብቻ የተሰረቀ ዕቃ የሚገዙና አትርፈው የሚሸጡ አካላት፣ በቅን ልቦናም ይሁን ሳያውቁ ቢገዙ ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ገልጸዋል። በሕግ ፊት " የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " የሚል ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል። " የተሰረቀ ዕቃ የዋጋ ቅናሽ ስላለውና ደረሰኝ ስለሌለው መግዛት፣ በሕጉ መሠረት የተሰረቀ ዕቃ በመግዛት እና ደረሰኝ የሌለው ዕቃ ይዞ በመገኘት እንደ ነገሩ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል። ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የሚቻለው ከሕጋዊ ነጋዴ በስሙ የተቆረጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ሲቻል ብቻ ነው " - አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ የአንድ ግብይት ሕጋዊነት የሚረጋገጠው በደረሰኝ ብቻ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው፤ ሻጩ ለሰጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ደረሰኝ የመስጠት፣ ገዢውም የከፈለበትን ደረሰኝ የመቀበል ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል። ግብይቱ በደረሰኝ እስካልተረጋገጠ ድረስ የትኛውም ግብይት የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል አሳስበዋል። የኦንላይን (ማኅበራዊ ሚዲያ) ግብይቶች ተጠያቂነት አለባቸው ? ከሰው ላይ የተሰረቁ ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ (የወንጀል ፍሬ የሆኑ) ዕቃዎችን ሰዎች ትክክለኛ መስሏቸው በቴሌግራም ቻናሎች፣ በፌስቡክ ገጾች እና በሌሎች የበይነመረብ አማራጮች ተታልለው ቢገዙና በኋላ የተሰረቀ ዕቃ መሆኑ ቢታወቅ፣ የወንጀል ተጠያቂነቱ በቀጥታ የሚያርፈው ዕቃውን ባሻሻጡት የኦንላይን ገጽ ባለቤቶች ወይም አንቀሳቃሾች (ኦፕሬተሮች) ላይ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል። አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያ " ዕቃ እናሻሽጣለን፣ ሻጭና ገዢ እናገናኛለን፣ የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን " የሚሉ አካላት በቀጥታ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል። እነዚህ አካላት ዕቃውን ከማስተዋወቃቸው በፊት ዕቃው በሕጋዊ መንገድ የተገኘና የወንጀል ፍሬ አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከትክክለኛ አቅራቢ ተገዝቶ ለትርፍ የቀረበ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ዕቃው በፖሊስ ቢወሰድ ገዢው ምን መብት አለው ? አንድ ገዢ በቅን ልቦና ያገለገለ ዕቃ ገዝቶ የተሰረቀ መሆኑ ተደርሶበት በፖሊስ ከተወሰደበት፣ ዕቃውን ለመግዛት ያወጣውን ገንዘብ ከካሳ ጋር በፍርድ ቤት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት እንዳለው አቶ ጥጋቡ ጠቁመዋል። ሆኖም የፍትሕ ሂደቱ እስከ 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ስለሚችል፣ ዜጎች ገና ከጅምሩ በደረሰኝ በመገበያየት ራሳቸውን ከእንግልትና ከኪሳራ መጠበቅ እንደሚገባቸው መክረዋል። የተሰረቀ ዕቃ በስጦታ መልክ መቀበል የሚያመጣው ችግርስ ? " የተሰረቀ ዕቃ መሆኑን ሳያውቁ በስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት ያድናል ወይ ? " ለሚለው ጥያቄም የሕግ ባለሙያው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡ የተሰረቀ ዕቃን በስጦታ የተቀበለ ሰው በሕግ ሲጠየቅ፤ " ዕቃው የተሰጠኝ በማኅበረሰቡ የመሰጣጣት ባህልና ልማድ መሠረት በስጦታ ነው፤ ቀደም ሲል በእኔ እጅ አልነበረም፤ እከሌ የሚባል ሰው ነው የሰጠኝ " ብሎ በሰው ምስክር ማረጋገጥ ከቻለ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ይሆናል። በሰነድ እንኳ ባይሆን በሰው ምስክር ማረጋገጥ ካልቻለ ግን፣ የተሰረቀ ዕቃን ለማሸሽ፣ ለመሸሸግ፣ ለመደበቅ፣ ለመሰወር ወይም አትርፎ ለመሸጥ የተደረገ ሙከራ ነው ተብሎ በወንጀል ይጠየቃል። በሕግ አግባብ ስጦታ መቀበል የሚቻለው ስጦታ ሰጪው ንብረቱ የራሱ ስለመሆኑ በውልና ማስረጃ መሥሪያ ቤት ሲያረጋግጥ ብቻ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለመደው መንገድ ብቻ ዝም ብሎ ስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም ማኅበረሰቡ ለሚፈጽማቸው ማናቸውም ግብይቶች ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠትና መቀበልን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 111,832 |
| 17 h | 178,220 |
| 31 h | 212,009 |
- After 24 hours178,220
- Total to date212,009
ኢንዶሚ ለሁሉም ተስማሚ በ ኢትዮጵያ ስንዴ የተመረተ ፤ በ አትክልት ዘይት የተሰራ ፤ በ 3 ደቂቃ ዝግጁ ኢንዶሚ ፤ ፈጣን ጣፋጭ የ ኢትዮጵያ ምርት ዛሬዉኑ ይሞክሩት
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 97,947 |
| 17 h | 153,818 |
| 31 h | 183,361 |
- After 24 hours153,818
- Total to date183,361
#SafaricomEthiopia ጊዜ⁺ ለፊልም! 📺 ዳታ አለቀብኝ ብለው ሳይጨነቁ በአንድ እና በሁለት ሰዓት የጊዜ+ ያልተገደበ ኢንተርኔት ጥቅል ፊልምዎን እያዩ ዘና ፈታ ይበሉ! አሁኑኑ *777*2# ላይ በመደወል ጥቅሉን ይግዙ! #SafaricomEthiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 94,374 |
| 17 h | 149,963 |
| 31 h | 190,402 |
- After 24 hours149,963
- Total to date190,402
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የግሉ ዘርፍ እና የውጭ አጋርነት ተሳትፎን ያካተቱ ሁለት አዳዲስ ኢንቨስትመንት ባንኮችን ወደ ገበያው አስገብቷል። ባለስልጣኑ ከሰፊ የፈቃድ ማመልከቻ ግምገማ ሂደት በኋላ ለኤ ኤም ጂ (AMG) ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ እና ለናይልብሪጅ (NileBridge) ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ የኢንቨስትመንት ባንክነት ፈቃድ መስጠቱ ታውቋል። ከፈቃድ አሰጣጡ ጎን ለጎን የሁለቱን አዳዲስ ተቋማት የ8 ተሿሚ እንደራሴዎች እና የ10 የቦርድ አባላት ሹመትንም አጽድቋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ዳግማዊት ሽፈራው፣ በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው አጠቃላይ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ቁጥር 23 መድረሱን የኢንቨስትመንት ባንኮች ቁጥርም ወደ 11 ከፍ ማለቱን ገልጸዋል። እስካሁን ፈቃድ ከተሰጣቸው ኢንቨስትመንት ባንኮች መካከል አብዛኞቹ የባንኮች እህት ኩባንያዎች (subsidiaries) እንደነበሩ አስታውሰው የአሁኖቹ ሁለት ተቋማት ግን ከግሉ ዘርፍ እና ከውጭ አጋርነት የመጡ መሆናቸው ለገበያው አዲስ እይታና አቅም እንደሚፈጥሩ አመልክተዋል። የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱ አራት ወራት ገደማ የፈጀ ምልልስ እንደነበረው የገለጹት ዳግማዊት ሽፈራው ገበያው ለሀገሪቱ አዲስ ከመሆኑ አንጻር ተቋማቱ መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ባለሙያዎችን (professionals) አግኝቶ በማቅረብ ረገድ ተግዳሮት እንደነበረባቸው ገልጸዋል። " በእኛ በኩል የጥቅም ግጭትን ከማስወገድ እና ከገበያው ደህንነት አንጻር የቦርድ አባላትን ታሪክ የመተዳደሪያ ሰነዶችን እና የሰው ኃይል ብቃትን በጥብቅ እንመረምራለን፤ በተለይ በወሳኝ የስራ መደቦች ላይ ትክክለኛውን ባለሙያ አግኝቶ በማቅረብ ሂደት ውስጥ ሰፊ ምልልስ ተደርጓል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 5 h | 149,001 |
| 20 h | 187,235 |
| 34 h | 214,039 |
- After 6 hours149,001
- After 24 hours187,235
- Total to date214,039
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 5 h | 147,819 |
| 20 h | 184,773 |
| 34 h | 209,831 |
- After 6 hours147,819
- After 24 hours184,773
- Total to date209,831
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 169,287 |
| 35 h | 222,250 |
- After 6 hours169,287
- Total to date222,250
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 164,040 |
| 35 h | 215,339 |
- After 6 hours164,040
- Total to date215,339
ትላንትና ምሽት በጉዞ ላይ እያለ ከመቐለ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደጉዓ ተምቤን አካባቢ በታጣቂዎች የተገደለው የ24 ዓመቱ ወጣት የብርጋዴር ጀነራል ገብረእግዚአብሔር በየነ (ወዲ አንጥሩ) ልጅ መዋእል ገብረእግዚአብሔር ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ። የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ዛሬ በመቐለ ሀወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲ ሽምድሑን በሚገኘው እንዳማሪያም ቤተ ክርስትያን የተፈጸመ ሲሆን የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል ሚኒስትሮች ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል አመራሮች መገኘታቸውን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 159,334 |
| 35 h | 203,295 |
- After 6 hours159,334
- Total to date203,295
⚠️ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ " ጋዜቦ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግንባታ ላይ ባለ ሕንፃ ላይ በደረሰ አደጋ የ3 ሠራተኞች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። ፖሊስ፣ አደጋው የተከሰተው ዛሬ ጠዋት መሆኑንና ሦስቱ ሠራተኞች በሥራ ላይ እያሉ ከሕንፃው ላይ በመውደቃቸው ሕይወታቸው ወዲያውኑ ማለፉን አስረድቷል። የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ እና ዝርዝር ሁኔታ ለማጣራት ምርመራ እያደረገ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። ምንም እንኳን የዚህኛው አደጋ ትክክለኛ መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ቢሆንም፣ በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች፣ ለፍቶአዳሪዎች ህልፈት እና ጉዳት እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የቁጥጥር ክፍተት መኖሩን በተለይም በመወጣጫዎች (ስካፎልዲንግ) ላይ ሲሠሩ በርካታ ሠራተኞች ከከፍታ በመውደቅ ለሞትና ለአካል ጉዳት እየተጋለጡ መሆኑን ገልጾ ነበር። አሠሪዎች ለሚያሰሯቸው ሠራተኞች ተገቢ የሆነ የደኅንነት መሣሪያዎች ማቅረብ እንዳለባቸው ፤ ያ ካልሆነ ችግሩን መፍታት እንደማይቻል አሳስቦ ነበር። በግንባታ ሥራዎች ላይ የሠራተኞች ደኅንነት የሚጠበቅበት ሥርዓት እና የቁጥጥር አፈጻጸምም እጅግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 8 h | 164,069 |
| 36 h | 203,271 |
- After 6 hours164,069
- Total to date203,271
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 8 h | 167,382 |
| 36 h | 221,949 |
- After 6 hours167,382
- Total to date221,949