#JimmaUniversity ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል። የምዝገባ ቦታ፦ ● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ እና በቬተርናሪ ሕክምና ኮሌጅ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው ● የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው ● አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ ● የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ልብስ ወደ ተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በሌላ ማስታወቂያ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል። @tikvahuniversity
Open in Telegram
Tikvah-University
Subscribers, 30 days
Oct 2 – Oct 3+221 (+0.1%)
Show as table
| Date | Subscribers |
|---|---|
| Oct 2, 2026 | 392,006 |
| Oct 3, 2026 | 392,227 |
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Sep 29, 2026 | 49,771 |
| Sep 30, 2026 | 40,570 |
| Oct 1, 2026 | 38,446 |
| Oct 2, 2026 | 10,109 |
| Oct 3, 2026 | 9,607 |
Most viewed this month
- 01Views55.4KForwards89Reactions—Comments—
- 02Views55.2KForwards99Reactions—Comments—
- 03Views52.9KForwards91Reactions243Comments20
- 04Views51.9KForwards36Reactions—Comments—
- 05Views47.8KForwards25Reactions85Comments16
Latest posts
No text
Open in Telegram#AASTU አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በጂኦተርማል ኢንጂነሪንግ እና በጂኦተርማል ጂኦሳይንስ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ለመጀመር የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል። በዩኒቨርሲቲው የማዕድን ፍለጋ፣ ማውጣት እና ማበልፀግ የልህቀት ማዕከል የውጪ ስርዓተ ትምህርት ግምገማውን አድርጓል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከማዕድን ሚኒስቴር ከቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኦፐሬሽንስ እና ከኮርቤቲ ጂኦተርማል የተውጣጡ ባለሙያዎች በስርዓተ ትምህርት ግምገማው ተሳትፈዋል። የሚጀመሩ የማስተርስ ፕሮግራሞች ● MSc in Geothermal Geoscience ● MSc in Geothermal Engineering የሚጀመር የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራም ● PhD in Geothermal Geoscience @tikvahuniversity
Open in Telegram#ሎርካን_ሜዲካል_ኮሌጅ የበርካታ ዓመታት ልምድ ባላቸው ሐኪሞችና ምሁራን ባለቤትነት የሚመራው ሎርካን ሜዲካል ኮሌጅ ምዝገባ ላይ ነው❗️ BSc Fields of Study: → Doctor of Medicine → Doctor of Dental Medicine → Bachelor of Dental Science → Nursing TVET Programs: → Dental Therapy → Nursing → Medical Laboratory → Pharmacy → Radiography ⭐️ የ CPD ማዕከል አገልግሎት! ☎️ 0913398780 / 0911596059 አድራሻ፦ CMC አደባባይ ከፀሐይ ሪል እስቴት ጀርባ ከ ICMC ጠቅላላ ሆስፒታል አጠገብ 📍 Addis Ababa, CMC Square, Behind Tsehay Real Estate, next to ICMC General Hospital Facebook: https://www.facebook.com/Lorcanmedicalcollege Tiktok: https://www.tiktok.com/@lorcan.medical.co
Open in Telegramየጂ.አይ.ኤስ. (Geographic Information System) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ጂኦ-ስፓሻል ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና 👉 ArcGIS + QGIS + Spatial Analysis + Remote Sensing በአንድ ላይ 👉 ንድፈ ሀሳብን ከእውነተኛ የካርታ ስራ እና ተግባራዊ ትንተና ጋር በማዛመድ የሚሰጥ ስልጠና የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ፣ ቁ.2: መገናኛ ደራርቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ እና ቁ.3: አዳማ ራስ ሆቴል 2ኛ ፎቅ ለመመዝገብ ድረ-ገጽ 👇 www.sageethiopia.com Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
Open in Telegram#WallagaUniversity የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተቋሙን ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት ለማሸጋገር በሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣ ተቋማዊ አቅም፣ የሰነድ ዝግጅት እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ውይይት አካሒዷል። ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመሔድ የተገኘ የቤንችማርኪንግ ተሞክሮ በመድረኩ ቀርቧል። ዩኒቨርሲቲው ለራስ ገዝነት ሽግግር አስፈላጊ በሆኑ የዲጂታላይዜሽን፣ የውስጥ ገቢ አቅም ማጠናከር እና መሠል ሥራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል። የሽግግር ሰነዶችና ፖሊሲዎች ማዘጋጀት፣ የራስ ገዝነት ጽ/ቤት ማቋቋም፣ የምርምርና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ተቋማዊ የሽግግር ካርታ ማዘጋጀት ቀጣይ ሥራዎች መሆናቸው በውይይቱ ተጠቁሟል። @tikvahuniversity
Open in TelegramNo text
Open in Telegram#ጥቆማ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም ያስቀመጠውን የዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ ያመጡና በፖሊስ ሙያ ዘርፍ ለማገልገል የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለአራት ዓመታት በፖሊስ ሳይንስ በዲግሪ ፕሮግራም አስተምሮ በረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ በማስመረቅ በፌደራል ፖሊስ የሥራ ክፍሎች በማስመደብ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ መስፈርቶች፦ ➻ በፖሊስ መኮንንነት ሀገሩን ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት፣ ➻ ከወንጀል ነጻ ስለመሆናቸው ከሚኖሩበት አካባቢ ፖሊስ ጽ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ ➻ ለፖሊስ ስልጠና ብቁ የሆነ አካላዊ አቋምና የአዕምሮ ጤንነት ያለው/ያላት፣ ➻ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/የሆነች፣ ➻ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣ ➻ ከተመረቁ በኋላ ለሰባት ዓመታት በተማሩበት የፖሊስ ሙያ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ተመድቦ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ፣ ➻ ሴት አመልካቾች ከእርግዝና ነጻ መሆን አለባቸው፣ ➻ ከዚህ በፊት የፖሊስ/የመከላከያ ስልጠና ያልወሰዱ፣ ➻ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጥን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ። በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ መቁረጫ ውጤት ያላቸው ወይም በ2017 ዓ.ም እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት የማለፊያ ውጤት ያመጡ ማስረጃ በማቅረብ ማመልከት ይችላሉ። ➻ ቁመት፦ ለወንድ 1.65 ሜ. እና ከዚያ በላይ ፤ ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ ➻ ዕድሜ፦ ከ18 እስከ 28 ዓመት በትምህርት ወቅት ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ፣ የምግብ እና የጤና አገልግሎት በተቋሙ ይሸፈናል። የምዝገባ ጊዜ 👇 እስከ መስከረም 29/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ ኦንላይን ለመመዝገብ 👇 https://forms.gle/cPBiWRzUDx4KFRiq9 @tikvahuniversity
Open in Telegram#ጥቆማ እንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም ክፍያ በማንኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ይማሩ! ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የተማሪዎችን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ለማሻሻል ባዘጋጀው ፖርታል ይጠቀሙ! ብቃትዎን ያሳድጉ! ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ለሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጀ ነው። በድምፅ፣ በፅሑፍ እና በምስል በተቀናበሩ ማስተማሪያዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያስችል ትምህርት ያገኛሉ። ፖርታሉ በስማርት ስልክ፣ በስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌት እና በኮምፒውተር ዌብ መፈለጊያ ላይ ይሰራል፡፡ ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት የሚያስፈልግ ቢሆንም ገንዘብ አይቆርጥም። ወደ ፖርታሉ ይግቡ👇 http://learn-english.moe.gov.et @tikvahuniversity
Open in TelegramNo text
Open in TelegramConnections
Similar channels
ABDII SABAA@abdii_sabaaEducation599K
ትምህርታዊ መረጃ™@tmhrt_ministers1Education246K
Sanyii Guddataa@segnigudetaEducation246K
Subhash Charan@officialsubhashcharanEducation394K
Kalam Academy Sikar@kalamacademysikarEducation390K
StudyAI | Нейросети@study24aiEducation389K
المهندس مصطفى جبار@suffy96Education396K
قناة تجميعات ستيب STEP الحساني@step_alhassaniEducation388K