Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 246 |
| 2 h | 426 |
- After 1 hour246
- Total to date426

By publication day
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 24, 2026 | 812 |
| Nov 25, 2026 | 429 |
Hours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 246 |
| 2 h | 426 |
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የቤተ መጻሕፍት ዲጂታል አገልግሎትን ለማዘመን ከአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ጋር የቴክኖሎጂ ትብብር ፈጠረ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የቤተ መጻሕፍት አገልግሎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማጠናከርና የዲጂታል እውቀት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ከአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ጋር የትብብር ሥራ ጀምሯል። በዚህም አብርሆት ቤተ መጻሕፍት በራሱ የቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ላይ ተግባራዊ ያደረገውን የተቀናጀ የቤተ መጻሕፍት አስተዳደር ሥርዓት (Integrated Library Management System – ILMS) ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለማጋራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርሟል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱን የሆስፒታሉ ሜዲካል ኮሌጅ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሮቮስት ዶ/ር ዱቤ ጃራ የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል። በወቅቱም ትብብሩ ለኮሌጁ የትምህርት የምርምርና የእውቀት ማግኛ አገልግሎቶች ያለውን ፋይዳ በማንሳት ሀሳባቸውን አቅርበዋል በተጨማሪም የቴክኖሎጂ ሽግግር ክፍል ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ግርማ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የተቀናጀው የቤተ መጻሕፍት አስተዳደር ሥርዓት የመጻሕፍት ካታሎግ አዘገጃጀትና አስተዳደር፣ የመጻሕፍት ግዢ፣ የአባልነት አስተዳደር፣ የመጻሕፍት ብድርና መመለስ፣ የኦንላይን የሕዝብ ተደራሽ ካታሎግ (OPAC)፣ የሪፖርትና ትንተና እንዲሁም የዲጂታል ሀብቶች አስተዳደርን ጨምሮ የቤተ መጻሕፍት አጠቃላይ የሥራ ሂደቶችን በአንድ የዲጂታል ሥርዓት ለመምራት ያስችላል። ይህ የቴክኖሎጂ ትብብር የኮሌጁን የቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የበለጠ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ከማድረጉም በላይ የመረጃና የእውቀት ሀብቶችን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተጠቃሚዎችን የአገልግሎት ልምድ ለማሻሻልና የተቋሙን የትምህርት፣ የምርምርና የሙያ ማበልጸግ ተግባራት ለመደገፍ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። በተጨማሪም ትብብሩ በተቋማት መካከል የቴክኖሎጂና የሙያ ልምድ ልውውጥን በማጠናከር የዲጂታል ለውጥን ለማፋጠንና ዘመናዊ የእውቀት አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ለማዳረስ የሚያግዝ አስፈላጊ እርምጃ ነው። የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 245 |
| 2 h | 432 |
Hours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 12 h | 538 |
| 24 h | 767 |
የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አብሮ የሚስራበትን የውል ስምምነት ተፈራረመ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር አብሮ የሚሰራበትን ስምምነት በዛሬው እለት የተፈራረመ ሲሆን በይበልጥም ለሰራተኞቹ በወር ደመወዛቸው መጠን ላይ ተመስርቶ ያለ ተጨማሪ ተያዥ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የስምምነት ውል ፈጽሟል። ስምምነቱ በሆስፒታሉ አመቻችነት ሰራተኞች ከደመወዛቸው ጋር በተያያዘ ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ የውሉን ሰነድ የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር አበበ ታደሰ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአራዳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ታምራት ዮሐንስ ፈርመዋል። በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ዶ/ር አበበ ታደሰ ስምምነቱ እውን እንዲሆን ላደረጉት አስተዋጽኦ፣ በተለይም ለአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሮቮስት አቶ አለሙ ክብረት ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም ለሰራተኞቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት፣ ከተመቻቸው የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጋብዘዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአራዳ ዲስትሪክት ዳይሬክተርም ስምምነቱ በመፈጸሙ ደስታቸውን በመግለጽ፣ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከተመቻቸው አጋጣሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል። ከየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጋር በመተባበር መስራታቸውም ደስተኛ እንደሆኑ ገልጸዋል። ይህ ስምምነት የሆስፒታሉን ሰራተኞች የፋይናንስ ተደራሽነት በማሳደግ የሰራተኞችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያግዝ አዲስ እድል ነው። 📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን 📅 ኅዳር 15/2019 ዓ.ም 📍 📌 Follow Us on Social Media 👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050 👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC 👉 Follow us on tiktok https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE 🔖 #Y12HMC 💛✨
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 13 h | 704 |
| 25 h | 874 |
Hours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 16 h | 737 |
| 24 h | 783 |
የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ሪፖርት ቀረበ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ሪፖርት ግምገማ አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ የሆስፒታሉ ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር አበበ ታደሰ፣ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሮቮስት አቶ አለሙ ክብረት፣ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ምክትል ፕሮቮስት ዶ/ር መዓዛ ሮሪሳ፣ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሮቮስት ዶ/ር ዱቤ ጃራ፣ የአበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ወገኔ አሰፋ፣ የዲፓርትመንትና የኬዝ ቲም ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተገኝተዋል። በዝግጅቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የሪፎርምና አክሬዲቴሽን የ90 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ሂደት ግምገማ ሪፖርት በሪፎርም ዳይሬክተሩ አቶ አበባው አበበ ቀርቧል። ሪፖርቱን ተከትሎ በአቶ አለሙ ክብረት አወያይነት የጋራ ውይይትና ግምገማ ተካሂዷል። በውይይቱም ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሶስቱ ምክትል ፕሮቮስቶችና በአበበች ጎበና እናቶችና ሕፃናት ማዕከል ዳይሬክተር ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በመድረኩ የተነሱ ጉድለቶችና የአፈጻጸም ክፍተቶች በሚቀጥለው ሩብ ዓመት እንዲሞሉ፣ የተጀመሩ ሥራዎችም በተሻለ ቅልጥፍናና ውጤታማነት እንዲፈጸሙ አቅጣጫ ተቀምጧል። እንዲሁም በሁለተኛው ሩብ ዓመት የተሻለ አፈጻጸምና ጥራት ያለው ሪፖርት እንደሚጠበቅ በአመራሮቹ ተገልጿል። በመጨረሻም የቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን የመምረጥ ሂደት ተካሂዶ ሶስት አባላት በመምረጥ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል። 📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን 📅 ኅዳር 15/2019 ዓ.ም 📍 📌 Follow Us on Social Media 👉 Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050 👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC 👉 Follow us on tiktok https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE 🔖 #Y12HMC 💛✨
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 16 h | 755 |
| 24 h | 811 |
በተቋሙ በሶሻል ወርክ አስተባባሪነት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በጎ ፈቃደኞች ለ20 ታካሚዎች 150,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ስማቸው በይፋ እንዳይጠቀስ የፈለጉ በጎ ፈቃደኞች በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሕክምና ላይ ለሚገኙ 20 ታካሚዎች በድምሩ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። በሶሻል ወርክ አማካኝነት የተሰጠው የገንዘብ ድጋፉ የታካሚዎቹን የኢኮኖሚ ችግር በማቃለል በሕክምና ሂደታቸው ላይ እገዛ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ ድጋፉን ያገኙ ታካሚዎችም በወቅቱ ለደረሰላቸው የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል። ይህ በጎ ተግባር የሰው ለሰው መደጋገፍን፣ ርህራሄንና ማህበራዊ ኃላፊነትን የሚያሳይ በመሆኑ ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው። የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለታካሚዎች ድጋፍ ላደረጉት ለእነዚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ ለፈለጉ በጎ ፈቃደኞች ከልብ ያመሰግናል።
Open in TelegramHours after publication
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 16 h | 780 |
| 25 h | 823 |
🚑👨🏻⚕️ Московская скорая помощь@mos_103_officialMedicine4.41K
Материалы по военной и тактической медицине🩺@warmedicineMedicine4.42K
الزمالة اليمنية | البورد اليمني@yemeni_fellowshipMedicine4.33K
ddoctors.ru@ddoctorsnewsMedicine4.43K
قناة قسم فحص البصر - بصريات@opthakhraMedicine4.33K
НМИЦ здоровья детей Минздрава России@nczd_ruMedicine4.33K
Avita Implant Center@avitaimplantcenterMedicine4.32K