Account
Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

ሸገር 102.1 መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር የእናንተ ነው! https://bit.ly/33KMCqz

Username
@shegerfmradio102_1
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers36,441
Avg views per post, 7d1,569last 7 days
ERR4.30%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 24, 20262,940
Nov 25, 20261,937
Nov 26, 2026975

Most viewed this month

  1. 01
    Views2.94K
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—
  2. 02

    ኅዳር 16 2019 አጋር ማይክሮ ፋይናንስ ጠቅላላ ሃብቴ 1.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል አለ። በሌላ በኩል የሰጠው ጠቅላላ ብድር ደግሞ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናግሯል። ኩባንያው ይህን ያለው አዲስ ያሻሻለውን የተቋሙን መለያ ዓርማ እና ህብረ-ዝማሬ ትላንት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። የተከፈለ ካፒታሉ 477.9 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 664.3 ሚሊዮን ብር ማደጉን የአጋር ማይክሮፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰረቀ ብርሃን ዘርአይ ተናግረዋል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ዋና ዋና የፋይናንስ አገልግሎቶችን በስፋት እያቀረበ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው መደበኛ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት፣ ለሴቶችና ወጣቶች የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል ብለዋል። እንዲሁም አካል ጉዳተኞችንም ያካተተ አካታች የብድር አገልግሎትም ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩም ነግረውናል። አጋር ማይክሮፋይናንስ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በአማራ እና በሲዳማ ክልሎች በሚገኙ 30 ቅርንጫፎች አማካኝነት ከ88 ሺህ 500 በላይ ደንበኞችን እንዳፈራም ሰምተናል፡፡ ፍቅሩ አምባቸው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

    Text
    Views2.44K
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—
  3. 03
    Views2.32K
    Forwards—
    Reactions7
    Comments—
  4. 04
    Views2.31K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—

Latest posts

#27311Text

ኀዳር 17 2019 ወደ ሀገር እንዳይገባም እንዳይሸጥም የተከለከለው ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ በህገወጥ መንገድ እየተሸጠ ነው ተባለ። ሲጋራው በትምህርት ቤቶች ጭምር በተማሪዎች እጅ  መገኘቱ ተነግሯል። ይህ የተባለው  የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ ሕገ ወጥ የንግድ አሠራሮችን ለመቆጣጠርና የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ በሚያስፈልገው የተቋማት የጋራ ኃላፊነትና ቅንጅት ዙሪያ ባሰናዳው የፓናል ውይይት ላይ ነው። በትምህርት ቤቶች አካባቢ በተሠራው የትምባሆ ቁጥጥር ለውጥ ቢመጣም፣ የሱቅ በደረቴ ነጋዴዎች ሲጋራ በነጠላ እየሸጡ መሆኑ ተነግሯል። አንዳንድ ሱቆች የተከለከሉ ሲጋራዎችን ይዘው እንደሚገኙና ግብይቱ በምሽት አካባቢ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል። ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ሲጋራ መሸጥና ማጨስ የተከለከለ ቢሆንም ድርጊቱ አሁንም እንደሚስተዋል ተነግሯል። የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በተለይም ቻይናውያን፣ በተከለከሉ ቦታዎች ሲያጨሱ እንደሚስተዋልም ተነስቷል። እነዚህንና መሠል ችግሮችን ለመፍታት በተደረገ ቁጥጥር  በ2018 ዓ.ም በ727 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶ ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕገ ወጥ ትምባሆ መወገዱን የባለሥልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ጠቁመዋል። 79 በመቶ የሚሆኑ ተቋማትን ከትምባሆ ነፃ ማድረግ መቻሉም ተናግረዋል። እነዚህ ስራዎች የተሰሩት የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ደንብ ማስከበር በቅንጅት ባከናወኑት የመቆጣጠር ተግባር ነው ተብሏል ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት በዳዳ በበኩላቸው  በተለይ በሆስፒታሎች በር አካባቢ ምግብና መጠጦች ፀሐይ ላይ እንደሚሸጡ ተናግረዋል። ምርቶቹ ተወርሰው ቢወገዱም በማግስቱ እየተተኩ መሆኑን አስረድተዋል። በ2018 ዓ.ም  በተሠራው ሥራ በ1,540 የምግብ ተቋማት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ከ40 ሚሊዮን በላይ የምግብና የመጠጥ ምርቶች ተወግደዋል ቸብሏል። ከተቋማቱ መካከል 170ዎቹ ታሽገዋል፣ የ3ቱ ፈቃድ ተሰርዟል፣ 120 የሚሆኑት በገንዘብ ተቀጥተዋል። ባለሥልጣኑ ፀሐይ እየመታቸው የሚሸጡ ምርቶች ለተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ስለሚያጋልጡ ኅብረተሰቡ ገዝቶ እንዳይጠቀም አሳስቧል። ገዛ ጌታሁን

Open in Telegram
Views338−78%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#27310Text
Views359−77%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#27309Text
Views975−38%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#27308Photo
Views996−37%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#27307Photo
Views884−44%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#27306Text
Views871−44%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#27305Text

ኅዳር 17 2019 “የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብ እና ዘመናዊ ፕሮጀክት በእኔ እድሜ ተሰርቶ አያውቅም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ። ከተወለድኩ እናንተ የፓርላማ አባላትም ከተወለዳችሁ የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብና በዘመናዊ መንገድ የሚመራ ፕሮጀክት ኖሮ አያውቅም ብለዋል። በአንድ ጊዜ አራት ሺህ የሚጠጋ ትራክ ተሽከርካሪ በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ነው ሱሉ አንስተዋል። ይህም ስራ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት(AI) ታግዞ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን የትራንስፖርት አስተዳደሩ በራሱ ከባድና ውስብስብ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አሁን እየተሰራ ያለው ቦታውን የማዘጋጀት ስራ ከሶስት ወር ባነሰ ጊዜ ይጠናቀቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፕላን መንገድ (የራን ዌይ) ግንባታውን ለመስራት የጨረታ ሂደት ላይ ነው ብለዋል። የጨረታው ውጤትም በአንድ እና ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ይታወቃል ሲሉ ተናግረዋል። የቢሾፍቱ ኤርፖርትን ጨምሮ ግዙፍ የሆኑት እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣የጋዝና ሌሎቹም ሜጋ ፕሮጀክቶች አትችሉም፣ገንዘብ ከየት ታመጣላችሁ የሚል ጥያቄ እየተነሳ የሚሰሩ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያን እድገት በማይፈልጉና እነሱ በገዟቸው ሀገራት በኩል ይህ ጥያቄ በስውርም በግልፅ በሚዲያም ጭምር ይቀርባል ሲሉ ተናግረዋል። የተለየ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በቀር እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በታሰበው ጊዜ ይጠናቀቃሉም ብለዋል። ቴዎድሮስ ወርቁ

Open in Telegram
Views1,140−27%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#27304Text

ኅዳር 17 2019 ኢትዮጵያ ባለፋት ሶስት ወራት ከውጭ ሀገር ላስገባቻቸው ምርቶች 6.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ ። ከዚህ ውስጥ ለነዳጅ የወጣው ወጪ ከባለው አመት አኳያ ሲታይ የ70 በመቶ ብልጫ እንዳሳየ አስረድተዋል። የነዳጅ ወጪ ሊጨምር የቻለውም በነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል። ከነበረው አለም አቀፍ ቀውስ አንፃር ሲታይ ኢትዮጵያ ነዳጅን በድጎማ ማቅረቧ ብቻ ሳይሆን ያስተዳደረችበት ሁኔታ አስደናቂ እንደነበረም አስረድተዋል። ባለፉት 3 ወራት ለገቢ ምርት 6.5 ቢሊን ዶላር ያወጣችው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ ለወጭ ገበያ ካቀረበችው ምርት ሽያጭ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ይህም ከቀዳሚው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል። ከሰርቪስ ወይንም ከአገልግሎት 2.9 ቢሊዮን ዶላር፣ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ደግሞ 1.28 ቢሊዮን ዶላር በ2019 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት መገኘቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ንጋቱ ሙሉ

Open in Telegram
Views1,110−29%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h109
3 h1,110
  1. Total to date1,110
#27303Text

ኅዳር 17 2019 “ሰራተኛ አጥተን ታራሚ እስረኞችን እያሰራን ነው” መንግስት በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ ሰራተኛ በማጣት ታራሚ እስረኞችን ለማሰራት እየተገደደ ነው ተባለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ችግር ቢኖርም የዛኑ ያክል ሰራተኛ ማግኘትም ችግር ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ቀለም ቀቢ፣ፅዳት ባሉ ስራዎች ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ማግኘት ከባድ እየሆነብን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የስራ አጥነት ችግር መኖሩን አንስተው የዛኑ ያክል ስራ መራጭ ትውልድም በዝቷል ብለዋል። ይህንን ሀሳብ የኢትዮጵያ ወላጆች በደንብ ያድምጡኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣በቀጥታ ክትትል የማደርግባቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሁሉ በቂ ሰራተኛ እያጣን እየተቸገርን ነው ብለዋል። በዚህ ምክንያት በቀን 600 እና 700 ብር እየከፈልን ታሳሪ ታራሚዎችን ቀጥረን ለማሰራት እየተገደድን ነው ብለዋል። እነሱ ላይ ሁሉ ስራው በዝቶ ጫና እየተፈጠረባቸው ነው ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ብዙ የስራ እድል መፈጠር ቢኖርበትም ስራ መራጭ የመሆን ችግርም መቀየር አለበት ነው ያሉት። ቴዎድሮስ ወርቁ

Open in Telegram
Views1,230−22%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h477
3 h1,230
  1. After 1 hour477
  2. Total to date1,230
#27302Text

ኅዳር 17 2019 የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት ከግብርናው ዘርፍ የበለጠ እድገት ማሳየት ጀምሯል ተባለ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢንዱስትሪው ግብርናውን እንዲመራው የማድረግ ፍላጎት ዘንድሮ የሚፈለገውን ሽግግር ማሳየት ጀምሯል ብለዋል። በዚህ ዓመት የግብርናው ዘርፍ እድገት 7.7 በመቶ ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢንዱስትሪው እድገት ግን 12.3 በመቶ ይሆናል ብለዋል። ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት(GDP) አንፃር የግብርና ድርሻ 31.4 በመቶ ሲሆን ግንባታን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ድርሻ ግን 31.8 በመቶ ነው ሲሉ አስረድተዋል። አገልግሎት አሁንም ቀዳሚው ዘርፍ ሲሆን የዘንድሮ እድገቱ 9.9 በመቶ ይሆናል፣ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ ደግሞ ድርሻው 33.8 በመቶ ነው ተብሏል። ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

Open in Telegram
Views1,300−17%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h576
4 h1,300
  1. After 1 hour576
  2. Total to date1,300

All posts

Connections