Account
Sheger Press️️

Sheger Press️️

Official channel of sheger press Contact @Birukepromo

Username
@sheger_press
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers35,685
Avg views per post, 7d3,709last 7 days
ERR10.39%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 23, 20264,683
Nov 24, 20264,536
Nov 25, 20263,800
Nov 26, 20261,393

Most viewed this month

  1. 01
    Views5.04K
    Forwards—
    Reactions39
    Comments—
  2. 02

    የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ረድኤት እና ምልጃቸው አይለየን 🙏 አባታቸው ይስሃቅ የሮም ነገሥታት ወገን ስለሆኑ ከነገሥታት ወገን የምትሆን ሚስት ቢትታጭላቸውም እምቢ ብለው ወደ አባ ጳኩሚስ ገዳም ገቡ፡፡ በምንኩስና ስማቸው ዘሚካኤል ተብለው የሚጠሩትና ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ አረጋዊ፡፡ ገና በትንሽ እድሜያቸው መመንኮስ ቢፈልጉም የንጉሥ ልጅ ስለነበሩ የአባታቸውን ንግስና ወራሽ ይሆናሉ ተብለው በመታሰባቸው፣ ዓለምን ንቀውና ቆርጠው ገዳም መግባታቸውን በተለያዩ ፈተናዎች ካረጋገጡ በኋላ በ14 ዓመታቸው ምንኩስና ሰጧቸው፡፡ ዘሚካኤልም ከእንጦንስና ከመቃርስ ከጳኩሚስም የምንኩስና መንፈሳዊ ሐረግ 4ኛ ትውልድ ሆኑ፡፡ የአባ ዘሚካኤል እናት ንግሥት ዕድናም የልጃቸውን ዜና ሰምተው መንኩሰው የሴቶች ገዳም ገብተዋል፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት በዘሚካኤል መሪነት በ460 ዓ.ም አክሱም ከተማ ሲገቡ እናታቸው ቅድስት ዕድናም ልጃቸውን ተከትለው መጥተዋል፡፡ ከሰንበት በስተቀር እህል የማይቀምሱት እነዚህ ቅዱሳን አባ ዘሚካኤልን የበላይ አድርገው ሾሙትና ስሙንም አረጋዊ አሉት፡፡ ተስዓቱ ቅዱሳን ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባርከዋታል፣ በትምህርታቸው የእምነቷን መሠረት አጽንተውታል፡፡ ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት በጸሎት እየተጉ አብረው ከተቀመጡ በኋላ ተለያዩ፡፡ አቡነ አረጋዊ ከሩቅ ሆነው የዳሞን ተራራ ባዩት ጊዜ እጅግ ወደውት ሲጠጉት ረጅሙን ገደል ጫፉ ላይ ለመድረስ መውጫ ቢያጡ ሌሊቱና ቀኑን ሁሉ በጸሎት አሳለፉ፡፡ ከሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በኋላ ቅዱስ ሚካኤል “እግዚአብሔር ወደ ተራራው ጫፍ የምትወጣበትን ነገር እስኪያዘጋጅልህ ጥቂት ታገስ” ብሏቸው ሁለት ሱባኤ በዚያ ቆዩ፡፡ ከዚያም ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ዘንዶ በቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አስወንጭፏቸው ደብረ ዳሞ ላይ ሲወጡ መስቀላቸውና መጎናጸፊያቸው ያረፈበትና ቅርጽ ዛሬም ድረስ በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ ጌታችን ለአቡነ አረጋዊ ተገልጦ  ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም፣ የእህል ችግርም አይኖርበትም፡፡ በልባዊ ጥሞና የገድልህን መጽሐፍ የሰማ ያለስንፍና በፍጹም መታመን የንባቡን ኃይለ ቃል ያሰማ እኔ ለችግሩ ሁሉ ፈጥኜ እደርስለታለሁ፣ አንተም የሞት ጥላ አያርፍብህም፣ እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ እንጂ” ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ አረጋዊም ደቀ መዝሙራቸው ማትያስን ጠርተው ጌታችን የሰጣቸውን ቃልኪዳን ከገድላቸው ጋር ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆን አዘዙት፡፡ ጌታችን እንደነገራቸውም በጥቅምት 14 ቀን ተሰውረዋል፡፡ ቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና ትጋታቸው የዘለዓለሙን መንግስት በመናፈቅ ነውና ዘወትር በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

    Text
    Views5.02K
    Forwards—
    Reactions27
    Comments—
  3. 03

    መዘዞ ከተማና አከባቢውን ለመውረር ተንቀሳቅሶ የነበረው የጠላት ሠራዊት ጠንካራ የፀረ ማጥቃት እርምጃ ተወስዶበት ከባድ ኪሳራ ተከናንቦ መበተኑ ተገለፀ! መነሻውን ከጣርማበር፣ ከደብረሲና እና ከሰላድንጋይ አድርጎ ወደ መዘዞ የተንቀሳቀሰው የፀረ-ሕዝቡ አገዛዝ ሠራዊት፡ በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ 501ኛ ኮር 72ኛ ክ/ጦር ተመትቶ ወደ መጣበት መመለሱን የኮሩ ቃል አቀባይ አስታወቀ። በርካታ የመካናይዝድ ኃይል አሰልፎ በሁለት አቅጣጫ ማለትም፡ በጣርማበርና በሰላድንጋይ በኩል ወደ መዘዞ ከተማ ለዘረፋና ጭፍጨፋ በቀን 14/03/2019 ዓ.ም ጥዋቱ 1:00 ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ ሲጋጋጥ የዋለው የጠላት ኃይል በአይበገሬዋ 72ኛ ክፍለ ጦር በመልሶ ማጥቃት ሲገረፍ መዋሉ ታውቋል። የፀረ-ሕዝቡ ስርዓት አገልጋይ የሆነው ሠራዊት በተደጋጋሚ የመካናይዝድ ኃይል በመጠቀም መንዝና ግሼ አውራጃን ለመቆጣጠር ሲጋጋጥ የከረመው ጠላት፡ ዛሬም በከፍተኛ ወኔ ከሦስት ከተማዎች በመካናይዝድ የታገዘ በርካታ እግረኛ ኃይልን ይዞ መዘዞን ለመቆጣጠር የሞከረው ከታላቅ ሽንፈት ጋር ከሽፎበታል።  ዛሬም ከትላቱ ያልተማረው ይሕ አረመኔ አገዛዝ ዛሬም እደትላቱ ከባድ ኪሳራ ያስተናገደው ጠላት፡ በርካታ የሠራዊት አባላት ማስጨረሱ ተረጋግጧል። በዚሕ አውደ ውጊያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ እግረኛ የሠራዊት አባላት መሞታቸውና መቁሰላቸው ሲታወቅ፡ ሙትና ቁስለኞችን በኦራል መኪና ማመላለሱ ሲገለፅ ያቀደውን ሳያሳካ ወደ መጣበት መመለሱ ተሠምቷል።

    Text
    Views5K
    Forwards—
    Reactions26
    Comments—
  4. 04

    ቅዱስ ቂርቆስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ 🙏 የሚያገኛቸውን መከራ ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ከመስከሩ የክብር አክሊል ከተቀዳጁ ሰማዕታት የሦስት ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ የሮም ግዛት በሆነው አንጌቤን በክርስትና ሃይማኖት ጸንታ የምትኖርና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስንም በስርዓት ያሳደገችው ደግ ሴት ነበርች፡፡ በዘመኑ የነበረውን አረማዊ አስተዳዳሪ እለእስክንድሮስን በመፍራት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ብትሰደድም እለእስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት። ወታደሮችም እርሷንና ልጇን ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧቸው። መኮንኑም “ስምሽን ንገሪኝ” ቢላት “ስሜ ክርስቲያን ነው” አለችው። መኮንኑ በብስጭት ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንም “ስምህን ንገረኝ” ሲለው “ስሜ ክርስቲያን ነው፤ እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው” ሲል መለሰለት። ቅድስት ኢየሉጣንም “ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል” ሲላት “የምንሰግድለት አንድ ክርስቶስ ብቻ ነው” አለችው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም እየደጋገመም “እኔ ክርስቲያን ነኝ” ብሎ በመጮሁ ምላሱን ቢያስቆረጠው እግዚአብሔር ፈውሶታል፡፡ መኮንኑ መከራ አጸናባቸው፤ በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ። በፈላ ውሃ ውስጥ ሲከታቸውም ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው፡፡ እናትና ልጅ በክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ። ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላም ጥር 15 ቅዱስ ቂርቆስን ጥር 16 ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣን ሰይፏቸው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል፣ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል። ዛሬም በየገዳማቱ ዓለምን ንቀው የሚኖሩ መነኮሳትና ገዳማውያን በጸሎታቸው ኃይል ያደርጋሉ፡፡ ከዓለም ክብር የክርስቶስን ክብር፣ ከሥጋ ደስታ መንግስተ ሰማያትን መርጠዋልና፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውን እናጽና፡፡        ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

    Text
    Views4.73K
    Forwards—
    Reactions17
    Comments—

Latest posts

#16079Text

የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።   በዚህ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በመመልከት በተለያዩ ወሳኝ እና አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱት ዋና ዋና ጥያቄዎች መካከል ቀጥሎ የተዘረዘሩት ይገኙበታል፦ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የወጪ ንግድ እና የታክስ አሰባሰብ፦ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት አሁን ያለበት ሁኔታ እንዴት ይገለጻል? የወጪ ንግድ ገቢው አፈጻጸም ምን ይመስላል? እንዲሁም የታክስ አሰባሰብ ሂደቱ ምን መልክ አለው የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት ተነስተዋል። የአካባቢ ምርጫ አለመካሄድ፦ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት የአካባቢ ምርጫ አለመደረጉ እንዴት ይታያል? ምርጫው በተጠቀሱት ዓመታት እንዳይካሄድ ያደረገው ምክንያት ምንድን ነው? የሕዝብና ቤት ቆጠራ፦ ከ1997 ዓ.ም በኋላ መካሄድ የነበረበት 3ኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ አለመደረጉ በዕቅድ፣ በሀብት ክፍፍል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር መፍጠሩ ተጠቁሟል። በዚህም ምክንያት ቆጠራው አለመካሄዱ ምን ችግር እንዳስከተለ እና መቼ ሊከናወን እንደሚችል ጥያቄ ቀርቧል። የፖለቲካና የፕሬስ ምህዳር እንዲሁም ሰብአዊ መብት፦ የፖለቲካ እና የፕሬስ ነጻነት ምህዳር ይበልጥ እንዲሰፋ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለማስቆም መንግሥት ምን እየሠራ እንደሆነ እና ለወደፊት ምን እንደታቀደ ተጠይቋል። የሰላምና የጸጥታ ችግሮች፦ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ የጸጥታ ችግሮች፣ የንጹሐን ሰዎች ሞት እና የንብረት ዝርፊያ እንደቀጠለ መሆኑ ተነስቷል። መንግሥት ይህንን ሁኔታ ለማስቆም በአጭር ጊዜ ምን እየሠራ እንደሆነ እና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ምን ዕቅድ እንዳለው ጥያቄ ቀርቧል። የሀገራዊ ምክክር ምክረ ሐሳቦች ትግበራ፦ በሀገራዊ ምክክር የተገኙ የጋራ ምክረ ሐሳቦችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር እንዲሁም በሕግ፣ በፖሊሲ እና በተቋማዊ ማሻሻያዎች ለመተግበር መንግሥት ምን ዝግጅት እና የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅቷል? በትግበራው ሂደትስ ከመላው ኢትዮጵያውያን እና ከኢትዮጵያ ወዳጆች ምን ይጠበቃል? በምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎች አሁንም የቀጠሉ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።   ለዓለም አሰፋ   ኀዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም

Open in Telegram
Views751−80%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#16078Photo

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑል ሲያሸንፍ ዩናይትድ አቻ ተለያየ በተካሄዱ የአውሮፓ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ሊቨርፑል እና ኢንተር ሚላን ድል ሲያስመዘግቡ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሎ ሙኒክ ሽንፈት አስተናግዷል። በሜዳው ስቱትጋርትን ያስተናገደው ኢንተር ሚላን በሱቺች እና በማርቲኔዝ ግቦች ታግዞ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሌላ በኩል ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ስፖርቲንግን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል። የሌሎች ጨዋታዎች አጠቃላይ ውጤት፦ * ብሩጅ 0-3 ሊቨርፑል፦ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ አይሳክ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች እና በቨርትዝ አንድ ግብ ታግዞ ሰፊ ድል አስመዝግቧል። * ሊል 2-1 ባየር ሙኒክ፦ የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በአፕሜካኖ አማካኝነት አንድ ግብ ቢያስቆጥርም፣ ኡዳ እና ፓቭሎቪች በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠሩት ግብ ሊል ድል ቀንቶታል። * ፒኤስጂ 2-2 ሮማ፦ ብርቱ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ለፒኤስጂ ዛባርኒ እና ዴምቤሌ፣ ለሮማ ደግሞ ሄርሞሶ እና ማለን ግቦቹን በማስቆጠር ነጥብ ተጋርተዋል። * አትሌቲኮ ማድሪድ 2-0 ቫይኪንግ፦ የስፔኑ ክለብ በሶርሎት እና በአልቫሬዝ ግቦች ንጹህ ድል አግኝቷል። * ሻካታር 0-1 ፌነርባቼ፦ ፌነርባቼ በሙሪክ ብቸኛ ግብ ከሜዳው ውጭ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ተመልሷል።

Open in Telegram
Views1,770−52%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#16077Text

የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን🙏 በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡ በኃይል በጸጋና በመንፈሳ ተሞልቶ የወንጌሉን ብስራት ይሰብክ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡  ታላቁ ሰማዕት የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ኋላም የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን ጠይቆ ወደ ጌታችን በመሔድ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፡፡ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐ ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን ተሹሟል፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን ቢያስፋፋ አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸውና በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በተወለደበት ጥር 1 ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ሲወግሩትም ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ እንደ አምላኩ ለሚወግሩት ሰዎች “የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ገዳማውያን ሰማዕቱን አብነት አድረገው በጸሎትና በጾም እየተጉ የሥጋ ፍላጎትን ድል ያደርጉታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡  ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Open in Telegram
Views1,580−57%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#16075Text

አምስት ሴቶችን የገደለው ግለሰብ‼ ​በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ሽረ ከተማ፣ ቀደም ሲል በግድያ ወንጀል የ22 ዓመት እስራት ተፈርዶበት የነበረው የ54 ዓመቱ ተስፋይ ገብረዮሐንስ ከእስር ከወጣ በኋላ በ20 ቀናት ውስጥ አምስት ሴቶችን ገድሎ ፆታዊ ጥቃት መፈጸሙን ፖሊስ ገለጸ። ​የዞኑ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ እንዳስታወቁት፣ ተጠርጣሪው መስከረም 25/2019 ዓ.ም. በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት ከእስር ከወጣ በኋላ ከጥቅምት 19 እስከ ኅዳር 8 ባሉት ቀናት ውስጥ ቢላዋ፣ መጥረቢያና ድንጋይ በመጠቀም ወንጀሉን ፈጽሟል። ​በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈው በሻይ ቡና ንግድና በዩኒቨርሲቲ ትምህርት ላይ የነበሩት ዮርዳኖስ ሓጎስ፣ የሻለም ዘነበ፣ ገነት ደጀን፣ ሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር እና ወሰንየለሽ መኮንን ናቸው። በተጨማሪም ተጠርጣሪው የአንዷን ሟች የ5 ዓመት ሕፃን ልጅ ያገተ ሲሆን፣ ሕፃኗ ያለችበት ሁኔታ እስካሁን አልታወቀም። ​ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ውሎ ድርጊቱን ያመነ ሲሆን፣ የሕፃኗን አድራሻ የማፈላለግ ምርመራ ቀጥሏል። የትግራይ ባላደራ አስተዳደር የሴቶች ጉዳይ ቢሮም ድርጊቱን በማውገዝ በወንጀለኛው ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል። ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

Open in Telegram
Views3,840+4%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#16074Text

እናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ከክፉ ነገር ትከልለን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ትሙላልን🙏 መንገስተ ሰማያት መግቢያ ኪዳን አባቶቻችን የሃዘን ብዛት የእንባ ጎርፍ አይን ያጠፋል፣ ፊት ያንጣጣል፣ ልብ ይሰውራል አካልንም ያዝላል ይላሉ፡፡ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደቷ ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ድረስ አልቅሳለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ ሆና ከእርሱ ከተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ጸልያለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ይህም ታላቅ በዓል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እየተባለ በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን ይከበራል፡፡ ይህ ዕለት ድንቅ ተአምራትም ያደረገችበት ነው፡፡ ስምዖን የሚባል የአባታችን የቅዱስ አብርሃምን ታሪክ የሰማና እንደ እርሱ እንግዳ መቀበል የሚወድ ሰው ነበር፡፡ ጠላታችን ሰይጣንም እንግዳ መስሎ ወደ ቤቱ በመምጣት ልጅህን አርደህ አብላኝ አለው፡፡ እርሱም “አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው” በሚል እሳቤ ያለውን አደረገ፡፡ ሲያቀርብለትም ቅመስልኝ አለው፤ እሺ ብሎ ሲቀምስለት በዚያው ተዋሐደው፡፡ ከዚህ በኋላ በላኤ ከቤተሰቦቹ ጀምሮ “በላዔ ሰብእ” ወይም “ሰው በላው” እስኪባል ድረስ 78 ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ የቆሰለ ነዳይ አይቶ ሊበላው ሲቀርብ ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፡፡ ነዳዩ ግን ውሃ አጠጣኝ ሲል በሥላሴ፣ በቅዱሳን ሁሉ ስም ቢለምነው፤ አልሰማውም፡፡ በድንግል ማርያም ስም ሲለው በአእመሮው አቃጨለበትና “ምህረት እንደምታሰጥ በልጅነቴ ሰምቻለሁ” ብሎ ከያዘው ውሃ ጥቂት አጠጣው፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አጊኝቶ ሊበላው ሲል “አንተ ያ በላዔ የምትባል ነህ?” አለው፡፡ ለካ ይህ ነገር ተሰምቶብኛል ብሎ ወደ አንድ ዋሻ ሔዶ በጸጸት ሞቷል፡፡ የጨለማ መላዕክት ነፍሱን በጌታ ፊት ሲያቀርቧትም እመቤታችን “ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ” አለችው፡፡ ጌታችንም ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋና ፈጣሪውን የካደ እንዴት ይማራል አላት፤ እመቤታችንም በስሜ የተጠማውን አጠጥቷል ስትል ነፍሱን አስምራዋለች፡፡ እኛንም በቃል ኪዳኗ ታስምረን፣ አማላጅነቷም አይለየን፡፡ አሜን!!! ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Open in Telegram
Views3,790+2%vs avg
Forwards—
Reactions20
Comments—
#16072Photo

በመቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች 12 ስራ ጀመሩ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች መካከል 12ቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ግርማይ አስታወቁ። በመቐለ ከተማ 750 የሕዝብ ትራንስፖርት ታክሲዎች እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊው፣ ለነዚህ ታክሲዎች ቅድሚያ የነዳጅ አቅርቦት እንዲሰጣቸው በማድረግ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እና አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉን ገልፀዋል። የተወሰዱት እነዚህ እርምጃዎች በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲሁም የነዳጅ ስርጭትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ያለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ነዳጅ ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋሉን እና አለመዋሉን ለመለየትና ለመቆጣጠር እንዲያስችል፣ የነዳጅ ሽያጭ በቴሌብር ዲጂታል ግብይት ብቻ እንዲፈጸም መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በነዳጅ አቅርቦት ላይ ምንም ዓይነት መቆራረጥ ወይም እጥረት እንዳይፈጠር ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑንም የቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋይ ግርማይ ጨምረው ገልጸዋል።

Open in Telegram
Views4,220+14%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#16071Text

እንኳን ለእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 #በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በግብጽ በስደቷ፣ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ከሙታን ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ለተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ጡዋፍ ዘቢብ መባእ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ እኛም ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከእመቤታችን ጋር ዕለቱን በየወሩ በ16ኛው ቀን በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ይህን ቃል ኪዳኗን ያመኑ፣ በእናትነት ፍቅሯ ከምልጃዋ በረከት የተካፈሉ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን ቅድስት ሆይ ለምኝንልን ይሏታል፡፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር ሳይበግራቸው በጸሎተው ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የእመቤታችን በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፡፡  ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Open in Telegram
Views4,160+12%vs avg
Forwards—
Reactions30
Comments—

All posts

Connections