Account
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

ዜና ከምንጩ

Username
@addismaleda
Category
News and media
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers33,700
Avg views per post, 7d2,605last 7 days
ERR7.73%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 24, 20264,025
Nov 25, 20263,022
Nov 26, 2026964

Most viewed this month

  1. 01

    በራያ አላማጣ ከ1,600 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ሪፖርት በማድረጋቸው የጥቅምት ወር ደመወዝ መከፈሉን የራያ አላማጣ ባለ አደራ አስተዳዴር ለአዲስ ማለዳ ገለጸ ማክሰኞ፣ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በራያ አላማጣ ከ1,600 በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ሪፖርት በማድረጋቸው የጥቅምት ወር ደመወዝ መከፈሉን የራያ ባለአደራ መንግስት አስተዳደር አስተባባሪ ሞላ ህሉፍ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ። ሞላ ከክልሉ ባለ አደራ አስተዳደር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ምርጫ ከተካሄደ በኋላ የመንግሥት ሠራተኞች ሪፖርት አድርገው ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጉን አንስተዋል። በዚሁ መሠረት በ2018 ዓ.ም በሥራ ላይ የነበሩ ሠራተኞች መጥተው ሪፖርት  ያደረጉ ከ1,600 በላይ ሠራተኞች ደመወዝ እንደተከፈላቸው ጠቁመዋል። ባለ አደራ አስተዳደሩ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የመንግስት ሰራተኞች የሚሰሩበት ተቋም በመሄድ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።  ለመንግሥት ሠራተኞቹ የ2019 ዓ.ም የጥቅምት ወር ደመወዝ መከፈሉን የገለጹት ሞላ የተከፈለው የአንድ ወር ማለትም የጥቅምት ብቻ መሆኑን አስረድተዋል። ከዚህ በፊት ባሉ ጊዜያት ያልተከፈለ ደመወዝን በተመለከተ “የሁሉም ጥያቄ” መሆኑን ጠቅሰው የፌደራል መንግሥትና የክልል መንግሥት እንዲሁም የአስተዳደሩ አካላት ተነጋግረው በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሠረት የሚፈጸም ይሆናል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። በፌደራሉ መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ የሚሰራው ባለአደራ አስተዳደር ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዝ እንደሚከፈል አስታውቆ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶችና አካባቢዎች ይከፈልበታል ከተባለበት ቀን አንጻር የደመወዝ ክፍያው መዘግየቱ ይታወሳል። ሞላ አሁን ላይ ሠራተኞች ሪፖርት አድርገው የጥቅምት ወር ደመወዝ በመከፈሉ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራን እንዲሁም ከወረዳ እስከ ቀበሌ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራ መግባትና ሥራ መሥራት መጀመራቸውን ገለጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል ተቀጥረው በአካባቢው ሲሰሩ የነበሩ ሠራተኞችን በተመለከተ ደግሞ፤ በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ ወይም በራያ አላማጣ ተቀጥረው ቆይተው ሪፖርት ላደረጉና ወደ ሥራ ለተመለሱ እየተከፈለ መሆኑን በመግለጽ፣ በአማራ ክልል ተቀጥሮ በአማራ ክልል ያለ ሠራተኛን የሚመለከተው ግን የአማራ ክልል መሆኑን ጠቁመዋል።  ይሁን እንጂ በእነዚህ  አካባቢዎች ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል ስር ይተዳደሩ በነበረበት ወቅት ሰራተኞች የደመወዝ ክፍያቸው ሳይቆራረጥ በአማራ ክልል እየተከፈላቸው እንደነበረ አዲስ ማለዳ ምንጮቿን ጠቅሳ መዘገቧ አይዘነጋም፡፡ አስተባባሪው ይህንን ጨምሮ ያልተከፈለ ደመወዝ ጉዳይ የፌደራል መንግስቱ እና የትግራይ ክልል መንግስትን ተጨማሪ ውይይቶች እና አቅጣጫን የሚጠይቅ መሆኑን ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንስተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ የፌደራል መንግስቱ በወቅቱ የደመወዝ ክፍያ ቢያስገባም አስተዳደሩ ለመክፈል ዘግይቷል ማለታቸው ይታወሳል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

    Link preview
    Views4.35K
    Forwards—
    Reactions7
    Comments—
  2. 02

    የእነ ዮሐንስ ቧያለው ጉዳይ ለታኅሣሥ 6 ሲቀጠር በርካታ ተከሳሾች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ወደ ሌላ ቦታ መዛወራቸውን ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ ማክሰኞ፣ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእነ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር ለማቅረብ ለታኅሣሥ 6 ቀን መቀጠሩን እና ከተከሳሾቹ መካከል ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ከዚህ ቀደም “ቅጣት” ከሚባለው ቦታ የወጡትን መልሰው “ታንከር” ተብሎ ወደሚጠራ ቦታ መወሰዳቸውን ጠበቃቸው ሰለሞን ገዝኸኝ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ። ጠበቃው እንደገለጹት በመዝገቡ ቀደም ብለው ተከስሰው ከነበሩ 16 ተከሳሾች ውስጥ 12ቱ ክስ ተቋርጦ የወጡ ሲሆን፣ አራቱ ተከሳሾች ደግሞ “የቅድመ ሁኔታውን አንፈርምም” በማለት ሳይወጡ ቀርተዋል። ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከ“ቅጣት” ቦታ ወጥተው የነበሩት ዮሐንስ ቧያለው  አሁን አብረው ባይመለሱም፣ ቅዳሜ ማታ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሌሎች ተከሳሾች ወደ “ታንከር” ተመልሰው እንዲገቡ መደረጉን ጠበቃው አመልክተዋል። በመሆኑም ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ፣ እስክንድር ሽፈራው፣ ሲሳይ አውግቸው (ዶ/ር)፣  ወንድወሰን አሰፋ (ዶ/ር)፣ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም (ዶ/ር) እና መንበረ አለሙ መመለሳቸውንና እሳቸውም ገብተው ለመጠየቅ እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል። የዛሬው ቀጠሮም አንዱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደነበር አንስተዋል። በተጨማሪም የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር ለማቅረብ ችሎቱ ለታኅሣሥ 6 ቀጠሮ የሰጠ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት የመከላከያ ማስረጃ ዝርዝር ያላቀረቡት ተከላከሉ የተባሉበት የብይን ግልባጭ እና የተገለበጠ የምስክሮች ቃል ባለመሰጠቱ መሆኑን ጠቁመዋል። ሪጅስትራር ገልብጦ ስላልጨረሰ ማስረጃውን ማዘጋጀት እንዳልቻሉና በቀጣይ ለማቅረብ እንዲቻል ብይኑና የምስክሮች ቃል እንዲሰጣቸው እንዲሁም ይግባኝ ለማለት የመዝገብ ግልባጭ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን አስረድተዋል። እንዲሁም ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ የተቋረጠው ክስን አስመልክቶ አላግባብ ታስረን ስለቆየን ችሎቱ ጉዳዩን ማየት መቀጠል የለበትም የሚል አቤቱታ ቀርቦ ብይን እየተጠበቀ መሆኑን እና የተወሰኑት ለሕዝብ አይጠቅሙም፣ የተወሰኑት ይጠቅማሉ በማለት የተሰጠውን ፍርድ ቤት ማየት እንደነበረበት ገልጸዋል። በመሆኑም እስራታቸው ሕገ ወጥ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ሊለቃቸው እንደሚገባ መናገራቸውንና የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በመጣስ የተፈጸመ የእስር ቦታ ዝውውር እንደተደረገ አንስተው እሳቸው ሊገቡ ሲሉ እንደተከለከሉ አንስተዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

    Link preview
    Views4.2K
    Forwards—
    Reactions21
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photo
    Views3.92K
    Forwards—
    Reactions—
    Comments—
  4. 04

    በጎጃም እና በጎንደር ሕዝብ ላይ በጅምላ የስም ማጥፋትና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ተፈጽሟል በሚል በአቶ ኢዩ ጩፋ ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ጥቆማ ቀረበ ረቡዕ ፣ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በአማራ ክልል በሚገኘው የጎጃምና የጎንደር አካባቢ ሕዝብ ላይ በኃይማኖት ስብከት ሽፋን በጅምላ የስም ማጥፋትና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በአቶ ኢዩ ጩፋ ላይ ለኢፌዲሪ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይፋዊ የወንጀል ጥቆማ መቅረቡ ታወቀ። የወንጀል ጥቆማውን ትናንት ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያቀረቡት ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝ ናቸው። አዲስ ማለዳ በተመለከተችው ደብዳቤ ላይ ጠበቃው እንደገለጹት፣ በኢፌዴሪ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ አንቀጽ 11 መሠረት ማንኛውም ሰው ወንጀል መፈጸሙን ሲያውቅ ለፖሊስ የማሳወቅ መብትና ግዴታ ስላለው፣ እንዲሁም ራሳቸው በአካባቢው በሚኖሩ ተወላጅ ዘመድ አዝማዶቻቸው አማካይነት ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸው በመሆኑ ይህንን ጥቆማ አቅርበዋል። በጥቆማ ደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው፣ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ) አካባቢ በሚኖረው ሕዝብ ላይ አንድ ግለሰብ በኃይማኖት ስብከት ሰበብ “ጠንቋይ” በማለት ስም በማጥፋቱ እና በማዋረዱ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበት በሕዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር መዋሉንና በኋላም በሽምግልና መታለፉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ሌሎች ግለሰቦች ከዚህ ድርጊት መማር ሲገባቸው፣ በተመሳሳይ መልኩ የሌላ አካባቢን ሕዝብ በመጥቀስ የመሳደብና የማንቋሸሽ ተግባር መፈጸማቸውን ቀጥለዋል ብለዋል - ጠበቃው። ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ በዝርዝር ባቀረቡት የወንጀል ጥቆማ ላይ ተጠሪው አቶ ኢዩ ጩፋ ሁለት ከባድ የወንጀል ድርጊቶችን መፈጸማቸውን አመልክተዋል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ተጠሪው በህዳር ወር 2019 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኝ አንድ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ በኃይማኖት ስብከት ሰበብ የምዕራብ ጎጃም፣ የምሥራቅ ጎጃም፣ የሰሜን ጎጃምና የአዊ አካባቢ ሕዝብን በጅምላ በመጠቅለል “መተተኞች ናቸው” በማለት መናገራቸውን ጠቅሰዋል። ይህ ንግግራቸውም በቪዲዮ ተቀርጾ በተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም በስፋት ተሰራጭቷል። የጎጃም አካባቢ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመሆን ሀብት በማፍራት የሀገሪቱ የሀብት ምንጭ ሆኖ የቆየ፣ አርሶ፣ አምርቶና አስተምሮ በላቡና በልፋቱ ሀብት፣ ዕውቀት፣ ዝና፣ ልዕልና፣ ቸርነትና ደግነት ያተረፈ ሕዝብ መሆኑ በጥቆማው ተገልጿል። ተጠሪው ይህንን ሁሉ የሕዝቡን የሥራ ትጋት፣ ባህል፣ ሀገር ወዳድነትና ጥበብ በመካድ ሕዝቡ ሀብትና ዕውቀት ያገኘው በአስማት፣ በጥንቆላና በመተት እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው የሕዝቡን መላ እሴት እጅግ ዝቅ ያደረገ መሆኑን ጠበቃው አስረድተዋል። ድርጊቱም በክልሉ ውስጥም ሆነ ከክልሉ ውጪ በመላው ሀገሪቱ የሚኖሩ የጎጃም ተወላጅ አርሶ አደሮችን፣ ነጋዴዎችን፣ ምሁራንን፣ የኃይማኖት ሰዎችንና ተማሪዎችን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ፣ እንዳይታመኑ የሚያደርግና በገንዘብ የማይተመን ከፍተኛ የሥነ-ልቦናና የማኅበራዊ ሕይወት ጉዳት ያስከተለ አደገኛ ድርጊት መሆኑ በማመልከቻው ተመላክቷል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ተጠሪው አቶ ኢዩ ጩፋ በሌላ የኃይማኖት ስብከት መድረክ ላይ የጎንደርን እና የጎጃምን ሕዝብ ዒላማ በማድረግ “የጎጃም የሌ፣ የጎንደር የሌ፤ እዚህ ቤት የገባ ሁሉ ይቀጠቀጣል፣ ይረገጣል፤ የትም ይሥራ እናፈርሰዋለን” በማለት በአደባባይ የጥላቻ፣ የውግዘትና የማስፈራሪያ ንግግር ማድረጋቸውን ጥቆማ አቅራቢው ገልጸዋል። እነዚህ ሁለት ንግግሮች በኢትዮጵያ ሕግ ሦስት ዋና ዋና የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚጥሱ መሆናቸውን ጠበቃ ሰለሞን በማመልከቻቸው ዘርዝረዋል። አንደኛው በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613 (ስም ማጥፋትና ማዋረድ) እንዲሁም አንቀጽ 486 (ሕዝብን ማነሳሳትና የሐሰት ወሬ ማሰራጨት) ሲሆን፣ በሕዝብ መካከል መጠራጠርን፣ ጥላቻን ወይም ግጭትን የሚፈጥር የሐሰት ወሬ ማሰራጨት እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም በገንዘብ መቀጮ የሚያስቀጣ ወንጀል መሆኑ ተጠቅሷል። ሁለተኛው የጥላቻ ንግግርንና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4፣ 5 እና 7(1) ሲሆን፣ ማንኛውም ሰው በአደባባይ ስብሰባዎች፣ በብሮድካስት ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በጽሑፍ፣ በምስል፣ በድምፅ ወይም በቪዲዮ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨት በሕግ የተከለከለ መሆኑንና እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተገልጿል። ሦስተኛው ደግሞ የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 እና 14 ሲሆን፣ ንግግሩ በኢንተርኔትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩቱዩብ ወዘተ) አማካኝነት በመሰራጨቱ በኮምፒውተር ሥርዓት የሚፈጸም ስም ማጥፋትና ሕዝብን የሚያነሳሳ ሐሳብ ማሰራጨት ወንጀል መሆኑን ያመለክታል። በመጨረሻም ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ተጠሪው እነዚህን ሁለት ንግግሮች ሲያደርጉ የሚያሳዩ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ከጥቆማው ጋር አያይዘው ማቅረባቸውን በመግለጽ፣ የኢፌዴሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተገቢውን ምርመራ አጣርቶ ተጠሪውን ለፍትሕ እንዲያቀርብና መሰል ወንጀሎች ወደፊት እንዳይደገሙ የፍትሕ አካላት ሕጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን አዲስ ማለዳ ከደብዳቤው ለመረዳት ችላለች። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

    Link preview
    Views3.63K
    Forwards—
    Reactions53
    Comments—

Latest posts

#23169Link preview

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲስ አበባ የሚሰሩ ኮሪደር ልማት ሥራዎች ሰው ለማፈናቀል ነው ከተባለ በሌሎች ከተሞች የሚሰራው ማንን ለማፈናቀል ነው ሲሉ ጠየቁ ሐሙስ ፣ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እየሰጡ በሚገኙት ምላሽ ከተነሱት ነጥቦች መካከል ኮሪደር ልማት ላይ እየቀረቡ ያሉ ትችቶች የሚገኙበት ሲሆን ሆነ ተብሎ ሰው ለማፈናቀል ነው የሚለውን ትችት በብርቱ ተከላክልከዋል፡፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤  የኮሪደር ልማት እንዴት ያለ እንደሆነ መንገር አያስፈልግም ሲሉ በሚቀርቡት ትችቶች ላይ ገለጻቸውን ይጀምራሉ፡፡ ብዙ የአፍሪካ ወንድሞቻችን መቼ ነው ለእኛ የሚደርሰው የሚሉ ነበሩ የሚሉት ዐቢይ፤ ሥራው ሲጀመር ባለማወቅም ቢሆን የማረከስ ሁኔታ ነበር ብለዋል። አክለውም “ አሁን ደግሞ በቅርብ ጊዜ የምሰማቸው ስሞታዎች እና ክሶች” ኮሪደር የሚሰራው ሰው ለማፈናቀል  ነው የሚል ደካማ ስሞታዎች እና ክሶች እንደሚሰሙ ተናግረዋል፡፡ ዐቢይ ሲቀጥሉም፤ ክሳቸውን፣ ሃሳባቸውን እንቀበለውና “አዲስ  አበባ ላይ የምንሰራው ኮሪደር ሰው ለማፈናቀል ነው፤ የማንፈልጋቸው ሰዎች በዝተው ማለት ነው” ያሉ ሲሆን እነማን እንደሆኑ ግን “እሱ ፈጣሪ ይወቀው” በማለት ይቀጥላሉ። ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ጂማ እና ጅግጅጋ የሚሰራው “ማንን ለማፈናቀል ነው” ሲሉ በጥያቄ መልክ ለእንደራሴዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነት ክሶች በስንፍና የተሞሉ በሀገር ልማት ላይ “ክፉ ጋሬጣ የሆኑ ክሶች”አይጠቅምም ያሉ ሲሆን፣ የሚጠቅመው ደግሞ ከቻልን መተባበር ካልተቻለ ደግሞ “እኛ እንሰራዋለን ዎክ እያደረጉ ፎቶ እየተነሱ መዝናናት ነው እንጂ” የሚሰሩ ስራዎች ማራከስ ጥሩ እንዳልሆነ አጽዕኖት ሰጥተዋል።   አክለውም በከተሞች የሚሰሩ የኮሪደር ስራዎች “ያለማጋነን” የብዙ አፍሪካውያን ፍላጎት እንደሆነ አንስተዋል። ከብዙ ትላልቅ አፍሪካ መሪዎች ጋር የማውራት እድል እንደነበራቸው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሻቸው ምን እንደሆነም አውቃለሁ ሲሉ በመንግስታቸው የተሰራውን ሥራ አወድሰዋል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA

Open in Telegram
Views1,280−51%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—

All posts

Connections