«የተዘረፈውን የሕዝብ ሀብት በማስመለስ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል» – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ብልሹ አሠራር እና ሙስና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል። የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ፣ ዜጎችን የሚያስለቅሱ እና ሥልጣናቸውን ለበደል የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል። እነዚህ ጥቂት ሙሰኞች የሕዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አባላቱ፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዲጂታል ሥርዓት ላይ እንደ ሀገር እየተሠራ ቢሆንም ሙስና አሁንም ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክተዋል። ለሀገር ልማት መዋል የሚገባው ሀብት በጥቂት ሙሰኞች ኪስ መግባቱ የትውልዱን ሞራል እየገደለ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ ችግሩን ማውገዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የዘረፉትን የሕዝብ ሀብት እንዲመልሱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in Telegram
አዲስ ሪፖርተር - NEWS
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addisreporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 24, 2026 | 4,765 |
| Nov 25, 2026 | 4,093 |
| Nov 26, 2026 | 1,780 |
Most viewed this month
- 01Views5.03KForwards—Reactions87Comments—
- 02Views4.79KForwards—Reactions30Comments—
- 03Views4.7KForwards—Reactions28Comments—
- 04Views4.67KForwards—Reactions1Comments—
Latest posts
በአፋርና በሶማሌ ኢሳ ማኅበረሰቦች መካከል ዳግም ያገረሸው ግጭት ወደ ሌሊት ውጊያ መስፋፋቱ ነዋሪዎችን ተናገሩ ለዓመታት በግጦሽ ሳር፣ በውኃና በመሬት ይገባኛል ምክንያት ሲከሰት የቆየው የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማኅበረሰቦች ግጭት ዳግም አገርሽቶ አንድ ወር ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁን ላይ ውጊያው ከቀን ወደ ሌሊት ተሸጋግሮ መቀጠሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለከፍተኛ ሥጋት መዳረጉ ተገለጸ። ቀደም ሲል በአፋር ክልል ዞን 3 በሚገኙት ሀሩካ፣ አቢዳ እና አርጋቶ የድንበር አካባቢዎች ተወስኖ የነበረው ይህ ግጭት፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ ወደ ዞን 1 ገርቢ አካባቢ መስፋፋቱን ነዋሪዎች አመልክተዋል። ከዚህ ቀደም በፌዴራል መንግሥትና በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት በተደጋጋሚ የተደረጉ የዕርቅ ስምምነቶች ዘላቂ መፍትሔ ባለማምጣታቸው፣ የአካባቢው ሰላም ተደጋግሞ እየተናጋና ዜጎች ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆናቸው ተጠቁሟል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 1,430 |
| 5 h | 2,520 |
- After 6 hours2,520
- Total to date2,520
ሲኤንኤን በኢትዮጵያ መቀመስ አለባቸው ያላቸውን 15 ምርጥ ምግቦች ይፋ አድርጓል ዓለም አቀፉ የዜና አውታር የሆነው ሲኤንኤን፡ የኢትዮጵያን የምግብ ባህል ልዩና ጣፋጭ ሲል በማድነቅ፣ ጎብኚዎች ሊቀምሷቸው የሚገቡ 15 ምርጥ የሀገሪቱን ምግቦች በዝርዝር አስቀምጧልል። በሲኤንኤን የጉዞ አምድ ላይ የቀረበው ዘገባ፣ የኢትዮጵያ የአመጋገብ ሥርዓት ከሌላው የአፍሪካ ክፍል የሚለይ የባህል ቅርስ ያለው መሆኑን ተገልጿል። ኢትዮጵያውያን በአንድ ገበታ ተሰብስበው ያለ ሹካና ማንኪያ በእጅና በእንጀራ የሚመገቡበት ማኅበራዊ ባህል እንዲሁም እስከ 16 ቅመማ ቅመሞችን የያዘው በርበሬ ለምግቦቹ ልዩ ጣዕም እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። ዘገባው ከዘረዘራቸው ምግቦች መካከል ሸክላ ጥብስ፣ ክትፎ፣ ዶሮ ወጥ፣ ጥሬ ሥጋ፣ ዱለት፣ ዶሮ ወጥ፣ በያይነት፣ ጥህሎ፣ ፉል፣ እንቁላል ፍርፍር፣ሽሮ፣ የአትክልት ጁስ፣ ዳቦ ፍርፍር፣ ጥብስ እንዲሁም ፓስታ በእንጀራ ይገኙበታል። ዘገባው አክሎም ኢትዮጵያ የጥራት ያለው ቡና መገኛ መሆኗን በማስታወስ፣ ከእነዚህ ጣፋጭ ምግቦች በኋላ የኢትዮጵያን ቡና መቅመስ አስፈላጊ ነው ሲል አስነብቧል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in Telegramመርጌታ ሊባኖስ የባህል መድህኒት ፈውስ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☞ ለመፍትሄ ሀብት ☞ ለህመም ☞ ለመስተፋቅር ☞ ቡዳ ለበላው ☞ ለገበያ ☞ ሚስጥር የሚነግር ☞ ለቀለም(ለትምህርት) ☞ ለመፍትሔ ስራይ ☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ ☞ ሌባ የማያስነካ ☞ ለበረከት ☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) ☞ ለግርማ ሞገስ ☞ መርበቡተ ሰለሞን ☞ ለዓይነ ጥላ ☞ ለሁሉ መስተፋቅር ☞ ጸሎተ ዕለታት ☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ ☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) ☞ ለትዳር ☞ ለድምፅ 👉 0924431917 ይደውሉ መፍትሄ አለን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹። 📞09 24431917 📞09 24431917 👉 የብልት ማነስ 👉የመልፈስፈስ 👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት ለበለጠ መረጃ 👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇 @mergitali በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም 🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር ውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን 🍀🌿🙏ልብ ይበሉ ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
Open in TelegramለChatGPT ወይም ለGemini "ሰላም" ስትለው፣ እሱ በዚያው ቅጽበት አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ጭልጥ አድርጎ እንደሚጠጣ ታውቃለህ? 😂💧 የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት፣ ክላውድ (Cloud) እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚያንቀሳቅሱት ግዙፍ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ጉሮሯቸው በጣም ደረቅ ነው! ሰርቨሮቻቸው ከመጠን በላይ ግለው እንዳይቃጠሉ ለማቀዝቀዝ በቀን እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ንጹሕ ውኃ ይጠጣሉ። እስቲ ይህንን አስቡት አንድ ትልቅ የዳታ ማዕከል በቀን ከ1 እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ ይጠቀማል። ይህ ማለት 50,000 ሕዝብ ያላትን አንዲት ሙሉ ከተማ የውኃ ፍጆታ ብቻውን ይጨርሳል ማለት ነው፤ ከእነዚህ ጋር ውኃ መጋራት ራሱ ይከብዳል! ዋናው ችግር ደግሞ የተጠቀሙት ውኃ ተመልሶ አለመገኘቱ ነው። "የጠጡት" ውኃ በትነት መልክ ወደ ሰማይ ስለሚወጣ፣ ተመልሶ ወደ ወንዙም ሆነ ወደ ቧንቧችን አይገባም። የሚገርመው ደግሞ ከ2022 ወዲህ ከተገነቡት አዳዲስ ማዕከላት መካከል ሁለት ሦስተኛው የተተከሉት ቀድሞውኑ ከፍተኛ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የአካባቢው ገበሬ ቤተሰቡና እንስሳቱ በውኃ ጥም እየተቸገሩ፣ ሰርቨሮቹ ግን "ውኃ አምጡ" ይላሉ። ይበልጥ አሳሳቢው ግን የወደፊቱ ስጋት ነው! በቴክሳስ ብቻ በ2025 ወደ 49 ቢሊዮን ጋሎን ውኃ የጠጡት እነዚህ ማዕከላት፣ በ2030 ጥማታቸው ጨምሮ 399 ቢሊዮን ጋሎን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል። ቴክኖሎጂው መልካም ነው፤ ሕይወታችንንም አቅልሎልናል። ሆኖም የሰው ልጅንና የተፈጥሮን ጉሮሮ እያደረቀ መሆን የለበትም አይደል? አዳዲስ የዳታ ማዕከላት ከመገንባታቸው በፊት "ውኃውን ከየት ነው የምታመጡት? ስንትስ ትጠቀማላችሁ?" ተብለው ሊጠየቁ ይገባል። @Addis_Reporter
Open in Telegramባድመ‼️ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በባድመ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙትን «ቢያራ» እና አጎራባች የሆነውን «ዓዲ አስመሮም» የተባሉ ሁለት ስፍራዎች መልሶ መቆጣጠሩን፣ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶችን የሚከታተለው «አክሌድ» (ACLED) ትናንት ህዳር 15/2019 ዓ.ም አዲስ ባወጣው መረጃ አረጋግጧል። ኤርትራ የክተት አዋጅ ማወጇም ተገልጿል። የኤርትራ ሰራዊት ከባድመ 80 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባሬንቱ በከፍተኛ ሁኔታ ምሽግ እየቆፈረ መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in Telegramቡርኪናፋሶ 61.5ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ግዙፍ የቴክኖሎጂ አካዳሚ መርቃ ከፈተች ቡርኪናፋሶ የወደፊት መሐንዲሶችን ለማፍራት፣ ሳይንሳዊ ነፃነትን ለማጎልበት እና የኢንዱስትሪ እድገትን ለማፋጠን ያለመ 61.5 ሚሊዮን ዶላር የፈጀ የቴክኖሎጂ አካዳሚ እ.ኤ.አ. ኅዳር 23 ቀን 2026 መርቃ ከፈተች። ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ፣ በሀገሪቱ ብሔራዊ በጀት በተመደበ 37.37 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እና በ11 ወራት ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀውን አካዳሚ ቴክኖሎጂክ ዱ ፋሶ የተሰኘውን ተቋም በይፋ መርቀው ከፍተዋል። 60 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ካምፓስ፣ በመጀመሪያ ዙር 250 ተማሪዎችን ተቀብሎ የኒውክሌር ምህንድስና፣ አቪዬሽን (ኤሮኖቲክስ)፣ ማዕድን ማውጣት፣ ብረታ ብረት፣ ኢነርጂ እና የሳይበር ደህንነትን ጨምሮ በ11 ስትራቴጂካዊ የትምህርት መስኮች ስልጠና ይሰጣል። የሀገሪቱ አመራሮች ተቋሙን የገነቡት በሀገር ውስጥ የበቀለ የቴክኒክ ባለሙያዎችን ለማፍራትና የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ይበልጥ ለማጠናከር በማለም ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in Telegramጥንቃቄ ‼️ ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦ • +947 • +371 • +563 • +370 • +255 ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381 እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል። የሀገራት መለያ ኮዶች፦ • +375 - ቤላሩስ (Belarus) • +371 - ላቲቪያ (Latvia) • +381 - ሰርቢያ (Serbia) • +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso) • +370 - ቪልኒየስ (Vilnius) • +255 - ታንዛኒያ (Tanzania) መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦ 1.ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ። 2.ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት። ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው። ይህንን የጥሰት ሙከራ ለመከላከል ይህንን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ለብዙ ጓደኞችዎ ያጋሩ (Forward ያድርጉ)!!! @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in Telegram🎈መገናኛ ዲያስፖራ ጫካ ፕሮጀክት ፊትለፊት ✅ 100% ለከፈለ 35% በነፃ ነው ✅ 40/60 አከፋፈል አመቻችተናል 👉 ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ 👉 ባለ 2 መኝታ 90,99 ካሬ 👉 ባለ 3 መኝታ 120 -145 ካሬ ዋጋ እና አከፋፈል ☑️ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ = 7.2 ሚልዮን ብር ቅድመ ክፍያ 20% = 1.4ሚልዮን 🔑100% ለሚከፍል=4.6ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 1 መኝታ 69ካሬ ጠቅላላ ክፍያ=8.2 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ=1.6 ሚሊዮን ብር 🔑100 % ለሚከፍል=5.3 ሚሊዮን ብር ☑️ ባለ 2 መኝታ 90ካሬ ጠቅላላ ክፍያ = 10.8 ሚልዮን ብር ቅድመ ክፍያ 20% = 2.1 ሚልዮን ብር 🔑100% ለሚከፍል= 7 ሚሊዮን ብር ☑️ ባለ 2 መኝታ 99 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ = 11.8 ሚልዮን ቅድመ ክፍያ 20% = 2.3 ሚልዮን 🔑100% ለሚከፍል=7.7 ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 3 መኝታ 120 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ=14.4 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ=2.8 ሚሊዮን ብር 🔑100% ለሚከፍል=10 ሚሊዮን ብር ☑️ባለ 3 መኝታ 145 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ=17.4 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ=3.4 ሚሊዮን ብር 🔑100% ለሚከፍል=12.1 ሚሊዮን ብር ቀሪ ክፍያ 👉 ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ 👉 ከወለድ ነፃ አከፍፈል 👉 በግንባታ ሂደት የሚከፈል ✅ WhatsApp call=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1 ✅Telegram =@Temerr34 ☎️ 09-82-15-16-64
Open in Telegramበጎጃምና በጎንደር ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም ማጥፋትና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ተፈጽሟል በሚል በአቶ ኢዩ ጩፋ ላይ ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ጥቆማ ቀረበ ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ አቶ ኢዩ ጩፋ በሃይማኖት ስብከት ሽፋን በጎጃምና በጎንደር አካባቢ ሕዝብ ላይ በጅምላ ስም የማጥፋት፣ የማዋረድና የጥላቻ ንግግር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ትናንት ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ለፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ይፋዊ የወንጀል ጥቆማ አቅርበዋል። በጥቆማው ላይ እንደተመለከተው፣ ተጠሪው በኅዳር ወር 2019 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የምዕራብ፣ የምሥራቅ፣ የሰሜን ጎጃምንና የአዊ አካባቢ ሕዝብን «መተተኞች» በማለት በጅምላ መፈረጃቸውና ይህም በማኅበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱ የሕዝቡን የሥራ ትጋትና እሴት የሚያንቋሽሽ፣ እንዲሁም ተወላጆቹን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ በጥርጣሬ እንዲታዩ የሚያደርግ ነው ተብሏል። በተጨማሪም በሌላ የስብከት መድረክ ላይ የጎንደርንና የጎጃምን ሕዝብ ዒላማ በማድረግ «የጎጃም የሌ፣ የጎንደር የሌ፤ እዚህ ቤት የገባ ሁሉ ይቀጠቀጣል፣ ይረገጣል፤ የትም ይሥራ እናፈርሰዋለን» በማለት የጥላቻና የማስፈራሪያ ንግግር ማድረጋቸው በጥቆማ ደብዳቤው ተጠቅሷል። ድርጊቱ የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግን (ስም ማጥፋትና ሕዝብን ማነሳሳት)፣ የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እንዲሁም የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008ን የሚጥስ መሆኑን ጠበቃው ገልጸው፤ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በማያያዝ ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ አጣርቶ ተጠሪውን ለፍትሕ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Open in TelegramConnections
Similar channels
Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)@shegerfmradio102_1News and media36.4K
Sheger Press️️@sheger_pressNews and media35.7K
Addis መረጃ™@addis_merejaNews and media34.9K
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ@addismaledaNews and media33.7K
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal@zena24nowNews and media40.8K
"ኡማ ቲቪ " Tv@ethioomahtvchannleNews and media44.3K
ቀዳሚ ዜና@kedami_newsNews and media28.4K
4-3-3 World News@ethionews433News and media49.8K