ኀዳር 17 2019 ወደ ሀገር እንዳይገባም እንዳይሸጥም የተከለከለው ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ በህገወጥ መንገድ እየተሸጠ ነው ተባለ። ሲጋራው በትምህርት ቤቶች ጭምር በተማሪዎች እጅ መገኘቱ ተነግሯል። ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ ሕገ ወጥ የንግድ አሠራሮችን ለመቆጣጠርና የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ በሚያስፈልገው የተቋማት የጋራ ኃላፊነትና ቅንጅት ዙሪያ ባሰናዳው የፓናል ውይይት ላይ ነው። በትምህርት ቤቶች አካባቢ በተሠራው የትምባሆ ቁጥጥር ለውጥ ቢመጣም፣ የሱቅ በደረቴ ነጋዴዎች ሲጋራ በነጠላ እየሸጡ መሆኑ ተነግሯል። አንዳንድ ሱቆች የተከለከሉ ሲጋራዎችን ይዘው እንደሚገኙና ግብይቱ በምሽት አካባቢ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል። ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ሲጋራ መሸጥና ማጨስ የተከለከለ ቢሆንም ድርጊቱ አሁንም እንደሚስተዋል ተነግሯል። የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በተለይም ቻይናውያን፣ በተከለከሉ ቦታዎች ሲያጨሱ እንደሚስተዋልም ተነስቷል። እነዚህንና መሠል ችግሮችን ለመፍታት በተደረገ ቁጥጥር በ2018 ዓ.ም በ727 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶ ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕገ ወጥ ትምባሆ መወገዱን የባለሥልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ጠቁመዋል። 79 በመቶ የሚሆኑ ተቋማትን ከትምባሆ ነፃ ማድረግ መቻሉም ተናግረዋል። እነዚህ ስራዎች የተሰሩት የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ደንብ ማስከበር በቅንጅት ባከናወኑት የመቆጣጠር ተግባር ነው ተብሏል ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት በዳዳ በበኩላቸው በተለይ በሆስፒታሎች በር አካባቢ ምግብና መጠጦች ፀሐይ ላይ እንደሚሸጡ ተናግረዋል። ምርቶቹ ተወርሰው ቢወገዱም በማግስቱ እየተተኩ መሆኑን አስረድተዋል። በ2018 ዓ.ም በተሠራው ሥራ በ1,540 የምግብ ተቋማት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ከ40 ሚሊዮን በላይ የምግብና የመጠጥ ምርቶች ተወግደዋል ቸብሏል። ከተቋማቱ መካከል 170ዎቹ ታሽገዋል፣ የ3ቱ ፈቃድ ተሰርዟል፣ 120 የሚሆኑት በገንዘብ ተቀጥተዋል። ባለሥልጣኑ ፀሐይ እየመታቸው የሚሸጡ ምርቶች ለተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ስለሚያጋልጡ ኅብረተሰቡ ገዝቶ እንዳይጠቀም አሳስቧል። ገዛ ጌታሁን
Open in TelegramPosts of Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)
ኅዳር 17 2019 በትግራይ ጦርነት ወቅት የውጪ ድሮን አስተኳሽ ባለሙያዎች መያዛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ በተደረገው ውጊያ ወቅት ከውጭ ሀገራት መጥተው ድሮን የሚያስተኩሱ ባለሙያዎች እንደነበሩ እና ውጊያው ሲካሄድ አንዳንዶቹ መያዛቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን መጠቃት ሲጀመርና ውጊያው እየገፋ ሲሄድ ባለሙያዎቹ “ደረሱብን፣ አውጡን፣ እኛ አንተኩስም፣ በቃ እንጥፋ” እያሉ መጨቃጨቃቸውን ጠቃላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በወቅቱ ያስቀሯቸው እንዳሉ እንዲሁም ያመለጡ መኖራቸውን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጉዳይ ያነሱት በውጭ ኃይሎች ድጋፍ ላይ መደገፍ በቀጠናው ሊያስከትል የሚችለውን ሁኔታ ባብራሩበት ወቅት ነው። ፍቅሩ አምባቸው
Open in Telegramኅዳር 17 2019 የሁርሶ ስልጠና ያስፈለገው ከኮብራ መኪና ወርዶ አልጋ ማንጠፍ እንደሚኖር ለማስተማር ነው። ሚኒስትሮች ሁርሶ ለስልጠና የገቡት ሠው ለመሆን፣ሀገር ለመውደድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። የሁርሶ ስልጠና ያስፈለገው ከኮብራ መኪና ወርዶ አልጋ ማንጠፍ እንደሚኖር ለማስተማር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ስልጠናው ሰው ለመሆን፣ሀገር ለመውደድና ባንዲራን ለማክበር በሚል የታሰበ መሆኑን አንስተዋል። ስልጠናው የሚሰጠውም ሰው ለመሆን እንጂ ወደ ውትድርና ለመግባት አይደለም ብለዋል። በውጤቱም ስልጠናውን የገቡ ሚኒስትሮች ብዙ እንደተጠቀሙ መናገራቸውንም አንስተዋል። አልጋ ማንጠፍ፣ካልሲ ማጠብ ያለው ስራ ሁሉ ለማገልገል፣የተሟላ ሰው ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። የፓርላማ አባላትን በተመለከተም እናንተን ለማዘዝ ባልችልም ክረምት ክረምት ግን ቢያንስ ልጆቻችሁን አስገቡ ብለዋቸዋል። ተመሳሳይ ስልጠና ከዚህ በኋላም ይቀጥላል ብለዋል። ቴዎድሮስ ወርቁ
Open in Telegramኅዳር 17 2019 ዝቅተኛ ደሞዝ ወለል ለመወሰን መንግስት ጥናት እያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይህን የተናገሩት ዛሬ ፓርላማ ቀርበው ከእንደራሴዎች ምክርቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡባት ወቅት ነው፡፡ ዝቅተኛ ደሞዝ ወለልን በተመለከተ የግሉን እና የመንግስትን ሰራተኛ ደሞዝ እንዴት ተደርጎ መስተካካል እንዳለበት እየተጠና ነው ብለዋል፡፡ እሱ ሲስተካካል ሙሉ በሙሉ ችግሩን ዜሮ ማድረግ ባይቻልም ለማቃለል ይረዳል ብለዋል ፡፡ ያሬድ እንዳሻው
Open in Telegramኅዳር 17 2019 ማንም ወደ ኢትዮጵያ ደንብር መጥቶ በክብር የሚመልስ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የተናገሩት ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ነው። መከላከያ መጠንከሩ ለወንድሞቻችን ስጋት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንም አገር ወርራ አታቅም፤ ወደፊትም የመውረር ፍላጎት የላትም ሲሉ አስረድተዋል። ትንሽም ይሁን ትልቅ ማወቅ ያለበት ግን ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ደንብር መጥቶ አገሪቱን ወሮ በክብር መመለስ አይችልም ብለዋል። ይሄ በጂኦግራፊ የታጠረ ሳይሆን ለማንም ነው ያለኩት ሲሉ አስረድተዋል። "አደዋ ይደጋመል አትሞክሩን ፤አትሞክሩን አንፈልጋችሁም ወደዚህ የሚመጣ ካለ ግን የአባቶቻቸን ተግባር ይደገማል" ብለዋል። ያሬድ እንዳሻው
Open in Telegramኅዳር 17 2019 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ዓመት ከወታደራዊ መሣሪያዎች ሽያጭና ጥገና በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ ማስገኘቱን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናገሩ ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፈው በጀት ዓመት ጥይት፣ ድሮን እንዲሁም የአውሮፕላን ጥገና አገልግሎቶችን ወደ ውጭ በመላክ የተገኘ ገቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል። የመከላከያ ተቋም ከተጠቃሚነት በመውጣት ራሱን በራሱ የሚደግፍ አምራች ተቋም እየሆነ መምጣቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል በነበሩ ግጭቶች ወቅት መከላከያ ሠራዊቱ አልባሳትን ከቻይና እንዲሁም ጥይቶችን ከውጭ ሀገራት ያስገባ እንደነበር አንስተዋል። ከዚህ ልምድ ትምህርት በመውሰድ በተሰራው ስራ፣ በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የራሱን ምግብ፣ አልባሳት እና ተተኳሽ ጥይቶችን በበቂ ሁኔታ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል። ፍቅሩ አምባቸው
Open in Telegramኅዳር 17 2019 “የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብ እና ዘመናዊ ፕሮጀክት በእኔ እድሜ ተሰርቶ አያውቅም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ። ከተወለድኩ እናንተ የፓርላማ አባላትም ከተወለዳችሁ የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብና በዘመናዊ መንገድ የሚመራ ፕሮጀክት ኖሮ አያውቅም ብለዋል። በአንድ ጊዜ አራት ሺህ የሚጠጋ ትራክ ተሽከርካሪ በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ነው ሱሉ አንስተዋል። ይህም ስራ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት(AI) ታግዞ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን የትራንስፖርት አስተዳደሩ በራሱ ከባድና ውስብስብ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አሁን እየተሰራ ያለው ቦታውን የማዘጋጀት ስራ ከሶስት ወር ባነሰ ጊዜ ይጠናቀቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፕላን መንገድ (የራን ዌይ) ግንባታውን ለመስራት የጨረታ ሂደት ላይ ነው ብለዋል። የጨረታው ውጤትም በአንድ እና ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ይታወቃል ሲሉ ተናግረዋል። የቢሾፍቱ ኤርፖርትን ጨምሮ ግዙፍ የሆኑት እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣የጋዝና ሌሎቹም ሜጋ ፕሮጀክቶች አትችሉም፣ገንዘብ ከየት ታመጣላችሁ የሚል ጥያቄ እየተነሳ የሚሰሩ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያን እድገት በማይፈልጉና እነሱ በገዟቸው ሀገራት በኩል ይህ ጥያቄ በስውርም በግልፅ በሚዲያም ጭምር ይቀርባል ሲሉ ተናግረዋል። የተለየ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በቀር እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በታሰበው ጊዜ ይጠናቀቃሉም ብለዋል። ቴዎድሮስ ወርቁ
Open in Telegramኅዳር 17 2019 ኢትዮጵያ ባለፋት ሶስት ወራት ከውጭ ሀገር ላስገባቻቸው ምርቶች 6.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ ። ከዚህ ውስጥ ለነዳጅ የወጣው ወጪ ከባለው አመት አኳያ ሲታይ የ70 በመቶ ብልጫ እንዳሳየ አስረድተዋል። የነዳጅ ወጪ ሊጨምር የቻለውም በነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል። ከነበረው አለም አቀፍ ቀውስ አንፃር ሲታይ ኢትዮጵያ ነዳጅን በድጎማ ማቅረቧ ብቻ ሳይሆን ያስተዳደረችበት ሁኔታ አስደናቂ እንደነበረም አስረድተዋል። ባለፉት 3 ወራት ለገቢ ምርት 6.5 ቢሊን ዶላር ያወጣችው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ ለወጭ ገበያ ካቀረበችው ምርት ሽያጭ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ይህም ከቀዳሚው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል። ከሰርቪስ ወይንም ከአገልግሎት 2.9 ቢሊዮን ዶላር፣ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ደግሞ 1.28 ቢሊዮን ዶላር በ2019 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት መገኘቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ንጋቱ ሙሉ
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 109 |
| 3 h | 1,110 |
- Total to date1,110
ኅዳር 17 2019 “ሰራተኛ አጥተን ታራሚ እስረኞችን እያሰራን ነው” መንግስት በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ ሰራተኛ በማጣት ታራሚ እስረኞችን ለማሰራት እየተገደደ ነው ተባለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ችግር ቢኖርም የዛኑ ያክል ሰራተኛ ማግኘትም ችግር ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ቀለም ቀቢ፣ፅዳት ባሉ ስራዎች ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ማግኘት ከባድ እየሆነብን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የስራ አጥነት ችግር መኖሩን አንስተው የዛኑ ያክል ስራ መራጭ ትውልድም በዝቷል ብለዋል። ይህንን ሀሳብ የኢትዮጵያ ወላጆች በደንብ ያድምጡኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣በቀጥታ ክትትል የማደርግባቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሁሉ በቂ ሰራተኛ እያጣን እየተቸገርን ነው ብለዋል። በዚህ ምክንያት በቀን 600 እና 700 ብር እየከፈልን ታሳሪ ታራሚዎችን ቀጥረን ለማሰራት እየተገደድን ነው ብለዋል። እነሱ ላይ ሁሉ ስራው በዝቶ ጫና እየተፈጠረባቸው ነው ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ብዙ የስራ እድል መፈጠር ቢኖርበትም ስራ መራጭ የመሆን ችግርም መቀየር አለበት ነው ያሉት። ቴዎድሮስ ወርቁ
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 477 |
| 3 h | 1,230 |
- After 1 hour477
- Total to date1,230
ኅዳር 17 2019 የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት ከግብርናው ዘርፍ የበለጠ እድገት ማሳየት ጀምሯል ተባለ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢንዱስትሪው ግብርናውን እንዲመራው የማድረግ ፍላጎት ዘንድሮ የሚፈለገውን ሽግግር ማሳየት ጀምሯል ብለዋል። በዚህ ዓመት የግብርናው ዘርፍ እድገት 7.7 በመቶ ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢንዱስትሪው እድገት ግን 12.3 በመቶ ይሆናል ብለዋል። ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት(GDP) አንፃር የግብርና ድርሻ 31.4 በመቶ ሲሆን ግንባታን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ድርሻ ግን 31.8 በመቶ ነው ሲሉ አስረድተዋል። አገልግሎት አሁንም ቀዳሚው ዘርፍ ሲሆን የዘንድሮ እድገቱ 9.9 በመቶ ይሆናል፣ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ ደግሞ ድርሻው 33.8 በመቶ ነው ተብሏል። ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 576 |
| 4 h | 1,300 |
- After 1 hour576
- Total to date1,300
ኅዳር 17 2019 የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን መንግስት እስከመቼ ነው የሚታገሰው የሚል ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀረበ፡፡ ጥያቄው የቀረበው የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የመጀመሪያ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛው መደበኛው ጉባዔውን ዛሬ እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በሰባተኛው አገራዊ ምርጫ አሸንፈው የፓርላማ ወንበር ያገኙት ተመራጮች ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው፡፡ ጥያቄ ካቀረቡት ውስጥ እንዱ የሆኑት አቶ ጋሻው ዳኛው የኤርትራ መንግስት ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን እያደረገ እና ታጣቂዎንን እያደገፈ መሆንኑ ጠቅሰው ለዚህ ድርጊቱ የመንግስት ታግባራዊ ምላሽ ምንድነው? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋትን የሚፈታተኑ ድርጊቶችንስ እስከመቼ እንታገሳልን ሲሉ ተወካዩ አክለዋል፡፡ ያሬድ እንዳሻው
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 1,010 |
| 5 h | 1,520 |
- After 6 hours1,520
- Total to date1,520
ኅዳር 16 2019 አሐዱ ባንክ ከ Aqua for All ጋር በመተባበር የ”Ahadu WASH Impact Loan” እና የአካታች አረንጓዴ ፋይናንስ ፕሮግራም አስጀመረ ፕሮግራሙ በ2 ሚሊዮን ዩሮ የሚተገበር ነው ተብሏል። 1.5 ሚሊዮን ዩሮው ከአሀዱባንክ፣ 500,000 ዩሮው ደግሞ በAqua for All የሚሸፈን ነው ተብሏል። ባንኩ ለአምስት ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትና ለአንድ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር የጅምላ ብድር ለማቅረብ መወሰኑንና ገንዘቡም ወደ ቤተሰቦችና አነስተኛ ንግዶች እንዲደርስ ለማድረግ ማቀዱን ተናግሯል። የፋይናንስ ተቋማት ሚና ገንዘብ መሰብሰብና ብድር መስጠት ብቻ አይደለም ያለው ባንኩ ፣ፋይናንስን ወደ ምርታማ ዘርፎች በማዋል የማኅበረሰቡን ሕይወት ማሻሻልና ለዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ የባንኩ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሷል። የWASH Impact Loan መጀመርም የዚህ ቁርጠኝነት ተግባራዊ መገለጫ ነው ብሏል። ፕሮግራሙ የተመሠረተው ባንኩ ካለው የፋይናንስ አቅምና Aqua for All ከሚሰጠው የቴክኒክ ድጋፍ ጋር በፈጠረው ቅንጅት ላይ ነው መባሉን ሰምተናል። ዓላማውም ለውሃ፣ ለንጽህናና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ የፋይናንስ መፍትሔዎችን ማስፋፋት እንደሆነ ጠቁሟል። አሀዱ ባንክና የኔዘርላንድስ ባለድርሻ ድርጅት የሆነው Aqua for All በትብብር ለመስራት የስምምነት አድርገዋል። ገዛ ጌታሁን
Open in Telegram#ሰሞነኛ ቤት ለመግዛት 50 ዓመት ይፈጃል ! ሁሉም ቤት ገዥ የግድ ማወቅ ያለበት https://youtu.be/jUJl1Neeg7M?si=pepLbk7JdW4iwoD5
Open in Telegram#ቤተኛ በአክስቴ ልጅ ተደፍሬ ባረግዝም አባቴ ቤት ተከራይቼ ለብቻሽ ትኖሪያለሽ አለኝ … ሰዉ እንዳይሰማበት https://youtu.be/FHO3Ok4QsYE?si=SkkvZljJF4-65AXX
Open in Telegramየኅዳር 16 2019 የውጪ ሀገር ወሬዎች #ቻይና በቻይና የአድራጊ ፈጣሪው የኮሙኒስቶች የፖለቲካ ማህበር የሻንጋይ ፅህፈት ቤት የበላይ ቼን ጂኒንግ በከፍተኛ ደረጃ እየተመረመሩ ነው ተባለ፡፡ ቼን ጂኒንግ ከሻንጋይ ከተማ የቻይና ኮሚኒስት የፖለቲካ ማህበር ዋና ፀሐፊነታቸው በተጨማሪ የዋናው የፖለቲካ ማህበሩ የፖሊት ቢሮ አባል እንደሆኑ አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡ የቻይና ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ከፍተኛ ሹሞች የቼን ጂኒንግ ምርመራ ከዲስፕሊን ጥሰት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በቻይና ሹማምንት ዘንድ ብዙውን ጊዜ የዲስፕሊን ጥሰት ትርጓሜው ከምዝበራ ፣ ጉቦኝነት እና ብልሹ አሰራር ጋር እንደሚያያዝ ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡ የቻይና ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር የከፍተኛ ሹሞች ምርመራ ብርቱ ጣጣ አስከታይም እንደሆነ ይነገራል፡፡ የቼን ጂኒንግ ጉዳይ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥንም በስፋት መዘገቡ ታውቋል፡፡ #ደቡብ_አፍሪካ የደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ከተሞች ነዋሪዎች ጥቅም ላይ የሚያውሉትን የውሃ መጠን ቀንሱ ተባሉ፡፡ ነዋሪዎቹ የሚጠቀሙትን የውሃ መጠን እንዲቀንሱ የተጠየቁት በኤልኒኖ የአየር መዛባት ክስተት የተነሳ ድርቁ እየበረታ በመምጣቱ እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአገሪቱ የውሃ መጠን ቅናሹ በግልጽ እየታየ ነው ተብሏል፡፡ እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሊመጣ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ድርቁ ከከተማ ነዋሪዎች የውሃ አቅርቦት በተጨማሪ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ እንደማይቀር ተጠቅሷል፡፡ በጣሙን እየጨመረ የመጣው ሙቀት በሰብሎች እና በአትክልቶች ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ #ማዳጋስካር የማዳጋስካር የምዝበራ ተከላካይ ዐቃቢያ ህግ በቀድሞው ፕሬዘዳንት አንድሬይ ራጂሊና እና ጠቅላይ ሚኒስትራቸው በነበሩት ክርስቲያን ንትሳይ ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ይውጣልን አሉ፡፡ ራጆሊና እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የመያዣ ትዕዛዝ እንዲወጣቸው የተጠየቀው በአገሪቱ የተገዙ 5 ቦይንግ 777 አውሮፕላኖች በህገ-ወጥ መንገድ ለኢራን እንዲተላለፉ አድርገዋል ተብለው እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡ አውሮፕላኖቹ የተላለፉለት የኢራን አየር መንገድ በአለም አቀፍ ማዕቀብ ውስጥ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ በዚህ የምዝበራ እና ብልሹ አሰራር እጃቸውን አስገብተዋል የተባሉ ሌሎች 13 ግለሰቦችም በምርመራ ጥፋተኞች ሆነው ተገኝተዋል ብለዋል አቃቢያነ ህጉ፡፡ አንድሬይ ራጆሊና ተቀስቅሶባቸው በነበረ ህዝባዊ እምቢታ ግፊት አገር ጥለው ከወጡ ከአመት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ የተጠየቀባቸው የመያዣ ትዕዛዝ ስራ ላይ እንዲውል የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚሻ መረጃው አስታውሷል፡፡ #ሱዳን በሱዳን አንድ ሌላ ከፍተኛ የRSF የፈጥኖ ደራሽ ሀይል አዛዥ ከድተው ወደ መንግስት ጦር ገቡ፡፡ RSFን ከድተው ወደ ሱዳን መንግስት ጦር የገቡት ሜጄር ጄኔራል አማር ሞሐመድ ዜይን ራቢ የተባሉ ከፍተኛ የጦር መኮንን እንደሆኑ ዘ ኒው አረብ ፅፏል፡፡ ከጂው የጦር መኮንን በኒያላ የእስራኤል የጦር አዋቂዎች ለRSF ታጣቂዎች የጦር ስልጠና እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኒያላ በደቡባዊ ዳርፉር RSF እንደ አስተዳደር ማእከል የሚገለገልበት ከተማ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ሜጄር ጄኔራሉ የRSF ታጣቂዎች በእስራኤል እየሰለጠኑ መሆኑን አጥብቀው እንደሚቃወሙ ተጠቅሷል፡፡ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት በድያለሁ ይቅር በሉኝ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ RSF ከጂዎች እንደበዙበት ይነገራል፡፡ ፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ከሱዳን መንግስት ጦር ጋር ሲዋጋ ከ3 አመታት ከመንፈቅ በላይ ሆኖታል፡፡ የኔነህ ከበደ
Open in Telegramኅዳር 16 2019 ቃሊቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ይዞት የነበረው ቦታ ለልማት ይፈለጋል ተባለ። የኢትዮዽያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራበት የነበረው ይህ ቦታ ለልማት የፈለገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ነው። ቢሮው በቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ይህንን ሰፋ ያለ ቦታ ለከተማ ልማት እፈልግዋለው ማለቱን ሰምተናል። የከተማው የመሬት ቢሮ ለኢትዮጵያ የባሕርና ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ በቃሊቲ የሚቀላጥፈውን ሥራ ወደ ገላን ሁለገብ ወደብ እንዲያዘዋውር በደብዳቤ መጠየቁን ሰምተናል። በዚህ መሰረት ከዚህ ቀደም ቦታውን በሐገሩ ህግና ሥርዓት ገቢ ወጭ ንግድ እንዲቀላጠፍ ይገለገልበት የነበረውም አንደኛው የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ለቀረበለት ተመሳሳይ ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል። ምድር ባቡሩ ይህንኑ ስራ ለማቀላጠፍ በገላን ሁለገብ ወደብ የጭነት ክምችትና መተላለፎችን ለማቀላጠፍ የሚያገለግል ቦታ በማዘጋጀት፤ ለጉምሩክ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቆጣጣሪ ቢሮና ተቋማትን ለስራ ምቹ በማድረግ፤ የተዘረከረከ ሎጂስቲክስ እና መመላለስ እንዳይኖር እና የትራንስፖርት ውጣ ውረድ እንዳይፈጠር ወደ ገላን ሁለገብ ወደብ ለመግባት ዝግጅቱን እየጨረሰ እንደሆነ አስረድቷል። በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሎጂስቲክስ እንዲፍታታ፤ በተለይ በገቢና ወጭ የንግድ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እና ውሳኔዎች ማን ያህል አገዘ ስንል፤ የሎጂስቲክስ ሚኒስትር ሚኒስትሩን ሳዳት ነሻን ጠይቀናቸዋል። እሳቸውም በዚህ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል። በተለይ ኢትዮጵያ በሎጂስቲክስ ወደ ኃላ የቀረችባቸውን ስራዎች እየተመለከትን ከመሬት እያነሳን ነው ሲሉ ነግረውናል። ከመልቲ ሞዳል ጋር በተገናኙ የሚጠናቀቁ ሥራዎች እንዳሉም ሚኒስትሩ አስረድተውናል። በተለይ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ተሳትፎ እንዲኖረው፣ በተለይም በገቢና ወጪ ንግድ፣ በፖሊሲ ማሻሻያዎች እና በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች ውስጥ የዘርፉ ባለድርሻዎች ሚና ምን እንደሚሆን ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ሳዳት ነሻን ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበንላቸዋል። በተለይም ኢትዮጵያ ወደኃላ ከቀረችበት የሎጂስቲክስ መንገድ ተላቃ በአዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገር፣ ከMultimodal Transport ጋር በተያያዙ የሚተገበሩ ሥራዎች መኖራቸውንም አስረድተዋል። ዘገባውን ያድምጡ..... https://short.do/bpP-0- ተህቦ ንጉሴ
Open in Telegramኅዳር 16 2019 #ቢዝነስ የሜትር ታክሲ ስራ እንዴት ነው? በዚሁ ስራ ላይ እያለች ያገኘናት ዘውድነሽ ኬር ከስደት መልስ ከአራት አመታት በላይ የቆየችበት ይኸው ስራ ተቀይሬበታለሁ ትላለች፡፡ ከኪራይ መኪና ወጥታ የራሷን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ እንድትገዛ ያገዛት ስራ እንደሆነ ነግራናለች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሜትር ታክሲ ስራ ገቢው እየቀነሰ መሆኑን በማንሳት የሚያማርሩም ሾፌሮችም አሉ፡፡ አሁንስ ቢዝነሱ እንዴት ነው? ዝርዝሩን ትዕግስት ዘሪሁን ትነግረናለች። ዘገባውን ያድምጡ.... https://short.do/mGrnnk የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Open in Telegramየኅዳር 16 2019 የቢዝነስ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ በቡና ምርት ስማቸው ከሚነሱ ሀገራት ከቀዳሚዎቹ መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት፡፡ በተያዘው በጀት አመት አራት ወራትም ከቡና ወጭ ንግድ 1.16 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተነግሯል፡፡ ሀገሪቱ ለቡና ምርት አፈሯ ተስማሚ መሆኑን ተመራማሪዎች ቢያነሱም ባላት አቅም ልክ ግን እያመረተች እንዳልሆነም ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌም ቡና በስፋት ይመረትባቸዋል ከሚባሉ የሀገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የሆነው ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለቡና ማብቀል ምቹ ቢሆንም የአቅሙን ያህል ግን እያመረተ አለመሆኑን የጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል ነግሮናል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቡና ምርት ላይ የተሰጠው ትኩረት ጥሩ የሚባል እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ከሚመረተው የቡና ዝርያ ጀምሮ እስከ ሽያጭ ድረስ ባለው ሂደት ክፍተቶች አሉ ተብሏል፡፡ በሰፋፊ እርሻ ላይ፣ በጓሮ ውስጥ እና በሌሎችም መንገዶች የቡና ምርት እየተመረተ እንዳለ የሚናገረው ማዕከሉ እንደ አመራረታቸው የተለያየ ችግሮች ይገጥሟቸዋል ብሏል፡፡ ዘገባውን ያድምጡ.... https://short.do/99HJz4 ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Open in Telegramኅዳር 16 2019 በሙስና ሊመዘበር የነበረ 12 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተናገረ። በተጨማሪም 47 ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት ከምዝበራ ማዳኑንም ተናግሯል። ኮሚሽኑ ይህንን ያለው ከህዳር 1 እስከ 30 ቀን 2019 ዓ.ም እየታሰበ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን በማስመልከት ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው። መግለጫውን የሰጡት በኮሚሽኑ የፀረ ሙስና ህጎችና አለም አቀፍ ስምምነት ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሃረጎት አብርሃ ባለፉት 5 ዓመታት በአስቸኳይ የሃብት ማዳን ስራ ሊባክን የነበረ 12 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን ተናግረዋል። ከዚህ የህግ ማስከበር ስራ ባልተናነሰ ሙስና ከመፈፀሙ በፊት ኮሚሽኑ ሂደታቸው እንዲቋረጥ፤ ሰንሰለታቸው እንዲበጠስ ያደረጋቸው ጉዳዮች ስለመኖራቸውም አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ትልቁ ችግር የሆነብን አስተዳደራዊ ሙስና ነው ያሉት አቶ ሃረጎት አገልግሎት እንዲሰጡ የሚቀመጡ የስራ ሃላፊዎች የዚህ ፈፃሚ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍም በተለይ ከሰዎች ንክኪ የፀዳ የዲጂታል አሰራርን መከተል አንዱ መከላከያ መንገድ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም በወረዳ፣ በቀበሌ፣ በወሳኝ ኩነት እና በኢሚግሬሽን መዋቅሮች ባሉ አንዳንድ ሙሰኞች አማካኝነት እድሜያቸው ላልሞላ ታዳጊዎች ሀሰተኛ የልደት ሰርተፊኬት፣ መታወቂያ እና ፓስፖርት በጉቦ ማዘጋጀት፤ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሲያዙ በፖሊስ፣ በዐቃቤ ህግና በፍርድ ቤት መዋቅሮች በሚፈጸም ሙስና መዝገብ ማጥፋት፣ ምስክር ማስፈራራት እና ያለ በቂ ዋስትና ማስፈታት የሙስና ወንጀሎች ከሚፈፀምባቸው ዘርፎች በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ ብለዋል ሃላፊው። ምንታምር ጸጋው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Open in Telegram#ሸገር_ትንታኔ ሜክሲኮ አጥብቃ የምትፈልገውን የአደንዛዥ እፅና የወንጀል ቡድን መሪን በወሰደችው ወታደራዊ እርምጃ በእጇ አስገብታለች፡፡ አሜሪካ ግለሰቡ ተላልፎ እንዲሰጣት ፍላጎት አላት መባሉ ግን ሁለቱን ሀገሮች አላስማማቸውም። ነገሩ በሜክሲኮና አሜሪካ መሀከል ላለው ቅራኔ ተጨማሪ ጉልበት እንዳይሆን አስግቷል፡፡ ትንታኔውን ያድምጡ..... ቴዎድሮስ ወርቁ https://www.youtube.com/watch?v=wH8wFVgrSuA
Open in Telegramየኅዳር 16 / 2019 የሸገር የቀትር ወሬዎችን በቀጥታ ይከታተሉ…… https://www.youtube.com/live/P6L5HnGYmzw?si=ehAC9t79XvcC7vi_
Open in Telegram#ሸገር_ስፖርት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ከስፖርቲንግ https://www.youtube.com/live/k4HR9EurXOk?si=NwbrRQ_esAbauukW #shegersport
Open in Telegramኅዳር 16 2019 አጋር ማይክሮ ፋይናንስ ጠቅላላ ሃብቴ 1.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል አለ። በሌላ በኩል የሰጠው ጠቅላላ ብድር ደግሞ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ተናግሯል። ኩባንያው ይህን ያለው አዲስ ያሻሻለውን የተቋሙን መለያ ዓርማ እና ህብረ-ዝማሬ ትላንት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። የተከፈለ ካፒታሉ 477.9 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 664.3 ሚሊዮን ብር ማደጉን የአጋር ማይክሮፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰረቀ ብርሃን ዘርአይ ተናግረዋል። ተቋሙ የደንበኞቹን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ዋና ዋና የፋይናንስ አገልግሎቶችን በስፋት እያቀረበ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው መደበኛ የባንክ አገልግሎት ማግኘት ላልቻሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት፣ ለሴቶችና ወጣቶች የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል ብለዋል። እንዲሁም አካል ጉዳተኞችንም ያካተተ አካታች የብድር አገልግሎትም ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩም ነግረውናል። አጋር ማይክሮፋይናንስ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በአማራ እና በሲዳማ ክልሎች በሚገኙ 30 ቅርንጫፎች አማካኝነት ከ88 ሺህ 500 በላይ ደንበኞችን እንዳፈራም ሰምተናል፡፡ ፍቅሩ አምባቸው የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Open in Telegram#HelloTomorrow “ቆሻሻን ወደ ሐብት ቀይሬያለሁ” https://youtu.be/VVSeVCpvlvI?si=bq7at4RYikmCzKBa
Open in Telegram