ኀዳር 17 2019 ወደ ሀገር እንዳይገባም እንዳይሸጥም የተከለከለው ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ በህገወጥ መንገድ እየተሸጠ ነው ተባለ። ሲጋራው በትምህርት ቤቶች ጭምር በተማሪዎች እጅ መገኘቱ ተነግሯል። ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን፣ ሕገ ወጥ የንግድ አሠራሮችን ለመቆጣጠርና የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ በሚያስፈልገው የተቋማት የጋራ ኃላፊነትና ቅንጅት ዙሪያ ባሰናዳው የፓናል ውይይት ላይ ነው። በትምህርት ቤቶች አካባቢ በተሠራው የትምባሆ ቁጥጥር ለውጥ ቢመጣም፣ የሱቅ በደረቴ ነጋዴዎች ሲጋራ በነጠላ እየሸጡ መሆኑ ተነግሯል። አንዳንድ ሱቆች የተከለከሉ ሲጋራዎችን ይዘው እንደሚገኙና ግብይቱ በምሽት አካባቢ እንደሚካሄድም ተጠቁሟል። ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ሲጋራ መሸጥና ማጨስ የተከለከለ ቢሆንም ድርጊቱ አሁንም እንደሚስተዋል ተነግሯል። የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በተለይም ቻይናውያን፣ በተከለከሉ ቦታዎች ሲያጨሱ እንደሚስተዋልም ተነስቷል። እነዚህንና መሠል ችግሮችን ለመፍታት በተደረገ ቁጥጥር በ2018 ዓ.ም በ727 ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዶ ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕገ ወጥ ትምባሆ መወገዱን የባለሥልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ጠቁመዋል። 79 በመቶ የሚሆኑ ተቋማትን ከትምባሆ ነፃ ማድረግ መቻሉም ተናግረዋል። እነዚህ ስራዎች የተሰሩት የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ደንብ ማስከበር በቅንጅት ባከናወኑት የመቆጣጠር ተግባር ነው ተብሏል ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት በዳዳ በበኩላቸው በተለይ በሆስፒታሎች በር አካባቢ ምግብና መጠጦች ፀሐይ ላይ እንደሚሸጡ ተናግረዋል። ምርቶቹ ተወርሰው ቢወገዱም በማግስቱ እየተተኩ መሆኑን አስረድተዋል። በ2018 ዓ.ም በተሠራው ሥራ በ1,540 የምግብ ተቋማት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ከ40 ሚሊዮን በላይ የምግብና የመጠጥ ምርቶች ተወግደዋል ቸብሏል። ከተቋማቱ መካከል 170ዎቹ ታሽገዋል፣ የ3ቱ ፈቃድ ተሰርዟል፣ 120 የሚሆኑት በገንዘብ ተቀጥተዋል። ባለሥልጣኑ ፀሐይ እየመታቸው የሚሸጡ ምርቶች ለተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ስለሚያጋልጡ ኅብረተሰቡ ገዝቶ እንዳይጠቀም አሳስቧል። ገዛ ጌታሁን
Открыть в Telegram
Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)
ሸገር 102.1 መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር የእናንተ ነው! https://bit.ly/33KMCqz
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 24 нояб. 2026 г. | 2 940 |
| 25 нояб. 2026 г. | 1 937 |
| 26 нояб. 2026 г. | 975 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры2,94 тыс.Пересылки—Реакции4Комментарии—
- 02Просмотры2,44 тыс.Пересылки—Реакции4Комментарии—
- 03Просмотры2,32 тыс.Пересылки—Реакции7Комментарии—
- 04Просмотры2,31 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
Новые посты
ኅዳር 17 2019 በትግራይ ጦርነት ወቅት የውጪ ድሮን አስተኳሽ ባለሙያዎች መያዛቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ በተደረገው ውጊያ ወቅት ከውጭ ሀገራት መጥተው ድሮን የሚያስተኩሱ ባለሙያዎች እንደነበሩ እና ውጊያው ሲካሄድ አንዳንዶቹ መያዛቸውን ተናግረዋል። ነገር ግን መጠቃት ሲጀመርና ውጊያው እየገፋ ሲሄድ ባለሙያዎቹ “ደረሱብን፣ አውጡን፣ እኛ አንተኩስም፣ በቃ እንጥፋ” እያሉ መጨቃጨቃቸውን ጠቃላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በወቅቱ ያስቀሯቸው እንዳሉ እንዲሁም ያመለጡ መኖራቸውን አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ጉዳይ ያነሱት በውጭ ኃይሎች ድጋፍ ላይ መደገፍ በቀጠናው ሊያስከትል የሚችለውን ሁኔታ ባብራሩበት ወቅት ነው። ፍቅሩ አምባቸው
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 የሁርሶ ስልጠና ያስፈለገው ከኮብራ መኪና ወርዶ አልጋ ማንጠፍ እንደሚኖር ለማስተማር ነው። ሚኒስትሮች ሁርሶ ለስልጠና የገቡት ሠው ለመሆን፣ሀገር ለመውደድ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ። የሁርሶ ስልጠና ያስፈለገው ከኮብራ መኪና ወርዶ አልጋ ማንጠፍ እንደሚኖር ለማስተማር ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ስልጠናው ሰው ለመሆን፣ሀገር ለመውደድና ባንዲራን ለማክበር በሚል የታሰበ መሆኑን አንስተዋል። ስልጠናው የሚሰጠውም ሰው ለመሆን እንጂ ወደ ውትድርና ለመግባት አይደለም ብለዋል። በውጤቱም ስልጠናውን የገቡ ሚኒስትሮች ብዙ እንደተጠቀሙ መናገራቸውንም አንስተዋል። አልጋ ማንጠፍ፣ካልሲ ማጠብ ያለው ስራ ሁሉ ለማገልገል፣የተሟላ ሰው ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። የፓርላማ አባላትን በተመለከተም እናንተን ለማዘዝ ባልችልም ክረምት ክረምት ግን ቢያንስ ልጆቻችሁን አስገቡ ብለዋቸዋል። ተመሳሳይ ስልጠና ከዚህ በኋላም ይቀጥላል ብለዋል። ቴዎድሮስ ወርቁ
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 ዝቅተኛ ደሞዝ ወለል ለመወሰን መንግስት ጥናት እያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይህን የተናገሩት ዛሬ ፓርላማ ቀርበው ከእንደራሴዎች ምክርቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡባት ወቅት ነው፡፡ ዝቅተኛ ደሞዝ ወለልን በተመለከተ የግሉን እና የመንግስትን ሰራተኛ ደሞዝ እንዴት ተደርጎ መስተካካል እንዳለበት እየተጠና ነው ብለዋል፡፡ እሱ ሲስተካካል ሙሉ በሙሉ ችግሩን ዜሮ ማድረግ ባይቻልም ለማቃለል ይረዳል ብለዋል ፡፡ ያሬድ እንዳሻው
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 ማንም ወደ ኢትዮጵያ ደንብር መጥቶ በክብር የሚመልስ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የተናገሩት ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ነው። መከላከያ መጠንከሩ ለወንድሞቻችን ስጋት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንም አገር ወርራ አታቅም፤ ወደፊትም የመውረር ፍላጎት የላትም ሲሉ አስረድተዋል። ትንሽም ይሁን ትልቅ ማወቅ ያለበት ግን ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ደንብር መጥቶ አገሪቱን ወሮ በክብር መመለስ አይችልም ብለዋል። ይሄ በጂኦግራፊ የታጠረ ሳይሆን ለማንም ነው ያለኩት ሲሉ አስረድተዋል። "አደዋ ይደጋመል አትሞክሩን ፤አትሞክሩን አንፈልጋችሁም ወደዚህ የሚመጣ ካለ ግን የአባቶቻቸን ተግባር ይደገማል" ብለዋል። ያሬድ እንዳሻው
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ዓመት ከወታደራዊ መሣሪያዎች ሽያጭና ጥገና በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ ማስገኘቱን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተናገሩ ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ባለፈው በጀት ዓመት ጥይት፣ ድሮን እንዲሁም የአውሮፕላን ጥገና አገልግሎቶችን ወደ ውጭ በመላክ የተገኘ ገቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል። የመከላከያ ተቋም ከተጠቃሚነት በመውጣት ራሱን በራሱ የሚደግፍ አምራች ተቋም እየሆነ መምጣቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል በነበሩ ግጭቶች ወቅት መከላከያ ሠራዊቱ አልባሳትን ከቻይና እንዲሁም ጥይቶችን ከውጭ ሀገራት ያስገባ እንደነበር አንስተዋል። ከዚህ ልምድ ትምህርት በመውሰድ በተሰራው ስራ፣ በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የራሱን ምግብ፣ አልባሳት እና ተተኳሽ ጥይቶችን በበቂ ሁኔታ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል። ፍቅሩ አምባቸው
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 “የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብ እና ዘመናዊ ፕሮጀክት በእኔ እድሜ ተሰርቶ አያውቅም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ። ከተወለድኩ እናንተ የፓርላማ አባላትም ከተወለዳችሁ የቢሾፍቱ ኤርፖርት አይነት ውስብስብና በዘመናዊ መንገድ የሚመራ ፕሮጀክት ኖሮ አያውቅም ብለዋል። በአንድ ጊዜ አራት ሺህ የሚጠጋ ትራክ ተሽከርካሪ በአሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ነው ሱሉ አንስተዋል። ይህም ስራ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት(AI) ታግዞ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን የትራንስፖርት አስተዳደሩ በራሱ ከባድና ውስብስብ ነው ሲሉ ተናግረዋል። አሁን እየተሰራ ያለው ቦታውን የማዘጋጀት ስራ ከሶስት ወር ባነሰ ጊዜ ይጠናቀቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፕላን መንገድ (የራን ዌይ) ግንባታውን ለመስራት የጨረታ ሂደት ላይ ነው ብለዋል። የጨረታው ውጤትም በአንድ እና ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ይታወቃል ሲሉ ተናግረዋል። የቢሾፍቱ ኤርፖርትን ጨምሮ ግዙፍ የሆኑት እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣የጋዝና ሌሎቹም ሜጋ ፕሮጀክቶች አትችሉም፣ገንዘብ ከየት ታመጣላችሁ የሚል ጥያቄ እየተነሳ የሚሰሩ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያን እድገት በማይፈልጉና እነሱ በገዟቸው ሀገራት በኩል ይህ ጥያቄ በስውርም በግልፅ በሚዲያም ጭምር ይቀርባል ሲሉ ተናግረዋል። የተለየ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በቀር እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በታሰበው ጊዜ ይጠናቀቃሉም ብለዋል። ቴዎድሮስ ወርቁ
Открыть в Telegramኅዳር 17 2019 ኢትዮጵያ ባለፋት ሶስት ወራት ከውጭ ሀገር ላስገባቻቸው ምርቶች 6.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ ። ከዚህ ውስጥ ለነዳጅ የወጣው ወጪ ከባለው አመት አኳያ ሲታይ የ70 በመቶ ብልጫ እንዳሳየ አስረድተዋል። የነዳጅ ወጪ ሊጨምር የቻለውም በነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል። ከነበረው አለም አቀፍ ቀውስ አንፃር ሲታይ ኢትዮጵያ ነዳጅን በድጎማ ማቅረቧ ብቻ ሳይሆን ያስተዳደረችበት ሁኔታ አስደናቂ እንደነበረም አስረድተዋል። ባለፉት 3 ወራት ለገቢ ምርት 6.5 ቢሊን ዶላር ያወጣችው ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ ለወጭ ገበያ ካቀረበችው ምርት ሽያጭ 3.1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ይህም ከቀዳሚው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ25 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል። ከሰርቪስ ወይንም ከአገልግሎት 2.9 ቢሊዮን ዶላር፣ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ደግሞ 1.28 ቢሊዮን ዶላር በ2019 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት መገኘቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል። ንጋቱ ሙሉ
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 109 |
| 3 ч | 1 110 |
- Всего сейчас1 110
ኅዳር 17 2019 “ሰራተኛ አጥተን ታራሚ እስረኞችን እያሰራን ነው” መንግስት በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ ሰራተኛ በማጣት ታራሚ እስረኞችን ለማሰራት እየተገደደ ነው ተባለ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ችግር ቢኖርም የዛኑ ያክል ሰራተኛ ማግኘትም ችግር ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። እንደ ቀለም ቀቢ፣ፅዳት ባሉ ስራዎች ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ማግኘት ከባድ እየሆነብን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ የስራ አጥነት ችግር መኖሩን አንስተው የዛኑ ያክል ስራ መራጭ ትውልድም በዝቷል ብለዋል። ይህንን ሀሳብ የኢትዮጵያ ወላጆች በደንብ ያድምጡኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣በቀጥታ ክትትል የማደርግባቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሁሉ በቂ ሰራተኛ እያጣን እየተቸገርን ነው ብለዋል። በዚህ ምክንያት በቀን 600 እና 700 ብር እየከፈልን ታሳሪ ታራሚዎችን ቀጥረን ለማሰራት እየተገደድን ነው ብለዋል። እነሱ ላይ ሁሉ ስራው በዝቶ ጫና እየተፈጠረባቸው ነው ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ብዙ የስራ እድል መፈጠር ቢኖርበትም ስራ መራጭ የመሆን ችግርም መቀየር አለበት ነው ያሉት። ቴዎድሮስ ወርቁ
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 477 |
| 3 ч | 1 230 |
- Через 1 час477
- Всего сейчас1 230
ኅዳር 17 2019 የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት ከግብርናው ዘርፍ የበለጠ እድገት ማሳየት ጀምሯል ተባለ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢንዱስትሪው ግብርናውን እንዲመራው የማድረግ ፍላጎት ዘንድሮ የሚፈለገውን ሽግግር ማሳየት ጀምሯል ብለዋል። በዚህ ዓመት የግብርናው ዘርፍ እድገት 7.7 በመቶ ይሆናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢንዱስትሪው እድገት ግን 12.3 በመቶ ይሆናል ብለዋል። ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት(GDP) አንፃር የግብርና ድርሻ 31.4 በመቶ ሲሆን ግንባታን ጨምሮ የኢንዱስትሪ ድርሻ ግን 31.8 በመቶ ነው ሲሉ አስረድተዋል። አገልግሎት አሁንም ቀዳሚው ዘርፍ ሲሆን የዘንድሮ እድገቱ 9.9 በመቶ ይሆናል፣ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ ደግሞ ድርሻው 33.8 በመቶ ነው ተብሏል። ቴዎድሮስ ወርቁ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s=2 LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 576 |
| 4 ч | 1 300 |
- Через 1 час576
- Всего сейчас1 300
Связи
Похожие каналы
አዲስ ሪፖርተር - NEWS@addis_reporterНовости и СМИ36,1 тыс.
Sheger Press️️@sheger_pressНовости и СМИ35,7 тыс.
Addis መረጃ™@addis_merejaНовости и СМИ34,9 тыс.
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ@addismaledaНовости и СМИ33,7 тыс.
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal@zena24nowНовости и СМИ40,8 тыс.
"ኡማ ቲቪ " Tv@ethioomahtvchannleНовости и СМИ44,3 тыс.
ቀዳሚ ዜና@kedami_newsНовости и СМИ28,4 тыс.
4-3-3 World News@ethionews433Новости и СМИ49,8 тыс.