ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጊዜ እንዲገለጽ እና የፕሬስ ነጻነት ትኩረት እንዲያገኝ በምክር ቤቱ ጥያቄ ቀረበ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ ጥያቄ፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በየአሥር ዓመቱ መካሄድ የነበረበትና ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መቼ እንደሚደረግ እንዲገለጽ፣ እንዲሁም የፕሬስና የፖለቲካ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ። የምክር ቤት አባሉ በንግግራቸው፣ ሕገ-መንግሥቱ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ እንዲካሄድ ቢደነግግም ከ1997 ዓ.ም በኋላ በ2007 ዓ.ም መካሄድ የነበረበት ቆጠራ አለመካሄዱን አስታውሰዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ቀመር ለማውጣት፣ ፍትሐዊ የበጀት ድልድል ለማድረግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና የምርጫ ክልሎችን አከላለል ለመወሰን መነሻ የሚያደርገው ይህንኑ ቆጠራ መሆኑን የገለጹት ተናጋሪው፤ ቆጠራው አለመካሄዱ ፍትሐዊነትን እንደሚያጓድልና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን እንደሚያቀጭጭ አስገንዝበዋል። በመሆኑም ቆጠራው መቼ እንደሚካሄድ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ ተካቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በተያያዘም በቅርቡ የተካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ቢጠናቀቅም በርካታ ሕጸጾች እንደነበሩበት ተናጋሪው ጠቅሰዋል። የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ከፖለቲካና ከፕሬስ ነጻነት መስፋት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተው፣ ነጻው ፕሬስ እንደ አራተኛ መንግሥት የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና የመንግሥት ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ ረገድ ድርሻውን እንዲወጣ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ይሁን እንጂ የመንግሥት ወይም የፐብሊክ ሚዲያዎች መንግሥትን ከመቆጣጠርና ዲሞክራሲን ከመገንባት ይልቅ የመንግሥት አፈ ቀላጤ ሆነው መቀጠላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዳይጎለብትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጥረቱ እንዳይጠናከር እያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል። ስለሆነም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ የፖለቲካ ነጻነትና የፕሬስ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግር ተካቶ የመንግሥት የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ጠይቀዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegram
አዲስ ነገር መረጃ
#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 25, 2026 | 5,427 |
| Nov 26, 2026 | 2,292 |
Most viewed this month
- 01Views6.08KForwards—Reactions37Comments—
- 02Views6KForwards—Reactions23Comments—
- 03Views5.95KForwards—Reactions27Comments—
- 04Views5.7KForwards—Reactions28Comments—
Latest posts
ልዩ አማራጭ እና አዲስ ነገር በወለል 1 ቤት ብቻ ‼️ 🏙️60,000 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ውስጥ 🏠G+1 ቪላ ቤቶች 🏘️G+2 ታውን ሃውስ 🏢 G+4 አፓርትመንት ✅ በወለል 1 ቤት ብቻ 🛏️ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶች ✅ በ1 ዓመት የሚረከቡት እና የተጠናቀቁ ✅ በሙሉ ግንባታ (Fully finished) 🏘️ የመኖሪያ ግቢ ብቻ (Gated compound) 💰 በ 30% ቅድመ ክፍያ 🛏️ ባለ 2 መኝታ 103.6 ካሬ 0️⃣ ምድር ወለል (Ground floor) 💰 ክፍያ=4,497,897.60 🛏️ ባለ 3 መኝታ 125.8 ካሬ 1️⃣ አንደኛ ወለል (1st floor) 💰 ክፍያ = 5,849,700 2️⃣ ሁለተኛ ወለል ( 2nd floor) 💰 ክፍያ = 5,623,260 3️⃣ ሶስተኛ ወለል ( 3rd floor) 💰 ክፍያ = 5,340,210 4️⃣ አራተኛ ወለል ( 4th floor) 💰 ክፍያ = 5,135,659.20 📍በ ቦሌ ቡልቡላ ✅አስፈላጊ መሰረተ ልማት የተሟላለት ግቢ በዙሪያው 🍝ዓለም አቀፍ ሬስቶራንት እና ካፌዎች ፥ 🏫ትምህርት ቤቶች ፥ 🎡መዝናኛ ፓርክ ፥ ⚽የ ስፓርት ማዘውተሪያዎች ፥ 🛒ሱፐር ማርኬቶች እና የንግድ ማዕከሎች ✈️ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በ 5 ደቃቃ ርቀት ℹ️ ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ጉብኝት በስልክ ቁጥራችን 💬 በቀጥታ በ 📲 Whatsapp_https://wa.me/qr/TY4MQPKPEFXSI1 📲 Telegram ☎️ 0934244544
Open in Telegramየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር አወቀ ሃምዛዬ፣ በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጹ። የምክር ቤት አባሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርትን በመጥቀስ እንዳብራሩት፣ የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፤ በመንግሥት ኃይሎች፣ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች፣ በተለያዩ ቡድኖች እንዲሁም በፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ አካል ማጉደልና ዘረፋዎች የሕዝቡን ሰላማዊ ኑሮ በእጅጉ በመጉዳት ህልውናውን አደጋ ላይ ጥለውታል። በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ አርሲ፣ በሞያሌ አካባቢ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶና አበሽጌ፣ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬና ቡርጂ ዞኖች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ፣ ከበባ፣ መንገድ መዝጋትና የዜጎች ሞት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ዶ/ር አወቀ ገልጸዋል። ዶ/ር አወቀ በንግግራቸው የኮሬ ሕዝብን ጉዳይ በልዩ ትኩረት በማንሳት፣ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ታሪክ ሰምቶትም ሆነ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ ላለፉት 11 ዓመታት በፅንፈኛ ታጣቂዎች እየተወረረ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለምክር ቤቱና ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢቀርብም ወረራው ከትላንት በስቲያም፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ በዚህ ሰዓት መቀጠሉን ጠቅሰው፣ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የክልሉ የፀጥታ አካላትም አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈሉና እየሞቱ መሆኑን አስረድተዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramየደረት ማቃጠል የደረት ማቃጠል በተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ምልክት ነው። ከሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ በመመለስ (Acid Reflux) ምክንያት ሲከሰት፥ በሌላ ጊዜ ከልብ በሽታዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ምክንያቶች የሆድ አሲድ መመለስ (Acid Reflux)፦ የሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ ሲመለስ በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት ይፈጥራል። የልብ ችግር፦ ወደ ልብ ጡንቻ የሚደርሰው ደም ሲቀንስ ወይም ሲቋረጥ የደረት ማቃጠልና ጫና ሊሰማ ይችላል። የጡንቻ ችግር፦ በደረት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ሲጎዱ ወይም ሲወጠሩ ሕመም ሊከሰት ይችላል። የሳንባ ችግር፦ አንዳንድ የሳንባ በሽታዎችም በደረት አካባቢ ሕመምና ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ። የደረት ማቃጠል መቼ አደገኛ ይሆናል? የደረት ማቃጠል በራሱ ሁልጊዜ የልብ ድካም ምልክት አይደለም። ነገር ግን ከሚከተሉት ሁኔታዎች ጋር ከተያያዘ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramቡርኪናፋሶ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባችውን ግዙፍ የቴክኖሎጂ አካዳሚ መርቃ ከፈተች የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በ11 ወራት ጊዜ ውስጥ የተገነባውን «አካዳሚ ቴክኖሎጂክ ዱ ፋሶ» የተሰኘ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኅዳር 23 ቀን 2026) መርቀው ከፈቱ። በ60 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ የትምህርትና ምርምር ተቋም፣ የሀገሪቱን ሳይንሳዊ ራስን መቻልና የኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠን ታልሞ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል። አካዳሚው በመጀመሪያው ዙር 250 ተማሪዎችን ተቀብሎ የኒውክሌር ምሕንድስና፣ አቪዬሽን፣ ማዕድን እና የሳይበር ደኅንነትን ጨምሮ በ11 ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሥልጠና እንደሚሰጥ ተመላክቷል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramመርጌታ ጌታቸው የባህል መድህኒት ፈውስ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☞ ለመፍትሄ ሀብት ☞ ለህመም ☞ ለመስተፋቅር ☞ ቡዳ ለበላው ☞ ለገበያ ☞ ሚስጥር የሚነግር ☞ ለቀለም(ለትምህርት) ☞ ለመፍትሔ ስራይ ☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ ☞ ሌባ የማያስነካ ☞ ለበረከት ☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) ☞ ለግርማ ሞገስ ☞ መርበቡተ ሰለሞን ☞ ለዓይነ ጥላ ☞ ለሁሉ መስተፋቅር ☞ ጸሎተ ዕለታት ☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ ☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) ☞ ለትዳር ☞ ለድምፅ 👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ ጌታቸው የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹። 📞09 21007264 📞09 21007264 👉 የብልት ማነስ 👉የመልፈስፈስ 👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት ለበለጠ መረጃ 👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23 በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም 🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር ውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን 🍀🌿🙏ልብ ይበሉ ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
Open in Telegramየቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን🙏 በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡ በኃይል በጸጋና በመንፈሳ ተሞልቶ የወንጌሉን ብስራት ይሰብክ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡ ታላቁ ሰማዕት የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ኋላም የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን ጠይቆ ወደ ጌታችን በመሔድ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፡፡ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐ ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን ተሹሟል፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን ቢያስፋፋ አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸውና በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በተወለደበት ጥር 1 ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ሲወግሩትም ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ እንደ አምላኩ ለሚወግሩት ሰዎች “የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ገዳማውያን ሰማዕቱን አብነት አድረገው በጸሎትና በጾም እየተጉ የሥጋ ፍላጎትን ድል ያደርጉታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡ ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Open in Telegramለዓመታት በግጦሽ ሳር፣ በውሃ እና በመሬት ይገባኛል ምክንያት ሲከሰት የቆየው የአፋር እና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰቦች ግጭት፣ አሁን ከቀን ወደ ሌሊት በተሸጋገረ ከባድ ውጊያ መቀጠሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለከፋ ስጋት ዳርጓል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የፌደራል መንግስት እና የሀገር ሽማግሌዎች ያደረጓቸው የእርቅ ስምምነቶች ዘላቂ ባለመሆናቸው፣ የአካባቢው ሰላም ተደጋግሞ እየተናጋ እና ዜጎች ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።ዳግም አገርሽቶ አንድ ወር እንዳስቆጠረ የሚነገረው የአፋር የሶማሌ ኢሳ ጎሳ የድንበር ግጭት ከዚህ ቀደም ከነበረበት የአፋር ክልል ዞን 3 ሀሩካ፣ አቢዳ እና አርጋቶ የድንበር አካባቢ አሁን ደግሞ ወደ ዞን 1 ገርቢ አካባቢ ከትላንት ሰኞ ጀምሮ መቀጠሉን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገልጹት። ዶቼቬሌ @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramየትራምፕ አስተዳደር በ14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮች ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) ጣለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለፋብሪካዎቻቸው ድጎማ በማድረግ ከፍላጎት በላይ ያመርታሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ገበያውን በርካሽ ምርት ያጥለቀልቃሉ ባላቸው 14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮቹ ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) መጣሉን አስታውቋል። እርምጃው ቻይናን ፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ ህንድን ፣ ጃፓንን ፣ ደቡብ ኮሪያን ፣ ቬትናምን ፣ ኢንዶኔዥያን ፣ ታይላንድን ፣ ማሌዥያን ፣ ሲንጋፖርን ፣ ታይዋንን ፣ ስዊዘርላንድን ፣ ባንግላዴሽን እና ካምቦዲያን ኢላማ ያደረገ ነው። በምርመራው ላይ ተካትተው የነበሩት ሜክሲኮ እና ኖርዌይ ግን ለጊዜው ከቅጣቱ ተርፈዋል። ከሁሉም ሀገራት በላይ ቻይና ቀደም ሲል ከነበረባት የ25 በመቶ ታሪፍ በተጨማሪ አዲስ የ20 በመቶ ቀረጥ በመጣሉ ከፍተኛውን ቅጣት ትሸከማለች። ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ ቀደም ሲል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣሉትን ታሪፍ ውድቅ ስላደረገባቸው አሁን እርምጃውን የወሰዱት እ.ኤ.አ በ1974 በወጣው የንግድ ህግ ሴክሽን 301 መሰረት ሲሆን ይህ ህግ የውጭ መንግስታት ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ አሰራር ሲከተሉ እና የአሜሪካን ኩባንያዎች ሲጎዱ ፕሬዝዳንቱ የአጸፋዊ ቀረጥ እንዲጥሉ ሙሉ ሥልጣን ይሰጣል። የንግድ ባለሙያዎች ይህ ውሳኔ በአሜሪካ የኑሮ ውድነትን ይበልጥ እንደሚያባብስ ፤ አነስተኛ ነጋዴዎችን እንደሚጎዳ እና ከቻይና እንዲሁም ከሌሎች አጋር ሀገራት ጋር ያለውን የንግድ ውጥረት እንደሚያከርረው ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramConnections
Similar channels
National ID Program - Ethiopia@idethiopiaNews and media104K
ETHIO-MEREJA®@ethio_merejaNews and media96.4K
ጉርሻ Tube@gurshatubeNews and media111K
ATC NEWS@atc_newsNews and media118K
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)@ebcnewsnowNews and media132K
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ@eliasmeseretNews and media135K
Meseret Media@meseretmediaNews and media75.7K
YeneTube@yenetubeNews and media143K