ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በምን ዓይነት ሰነድ መጠቀም ይቻላል? ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ማንኛውም ማንነትን የሚያረጋግጥ እና የግለሰቡ ፎቶ ያለበት ሰነድ መቅረብ ይኖርበታል። (id.gov.et/proof) 📌 በቅርብ ጊዜ ያስተዋልነው ጉዳይ፤ ብዙ ተመዝጋቢዎች በምዝገባ ወቅት የልደት ቀናቸውን በጥንቃቄ ስለማያስገቡ፣ በኋላ ላይ መረጃቸውን ለማዘመንና ለማስተካከል በድጋሚ ለመመላለስ እየተገደዱ ይገኛል። ስለሆነም በምዝገባ ጊዜ የልደት ቀንዎን በሚገባ አስተውለው ትክክለኛውን መረጃ ብቻ እንዲያስገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። 📌 ለፋይዳ ሲመዘገቡ ሙሉ ስም፣ የልደት ቀን እና ሌሎች ወሳኝ መረጃዎችን በግልጽ የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ እንዲሁም በምዝገባ ወቅት የሚያስገቡት መረጃ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። መረጃን ለማስተካከል ወይም ለማዘመን የሚወስድብዎትን ተጨማሪ ጊዜና ወጪ አስቀድመው ይቆጥቡ!
Open in Telegram
National ID Program - Ethiopia
Identity is the new collateral! መታወቅ ለመተማመን። የፋይዳ ቁጥር ለማግኘት ወደ *9779# ይደውሉ። ሁሉን አገልግሎቶች በአንድ የሚያገኙበትን የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ከአፕ ስቶር (https://play.google.com/store/apps/details?id=et.fayda.nidfaydaApp) ወይም https://apps.apple.com/app/fayda-i) ያውርዱ።
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 4, 2026 | 25,451 |
| Nov 5, 2026 | 27,294 |
| Nov 6, 2026 | 28,755 |
| Nov 8, 2026 | 26,042 |
| Nov 9, 2026 | 26,502 |
| Nov 10, 2026 | 29,335 |
| Nov 12, 2026 | 31,118 |
| Nov 15, 2026 | 25,377 |
| Nov 18, 2026 | 19,900 |
| Nov 19, 2026 | 19,164 |
| Nov 20, 2026 | 17,171 |
| Nov 21, 2026 | 11,704 |
| Nov 26, 2026 | 1,090 |
Most viewed this month
- 01Views31.1KForwards27Reactions55Comments397
- 02Views29.3KForwards64Reactions64Comments281
- 03Views28.8KForwards67Reactions51Comments360
- 04Views28.1KForwards55Reactions58Comments147
Latest posts
በኦንላይን ወይም መተግበሪያ በመጠቀም ብቻ የፋይዳ መታወቂያ ማግኘት ይቻላል? የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እያንዳንዱን ሰው በልዩ ሁኔታ የሚለይ መታወቂያ በመሆኑ፤ የምዝገባ ሂደቱ የባዮሜትሪክ መረጃዎችን (የፊት ፎቶ፣ የጣት እና የአይን አሻራ) ማካተት እንዲሁም እንደ ምስክር ሆኖ የሚመዘግብ መዝጋቢ ኦፊሰር ያስፈልጋል። ይህንን አስፈላጊ ሂደት ለማጠናቀቅ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመሄድ መመዝገብ ይኖርብዎታል። #ፋይዳለኢትዮጵያ
Open in Telegramኑ በላይቭ እንወያይ! ነገ አርብ ህዳር 11፣ 2019 ከቀኑ 10፡00 በቲክቶክ፣ እና ቴሌግራም ገጾቻችን በቀጥታ ስርጭት እንገናኛለን። ✅ የቲክቶክ ቻናላችን፡ tiktok.com/@idethiopia ✅ የቴሌግራም ቻናላችን፡ https://t.me/IDethiopia እንዳያመልጥዎ! ጥያቄና እና አስተያየትዎን ይዘው ይቀላቀሉን!
Open in Telegramየዴሞግራፊክ መረጃ ለማዘመን በኦንላይን ላይ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሊደረግባቸው የሚችሉት ምክንያቶችን በዝርዝር ይመልከቱ። ✅ ጥያቄዎ ውድቅ የተደረገበትን ትክክለኛ ምክንያት በፅሁፍ መልዕክት (SMS) ወይም በኢሜይል ሲለሚላክልዎ እሱን በማየት እና ስህተቱን በማረም በድጋሚ በ id.et/update ላይ ማመልከት ይችላሉ። #ፋይዳለኢትዮጵያ
Open in Telegramየዴሞግራፊክ መረጃ «እርማት» እና «ማሻሻያ» የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን ያውቃሉ? የመረጃ እርማት ወይም ለውጥ ሲያስፈልግዎ፣ በድረ-ገጻችን id.et/update በመግባት የትኞቹን መረጃዎች በቀላሉ ማስተካከል እንደሚችሉ እና የትኞቹ ደግሞ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንደሚያስፈልጋቸው ግራ ከተጋቡ ይህንን ቪዲዮ እስከ መጨረሻው ይመልከቱ፡፡ ለበለጠ መረጃ፡ id.et/resources ይጎብኙ። #ፋይዳለኢትዮጵያ
Open in Telegramለፋይዳ መታወቂያ ሲመዘገቡ የራስዎ ስልክ ቁጥር አልነበረዎትም? ወይስ በምዝገባ ወቅት ያስገቡት ስልክ ቁጥር ተሳስቷል? እነዚህን ለማስተካከል ከሚከተሉት ትክክለኛ አማራጮች መካከል ይጠቀሙ ፡ 1. ለፋይዳ ሲመዘገቡ በሌላ ሰው ስልክ ቁጥር ተመዝገበው ከነበረ እና አሁን ወደ ራስዎ ስልክ ቁጥር ለመቀየር ከፈለጉ ድረገፅ id.et/update ላይ በመግባት በአካል መሄድ ሳያስፈልግዎ ወይም በምዝገባ ጣቢያዎች በመሔድ መቀየር ይችላሉ። (ያስተውሉ፡ በዚህ ሂደት ወደ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል ወይም OTP ነባሩም አዲሱም ስልክ ስለሚላክ ሁለቱም ስልክ በእጅዎ ሊሆን ይገባል) 2. እንዲሁም በምዝገባ ወቅት የራስዎ ስልክ ቁጥር ሲሞላ የቁጥር ስህተት ካጋጠሞት ወይም ደግሞ ስልክ ቁጥሩ ከጠፋብዎ በአቅራቢያ በሚያገኟቸው የምዝገባ ጣቢያዎች በአካል በመሄድ መቀየር ይችላሉ። #ፋይዳለኢትዮጵያ
Open in Telegramፋይዳ ከሰሞኑ: ዋና ዋና ክንውኖች በምስል በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን ፡ ፌስቡክ | X | ሊንክዲን | ቴሌግራም | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ብሉስካይ | ዋትስአፕ | ኢንስታግራም
Open in TelegramConnections
Similar channels
አዲስ ነገር መረጃ@addis_newsNews and media102K
ጉርሻ Tube@gurshatubeNews and media111K
ETHIO-MEREJA®@ethio_merejaNews and media96.4K
ATC NEWS@atc_newsNews and media118K
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)@ebcnewsnowNews and media132K
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ@eliasmeseretNews and media135K
YeneTube@yenetubeNews and media143K
Meseret Media@meseretmediaNews and media75.7K
Mentions
telebirr@telebirr1 repost