የመንግሥትና የግል ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ:: በኢትዮጵያ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዴት መስተካከል እንዳለበት የሚያመላክት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው። በማብራሪያቸውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ያነሱት ዶክተር ዐቢይ፣ የአገሪቱ የዕዳ ጫና ሽግሽግ ተደርጎለት ወደ መካከለኛ ደረጃ መውረዱን ለዚህ በማሳያነት ጠቅሰዋል። የዋጋ ግሽበት በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል፦ 1. የመንግሥት ድጎማዎችን ማድረግ 2. የደሞዝ ጭማሪዎችን ተግባራዊ ማድረግ 3. ሌሎች የዜጎችን ጫና የሚያቃልሉ አማራጮችን መጠቀም የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥልና የሚያጋጥሙ ውስን የኑሮ ጫናዎችን ለመቅረፍ ተከታታይ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegram
ጉርሻ Tube
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 25, 2026 | 9,519 |
| Nov 26, 2026 | 3,622 |
Most viewed this month
- 01Views11KForwards—Reactions183Comments—
- 02Views10.7KForwards—Reactions97Comments—
- 03Views10.7KForwards—Reactions203Comments—
- 04Views10.6KForwards—Reactions42Comments—
Latest posts
ሥራ የለም” የሚሉት የሥራ ዕድሉን ስለናቁት ነው እንጂ ሠራተኛ በመጥፋቱ እስረኞችን በቀን እስከ 700 ብር እየከፈልን እያሠራን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመከናወን ላይ ባሉ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሰው ኃይል እጥረት በማጋጠሙ፣ መንግሥት እስረኞችን በቀን ከ500 እስከ 700 ብር ክፍያ በመመደብ እንዲሠሩ እያደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። በአገሪቱ “ሥራ የለም” የሚል ወቀሳ ቢሰማም፣ እሳቸው በቀጥታ በሚከታተሏቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ ግን ሠራተኛ ማግኘት ፈታኝ መሆኑን ጠቁመዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች እስረኞቹ ራሳቸው “ደከመን አንሠራም” እስከማለት መድረሳቸውንም አክለው ገልጸዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ በተለይም እንደ * ሹፌርነት፣ * ቀለም ቅብ፣ * ጽዳት እና * ወለል ማንጠፍ ባሉ የሙያ ዘርፎች ላይ ሰው አግኝቶ ማሠራት አስቸጋሪ ሆኗል። ለዚህ ችግር መንስኤዎቹ የሥራ መምረጥ ባህል መስፋፋት እና በሥራ ቦታ የሚታይ ሌብነት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በቀን ከ500 እስከ 600 ብር የሚከፈልበትን የቀን ሥራ በወር ለ20 እና 25 ቀናት የሚሠራ ሰው ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደሚችል ያስረዱት ዶክተር ዐቢይ፣ ይህንን ዕድል ንቆ “ሥራ የለም” በሚል ከአገር መሰደድ ተገቢ አለመሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ወላጆችም በየአካባቢው ስላለው ሰፊ የሥራ ዕድል ትኩረት ሰጥተው እንዲያጤኑት ጥሪ አቅርበዋል። ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramበሪያድ 17 ኪሎ ግራም ሃሺሽ ይዞ የተገኘ ኢትዮጵያዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ እንደ ሳዑዲ ጋዜት (Saudi Gazette) ዘገባ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ የአደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር ዋና ዳይሬክቶሬት በዋና ከተማዋ ሪያድ ውስጥ 17 ኪሎ ግራም ሃሺሽ ለማሰራጨት ሲንቀሳቀስ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ ተጠርጣሪ መያዙን ይፋ አድርጓል። ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ሕገ-ወጥ ዕፁን በከተማዋ ለማዘዋወር ሲሞክር በተደረገበት ጥርጣሬ መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል። Via Saudi Gazette ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramየቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን🙏 በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡ በኃይል በጸጋና በመንፈሳ ተሞልቶ የወንጌሉን ብስራት ይሰብክ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡ ታላቁ ሰማዕት የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ኋላም የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን ጠይቆ ወደ ጌታችን በመሔድ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፡፡ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐ ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን ተሹሟል፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን ቢያስፋፋ አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸውና በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በተወለደበት ጥር 1 ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ሲወግሩትም ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ እንደ አምላኩ ለሚወግሩት ሰዎች “የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ገዳማውያን ሰማዕቱን አብነት አድረገው በጸሎትና በጾም እየተጉ የሥጋ ፍላጎትን ድል ያደርጉታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡ ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444 🙏🙏🙏
Open in Telegramበአውሮፓ መድረክ ኢንተር ሚላን ድል ሲቀናው ማንችስተር ዩናይትድ ከመመራት ተነስቶ አቻ ተለያየ በተካሄዱ የአውሮፓ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የጣሊያኑ ክለብ ኢንተር ሚላን ጣፋጭ ድል ሲያስመዘግብ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። በሜዳው ስቱትጋርትን ያስተናገደው ኢንተር ሚላን በሱቺች እና በማርቲኔዝ ግቦች ታግዞ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ቡድኑ በጨዋታው ላይ ያሳየው ብልጫ መረቡን ሳያስደፍር ወሳኝ ድል እንዲቀዳጅ አስችሎታል። በሌላ በኩል ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ስፖርቲንግን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል። የሌሎች ጨዋታዎች አጠቃላይ ውጤት፦ * ብሩጅ 0-3 ሊቨርፑል፦ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ አይሳክ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች እና በቨርትዝ አንድ ግብ ታግዞ ሰፊ ድል አስመዝግቧል። * ሊል 2-1 ባየር ሙኒክ፦ የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየር ሙኒክ በአፕሜካኖ አማካኝነት አንድ ግብ ቢያስቆጥርም፣ ኡዳ እና ፓቭሎቪች በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠሩት ግብ ሊል ድል ቀንቶታል። * ፒኤስጂ 2-2 ሮማ፦ ብርቱ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ለፒኤስጂ ዛባርኒ እና ዴምቤሌ፣ ለሮማ ደግሞ ሄርሞሶ እና ማለን ግቦቹን በማስቆጠር ነጥብ ተጋርተዋል። * አትሌቲኮ ማድሪድ 2-0 ቫይኪንግ፦ የስፔኑ ክለብ በሶርሎት እና በአልቫሬዝ ግቦች ንጹህ ድል አግኝቷል። * ሻካታር 0-1 ፌነርባቼ፦ ፌነርባቼ በሙሪክ ብቸኛ ግብ ከሜዳው ውጭ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ ተመልሷል። ⚽️⚽️⚽️ 📷Tikvah Sport ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramየዱባይ ታዋቂው የሬዲዮ አቅራቢ ክሪስ ፌድ ኢትዮጵያዊውን የታክሲ ሹፌር ከናፈቀው ልጁ ጋር ለማገናኘት የ10 ሺህ ድርሃም ስጦታ አበረከተ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ነዋሪ የሆነው ኢትዮጵያዊው የታክሲ ሹፌር ብስራት፣ ለሁለት ዓመታት ተለይቶት የኖረውን የአራት ዓመት ልጁን ለመጠየቅ የሚያስችለውን የገንዘብ ድጋፍ በታዋቂው የሬዲዮ አቅራቢ ክሪስ ፌድ (Kris Fade) አማካኝነት አግኝቷል። ክስተቱ የተፈጠረው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አድማጮች በሚከታተሉት የክሪስ ፌድ የጠዋት የቀጥታ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ነው። ብስራት ወደ ፕሮግራሙ በስልክ በደወለበት ወቅት የሬዲዮ አቅራቢው ስለ ስራውና ስለ ህይወቱ ጥያቄ አቅርቦለታል። ብስራትም በታክሲ ሹፌርነት ተሰማርቶ እንደሚሰራ እና “አሜን” የተባለ የአራት ዓመት ልጅ እንዳለው በመግለጽ፣ ልጁን ካየው ሁለት ዓመታት እንደተቆጠሩ ተናግሯል። ይህንን የሰማው ትውልደ ሊባኖሳዊው አውስትራሊያዊ አቅራቢ፣ ብስራት ወደ ሀገሩ ተጉዞ ልጁን ለማየት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ጠይቆታል። ብስራትም 10 ሺህ ድርሃም (በኢትዮጵያ ብር ወደ 500 ሺህ ብር ገደማ) እንደሚያስፈልገው ሲገልጽ፣ ክሪስ ፌድ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ እንደሚሸፍንለት ቃል በመግባት 10 ሺህ ድርሃሙ በባንክ አካውንቱ እንዲገባለት አድርጓል። ለበርካታ ዓመታት በዱባይ የሬዲዮ ፕሮግራም አቅራቢነት የሚታወቀው ክሪስ ፌድ ያደረገው ይህ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ አባትና ልጅን ዳግም ለማገናኘት ትልቅ ዕድል ፈጥሯል። 👏👏👏 ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramየወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሾፌር በስህተት የገባላቸውን 399,000 ብር ሳያውኩ መለሱ:: ወራቤ፣ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም — በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሸምሴ ሙሰማ ራህመቶ፣ በስህተት ወደ ባንክ ሂሳባቸው የገባን 399,000 ብር ለባለቤቱ መመለሳቸውን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ። በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሾፌርነት የሚያገለግሉት አቶ ሸምሴ፣ ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ወደ አካውንታቸው መግባቱን ሲመለከቱ ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ በማምራት ገንዘቡ የእርሳቸው አለመሆኑን አሳውቀዋል። በዚህም መሠረት የገንዘቡ ባለቤት የሆኑት አቶ ሙሰፋ አብደላ ተለይተው 399,000 ብሩ ወደ ባለቤቱ ሂሳብ እንዲመለስ ተደርጓል። ላሳዩት ታማኝነትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ይፋዊ የምስጋና ደብዳቤ አበርክቶላቸዋል። የዲጂታል ክፍያ አማራጮች መስፋፋትን ተከትሎ በስህተት ወደ ሌላ ሰው አካውንት ገንዘብ የመላክ አጋጣሚዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። በህግ መሠረት በስህተት የተላለፈ ገንዘብን መመለስ ግዴታ ሲሆን፣ ያለአግባብ አስቀርቶ መጠቀም በወንጀል ያስጠይቃል። የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አቶ ሸምሴ ህሊናቸውን አስቀድመው ላሳዩት መልካም ሥነ-ምግባር ምስጋና በማቅረብ፣ ህብረተሰቡም ይህንኑ አርአያነት ያለው ተግባር እንዲከተል ጥሪ አቅርቧል። Via በብሩክ አሰፋ (ምክትል ኢንስፔክተር) ©️ Central Ethiopia Police Commission ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramበስህተት ወደ አካውንቱ የገባውን 150 ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሱት የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ አባል የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ አባል የሆኑት ኢንስፔክተር ለማ ፀጋዬ፣ በስህተት ወደ አካውንታቸው ገቢ የተደረገውን 150 ሺህ ብር ለባለቤቱ፣ ለአቶ ገብረሰላም ገብሩ መኮንን በመመለስ የታማኝነት ተግባር መፈጸማቸው ተገለጸ። የገንዘብ ዝውውር እና የባንክ አሠራር በሰፊው በሚዘወተርበት በአሁኑ ወቅት፣ በስህተት የሚተላለፉ ገንዘቦችን ያለምንም ማመንታት ወደ ትክክለኛው ባለቤት መመለስ ከፍተኛ የሥነ-ምግባር እና የኃላፊነት ስሜትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። የኢንስፔክተር ለማ ፀጋዬ ይህንን እርምጃ መውሰድ፣ የሕግ አስከባሪ አካላት በኅብረተሰቡ ዘንድ ያላቸውን መልካም ገጽታ እና ታማኝነት ይበልጥ የሚያጎላ ሆኖ ተወስዷል። በዕለት ተዕለት የሕይወት እና የሥራ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚታዩ እንዲህ ያሉ አዎንታዊ ድርጊቶች፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የመተማመን እና የመረዳዳት ባህል እንዲጎለብት በጎ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። ጉርሻ Page 🌴🌴🌴
Open in Telegramእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ከክፉ ነገር ትከልለን፤ የልባችንን መልካም መሻትም ትሙላልን🙏 መንገስተ ሰማያት መግቢያ ኪዳን አባቶቻችን የሃዘን ብዛት የእንባ ጎርፍ አይን ያጠፋል፣ ፊት ያንጣጣል፣ ልብ ይሰውራል አካልንም ያዝላል ይላሉ፡፡ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በምድረ ግብጽ በስደቷ ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ድረስ አልቅሳለች፡፡ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ ሆና ከእርሱ ከተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ጸልያለች፡፡ ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ይህም ታላቅ በዓል ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እየተባለ በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን ይከበራል፡፡ ይህ ዕለት ድንቅ ተአምራትም ያደረገችበት ነው፡፡ ስምዖን የሚባል የአባታችን የቅዱስ አብርሃምን ታሪክ የሰማና እንደ እርሱ እንግዳ መቀበል የሚወድ ሰው ነበር፡፡ ጠላታችን ሰይጣንም እንግዳ መስሎ ወደ ቤቱ በመምጣት ልጅህን አርደህ አብላኝ አለው፡፡ እርሱም “አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው” በሚል እሳቤ ያለውን አደረገ፡፡ ሲያቀርብለትም ቅመስልኝ አለው፤ እሺ ብሎ ሲቀምስለት በዚያው ተዋሐደው፡፡ ከዚህ በኋላ በላኤ ከቤተሰቦቹ ጀምሮ “በላዔ ሰብእ” ወይም “ሰው በላው” እስኪባል ድረስ 78 ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ የቆሰለ ነዳይ አይቶ ሊበላው ሲቀርብ ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፡፡ ነዳዩ ግን ውሃ አጠጣኝ ሲል በሥላሴ፣ በቅዱሳን ሁሉ ስም ቢለምነው፤ አልሰማውም፡፡ በድንግል ማርያም ስም ሲለው በአእመሮው አቃጨለበትና “ምህረት እንደምታሰጥ በልጅነቴ ሰምቻለሁ” ብሎ ከያዘው ውሃ ጥቂት አጠጣው፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አጊኝቶ ሊበላው ሲል “አንተ ያ በላዔ የምትባል ነህ?” አለው፡፡ ለካ ይህ ነገር ተሰምቶብኛል ብሎ ወደ አንድ ዋሻ ሔዶ በጸጸት ሞቷል፡፡ የጨለማ መላዕክት ነፍሱን በጌታ ፊት ሲያቀርቧትም እመቤታችን “ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ” አለችው፡፡ ጌታችንም ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋና ፈጣሪውን የካደ እንዴት ይማራል አላት፤ እመቤታችንም በስሜ የተጠማውን አጠጥቷል ስትል ነፍሱን አስምራዋለች፡፡ እኛንም በቃል ኪዳኗ ታስምረን፣ አማላጅነቷም አይለየን፡፡ አሜን!!! ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444 🙏🙏🙏
Open in TelegramConnections
Similar channels
ATC NEWS@atc_newsNews and media118K
National ID Program - Ethiopia@idethiopiaNews and media104K
አዲስ ነገር መረጃ@addis_newsNews and media102K
ETHIO-MEREJA®@ethio_merejaNews and media96.4K
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)@ebcnewsnowNews and media132K
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ@eliasmeseretNews and media135K
YeneTube@yenetubeNews and media143K
Meseret Media@meseretmediaNews and media75.7K