Кабинет
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Юзернейм
@addis_news
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики101 741
Просмотров на пост, 7 дн.3 867за 7 дней
ERR3,80 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
25 нояб. 2026 г.5 427
26 нояб. 2026 г.2 931

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    ለChatGPT ወይም ለGemini "ሰላም" ስትለው፣ እሱ በዚያው ቅጽበት አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ጭልጥ አድርጎ እንደሚጠጣ ታውቃለህ? 😂💧 የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት፣ ክላውድ (Cloud) እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚያንቀሳቅሱት ግዙፍ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ጉሮሯቸው በጣም ደረቅ ነው! ሰርቨሮቻቸው ከመጠን በላይ ግለው እንዳይቃጠሉ ለማቀዝቀዝ በቀን እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ንጹሕ ውኃ ይጠጣሉ። እስቲ ይህንን አስቡት አንድ ትልቅ የዳታ ማዕከል በቀን ከ1 እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ ይጠቀማል። ይህ ማለት 50,000 ሕዝብ ያላትን አንዲት ሙሉ ከተማ የውኃ ፍጆታ ብቻውን ይጨርሳል ማለት ነው፤ ከእነዚህ ጋር ውኃ መጋራት ራሱ ይከብዳል! ዋናው ችግር ደግሞ የተጠቀሙት ውኃ ተመልሶ አለመገኘቱ ነው። "የጠጡት" ውኃ በትነት መልክ ወደ ሰማይ ስለሚወጣ፣ ተመልሶ ወደ ወንዙም ሆነ ወደ ቧንቧችን አይገባም። የሚገርመው ደግሞ ከ2022 ወዲህ ከተገነቡት አዳዲስ ማዕከላት መካከል ሁለት ሦስተኛው የተተከሉት ቀድሞውኑ ከፍተኛ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የአካባቢው ገበሬ ቤተሰቡና እንስሳቱ በውኃ ጥም እየተቸገሩ፣ ሰርቨሮቹ ግን "ውኃ አምጡ" ይላሉ። ይበልጥ አሳሳቢው ግን የወደፊቱ ስጋት ነው! በቴክሳስ ብቻ በ2025 ወደ 49 ቢሊዮን ጋሎን ውኃ የጠጡት እነዚህ ማዕከላት፣ በ2030 ጥማታቸው ጨምሮ 399 ቢሊዮን ጋሎን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል። ቴክኖሎጂው መልካም ነው፤ ሕይወታችንንም አቅልሎልናል። ሆኖም የሰው ልጅንና የተፈጥሮን ጉሮሮ እያደረቀ መሆን የለበትም አይደል? አዳዲስ የዳታ ማዕከላት ከመገንባታቸው በፊት "ውኃውን ከየት ነው የምታመጡት? ስንትስ ትጠቀማላችሁ?" ተብለው ሊጠየቁ ይገባል። @Addis_News @Addis_News

    Фото
    Просмотры6,08 тыс.
    Пересылки—
    Реакции37
    Комментарии—
  2. 02

    የትራምፕ አስተዳደር በ14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮች ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) ጣለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለፋብሪካዎቻቸው ድጎማ በማድረግ ከፍላጎት በላይ ያመርታሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ገበያውን በርካሽ ምርት ያጥለቀልቃሉ ባላቸው 14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮቹ ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) መጣሉን አስታውቋል። እርምጃው ቻይናን ፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ ህንድን ፣ ጃፓንን ፣ ደቡብ ኮሪያን ፣ ቬትናምን ፣ ኢንዶኔዥያን ፣ ታይላንድን ፣ ማሌዥያን ፣ ሲንጋፖርን ፣ ታይዋንን ፣ ስዊዘርላንድን ፣ ባንግላዴሽን እና ካምቦዲያን ኢላማ ያደረገ ነው። በምርመራው ላይ ተካትተው የነበሩት ሜክሲኮ እና ኖርዌይ ግን ለጊዜው ከቅጣቱ ተርፈዋል። ከሁሉም ሀገራት በላይ ቻይና ቀደም ሲል ከነበረባት የ25 በመቶ ታሪፍ በተጨማሪ አዲስ የ20 በመቶ ቀረጥ በመጣሉ ከፍተኛውን ቅጣት ትሸከማለች። ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ ቀደም ሲል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣሉትን ታሪፍ ውድቅ ስላደረገባቸው አሁን እርምጃውን የወሰዱት እ.ኤ.አ በ1974 በወጣው የንግድ ህግ ሴክሽን 301 መሰረት ሲሆን ይህ ህግ የውጭ መንግስታት ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ አሰራር ሲከተሉ እና የአሜሪካን ኩባንያዎች ሲጎዱ ፕሬዝዳንቱ የአጸፋዊ ቀረጥ እንዲጥሉ ሙሉ ሥልጣን ይሰጣል። የንግድ ባለሙያዎች ይህ ውሳኔ በአሜሪካ የኑሮ ውድነትን ይበልጥ እንደሚያባብስ ፤ አነስተኛ ነጋዴዎችን እንደሚጎዳ እና ከቻይና እንዲሁም ከሌሎች አጋር ሀገራት ጋር ያለውን የንግድ ውጥረት እንደሚያከርረው ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። @Addis_News @Addis_News

    Фото
    Просмотры6 тыс.
    Пересылки—
    Реакции23
    Комментарии—
  3. 03

    ግብፅና ሱዳን የባሕር ጠረፍ ለሌላቸው ሀገራት የሚሰጥ የባሕር በር ተደራሽነትንና ቀይ ባሕርን ወታደራዊ ቀጠና የማድረግ ሙከራዎችን ውድቅ አደረጉ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል እድሪስ ትናንት ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም በካይሮ ባደረጉት ውይይትና ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የቀይ ባሕር አስተዳደር የባሕር ጠረፍ ሀገራት ብቻ መብት መሆኑን በመግለጽ የባሕር ጠረፍ ሀገራትን ሉዓላዊነት በሚጎዳ መልኩ የባሕር በር ለሌላቸው ሀገራት የሚሰጥ ተደራሽነትን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። ሁለቱ መሪዎች የባሕር መስመሩን ወታደራዊ ቀጠና ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎችን በጋራ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ከጦርነት በኋላ ለሚከናወነው የሱዳን መልሶ ግንባታ ቅድሚያ ለመስጠትና ፖለቲካዊ አጋርነታቸውን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚና የልማት ፕሮጀክቶች ለመለወጥ ተስማምተዋል። ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ የሱዳን ዜጎች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ እንዲሁም በግብፅ እስር ቤቶች የሚገኙ ሱዳናውያን ቀሪ የእስር ጊዜያቸውን በሀገራቸው እንዲጨርሱ የሚያስችል ዕቅድ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጥተዋል። የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል በበኩላቸው ሱዳን በአፍሪካ ሕብረትና በሌሎች አህጉራዊ ተቋማት ያላትን ተሳትፎ እንድትመልስ የግብፅን ድጋፍ የጠየቁ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በቀይ ባሕር ጸጥታ ዙሪያ ከኤርትራና ከሶማሊያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ቅንጅት አጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል። @Addis_News @Addis_News

    Фото
    Просмотры5,95 тыс.
    Пересылки—
    Реакции27
    Комментарии—
  4. 04

    ጥንቃቄ ‼️ ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦ •  +947 •  +371 •  +563 •  +370 •  +255 ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381 እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል። የሀገራት መለያ ኮዶች፦ •  +375 - ቤላሩስ (Belarus) •  +371 - ላቲቪያ (Latvia) •  +381 - ሰርቢያ (Serbia) •  +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso) •  +370 - ቪልኒየስ (Vilnius) •  +255 - ታንዛኒያ (Tanzania)                                                                                                                            መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦ 1.ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ። 2.ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት። ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው።                                                                ይህንን የጥሰት ሙከራ ለመከላከል ይህንን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ለብዙ ጓደኞችዎ ያጋሩ (Forward ያድርጉ)!!! @Addis_News @Addis_News

    Фото
    Просмотры5,7 тыс.
    Пересылки—
    Реакции28
    Комментарии—

Новые посты

#64490Фото
Просмотры91−98%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#64489Фото

አትሞክሩን አንፈልጋችሁም፤ የሚመጣብን ካለ ግን አድዋ ይደገማል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ወርራ አታውቅም፤ ወደፊትም ይህ ፍላጎት የላትም፡፡ ትንሽም ይሁኑ ትልቅ ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ግን፤ ማንም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ፤ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ይህ በመልክዓምድራዊ ቅርበትና በርቀት የተገደበ ጉዳይ አይደለም፤ አትሞክሩን አንፈልጋችሁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሚመጣብን ካለ ግን አድዋ ይደገማል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በመከላከያ ስትራቴጂ አማካኝነት በሁሉም ምሶሶዎች ሸብረክ የማይል ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ መሆኑን በመግለጽ፤ መከላከያ ቴክኖሎጂን በሚገባ የሚጠቀም ተቋም መደረጉ በውጤቱ እየታየ ይገኛል ነው ያሉት፡፡ @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры1 770−54%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#64488Фото

የመንግሥትና የግል ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ:: በኢትዮጵያ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዴት መስተካከል እንዳለበት የሚያመላክት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው። በማብራሪያቸውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ያነሱት ዶክተር ዐቢይ፣ የአገሪቱ የዕዳ ጫና ሽግሽግ ተደርጎለት ወደ መካከለኛ ደረጃ መውረዱን ለዚህ በማሳያነት ጠቅሰዋል። የዋጋ ግሽበት በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል፦ 1. የመንግሥት ድጎማዎችን ማድረግ 2. የደሞዝ ጭማሪዎችን ተግባራዊ ማድረግ 3. ሌሎች የዜጎችን ጫና የሚያቃልሉ አማራጮችን መጠቀም የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥልና የሚያጋጥሙ ውስን የኑሮ ጫናዎችን ለመቅረፍ ተከታታይ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры2 550−34%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#64487Фото

📍መገናኛ ዲያስፖራ  ጫካ ፕሮጀክት ፊትለፊት      🟢 100% ለከፈለ 35% በነፃ ነው      🟢  40/60 አከፋፈል አመቻችተናል ➡️ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ ➡️ ባለ 2 መኝታ 90,99 ካሬ ➡️ ባለ 3 መኝታ 120 -145 ካሬ ዋጋ እና አከፋፈል ✅ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ ➖ 7.2 ሚልዮን ብር        ቅድመ ክፍያ 20% ➖ 1.4ሚልዮን    🗝100% ለሚከፍል ➖ 4.6ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 1 መኝታ 69ካሬ      ጠቅላላ ክፍያ ➖ 8.2 ሚሊዮን ብር       ቅድመ ክፍያ ➖ 1.6 ሚሊዮን ብር 🗝100 % ለሚከፍል ➖ 5.3 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 2 መኝታ 90ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ ➖ 10.8 ሚልዮን ብር        ቅድመ ክፍያ 20% ➖  2.1 ሚልዮን ብር    🗝100% ለሚከፍል ➖ 7 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 2 መኝታ 99 ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ ➖ 11.8 ሚልዮን        ቅድመ ክፍያ 20% ➖ 2.3 ሚልዮን   🗝100% ለሚከፍል ➖ 7.7 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 3 መኝታ 120 ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ ➖ 14.4 ሚሊዮን ብር        ቅድመ ክፍያ ➖ 2.8 ሚሊዮን ብር   🗝100% ለሚከፍል ➖ 10 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 3 መኝታ 145  ካሬ        ጠቅላላ ክፍያ ➖ 17.4 ሚሊዮን ብር       ቅድመ ክፍያ ➖ 3.4 ሚሊዮን ብር 🗝100% ለሚከፍል ➖ 12.1 ሚሊዮን ብር       ቀሪ ክፍያ ✅ ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ ✅ ከወለድ ነፃ አከፍፈል ✅ በግንባታ ሂደት የሚከፈል 📞WhatsApp call=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1 ✈️Telegram =@Temerr34    📞 09-82-15-16-64

Открыть в Telegram
Просмотры452−88%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#64486Фото

​1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ ! በጉባ መድረክ ይፋ የተደረገው 1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ሀገራዊ ዕቅድ ከንግግር ባለፈ በአዲስ አበባና በክልሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ወደ መገንባት ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ​የፖሊሲና የመሬት ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዜጎች ቤት ገዝተው እየሠሩ የሚከፍሉበት ከባንክ ጋር የተሳሰረ ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ከ15 ቀን እስከ አንድ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ቪላ ቤቶችን ማጠናቀቅ የሚችሉ የቱርክና የቻይና ዘመናዊ ፋብሪካዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሙከራ ሥራ መጀመራቸውን አብራርተዋል። ​በሙከራ ቦታዎች የታዩ የፍሳሽ መስመርና የግብአት አቅርቦት ፈተናዎችን በማረም ግንባታው በስፋት መቀጠሉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢኮኖሚው እያደገ ሲሄድ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ለመንገድ፣ ለባቡርና ለቤት ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ ማጠናቀቅ የግድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры2 490−36%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#64485Фото

«የተዘረፈውን የሕዝብ ሀብት በማስመለስ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል» – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት   የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ብልሹ አሠራር እና ሙስና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል።   የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ፣ ዜጎችን የሚያስለቅሱ እና ሥልጣናቸውን ለበደል የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል።   እነዚህ ጥቂት ሙሰኞች የሕዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አባላቱ፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዲጂታል ሥርዓት ላይ እንደ ሀገር እየተሠራ ቢሆንም ሙስና አሁንም ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክተዋል።   ለሀገር ልማት መዋል የሚገባው ሀብት በጥቂት ሙሰኞች ኪስ መግባቱ የትውልዱን ሞራል እየገደለ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ ችግሩን ማውገዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የዘረፉትን የሕዝብ ሀብት እንዲመልሱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።   @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры2 890−25%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
#64483Фото
Просмотры3 240−16%к среднему
Пересылки—
Реакции43
Комментарии—
#64482Текст

ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጊዜ እንዲገለጽ እና የፕሬስ ነጻነት ትኩረት እንዲያገኝ በምክር ቤቱ ጥያቄ ቀረበ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ ጥያቄ፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በየአሥር ዓመቱ መካሄድ የነበረበትና ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መቼ እንደሚደረግ እንዲገለጽ፣ እንዲሁም የፕሬስና የፖለቲካ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ። የምክር ቤት አባሉ በንግግራቸው፣ ሕገ-መንግሥቱ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ እንዲካሄድ ቢደነግግም ከ1997 ዓ.ም በኋላ በ2007 ዓ.ም መካሄድ የነበረበት ቆጠራ አለመካሄዱን አስታውሰዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ቀመር ለማውጣት፣ ፍትሐዊ የበጀት ድልድል ለማድረግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና የምርጫ ክልሎችን አከላለል ለመወሰን መነሻ የሚያደርገው ይህንኑ ቆጠራ መሆኑን የገለጹት ተናጋሪው፤ ቆጠራው አለመካሄዱ ፍትሐዊነትን እንደሚያጓድልና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን እንደሚያቀጭጭ አስገንዝበዋል። በመሆኑም ቆጠራው መቼ እንደሚካሄድ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ ተካቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በተያያዘም በቅርቡ የተካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ቢጠናቀቅም በርካታ ሕጸጾች እንደነበሩበት ተናጋሪው ጠቅሰዋል። የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ከፖለቲካና ከፕሬስ ነጻነት መስፋት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተው፣ ነጻው ፕሬስ እንደ አራተኛ መንግሥት የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና የመንግሥት ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ ረገድ ድርሻውን እንዲወጣ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ይሁን እንጂ የመንግሥት ወይም የፐብሊክ ሚዲያዎች መንግሥትን ከመቆጣጠርና ዲሞክራሲን ከመገንባት ይልቅ የመንግሥት አፈ ቀላጤ ሆነው መቀጠላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዳይጎለብትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጥረቱ እንዳይጠናከር እያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል። ስለሆነም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ የፖለቲካ ነጻነትና የፕሬስ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግር ተካቶ የመንግሥት የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ጠይቀዋል።   @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры3 520−9%к среднему
Пересылки—
Реакции10
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч963
3 ч3 520
  1. Через 1 час963
  2. Всего сейчас3 520
#64481Фото

ልዩ አማራጭ እና አዲስ ነገር በወለል 1 ቤት ብቻ ‼️ 🏙️60,000 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ውስጥ 🏠G+1 ቪላ ቤቶች 🏘️G+2 ታውን ሃውስ 🏢 G+4 አፓርትመንት ✅ በወለል 1 ቤት ብቻ 🛏️ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶች ✅ በ1 ዓመት የሚረከቡት እና የተጠናቀቁ ✅ በሙሉ ግንባታ (Fully finished) 🏘️ የመኖሪያ ግቢ ብቻ (Gated compound) 💰 በ 30% ቅድመ ክፍያ 🛏️ ባለ 2 መኝታ 103.6 ካሬ 0️⃣ ምድር ወለል (Ground floor) 💰 ክፍያ=4,497,897.60 🛏️ ባለ 3 መኝታ 125.8 ካሬ 1️⃣ አንደኛ ወለል (1st floor) 💰 ክፍያ = 5,849,700 2️⃣ ሁለተኛ ወለል ( 2nd floor) 💰 ክፍያ = 5,623,260 3️⃣ ሶስተኛ ወለል ( 3rd floor) 💰 ክፍያ = 5,340,210 4️⃣ አራተኛ ወለል ( 4th floor) 💰 ክፍያ = 5,135,659.20 📍በ ቦሌ ቡልቡላ ✅አስፈላጊ መሰረተ ልማት የተሟላለት ግቢ በዙሪያው 🍝ዓለም አቀፍ ሬስቶራንት እና ካፌዎች ፥ 🏫ትምህርት ቤቶች ፥ 🎡መዝናኛ ፓርክ ፥ ⚽የ ስፓርት ማዘውተሪያዎች ፥ 🛒ሱፐር ማርኬቶች እና የንግድ ማዕከሎች ✈️ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በ 5 ደቃቃ ርቀት ℹ️ ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ጉብኝት በስልክ ቁጥራችን 💬 በቀጥታ በ   📲 Whatsapp_https://wa.me/qr/TY4MQPKPEFXSI1 📲 Telegram ☎️ 0934244544

Открыть в Telegram
Просмотры3 310−14%к среднему
Пересылки—
Реакции7
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч1 100
4 ч3 310
  1. Через 1 час1 100
  2. Всего сейчас3 310
#64478Фото

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር አወቀ ሃምዛዬ፣ በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጹ። የምክር ቤት አባሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርትን በመጥቀስ እንዳብራሩት፣ የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፤ በመንግሥት ኃይሎች፣ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች፣ በተለያዩ ቡድኖች እንዲሁም በፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ አካል ማጉደልና ዘረፋዎች የሕዝቡን ሰላማዊ ኑሮ በእጅጉ በመጉዳት ህልውናውን አደጋ ላይ ጥለውታል። በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ አርሲ፣ በሞያሌ አካባቢ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶና አበሽጌ፣ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬና ቡርጂ ዞኖች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ፣ ከበባ፣ መንገድ መዝጋትና የዜጎች ሞት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ዶ/ር አወቀ ገልጸዋል። ዶ/ር አወቀ በንግግራቸው የኮሬ ሕዝብን ጉዳይ በልዩ ትኩረት በማንሳት፣ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ታሪክ ሰምቶትም ሆነ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ ላለፉት 11 ዓመታት በፅንፈኛ ታጣቂዎች እየተወረረ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለምክር ቤቱና ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢቀርብም ወረራው ከትላንት በስቲያም፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ በዚህ ሰዓት መቀጠሉን ጠቅሰው፣ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የክልሉ የፀጥታ አካላትም አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈሉና እየሞቱ መሆኑን አስረድተዋል። @Addis_News @Addis_News

Открыть в Telegram
Просмотры3 550−8%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч1 950
4 ч3 550
  1. Через 1 час1 950
  2. Через 6 часов3 550
  3. Всего сейчас3 550

Все посты

Связи