Кабинет
ETHIO-MEREJA®

ETHIO-MEREJA®

News & Media Channel® Addis ababa, Ethiopia🇪🇹 ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን። ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉 @ethio_merejabot

Юзернейм
@ethio_mereja
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики96 356
Просмотров на пост, 7 дн.7 962за 7 дней
ERR8,26 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
23 нояб. 2026 г.11 100
24 нояб. 2026 г.9 065
25 нояб. 2026 г.7 598
26 нояб. 2026 г.1 300

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    "አውሮፕላኖች በትዕዛዝ ቢከማቹም ትርፍ የሚባል ነገር የለም!" የዓለማችን ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ አሁንም ከኪሳራ መውጣት አልቻለም። የዓለም አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቁንጮ የሆነው የአሜሪካው የአውሮፕላን እና የጠፈር ምርምር ኩባንያ ቦይንግ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የገጠመውን የፋይናንስ ቀውስ ተሻግሮ ወደ ትርፋማነት መመለስ አለመቻሉን የፋይናንስ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ኩባንያው ለመጨረሻ ጊዜ ዓመታዊ ትርፍ ያስመዘገበው እ.ኤ.አ በ2018 ላይ ነበር። ከዚያ በኋላ በተከሰቱት የ737 MAX አውሮፕላኖች አደጋ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጥራት ቁጥጥር ችግሮች እና በሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ምክንያት ከ35 ቢሊዮን ዶላር በላይ አጠቃላይ ኪሳራ አስተናግዷል። በአቪዬሽን ዘርፍ አምራች ኩባንያዎች አብዛኛውን ክፍያ የሚያገኙት አውሮፕላኖችን ገጣጥመው ለደንበኞች ሲያስረክቡ ቢሆንም ቦይንግ በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና በምርት ገደብ ምክንያት ትዕዛዞችን በፍጥነት ማድረስ አልቻለም። ይህም ኩባንያው ከሚያገኘው ገቢ ይልቅ የሚያወጣው ወጪ እንዲበልጥ እና ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ጫና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። በተጨማሪም የኩባንያው የመከላከያ እና የጠፈር ምርምር ዘርፍ በቋሚ ዋጋ በገባቸው ኮንትራቶች በተለይም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አውሮፕላን እና የስታርላይነር የጠፈር መንኮራኩር ፕሮጀክቶች ላይ የግብዓት ዋጋ በመናሩ ተጨማሪ ኪሳራ እያስመዘገበ ይገኛል። ምንም እንኳን ቦይንግ ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ከ5,500 በላይ የንግድ አውሮፕላኖች ትዕዛዝ በእጁ ቢይዝም በአሁኑ ወቅት በየመልሶ ማቋቋም እና የማገገም ሂደት ላይ እንጂ በትርፋማነት ደረጃ ላይ እንደማይገኝ የኢኮኖሚ ተንታኞች ይገልጻሉ።       -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

    Видео
    Просмотры11,2 тыс.
    Пересылки—
    Реакции45
    Комментарии—
  2. 02

    የድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ በተወዳጅ ዜማዎቹ በርካታ የሙዚቃ አድማጮችን ልብ ያሸነፈው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በአዲስ አበባ በሚገኘው መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። ድምፃዊው በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል። "የኔ ደሃ"፣ "አሁን ገባኝ"፣ "ግርማ ሞገሴ ነሽ"፣ "ኪያዬ" እና "አትጨናነቅ" በተሰኙ ተወዳጅ ዜማዎቹ የሚታወቀው ሚኪያስ ቸርነት፣ "ሰላም አላት" እና "10 ከ10 ይገባሻል" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ጨምሮ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ለሙዚቃ አድማጮች አበርክቷል። ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆን፣ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን ትቶ ነው ያረፈው። በ45 ዓመቱ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊው፣ በሙዚቃ ሥራዎቹና በተወዳጅ ዜማዎቹ በአድማጮቹ ልብ ውስጥ ሲታወስ ይኖራል። ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪዎች መጽናናትን እመኛለሁ።       -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

    Фото
    Просмотры11 тыс.
    Пересылки—
    Реакции23
    Комментарии—
  3. 03

    እስራኤል ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በልብ ሕክምና እንደረዳች ተገለጸ እስራኤል በ30 ዓመታት የሕክምና ትብብር ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገናና የካቴተር ሕክምና እንዲያገኙ መደገፏ ተገለጸ። በእስራኤሉ Save a Child’s Heart እና በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል መካከል የተጀመረውን የ30 ዓመታት ትብብር በማስመልከት የእስራኤል የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ የሕክምና ዘመቻ እያካሄደ ነው። የሕክምና ልዑካኑ የሕፃናት ልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሞችን፣ የልብ ሕክምና ስፔሻሊስቶችንና ነርሶችን ያካተተ ሲሆን፣ ዘመቻው በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲና በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሩይ አሊ እንደገለጹት፣ የሕክምና ቡድኑ በቆይታው የልብ ሕመም ምርመራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ አስቸኳይ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው 30 ሕፃናት ከኢትዮጵያውያን ሐኪሞችና ነርሶች ጋር በመተባበር ሕክምና ይሰጣል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶክተር አቭርሃም ንጉሴ በበኩላቸው፣ Save a Child’s Heart በኢትዮጵያ የበርካታ ሕፃናትን ሕይወት የማዳን ሥራ ማከናወኑን ገልጸዋል። በድርጅቱ እርዳታ ሕይወታቸው የተረፉ አንዳንድ ሕፃናት አድገው በልብ ሕክምና ሙያ በመሰማራት በማዕከሉ ውስጥ እያገለገሉ መሆኑንም አስረድተዋል። አምባሳደሩ አክለውም፣ ኢትዮጵያ በልብ ሕክምና ዘርፍ በራሷ አቅም እንድትቆም የኢትዮጵያውያን ዶክተሮችና ነርሶች ወደ እስራኤል በመሄድ የሙያ ሥልጠና እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ሥልጠና የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በራሳቸው ከ20 ያላነሱ ሕፃናትን በቀዶ ጥገና ማዳናቸውንም አንስተዋል።      T.me/ethio_mereja

    Фото
    Просмотры9,1 тыс.
    Пересылки—
    Реакции32
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры9,03 тыс.
    Пересылки—
    Реакции6
    Комментарии—

Новые посты

#33829Фото

«ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ሀገር ወራ አታውቅም፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ በክብር መመለስ የሚችል ማንም የለም» – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ሀገር ወራ እንደማታውቅና ወደፊትም ወረራ የማካሄድ ፍላጎት እንደሌላት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ዶ/ር ዐቢይ በንግግራቸው፣ ሌሎች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ቢኖር ትንሽም ይሁን ትልቅ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወሮ በክብር መመለስ የሚችል ማንም አካል አለመኖሩን አስገንዝበዋል። ይህም በጂኦግራፊ የታጠረ ጉዳይ ሳይሆን «ማንም» መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። አክለውም «አድዋ ይደገማል አትሞክሩን፤ አንፈልጋችሁም ከተመጣ ወደዚህ፤ የሚመጣ ካለ ግን ያው የተለመደው የአባቶቻችን ታሪክ ይደገማል» ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስጠንቅቀዋል።        -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

Открыть в Telegram
Просмотры1 080−86%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#33828Фото

#ነጋዴዎች   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜያቸውን በግብር ስወራ እንደሚያሳልፉ ተናገሩ።   ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ የገቢ ግብር በዝቷል ሲሉ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።   በሀገሪቱ ግብር የሚከፍሉት ጥቂት ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ ይህ አካሄድ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል። የነጋዴዎች ቁጥርም ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።   በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ዋነኛ ግብር ከፋዮች የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።   የንግዱ ማኅበረሰብ ግብር መክፈልን የሥልጣኔ መገለጫ አድርጎ መውሰድ እንዳለበት ያሳሰቡት ዶ/ር ዐቢይ፣ ማንኛውም ዜጋ ሥራ በሠራ ቁጥር ግብር መክፈልን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባው አመልክተዋል።   የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት ለማሟላትም የገቢ ግብር አሰባሰቡ አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ መስፋትና መጠናከር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።          -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

Открыть в Telegram
Просмотры1 580−80%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#33826Фото

#Arsi "በአካባቢው ያለውን የመንግሥትዎን መዋቅር ቢፈትሹ ! " - የምክር ቤት አባል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴሀን) አባል የሆኑት የምክር ቤት አባል መ/ር ገብረመስቀል አደመ፣ በሀገሪቱ ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል። የምክር ቤት አባሉ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በአዋሳኝ ክልሎች የፀጥታ ችግሮች መቀጠላቸውን ገልጸው፣ በተለይም በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ አካባቢ አሰቃቂና ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የንጹሐን ዜጎች እልቂት፣ ሞትና መፈናቀል መፈጸሙን አስታውሰዋል። በአርሲ አካባቢ በተደጋጋሚ የዜጎች ሞትና መፈናቀል እንደሚፈጸምና አሁንም ድረስ የድረሱልኝ ጩኸት እየተሰማ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከመንግሥት መግለጫ ባለፈ ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ "የውጭ አልጋ የውስጥ ቀጋ " አይጠፉምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥታቸውን መዋቅር እንዲፈትሹ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ምክንያታቸውን ሲያስረዱ፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የመንግሥት ወይም የሕዝብ ቅቡልነት እና የዜጎች መተማመን ሲፈጠር ብቻ መሆኑን አመልክተዋል። በመጨረሻም መንግሥት ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ፣ አሁንም ድረስ የፀጥታ ስጋት ስላለባቸው አስፈላጊውን የሕግ ከለላ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ እንዲሁም በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ አንጻር ምን የታሰበ ነገር እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል።        -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

Открыть в Telegram
Просмотры3 260−59%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—
#33825Фото
Просмотры2 940−63%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#33824Фото
Просмотры3 860−52%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч1 300
4 ч3 860
  1. Через 1 час1 300
  2. Всего сейчас3 860
#33823Фото
Просмотры5 420−32%к среднему
Пересылки—
Реакции39
Комментарии—
#33822Фото
Просмотры8 130+2%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#33821Фото
Просмотры8 220+3%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#33820Фото
Просмотры7 860−1%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#33818Фото

የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ - ለሕንጻ ገንቢዎች በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሕንጻዎች በፍጥነትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ከቀጣዩ ዓመት በፊት ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 የዓለም አቀፍ መድረክ ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ በከተማዋ የሚገኙ የሪል እስቴት ፣ የአፓርታማ ፣ የሆቴልና የገስት ሀውስ አልሚዎች እና የሕንፃ ባለሀብቶች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መገኘታቸው ታውቋል። በከተማዋ የሚገኙ ነባር ሕንፃዎችም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው ለመድረኩ ዝግጁ እንዲደረጉ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል። ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧ ለኢኮኖሚ ዕድገት ፣ ለቱሪዝም መስፋፋትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ዕድል ይዞ የሚመጣ ነው። ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የመሠረተ ልማት አቅራቢና የፋይናንስ ተቋማት በቅንጅት በመስራት ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።       -ETHIO-MEREJA-      T.me/ethio_mereja

Открыть в Telegram
Просмотры8 360+5%к среднему
Пересылки—
Реакции28
Комментарии—

Все посты

Связи