«ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ሀገር ወራ አታውቅም፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ በክብር መመለስ የሚችል ማንም የለም» – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ሀገር ወራ እንደማታውቅና ወደፊትም ወረራ የማካሄድ ፍላጎት እንደሌላት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ዶ/ር ዐቢይ በንግግራቸው፣ ሌሎች ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ቢኖር ትንሽም ይሁን ትልቅ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወሮ በክብር መመለስ የሚችል ማንም አካል አለመኖሩን አስገንዝበዋል። ይህም በጂኦግራፊ የታጠረ ጉዳይ ሳይሆን «ማንም» መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። አክለውም «አድዋ ይደገማል አትሞክሩን፤ አንፈልጋችሁም ከተመጣ ወደዚህ፤ የሚመጣ ካለ ግን ያው የተለመደው የአባቶቻችን ታሪክ ይደገማል» ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስጠንቅቀዋል። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в TelegramПосты канала ETHIO-MEREJA®
#ነጋዴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ ነጋዴዎች ብዙውን ጊዜያቸውን በግብር ስወራ እንደሚያሳልፉ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ፣ የገቢ ግብር በዝቷል ሲሉ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። በሀገሪቱ ግብር የሚከፍሉት ጥቂት ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ያነሱት ዶ/ር ዐቢይ፣ ይህ አካሄድ ትክክል አለመሆኑን አስገንዝበዋል። የነጋዴዎች ቁጥርም ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ዋነኛ ግብር ከፋዮች የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል። የንግዱ ማኅበረሰብ ግብር መክፈልን የሥልጣኔ መገለጫ አድርጎ መውሰድ እንዳለበት ያሳሰቡት ዶ/ር ዐቢይ፣ ማንኛውም ዜጋ ሥራ በሠራ ቁጥር ግብር መክፈልን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባው አመልክተዋል። የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት ለማሟላትም የገቢ ግብር አሰባሰቡ አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ መስፋትና መጠናከር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegram#Arsi "በአካባቢው ያለውን የመንግሥትዎን መዋቅር ቢፈትሹ ! " - የምክር ቤት አባል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴሀን) አባል የሆኑት የምክር ቤት አባል መ/ር ገብረመስቀል አደመ፣ በሀገሪቱ ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል። የምክር ቤት አባሉ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በአዋሳኝ ክልሎች የፀጥታ ችግሮች መቀጠላቸውን ገልጸው፣ በተለይም በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ አካባቢ አሰቃቂና ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ የንጹሐን ዜጎች እልቂት፣ ሞትና መፈናቀል መፈጸሙን አስታውሰዋል። በአርሲ አካባቢ በተደጋጋሚ የዜጎች ሞትና መፈናቀል እንደሚፈጸምና አሁንም ድረስ የድረሱልኝ ጩኸት እየተሰማ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከመንግሥት መግለጫ ባለፈ ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ "የውጭ አልጋ የውስጥ ቀጋ " አይጠፉምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥታቸውን መዋቅር እንዲፈትሹ ጥሪ አቅርበዋል። ለዚህም ምክንያታቸውን ሲያስረዱ፣ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የመንግሥት ወይም የሕዝብ ቅቡልነት እና የዜጎች መተማመን ሲፈጠር ብቻ መሆኑን አመልክተዋል። በመጨረሻም መንግሥት ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ፣ አሁንም ድረስ የፀጥታ ስጋት ስላለባቸው አስፈላጊውን የሕግ ከለላ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ እንዲሁም በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተገቢው ማጣራት ተደርጎ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ አንጻር ምን የታሰበ ነገር እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegram👉ርካሽ ነገር ምንጊዜም ዉድ ነዉ የሚለዉ ዲማ ሆፕ ሪል እስቴት በጥራት በተመረጡ ቦታዎች በመገንባት አብረን እንስራ ይሎታል። 👉የአደይ ሁለት ሳይታችን 140ሺ ሲሸጥ የነበረዉ እስከ ህዳር 21 ብቻ በሚቆየዉ ቅናሹ በካሬ 105ሺ እየሸጠ ይገኛል ይፍጠኑ። 👉ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ለማየት፦ በ09-68-48-03-84 ይደዉሉ።
Открыть в Telegramወርቅ ነሽ Skin Care በተፈጥሯዊ ግብዓቶች የሚዘጋጅ ተፈጥሮአዊ የቆዳ መንከባከብያ ሲሆን ለማድያት ለብጉር ለብጉር ጠባሳ በፀሃይ የተጎዳን ቆዳ የሚያክም ተፈጥሮአዊ ማስክ ነው ከ እኛ ጋር በ ሽይጭ መስራት ምትፍልጉ based on commission also any cosmetic shop you can contact too you can contact us 📲 0936650830 telegram @mesob9/@Nordi_ay
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 1 300 |
| 4 ч | 3 860 |
- Через 1 час1 300
- Всего сейчас3 860
"በእርሶ አመራር ሙሉ እምነት አለኝ!" የኤር ኢንዲያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም ከፍተኛ አመራሩን የማዋቀር ሙሉ ስልጣን ተሰጣቸው። የኤር ኢንዲያ (Air India) ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም የአየር መንገዱን የፋይናንስ አቋም ለማሻሻል ሲሉ ከፍተኛ የአመራር መዋቅር ለውጥ እንዲያደርጉ ሙሉ ስልጣን መሰጠቱን የኢኮኖሚክ ታይምስ መረጃ አመለከተ። አየር መንገዱ ስራዎቹን ለማስፋፋትና መልሶ ለማዋቀር ጥረት እያደረገ በሚገኝበት በዚህ ሰአት ከፍተኛ የተጣራ ኪሳራ ማስመዝገቡ ተገልጿል። ይህንን አየር መንገዱን ወደ ትርፋማነትና ጠንካራ አቋም ለመመለስ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ለውጦችን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ነው የተባለው። በዚህም መሰረት ተወልደ ገ/ማርያም የተሻለ የስራ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በአሰራር ቅልጥፍና በበረራ መስመሮች ስትራቴጂ እና በወጪ ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርገው ለማዋቀር ማቀዳቸው ተመልክቷል። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegramጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በነገው ዕለት ለምክር ቤቱ አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት በነገው ዕለት ያካሂዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ምክር ቤቱ ነገ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው ላይ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegram🌺100 ሪሴለሮችን እንፈልጋለን። ከቤትዎ ሆነው በኦንላይን ከኛ ጋር ይስሩ!!! እቃዎችን በተለያዩ የኦንላይን አማራጮች ከኛ በኦንላይን በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ያግኙ፣ Contact 👉 @Addisekachat እቃዎቹን በልዩ ቅናሽ እናቀርባለን። ዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን። JOIN አድርገው አብረውን መስራት ይጀምሩ!
Открыть в Telegramድህረ ገፃችን በመጓብኘት ያሻዎትን ላፕቶፖችን ከነዎጋቸው እና ከነመግለጫቸው በመመልከት አሁኑኑ ዘመናዊነትንና ቴክኖሎጂን ይሸምቱ። 🌐 https://www.ethio-spark.com 💻ETHIOSPARK COMPUTER SHOP ፈጣን እና ዘመናዊ የሆኑ የዓለምችንን ምርጥ ምርጥ 👉 አዳዲስ ላፕቶፖችን 👉 ጌሚንግ ላፕቶፖችን 👉 ቢዝነስ ላፕቶፖችን 👉 ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን እና 👉 የተለየዩ የላፕቶፕ አክሰሰሪዎችን ከ አንድ አመት ዋስትና እና እንዲሁም ከልዩ መስተንግዶ ጋር ይዘን እንጠብቆታለን። ይደውሉ ☎️ +251974967884 ☎️ +251994881745 የፁሁፍ መልዕክት ✉️ @Dm4ethio ✍️ https://t.me/EthioSpark16
Открыть в Telegramየከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ - ለሕንጻ ገንቢዎች በአዲስ አበባ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሕንጻዎች በፍጥነትና በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ከቀጣዩ ዓመት በፊት ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 የዓለም አቀፍ መድረክ ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ በከተማዋ የሚገኙ የሪል እስቴት ፣ የአፓርታማ ፣ የሆቴልና የገስት ሀውስ አልሚዎች እና የሕንፃ ባለሀብቶች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት መገኘታቸው ታውቋል። በከተማዋ የሚገኙ ነባር ሕንፃዎችም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ታድሰው ለመድረኩ ዝግጁ እንዲደረጉ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል። ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን እንድታዘጋጅ መመረጧ ለኢኮኖሚ ዕድገት ፣ ለቱሪዝም መስፋፋትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ዕድል ይዞ የሚመጣ ነው። ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የመሠረተ ልማት አቅራቢና የፋይናንስ ተቋማት በቅንጅት በመስራት ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegramእስራኤል ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በልብ ሕክምና እንደረዳች ተገለጸ እስራኤል በ30 ዓመታት የሕክምና ትብብር ከ1,000 በላይ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገናና የካቴተር ሕክምና እንዲያገኙ መደገፏ ተገለጸ። በእስራኤሉ Save a Child’s Heart እና በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል መካከል የተጀመረውን የ30 ዓመታት ትብብር በማስመልከት የእስራኤል የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን ለአንድ ሳምንት በአዲስ አበባ የሕክምና ዘመቻ እያካሄደ ነው። የሕክምና ልዑካኑ የሕፃናት ልብ ቀዶ ጥገና ሐኪሞችን፣ የልብ ሕክምና ስፔሻሊስቶችንና ነርሶችን ያካተተ ሲሆን፣ ዘመቻው በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲና በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ህሩይ አሊ እንደገለጹት፣ የሕክምና ቡድኑ በቆይታው የልብ ሕመም ምርመራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ አስቸኳይ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው 30 ሕፃናት ከኢትዮጵያውያን ሐኪሞችና ነርሶች ጋር በመተባበር ሕክምና ይሰጣል። በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶክተር አቭርሃም ንጉሴ በበኩላቸው፣ Save a Child’s Heart በኢትዮጵያ የበርካታ ሕፃናትን ሕይወት የማዳን ሥራ ማከናወኑን ገልጸዋል። በድርጅቱ እርዳታ ሕይወታቸው የተረፉ አንዳንድ ሕፃናት አድገው በልብ ሕክምና ሙያ በመሰማራት በማዕከሉ ውስጥ እያገለገሉ መሆኑንም አስረድተዋል። አምባሳደሩ አክለውም፣ ኢትዮጵያ በልብ ሕክምና ዘርፍ በራሷ አቅም እንድትቆም የኢትዮጵያውያን ዶክተሮችና ነርሶች ወደ እስራኤል በመሄድ የሙያ ሥልጠና እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ሥልጠና የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በራሳቸው ከ20 ያላነሱ ሕፃናትን በቀዶ ጥገና ማዳናቸውንም አንስተዋል። T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegram🏢 ቴምር ሪል እስቴት በአዲስ አበባ ተመራጭ አካባቢዎች የተለያዩ የአፓርታማ አማራጮችን 🎯ቡልጋሪያ(አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት) 👉Studio 40ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 920,000ብር ሙሉ ክፍያ 4.6ሚሊዮን ብር 👉ባለ 1 መኝታ 62ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 1.3ሚሊዮን ብር ሙሉ ክፍያ 6.8ሚሊዮን ብር 👉ባለ 2 መኝታ 110ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ 12ሚሊዮን ብር 👉ባለ 3 መኝታ 135ካሬ 20% ቅድመ ክፍያ 2.9ሚሊዮን ብር ሙሉ ክፍያ 14.8ሚሊዮን 🎯በተጨማሪም በ Cmc,በመገናኛ እና በአዋሬ ሳይት ላይ ከ studio እስከ ባለ 3 መኝታ ለሽያጭ አውጥተናል 🎯3 አይነት የክፍያ አማራጮች ስላላቸው ለእርሶ ምቹ የሆነውን መምረጥ ይችላሉ ✅ 20/80 አከፋፈል — 20% ቅድመ ክፍያ ቀሪውን በ 16ዙር የሚከፈል ✅ 40/60 አከፋፈል — 40% ቅድመ ክፍያ ሲከፍሉ የ10% ቅናሽ ያግኙ፤ ቀሪውን ቤቱን ሲረከቡ ይክፈሉ። ✅ 70/30 አከፋፈል — 100% ለሚከፍል 30% ቅናሽ አለን +251939 770 177 +251996 856 273 WhatsApp: https://wa.me/251939770177
Открыть в Telegram"አውሮፕላኖች በትዕዛዝ ቢከማቹም ትርፍ የሚባል ነገር የለም!" የዓለማችን ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ አሁንም ከኪሳራ መውጣት አልቻለም። የዓለም አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ቁንጮ የሆነው የአሜሪካው የአውሮፕላን እና የጠፈር ምርምር ኩባንያ ቦይንግ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የገጠመውን የፋይናንስ ቀውስ ተሻግሮ ወደ ትርፋማነት መመለስ አለመቻሉን የፋይናንስ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ኩባንያው ለመጨረሻ ጊዜ ዓመታዊ ትርፍ ያስመዘገበው እ.ኤ.አ በ2018 ላይ ነበር። ከዚያ በኋላ በተከሰቱት የ737 MAX አውሮፕላኖች አደጋ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጥራት ቁጥጥር ችግሮች እና በሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ምክንያት ከ35 ቢሊዮን ዶላር በላይ አጠቃላይ ኪሳራ አስተናግዷል። በአቪዬሽን ዘርፍ አምራች ኩባንያዎች አብዛኛውን ክፍያ የሚያገኙት አውሮፕላኖችን ገጣጥመው ለደንበኞች ሲያስረክቡ ቢሆንም ቦይንግ በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና በምርት ገደብ ምክንያት ትዕዛዞችን በፍጥነት ማድረስ አልቻለም። ይህም ኩባንያው ከሚያገኘው ገቢ ይልቅ የሚያወጣው ወጪ እንዲበልጥ እና ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ጫና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። በተጨማሪም የኩባንያው የመከላከያ እና የጠፈር ምርምር ዘርፍ በቋሚ ዋጋ በገባቸው ኮንትራቶች በተለይም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አውሮፕላን እና የስታርላይነር የጠፈር መንኮራኩር ፕሮጀክቶች ላይ የግብዓት ዋጋ በመናሩ ተጨማሪ ኪሳራ እያስመዘገበ ይገኛል። ምንም እንኳን ቦይንግ ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ከ5,500 በላይ የንግድ አውሮፕላኖች ትዕዛዝ በእጁ ቢይዝም በአሁኑ ወቅት በየመልሶ ማቋቋም እና የማገገም ሂደት ላይ እንጂ በትርፋማነት ደረጃ ላይ እንደማይገኝ የኢኮኖሚ ተንታኞች ይገልጻሉ። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegramየድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ በተወዳጅ ዜማዎቹ በርካታ የሙዚቃ አድማጮችን ልብ ያሸነፈው ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በአዲስ አበባ በሚገኘው መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። ድምፃዊው በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል። "የኔ ደሃ"፣ "አሁን ገባኝ"፣ "ግርማ ሞገሴ ነሽ"፣ "ኪያዬ" እና "አትጨናነቅ" በተሰኙ ተወዳጅ ዜማዎቹ የሚታወቀው ሚኪያስ ቸርነት፣ "ሰላም አላት" እና "10 ከ10 ይገባሻል" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ጨምሮ በርካታ ነጠላ ዜማዎችን ለሙዚቃ አድማጮች አበርክቷል። ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆን፣ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን ትቶ ነው ያረፈው። በ45 ዓመቱ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ድምፃዊው፣ በሙዚቃ ሥራዎቹና በተወዳጅ ዜማዎቹ በአድማጮቹ ልብ ውስጥ ሲታወስ ይኖራል። ለቤተሰቡ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የሙዚቃ አፍቃሪዎች መጽናናትን እመኛለሁ። -ETHIO-MEREJA- T.me/ethio_mereja
Открыть в Telegram