
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
FDRE, Ministry of Labor and Skills
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 28 окт. 2026 г. | 23 400 |
| 29 окт. 2026 г. | 22 700 |
| 30 окт. 2026 г. | 23 000 |
| 2 нояб. 2026 г. | 16 500 |
| 3 нояб. 2026 г. | 14 267 |
| 4 нояб. 2026 г. | 13 700 |
| 5 нояб. 2026 г. | 15 267 |
| 6 нояб. 2026 г. | 18 500 |
| 26 нояб. 2026 г. | 1 151 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры23,4 тыс.Пересылки—Реакции77Комментарии—
- 02Просмотры23 тыс.Пересылки—Реакции63Комментарии—
- 03Просмотры22,7 тыс.Пересылки—Реакции47Комментарии—
- 04Просмотры18,7 тыс.Пересылки—Реакции180Комментарии—
Новые посты
የኢትዮጵያ እዳ ከከፍተኛ ተጋላጭነት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱ የሪፎርሙ ትልቁ ስኬት ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Открыть в Telegram"የሥራ ማዕከላት ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው ለታለመላቸው ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።" ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን ዘመናዊ የሥራ ማዕከላት የግንባታ ሂደትና ያሉበትን የአፈጻጸም ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል። በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለጸው፤ የተጀመሩት የሥራ ማዕከላት ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለታለመላቸው የልማትና የወጣቶች አገልግሎት ዓላማ መዋል እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል። የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ እንደገለጹት እየተገነቡ ያሉ የሥራ ማዕከላት ለወጣቶችና ለሥራ ፈላጊዎች በአንድ ማዕከል (One-Stop Service) ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግንባታው ጥራትና ደረጃ ሳይጓደል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ መዋል ይገባቸዋል። ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸዉ የግንባታውን ሥራ ጥራትና ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ሙሉ አቅማችዉን አቀናጅተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል። የሥራ ማዕከላት የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ ፣ የሥራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጓቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላል ሲል የዘገበው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።
Открыть в Telegramሥልጠናን ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሰራ ነው፡፡ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱን ከሥራ ገበያውና ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትር ዴኤታው ይህን የገለጹት የSTEP IV – Horti-Skills የሆርቲካልቸር ክህሎት ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያና የትግበራ ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው። የክህሎት ልማት ስኬት የሚለካው በሚሰለጥኑ ዜጎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ሠልጣኞች በሥራ ገበያው በሚኖራቸው ተሳትፎ፣ በሚያገኙት የሥራ ዕድል፣ በሚፈጥሩት የራስ ሥራና ለኢኮኖሚው በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መሆኑን አስረድተዋል። ፕሮጀክቱ በሥልጠና ተቋማትና በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በማጠናከር ላይ ያተኩራል። ሆርቲካልቸር የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማጠናከርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም ያለው ዘርፍ ነው። ይህንን አቅም ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኒካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ዲጂታልና የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች የተላበሰ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ ነው። ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ በክህሎት ፍላጎት መለየትና በሙያ ደረጃዎች ዝግጅት ላይ በማሳተፍ፣ ተግባራዊ ሥልጠናንና የሥልጠና ጥራትን በማሻሻል፣ የተቋማትን ባለቤትነትና የውጤቶችን ዘላቂነት በማጠናከር ላይ ያተኩራል። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ የሥራ ቅጥርና የሥራ ፈጠራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል። ፕሮጀክቱ በጀርመንና በኔዘርላንድስ መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ፣ በGIZ ትግበራና ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የሚከናወን ነው፡፡ ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramበ22 ቀናት ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ22 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ ዕቅድ አፈጻጸምን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ጋር ገምግሟል። በግምገማው በንቅናቄው ወቅት 25,944 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸው፣ ከ406.6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱና 746 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸው ተገልጿል። በተጨማሪም 29,409 ሥራ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ56 ሺህ በላይ ዜጎች በለስላሳና ቴክኒክ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሳትፈዋል። የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮው የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣ ከመጀመሪያው ዙር ንቅናቄ የተገኙ ልምዶችንና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተቀናጀና ውጤትን ያማከለ አፈጻጸም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአንድ ዕቅድና የሪፖርት ሥርዓት በመመራት፣ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩም አቅጣጫ ሰጥተዋል። ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ማሳደግና አስተዳደሩን ማጠናከር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነው የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትና አስተዳደርን ማሻሻል የኢንተርፕራይዞችን ዘላቂ ዕድገት ከማረጋገጥ ባለፈ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ለዚህም የመሥሪያ ቦታዎችን በበቂ መጠን ከማቅረብ ባሻገር በፍትሐዊነትና በግልጽ የአስተዳደር ሥርዓት መምራት ይጠይቃል። በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ ውስጥ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንደ ወሳኝ ግብዓት ተቀምጧል። በዚህ መሠረት በ2019 በጀት ዓመት 11,487 ሼዶችን በመገንባት፣ ሼድ ለሚፈልጉና ለማይፈልጉ የሥራ መስኮች 126,300 ሄክታር የለማ መሬት በማዘጋጀት 49,500 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል። በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ መላኩ ወልደዮሐንስ እንዳብራሩት፣ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች የሥራ መጀመሪያ መሠረት ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ዕድገታቸውና ለሽግግር ሂደታቸው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሼድ እጥረት እንዲባባስና አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ወደ ሥራ እንዳይገቡ እንቅፋት እንደሚሆንም አመልክተዋል። በመሆኑም የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማስፋፋትና አስተዳደሩን ለማሻሻል በተለይ የግሉን ዘርፍ በሼድ ግንባታና አቅርቦት ማሳተፍ፣ ክፍት የሆኑ የመንግሥትና የወል ቦታዎችን ለመሥሪያ ቦታነት ማዋል እንዲሁም የሼድ አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው። በተለይም የሼድ ማኔጅመንት ሲስተምን በመጠቀም ያሉትን ሼዶች በሙሉ ወደ ሲስተሙ ማስገባት፣ የመሥሪያ ቦታ ምደባን በግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከናወንና ዜጎች በእኩል ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል። ከአሠራር ሥርዓት ውጪ የተያዙ ሼዶችን ማስመለስም የሼድ አቅርቦትን ለማሳደግና የተሻለ የቦታ አጠቃቀም ለመፍጠር አስፈላጊ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢንተርፕራይዞች የሽግግር ጊዜ በአግባቡ መምራት ይገባል። የሽግግር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገሩና የለቀቁት ሼድ ለሌሎች አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገር በተገቢው ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል። ይህም ውስን የመሥሪያ ቦታዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀምና ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል። በአጠቃላይ የመሥሪያ ቦታ ጉዳይ የሼድ ግንባታና ምደባ ብቻ ሳይሆን የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ጉዞ የሚወስን ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው። ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት የሼድ አስተዳደር ሥርዓቱን በተግባር በማዋል፣ የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎችን በቁርጠኝነት በመፈጸምና የመሥሪያ ቦታዎችን በፍትሐዊነት በማስተዳደር ለኢንተርፕራይዞች ዘላቂ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ በማዋል የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል። ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramበክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገመገመ፡፡ በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆች የሚሰጡት የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ከተቋሙ ጋር በቅንጅት የሚተገበር በመሆኑ በእያንዳንዱ አፈጻጸም ላይ ተናቦና ተባብሮ መስራት እንደሚጠበቅ አብራርተዋል። በዚህም ረገድ የተቋማቱን እቅድና አፈጻጸም በጋራ መገምገም እና እንደአስፈላጊነቱ ተደጋግፎ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። አክለውም የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁና ለሌሎች ተቋማት ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ እቅዶችን መከለስና ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር አብሮ መለወጥ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አመላክተዋል። የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተመስገን ሀይሉ የኮሌጁን የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፤ እንደዝግጅት ምዕራፍ በመደበኛ እና በማታው እንዲሁም በተለያየ ደረጃ በአጫጭር ስልጠናዎች ሰልጣኞች እየሰለጠኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በሩብ ዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት የነበረው የተመዛኞችን ውጤታማነት የማሻሻል ስራም በሚጠበቀው ልክ ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል። በተጨማሪም ኮሌጁ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን ማስተዋወቁን፣ ሰልጣኞች ወደ ተቋሙ እንዲመጡ በተለያየ ደረጃ የንቅናቄ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከስልጠና ባሻገር ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመድረስና በማህበራዊ እና ሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ላይ በመሳተፍ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ዲኑ አክለውም ተቋሙ የውስጥ አሰራሩን ከማዘመንና ለሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የምርትና አገልግሎት አቅሙን በማሻሻል በሩብ ዓመቱ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የውስጥ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አብራርተዋል። በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ኮሌጁ እንደተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣበት ያለው መንገድ ለሌሎች አርአያ እንደሚሆንና በማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። ከምንም በላይ ተቋሙ የተቀናጀ አመራር በመስጠት ብቁ የሰው ሀይል ከማፍራት ባሻገር የውስጥ ገቢውን በአስደናቂ ሁኔታ ማሳደግ መቻሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። መረጃው -የቤ/ጉ/ክ/መ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡ ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramየክህሎት ሥነ-ምህዳርን ማዘመን ለዘላቂ ሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚሁ መድረክ ላይ ከፍተኛ የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ተሳትፈዋል። በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በተነሳሽነት፣ በቁርጠኝነትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡ የመፍጠን፣ የመፍጠር እንዲሁም የመስፈንጠር ስልቶችን መከተልና ለጋራ ግብ የየዘርፎቹ መስተጋብር መቀናጀትና መጠናከር እንዳለበትም በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፤ ሀገራዊ እና ክልላዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ጥራቱን የጠበቀ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ እና አምራች የሆነ የሰለጠነ የሰው ሃይል ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። አቶ ሙስጠፋ አያይዘውም ከድህነት እና ከሥራ አጥነት ለመላቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀና አዲስ አስተሳሰብን የተከተለ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ይህ የንቅናቄ መድረክ የክልሉን የሥራ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥነ-ምህዳር በማዘመን ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን ከመድረኩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ቀርበው የዳበረ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል። መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡ ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramበሥራና ተግባር ትምህርት ብቁና ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የሥራና ተግባር ትምህርት አተገባበር የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለፁት፤ በክልሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውን የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ ኢንሼቲቮችን በመንደፍ ወደ ተግባር ተገብቷል። ዘርፉ እንደ ሀገር በሥራ እድል ፈጠራ ረገድ የተቀመጠለትን ግብ ያሳካ ዘንድ ትምህርት ቤቶች ላይ ክህሎትን ከማስረጽ ባለፈ በሙያ የተደገፈ ትምህርትን መስጠት ይገባል ብለዋል። በዚሁ መሰረት በክልሉ በአንደኛ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ግንዛቤውን በማስረጽ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቂ የሆነ የሥራና ተግባር ትምህርት በማቅረብ ብቁና ሥራ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ባለፉት ሁለት አመታት ከ24ሺ በላይ ተማሪዎች የሥራና ተግባር ትምህርት ወስደው መመረቃቸውንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። ይህ ተግባር ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው በደረጃ ሁለት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ያሉት አቶ አንተነህ በቀጣይም ይህን በማጠናከር ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ትምህርት ቤቶች ከቴክኒክና ሙያ፣ ከጤናና ከግብርና መዋቅሮች ጋር ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል። በሌላ በኩልም አቶ አንተነህ እንደገለጹት የተማሪዎችን መጠነ ማለፍ ለማሻሻል «ኢጁኬሽናል ዴቨሎፕመንት ትረስት» ከሚባል ሀገራዊ ኢንሼቲቭ ጋር በመቀናጀት ወደ ዩኒቨርስቲ፣ ወደ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ወደ ሌሎች የሥራ መስኮች የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ኢንሼቲቩ ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በማድረግ፣ ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ የማጠቃሻ መጽሃፍት ድጋፍ በማድረግና የአይሲቲ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት በኩል ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነው ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
Открыть в Telegramየሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ትብብር በሥስት ዙሮች በተለያዩ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው የፋውንዴሽን ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉን ለማሻሻልና ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውን ከማሻሻል ጀምሮ አዲስ ስትራቴጂ ተቀርጾ በእነሱም ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማወያየት ስራዎች መሰራታቸውን አውስተዋል፡፡ የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶችን በመለየት በተሰጡ ስልጠናዎችም ለውጥ ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ አሁን ላይ የተገኘው ክፍተት የልል ክህሎት (soft skills) በመሆኑ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድ ዜጋ ቴክኒካል ክህሎት ስላለው ብቻ ተወዳዳሪ መሆን ስለማይችል ዜጎች ለሁሉም ነገር ዝግጁ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሰልጣኖች ይህንን የልል ክህሎት ስልጠና በትምህርታቸው ተካቶ እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም አሰራር ግዴታ በመሆኑ ሰልጣኞች የማስፈጸም ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ስልጠናውን ከላይኛው መዋቅር ጀምሮ እስከ ክላስተር ደረጃ ማስፋፋት እንደሚጠበቅ በመግለጽ፣ በእስካሁኑ ሂደት አበርክቶ ለነበራቸው አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደ/ር ሐሰን ሁሴን በበኩላቸው፤ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡም አርአያ የሚሆን ዜጋ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ ልጣኞችም በሙያቸው ለተማሪዎችና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እንዲሁም ዜጎችን መለወጥ የሚችሉ እንዲሆኑ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላት ትልቁ ሀብት ወጣት በመሆኑ እነሱን ለአለም ተወዳዳሪ አድርጎ የማውጣት እና የነገውን የኢንተርፕራይዝ ማስፋፊያ አሻራ የማሳረፉ ኃላፊነት በእጃቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን መሰል ስልጠና በማዘጋጀቱ ደስታቸውን ገልጸው የተሰጣቸው ኃላፊነት ትልቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Meseret Media@meseretmediaНовости и СМИ75,8 тыс.
Muktarovich Ousmanova@muktarovichousmanovaНовости и СМИ59,5 тыс.
DW Amharic@dw_amharicНовости и СМИ56,8 тыс.
ሰሌዳ | Seleda@seledadotioНовости и СМИ53,6 тыс.
Zehabesha@zehabeshanewsНовости и СМИ53,5 тыс.
ETHIO-MEREJA®@ethio_merejaНовости и СМИ96,4 тыс.
BBC News Afaan Oromoo@bbcafaanoromooНовости и СМИ51,5 тыс.
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ@sputnik_ethiopiaНовости и СМИ50,8 тыс.