Кабинет
Zehabesha

Zehabesha

Ethiopian News

Юзернейм
@zehabeshanews
Категория
Новости и СМИ
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики53 477
Просмотров на пост, 7 дн.6 253за 7 дней
ERR11,69 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
21 нояб. 2026 г.7 230
22 нояб. 2026 г.6 795
23 нояб. 2026 г.6 690
24 нояб. 2026 г.5 205
25 нояб. 2026 г.3 085

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры8,2 тыс.
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры7,89 тыс.
    Пересылки—
    Реакции1
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры7,44 тыс.
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04

    የጄኔራል አልብሩሀን ተቀናቃኞች ከዳማዚን 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መድረሳቸው ተዘገበ፡፡ የግብፁ አይን ኔትወርክ እንደዘገበው በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው ጦር ሀይል ባለፉት ጥቂት ቀናት በምስራቃዊ ጦር ግንባር ድል እየቀናው አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር ድንበር በሚዋሰነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ በሚደረገው በዚህ ውጊያ ተቀናቃኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ሀይልና የሱዳን ነፃ አውጭ ግንባር ሰሜን ሀይሎች ወደፊት እየገሰገሱ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ እንደዘገባው ተቀናቃኞቹ ባው የተባለ ጦር ሰፈርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደጌሰንና ማዲና 11 ያመሩ ሲሆን ይህ ግስጋሴያቸውም የግዛቱ ዋና ከተማ ከሆነን ዳማዚን በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲደርሱ አስችሏቸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ የዳማዚን ነዋሪዎች ከተማውን ለቀው መውጣት መጀመራቸውን የጠቀሰው ዘገባው የብሉ ናይል ግዛት መንግስት ቃል አቀባይ ግን ነዋሪዎቹ እንዲረጋጉ በቴሌቪዥን ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ሌተና ጄኔራል አልብሩሀን ዛሬ ባደረጉት ንግግር አገራቸው በውጭ ሀይሎች ‹‹ኢኮኖሚያዊ ጦርነት›› እንደተከፈተባት አስታውቀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ዜጎቻችን አሁን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር እንደገጠማቸው እናውቃለን፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻውን የሚደግፉ አንዳንድ አገራት የከፈቱብን ኢኮኖሚያዊ ጦርነት ነው›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ሚሊሻው እስከሚጠፋ ድረስ ጦርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

    Текст
    Просмотры7,43 тыс.
    Пересылки—
    Реакции19
    Комментарии—

Новые посты

#16008Текст
Просмотры5 080−19%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#16006Текст

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሱዳን የሚገኙ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ሲቪል አካላትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች፣ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነትና አመቻችነት ለሚካሄድ ግልጽና ሁሉን አቀፍ ሱዳናዊ ውይይት ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ይፋዊ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በዓረብኛ ቋንቋ ይፋ ባደረጉት ሰፊ መግለጫ፣ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም. የተቀሰቀሰው የሱዳን ግጭት ወደ አራተኛ ዓመቱ በገባበትና ሰብዓዊ ቀውሱ ከምንጊዜውም በላይ በተባባሰበት በዚህ ወቅት፣ ወንድማማች አገሮች እጃቸውን አጣጥፈው መቀመጥ እንደማይችሉ አስታውቀዋል፡፡ በግጭቱ ምክንያት የሱዳን ሕዝብ ከፍተኛ የሕይወት ዋጋ መክፈሉን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ለመፈናቀልና ለስደት መዳረጋቸውን፣ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችና የመንግሥት ተቋማት ለከፍተኛ ውድመት መጋለጣቸውን በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበው ይህ ተነሳሽነት ከየትኛውም ፖለቲካዊ አጀንዳ የጸዳና በየትኛውም የሱዳን ወገን ኪሳራ ጥቅም ለማግኘት ያለመ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሁሉም ወገኖች በእኩል ርቀት በመቆም ግልጽ፣ ቁም ነገረኛና መከባበር የሰፈነበት የውይይት መድረክ ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኗን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፣ የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ የአንድ ወገን አሸናፊነት ሳይሆን የሱዳንና የሕዝቧ አሸናፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በመግለጫው እንደተመለከተው፣ ኢትዮጵያ ይህ በሱዳናውያን የሚመራ ውይይት ግጭቱን የሚያስቆም፣ ሁሉን አቀፍ አገራዊ ሂደትን የሚጀምርና ሰፊ ተቀባይነት ያለው የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ለማቋቋም የሚያስችሉ ፖለቲካዊ መግባባቶችን እንደሚያስገኝ ትጠብቃለች፡፡ ይህም የመንግሥት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት፣ የሱዳንን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ እንዲሁም ዘላቂና ፍትሐዊ ሰላም ለማስፈን መሠረት እንደሚጥል ተጠቅሷል፡፡ ከውጭ የሚጫን መፍትሔ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሱዳንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መወሰን ያለባቸው ሱዳናውያን ራሳቸው ብቻ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያና ሱዳን ከጂኦግራፊና ከፖለቲካ ባሻገር በጥልቅ ታሪካዊ፣ ባህላዊና የሕዝብ ለሕዝብ ወንድማማችነት የተሳሰሩ መሆናቸውን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹የሱዳን ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም፣ ደኅንነቷም የኢትዮጵያ ደኅንነት ነው፤ መረጋጋቷም ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ዋነኛ ምሰሶ ነው›› ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2019 በሱዳን የሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤትና በሲቪል ኃይሎች መካከል መግባባት እንዲፈጠር የተጫወተችውን ገንቢ ሚና በማስታወስም፣ አሁንም ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በመጠቀም ተነሳሽነቱ እንዲሳካ ከሚመለከታቸው አጋሮች ጋር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አመልክተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ ወዳጅ አገሮችና ቀጣናዊ ተቋማት ከጠባብ ስሌቶችና ጽንፍ ከረገጡ አሰላለፎች በመራቅ የሱዳንን ሕዝብ የሰላም ፍላጎት እንዲደግፉና ለተፈናቃዮች የሚደረገውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል፡፡ ሁሉም የሱዳን ወገኖች የአገራቸውን ከፍተኛ ጥቅም ከግጭት ስሌት በማስቀደም ለቀረበው የወንድማማችነት ጥሪ በኃላፊነት መንፈስ ምላሽ እንዲሰጡም አሳስበዋል፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры5 010−20%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#16004Текст

የሱዳን መንግስት ተፋላሚዎቹ የጦር ምርኮኞችን መግደላቸውን አስታወቀ፡፡ የሱዳን መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በብሉ ናይል ግዛት ውስጥ በተካሄደው ውጊያ በርካታ አባላቱ በተቀናቃኞቹ በምርኮ መያዛቸውን ገልፆ እነዚህ መገደላቸውን አጥብቆ እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡ በመግለጫው ‹‹እስረኞችን መግደል አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግን በግልፅ መጣስ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚገባ አጥብን እናሳስባለን›› ብሏል፡፡ ጨምሮም አሁንም በምርኮ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመጠበቅ አለም አቀፉ ማህበረሰብና በቀጠናው የሚገኙ ተቋማት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በካርቱም በተደረገው የድሮን ጥቃት የተመድ ሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ወይንም ኦቻ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ድሮኖቹ በሰራተኞቹ መኖሪያ ህንፃ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቆ በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ መሰረት የእርዳታ ሰራተኞችና ንብረታቸው መጠበቅ እንዳለበት አሳስቧል፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры6 690+7%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#16003Текст

የጄኔራል አልብሩሀን ተቀናቃኞች ከዳማዚን 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ መድረሳቸው ተዘገበ፡፡ የግብፁ አይን ኔትወርክ እንደዘገበው በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው ጦር ሀይል ባለፉት ጥቂት ቀናት በምስራቃዊ ጦር ግንባር ድል እየቀናው አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር ድንበር በሚዋሰነው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ በሚደረገው በዚህ ውጊያ ተቀናቃኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ሀይልና የሱዳን ነፃ አውጭ ግንባር ሰሜን ሀይሎች ወደፊት እየገሰገሱ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ እንደዘገባው ተቀናቃኞቹ ባው የተባለ ጦር ሰፈርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደጌሰንና ማዲና 11 ያመሩ ሲሆን ይህ ግስጋሴያቸውም የግዛቱ ዋና ከተማ ከሆነን ዳማዚን በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲደርሱ አስችሏቸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ የዳማዚን ነዋሪዎች ከተማውን ለቀው መውጣት መጀመራቸውን የጠቀሰው ዘገባው የብሉ ናይል ግዛት መንግስት ቃል አቀባይ ግን ነዋሪዎቹ እንዲረጋጉ በቴሌቪዥን ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ሌተና ጄኔራል አልብሩሀን ዛሬ ባደረጉት ንግግር አገራቸው በውጭ ሀይሎች ‹‹ኢኮኖሚያዊ ጦርነት›› እንደተከፈተባት አስታውቀዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹ዜጎቻችን አሁን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር እንደገጠማቸው እናውቃለን፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻውን የሚደግፉ አንዳንድ አገራት የከፈቱብን ኢኮኖሚያዊ ጦርነት ነው›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ሚሊሻው እስከሚጠፋ ድረስ ጦርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

Открыть в Telegram
Просмотры7 430+19%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#16002Текст

• የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ ከ5 ሰዓት ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል • ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ይካሄዳል (ዘ-ሐበሻ ዜና) ትናንት ቅዳሜ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም. በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር፣ ነገ ሰኞ ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ተገለጸ። ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተሰራጨው መልዕክት መሠረት፣ የድምፃዊው የሙያ አጋሮችና አድናቂዎች ነገ ሰኞ ከረፋዱ 5 ሰዓት ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በመገኘት የመጨረሻ ሽኝት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። መልዕክቱ ትናንት የደረሰውን ድንገተኛ ሕልፈት «እጅግ የከፋ፣ የኢትዮጵያውያንን ልብ የሰበረና ይህን ከንቱ ዓለም ያጋለጠ ብርቱ መከራ» ሲል በጥልቅ ሐዘን ገልጾታል። ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በሙዚቃ ሥራ ላይ በነበረበት ወቅት በድንገት ባጋጠመው ሕመም ሕይወቱ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን፣ ዜናው በኪነ ጥበቡ ማኅበረሰብና በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ፈጥሯል። ለዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ በለስላሳና ልብ በሚነካ ድምፁ የራሱን አሻራ ያኖረው ድምፃዊው፣ «የኔ ደሃ»፣ «ዛሬም እወድሻለሁ»፣ «ግርማ ሞገሴ»፣ «ቱሪናፋ» እንዲሁም በቅርቡ ባወጣው «እንዳማረ» እና መሰል ተወዳጅ ሥራዎቹ በአድማጮች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፎ ቆይቷል። በነገው የሽኝትና የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ የከያኒው ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የሙያ አጋሮቹና በርካታ አድናቂዎቹ ከቃሊቲ መኖሪያ ቤቱ ጀምሮ እስከ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ድረስ በመገኘት የመጨረሻ ክብር እንደሚሰጡት ይጠበቃል። ድምጻዊ ሚኪያስ ቸርነት በመጨረሻው ሰዓት የሚያሳይ ዘገባ VOEA Amharic፡ዩቱብ ቻናል ላይ ቀርቧል።

Открыть в Telegram
Просмотры6 850+10%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—

Все посты

Связи