✨ ውበት እና ምቾት ያላቸው ኮምፈርቶች እናንተ በመረጣችሁት ከለር 🎨፣ እንደ አልጋዎቻችሁ ስፋት 📏 (በተለያዩ ሜትሮች) እንዲሁም የተለያዩ የዋጋ አማራጮች 💰 አሟልተን አስገብተናል። ምቾትና ጥራታቸው በገበያው ላይ ካሉት ኮምፈርቶች ሁሉ በግልጽ የሚታይ ልዩነት አሏቸው። ነጻ ዴሊቨሪ 🚚📦🏍 በአዲስ አበባ የምትገኙ ደንበኞቻችን ባላችሁበት በነጻ እናደርሳለን። በክፍለሀገር የምትገኙ ደንበኞቻችን ደግሞ አዲስ በጀመርነው የስርጭት አገልግሎት 🚛ዴሊቨሪ እናደርጋለን። በፍጥነት ይደውሉ! 📞 📞 ስልክ: 0910975512 📩: @Kelal1online የቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇 https://t.me/joinkelalshopping
Open in TelegramPosts of አዲስ ነገር መረጃ
አትሞክሩን አንፈልጋችሁም፤ የሚመጣብን ካለ ግን አድዋ ይደገማል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ማንንም ወርራ አታውቅም፤ ወደፊትም ይህ ፍላጎት የላትም፡፡ ትንሽም ይሁኑ ትልቅ ማወቅ ያለባቸው ጉዳይ ግን፤ ማንም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ፤ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ይህ በመልክዓምድራዊ ቅርበትና በርቀት የተገደበ ጉዳይ አይደለም፤ አትሞክሩን አንፈልጋችሁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሚመጣብን ካለ ግን አድዋ ይደገማል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በመከላከያ ስትራቴጂ አማካኝነት በሁሉም ምሶሶዎች ሸብረክ የማይል ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ መሆኑን በመግለጽ፤ መከላከያ ቴክኖሎጂን በሚገባ የሚጠቀም ተቋም መደረጉ በውጤቱ እየታየ ይገኛል ነው ያሉት፡፡ @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramየመንግሥትና የግል ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ:: በኢትዮጵያ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዴት መስተካከል እንዳለበት የሚያመላክት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት፣ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው። በማብራሪያቸውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ያነሱት ዶክተር ዐቢይ፣ የአገሪቱ የዕዳ ጫና ሽግሽግ ተደርጎለት ወደ መካከለኛ ደረጃ መውረዱን ለዚህ በማሳያነት ጠቅሰዋል። የዋጋ ግሽበት በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል። ሆኖም የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዜጎች ላይ የሚያሳድረውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። ከእነዚህም መካከል፦ 1. የመንግሥት ድጎማዎችን ማድረግ 2. የደሞዝ ጭማሪዎችን ተግባራዊ ማድረግ 3. ሌሎች የዜጎችን ጫና የሚያቃልሉ አማራጮችን መጠቀም የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤታማ ሆኖ እንዲቀጥልና የሚያጋጥሙ ውስን የኑሮ ጫናዎችን ለመቅረፍ ተከታታይ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegram📍መገናኛ ዲያስፖራ ጫካ ፕሮጀክት ፊትለፊት 🟢 100% ለከፈለ 35% በነፃ ነው 🟢 40/60 አከፋፈል አመቻችተናል ➡️ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ ➡️ ባለ 2 መኝታ 90,99 ካሬ ➡️ ባለ 3 መኝታ 120 -145 ካሬ ዋጋ እና አከፋፈል ✅ ባለ 1 መኝታ 60 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 7.2 ሚልዮን ብር ቅድመ ክፍያ 20% ➖ 1.4ሚልዮን 🗝100% ለሚከፍል ➖ 4.6ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 1 መኝታ 69ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 8.2 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ➖ 1.6 ሚሊዮን ብር 🗝100 % ለሚከፍል ➖ 5.3 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 2 መኝታ 90ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 10.8 ሚልዮን ብር ቅድመ ክፍያ 20% ➖ 2.1 ሚልዮን ብር 🗝100% ለሚከፍል ➖ 7 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 2 መኝታ 99 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 11.8 ሚልዮን ቅድመ ክፍያ 20% ➖ 2.3 ሚልዮን 🗝100% ለሚከፍል ➖ 7.7 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 3 መኝታ 120 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 14.4 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ➖ 2.8 ሚሊዮን ብር 🗝100% ለሚከፍል ➖ 10 ሚሊዮን ብር ✅ ባለ 3 መኝታ 145 ካሬ ጠቅላላ ክፍያ ➖ 17.4 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ➖ 3.4 ሚሊዮን ብር 🗝100% ለሚከፍል ➖ 12.1 ሚሊዮን ብር ቀሪ ክፍያ ✅ ያለ ምንም ዋጋ ጭማሪ ✅ ከወለድ ነፃ አከፍፈል ✅ በግንባታ ሂደት የሚከፈል 📞WhatsApp call=https://wa.me/message/Z5LFLDJBTZUDK1 ✈️Telegram =@Temerr34 📞 09-82-15-16-64
Open in Telegram1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ ! በጉባ መድረክ ይፋ የተደረገው 1.5 ሚሊየን ቤቶችን የመገንባት ሀገራዊ ዕቅድ ከንግግር ባለፈ በአዲስ አበባና በክልሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ወደ መገንባት ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። የፖሊሲና የመሬት ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዜጎች ቤት ገዝተው እየሠሩ የሚከፍሉበት ከባንክ ጋር የተሳሰረ ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪም ከ15 ቀን እስከ አንድ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ቪላ ቤቶችን ማጠናቀቅ የሚችሉ የቱርክና የቻይና ዘመናዊ ፋብሪካዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሙከራ ሥራ መጀመራቸውን አብራርተዋል። በሙከራ ቦታዎች የታዩ የፍሳሽ መስመርና የግብአት አቅርቦት ፈተናዎችን በማረም ግንባታው በስፋት መቀጠሉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢኮኖሚው እያደገ ሲሄድ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ለመንገድ፣ ለባቡርና ለቤት ግንባታ ቅድሚያ ሰጥቶ ማጠናቀቅ የግድ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegram«የተዘረፈውን የሕዝብ ሀብት በማስመለስ ተጠያቂነት ሊሰፍን ይገባል» – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የ7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ሲሆን፣ ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል ብልሹ አሠራር እና ሙስና ዋነኛው መሆኑ ተገልጿል። የምክር ቤቱ አባላት በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የግል ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ፣ ዜጎችን የሚያስለቅሱ እና ሥልጣናቸውን ለበደል የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለውን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል። እነዚህ ጥቂት ሙሰኞች የሕዝብን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሚገኙ የጠቆሙት አባላቱ፣ ችግሩን ለመቅረፍ በዲጂታል ሥርዓት ላይ እንደ ሀገር እየተሠራ ቢሆንም ሙስና አሁንም ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አመላክተዋል። ለሀገር ልማት መዋል የሚገባው ሀብት በጥቂት ሙሰኞች ኪስ መግባቱ የትውልዱን ሞራል እየገደለ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ አባላት፣ ችግሩን ማውገዝ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የዘረፉትን የሕዝብ ሀብት እንዲመልሱ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramእስረኞች እየተከፈላቸው ስራ ጀምረዋል - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተገናኘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በበርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሠራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት እስረኞችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መጀመሩን አስታውቀዋል። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በቂ የሰው ኃይል ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ እስረኞች ተገቢው ክፍያ እየተፈጸመላቸው በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ እየተደረገ ይገኛል። በተለይም በሹፍርና፣ በቀለም ቅብ፣ በጽዳት፣ በወለል ንጣፍ እና በሌሎችም መሰል የሙያ መስኮች ላይ ሠራተኛ ማግኘት ፈታኝ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዜጎች ሥራን ሳይንቁ የተገኙትን የሥራ ዕድሎች በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አሳስበዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ጊዜ እንዲገለጽ እና የፕሬስ ነጻነት ትኩረት እንዲያገኝ በምክር ቤቱ ጥያቄ ቀረበ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበ ጥያቄ፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በየአሥር ዓመቱ መካሄድ የነበረበትና ያልተካሄደው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ መቼ እንደሚደረግ እንዲገለጽ፣ እንዲሁም የፕሬስና የፖለቲካ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ። የምክር ቤት አባሉ በንግግራቸው፣ ሕገ-መንግሥቱ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በየአሥር ዓመቱ እንዲካሄድ ቢደነግግም ከ1997 ዓ.ም በኋላ በ2007 ዓ.ም መካሄድ የነበረበት ቆጠራ አለመካሄዱን አስታውሰዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የበጀት ቀመር ለማውጣት፣ ፍትሐዊ የበጀት ድልድል ለማድረግ፣ የልማት ዕቅዶችን ለመንደፍ እና የምርጫ ክልሎችን አከላለል ለመወሰን መነሻ የሚያደርገው ይህንኑ ቆጠራ መሆኑን የገለጹት ተናጋሪው፤ ቆጠራው አለመካሄዱ ፍትሐዊነትን እንደሚያጓድልና የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታውን እንደሚያቀጭጭ አስገንዝበዋል። በመሆኑም ቆጠራው መቼ እንደሚካሄድ በፕሬዝዳንቱ ንግግርና ሞሽን ውስጥ ተካቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። በተያያዘም በቅርቡ የተካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ ቢጠናቀቅም በርካታ ሕጸጾች እንደነበሩበት ተናጋሪው ጠቅሰዋል። የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ከፖለቲካና ከፕሬስ ነጻነት መስፋት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተው፣ ነጻው ፕሬስ እንደ አራተኛ መንግሥት የመብት ጥሰቶችን በማጋለጥና የመንግሥት ተጠያቂነት እንዲኖር በማድረግ ረገድ ድርሻውን እንዲወጣ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል። ይሁን እንጂ የመንግሥት ወይም የፐብሊክ ሚዲያዎች መንግሥትን ከመቆጣጠርና ዲሞክራሲን ከመገንባት ይልቅ የመንግሥት አፈ ቀላጤ ሆነው መቀጠላቸው የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እንዳይጎለብትና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጥረቱ እንዳይጠናከር እያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል። ስለሆነም የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣ የፖለቲካ ነጻነትና የፕሬስ ነጻነት መስፋት ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ ንግግር ተካቶ የመንግሥት የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ጠይቀዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 963 |
| 3 h | 3,520 |
- After 1 hour963
- Total to date3,520
ልዩ አማራጭ እና አዲስ ነገር በወለል 1 ቤት ብቻ ‼️ 🏙️60,000 ካሬ ሜትር ላይ ባረፈ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ውስጥ 🏠G+1 ቪላ ቤቶች 🏘️G+2 ታውን ሃውስ 🏢 G+4 አፓርትመንት ✅ በወለል 1 ቤት ብቻ 🛏️ ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤቶች ✅ በ1 ዓመት የሚረከቡት እና የተጠናቀቁ ✅ በሙሉ ግንባታ (Fully finished) 🏘️ የመኖሪያ ግቢ ብቻ (Gated compound) 💰 በ 30% ቅድመ ክፍያ 🛏️ ባለ 2 መኝታ 103.6 ካሬ 0️⃣ ምድር ወለል (Ground floor) 💰 ክፍያ=4,497,897.60 🛏️ ባለ 3 መኝታ 125.8 ካሬ 1️⃣ አንደኛ ወለል (1st floor) 💰 ክፍያ = 5,849,700 2️⃣ ሁለተኛ ወለል ( 2nd floor) 💰 ክፍያ = 5,623,260 3️⃣ ሶስተኛ ወለል ( 3rd floor) 💰 ክፍያ = 5,340,210 4️⃣ አራተኛ ወለል ( 4th floor) 💰 ክፍያ = 5,135,659.20 📍በ ቦሌ ቡልቡላ ✅አስፈላጊ መሰረተ ልማት የተሟላለት ግቢ በዙሪያው 🍝ዓለም አቀፍ ሬስቶራንት እና ካፌዎች ፥ 🏫ትምህርት ቤቶች ፥ 🎡መዝናኛ ፓርክ ፥ ⚽የ ስፓርት ማዘውተሪያዎች ፥ 🛒ሱፐር ማርኬቶች እና የንግድ ማዕከሎች ✈️ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በ 5 ደቃቃ ርቀት ℹ️ ለበለጠ መረጃ እና ሳይት ጉብኝት በስልክ ቁጥራችን 💬 በቀጥታ በ 📲 Whatsapp_https://wa.me/qr/TY4MQPKPEFXSI1 📲 Telegram ☎️ 0934244544
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,100 |
| 4 h | 3,310 |
- After 1 hour1,100
- Total to date3,310
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶ/ር አወቀ ሃምዛዬ፣ በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገለጹ። የምክር ቤት አባሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርትን በመጥቀስ እንዳብራሩት፣ የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት አሳሳቢ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፤ በመንግሥት ኃይሎች፣ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች፣ በተለያዩ ቡድኖች እንዲሁም በፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎች፣ አካል ማጉደልና ዘረፋዎች የሕዝቡን ሰላማዊ ኑሮ በእጅጉ በመጉዳት ህልውናውን አደጋ ላይ ጥለውታል። በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ፣ አርሲ፣ በሞያሌ አካባቢ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሶዶና አበሽጌ፣ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬና ቡርጂ ዞኖች ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ጋር በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የንጹሐን ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ፣ ከበባ፣ መንገድ መዝጋትና የዜጎች ሞት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ዶ/ር አወቀ ገልጸዋል። ዶ/ር አወቀ በንግግራቸው የኮሬ ሕዝብን ጉዳይ በልዩ ትኩረት በማንሳት፣ ሕዝቡ በኢትዮጵያ ታሪክ ሰምቶትም ሆነ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ ላለፉት 11 ዓመታት በፅንፈኛ ታጣቂዎች እየተወረረ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። ጉዳዩ በተደጋጋሚ ለምክር ቤቱና ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢቀርብም ወረራው ከትላንት በስቲያም፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ በዚህ ሰዓት መቀጠሉን ጠቅሰው፣ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የክልሉ የፀጥታ አካላትም አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈሉና እየሞቱ መሆኑን አስረድተዋል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 1,950 |
| 4 h | 3,550 |
- After 1 hour1,950
- After 6 hours3,550
- Total to date3,550
የደረት ማቃጠል የደረት ማቃጠል በተለያዩ የጤና ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ምልክት ነው። ከሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ በመመለስ (Acid Reflux) ምክንያት ሲከሰት፥ በሌላ ጊዜ ከልብ በሽታዎች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። ምክንያቶች የሆድ አሲድ መመለስ (Acid Reflux)፦ የሆድ አሲድ ወደ ምግብ ቧንቧ ሲመለስ በደረት አካባቢ የማቃጠል ስሜት ይፈጥራል። የልብ ችግር፦ ወደ ልብ ጡንቻ የሚደርሰው ደም ሲቀንስ ወይም ሲቋረጥ የደረት ማቃጠልና ጫና ሊሰማ ይችላል። የጡንቻ ችግር፦ በደረት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ሲጎዱ ወይም ሲወጠሩ ሕመም ሊከሰት ይችላል። የሳንባ ችግር፦ አንዳንድ የሳንባ በሽታዎችም በደረት አካባቢ ሕመምና ማቃጠል ሊያስከትሉ ይችላሉ። የደረት ማቃጠል መቼ አደገኛ ይሆናል? የደረት ማቃጠል በራሱ ሁልጊዜ የልብ ድካም ምልክት አይደለም። ነገር ግን ከሚከተሉት ሁኔታዎች ጋር ከተያያዘ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 2,890 |
| 5 h | 4,210 |
- After 6 hours4,210
- Total to date4,210
ቡርኪናፋሶ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባችውን ግዙፍ የቴክኖሎጂ አካዳሚ መርቃ ከፈተች የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ በ61.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በ11 ወራት ጊዜ ውስጥ የተገነባውን «አካዳሚ ቴክኖሎጂክ ዱ ፋሶ» የተሰኘ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ. ኅዳር 23 ቀን 2026) መርቀው ከፈቱ። በ60 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ የትምህርትና ምርምር ተቋም፣ የሀገሪቱን ሳይንሳዊ ራስን መቻልና የኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠን ታልሞ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል። አካዳሚው በመጀመሪያው ዙር 250 ተማሪዎችን ተቀብሎ የኒውክሌር ምሕንድስና፣ አቪዬሽን፣ ማዕድን እና የሳይበር ደኅንነትን ጨምሮ በ11 ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ሥልጠና እንደሚሰጥ ተመላክቷል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 2,810 |
| 6 h | 3,910 |
- After 6 hours3,910
- Total to date3,910
መርጌታ ጌታቸው የባህል መድህኒት ፈውስ የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☞ ለመፍትሄ ሀብት ☞ ለህመም ☞ ለመስተፋቅር ☞ ቡዳ ለበላው ☞ ለገበያ ☞ ሚስጥር የሚነግር ☞ ለቀለም(ለትምህርት) ☞ ለመፍትሔ ስራይ ☞ ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ ☞ ሌባ የማያስነካ ☞ ለበረከት ☞ ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) ☞ ለግርማ ሞገስ ☞ መርበቡተ ሰለሞን ☞ ለዓይነ ጥላ ☞ ለሁሉ መስተፋቅር ☞ ጸሎተ ዕለታት ☞ ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ ☞ ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) ☞ ለትዳር ☞ ለድምፅ 👉 0921007264 ይደውሉ መፍትሄ አለን 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🍀🌿🙏 መርጌታ ጌታቸው የባህል ህክምና ቀማሚ ከፈጣሪ በታች በተሰጠን ሰለሞናዊ ጥበባችን በአለም አቀፋ እዉቃና አግኝተን የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን🇪🇹። 📞09 21007264 📞09 21007264 👉 የብልት ማነስ 👉የመልፈስፈስ 👉ቶሎ የመጨረስ(የመርጨት) ችግር አለብዎት ባልሽስ አለበት ለበለጠ መረጃ 👉በቴሌግራም ማውራት ለሚፈልግ ከታች ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇@Mgetachew23 በከመ ፈቀደ ይገብር ወበከመ ሀለየ ይፌፅም 🍀🌿 🙏በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር ውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ መዳኒቱን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን 🍀🌿🙏ልብ ይበሉ ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ ራሳችሁን ከአጭበርባሪወች ጠብቁ!
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 3 h | 2,600 |
| 6 h | 3,730 |
- After 6 hours3,730
- Total to date3,730
የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን🙏 በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡ በኃይል በጸጋና በመንፈሳ ተሞልቶ የወንጌሉን ብስራት ይሰብክ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡ ታላቁ ሰማዕት የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ኋላም የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን ጠይቆ ወደ ጌታችን በመሔድ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፡፡ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐ ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን ተሹሟል፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን ቢያስፋፋ አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸውና በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በተወለደበት ጥር 1 ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ሲወግሩትም ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ እንደ አምላኩ ለሚወግሩት ሰዎች “የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ገዳማውያን ሰማዕቱን አብነት አድረገው በጸሎትና በጾም እየተጉ የሥጋ ፍላጎትን ድል ያደርጉታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡ ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 4 h | 3,180 |
| 7 h | 4,310 |
- After 6 hours4,310
- Total to date4,310
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 4 h | 2,840 |
| 7 h | 3,940 |
- After 6 hours3,940
- Total to date3,940
ለዓመታት በግጦሽ ሳር፣ በውሃ እና በመሬት ይገባኛል ምክንያት ሲከሰት የቆየው የአፋር እና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰቦች ግጭት፣ አሁን ከቀን ወደ ሌሊት በተሸጋገረ ከባድ ውጊያ መቀጠሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለከፋ ስጋት ዳርጓል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የፌደራል መንግስት እና የሀገር ሽማግሌዎች ያደረጓቸው የእርቅ ስምምነቶች ዘላቂ ባለመሆናቸው፣ የአካባቢው ሰላም ተደጋግሞ እየተናጋ እና ዜጎች ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።ዳግም አገርሽቶ አንድ ወር እንዳስቆጠረ የሚነገረው የአፋር የሶማሌ ኢሳ ጎሳ የድንበር ግጭት ከዚህ ቀደም ከነበረበት የአፋር ክልል ዞን 3 ሀሩካ፣ አቢዳ እና አርጋቶ የድንበር አካባቢ አሁን ደግሞ ወደ ዞን 1 ገርቢ አካባቢ ከትላንት ሰኞ ጀምሮ መቀጠሉን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገልጹት። ዶቼቬሌ @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramየትራምፕ አስተዳደር በ14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮች ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) ጣለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለፋብሪካዎቻቸው ድጎማ በማድረግ ከፍላጎት በላይ ያመርታሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ገበያውን በርካሽ ምርት ያጥለቀልቃሉ ባላቸው 14 ዋና ዋና የንግድ አጋሮቹ ላይ አዲስ የንግድ ታሪፍ (ቀረጥ) መጣሉን አስታውቋል። እርምጃው ቻይናን ፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ ህንድን ፣ ጃፓንን ፣ ደቡብ ኮሪያን ፣ ቬትናምን ፣ ኢንዶኔዥያን ፣ ታይላንድን ፣ ማሌዥያን ፣ ሲንጋፖርን ፣ ታይዋንን ፣ ስዊዘርላንድን ፣ ባንግላዴሽን እና ካምቦዲያን ኢላማ ያደረገ ነው። በምርመራው ላይ ተካትተው የነበሩት ሜክሲኮ እና ኖርዌይ ግን ለጊዜው ከቅጣቱ ተርፈዋል። ከሁሉም ሀገራት በላይ ቻይና ቀደም ሲል ከነበረባት የ25 በመቶ ታሪፍ በተጨማሪ አዲስ የ20 በመቶ ቀረጥ በመጣሉ ከፍተኛውን ቅጣት ትሸከማለች። ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕ ቀደም ሲል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣሉትን ታሪፍ ውድቅ ስላደረገባቸው አሁን እርምጃውን የወሰዱት እ.ኤ.አ በ1974 በወጣው የንግድ ህግ ሴክሽን 301 መሰረት ሲሆን ይህ ህግ የውጭ መንግስታት ፍትሃዊ ያልሆነ የንግድ አሰራር ሲከተሉ እና የአሜሪካን ኩባንያዎች ሲጎዱ ፕሬዝዳንቱ የአጸፋዊ ቀረጥ እንዲጥሉ ሙሉ ሥልጣን ይሰጣል። የንግድ ባለሙያዎች ይህ ውሳኔ በአሜሪካ የኑሮ ውድነትን ይበልጥ እንደሚያባብስ ፤ አነስተኛ ነጋዴዎችን እንደሚጎዳ እና ከቻይና እንዲሁም ከሌሎች አጋር ሀገራት ጋር ያለውን የንግድ ውጥረት እንደሚያከርረው ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramለChatGPT ወይም ለGemini "ሰላም" ስትለው፣ እሱ በዚያው ቅጽበት አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውኃ ጭልጥ አድርጎ እንደሚጠጣ ታውቃለህ? 😂💧 የምንጠቀምበትን ኢንተርኔት፣ ክላውድ (Cloud) እና ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚያንቀሳቅሱት ግዙፍ የዳታ ማዕከላት (Data Centers) ጉሮሯቸው በጣም ደረቅ ነው! ሰርቨሮቻቸው ከመጠን በላይ ግለው እንዳይቃጠሉ ለማቀዝቀዝ በቀን እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ንጹሕ ውኃ ይጠጣሉ። እስቲ ይህንን አስቡት አንድ ትልቅ የዳታ ማዕከል በቀን ከ1 እስከ 5 ሚሊዮን ጋሎን ውኃ ይጠቀማል። ይህ ማለት 50,000 ሕዝብ ያላትን አንዲት ሙሉ ከተማ የውኃ ፍጆታ ብቻውን ይጨርሳል ማለት ነው፤ ከእነዚህ ጋር ውኃ መጋራት ራሱ ይከብዳል! ዋናው ችግር ደግሞ የተጠቀሙት ውኃ ተመልሶ አለመገኘቱ ነው። "የጠጡት" ውኃ በትነት መልክ ወደ ሰማይ ስለሚወጣ፣ ተመልሶ ወደ ወንዙም ሆነ ወደ ቧንቧችን አይገባም። የሚገርመው ደግሞ ከ2022 ወዲህ ከተገነቡት አዳዲስ ማዕከላት መካከል ሁለት ሦስተኛው የተተከሉት ቀድሞውኑ ከፍተኛ የውኃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የአካባቢው ገበሬ ቤተሰቡና እንስሳቱ በውኃ ጥም እየተቸገሩ፣ ሰርቨሮቹ ግን "ውኃ አምጡ" ይላሉ። ይበልጥ አሳሳቢው ግን የወደፊቱ ስጋት ነው! በቴክሳስ ብቻ በ2025 ወደ 49 ቢሊዮን ጋሎን ውኃ የጠጡት እነዚህ ማዕከላት፣ በ2030 ጥማታቸው ጨምሮ 399 ቢሊዮን ጋሎን ሊደርስ እንደሚችል ተተንብዮአል። ቴክኖሎጂው መልካም ነው፤ ሕይወታችንንም አቅልሎልናል። ሆኖም የሰው ልጅንና የተፈጥሮን ጉሮሮ እያደረቀ መሆን የለበትም አይደል? አዳዲስ የዳታ ማዕከላት ከመገንባታቸው በፊት "ውኃውን ከየት ነው የምታመጡት? ስንትስ ትጠቀማላችሁ?" ተብለው ሊጠየቁ ይገባል። @Addis_News @Addis_News
Open in TelegramForwarded from TGod Jeremiah
📌 በ 48 ሰዓት ውስጥ Ps 5 ልንሸልማቹህ ነው 📌 Hulu ማዕድን Tiktok creative award ላይ በ 100 ብር ብቻ Vote በማድረግ አሁኑኑ PS 5 ያሸንፉ 📀 አሸናፊዎች በ 48 ሰዓት ይለያሉ ከ 1-3 ለወጡ Vote ላደረጉ እድለኞች የ PS 5 አሸናፊ ይሆናሉ 💖 Hulu ማዕድ 📌 Vote ለማድረግ ሊንኩን ተጭነው በ 100 ብር ብቻ 50 vote ይስጡ Vote ለማድረግ ሊንኩን ይጫኑ 🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽 https://creativeawards.et/nominees/hulumaed-hulumaedd
Open in Telegramጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በነገው ዕለት ለምክር ቤቱ አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት በነገው ዕለት ያካሂዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ምክር ቤቱ ነገ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው ላይ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramጥንቃቄ ‼️ ሰዎች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ጥሪ እየደረሳቸው ይገኛል፦ • +947 • +371 • +563 • +370 • +255 ወይም በእነዚህ መነሻዎች የሚጀምሩ ማንኛውም ቁጥሮች፦ +371፣ +375፣ +381 እነዚህ አካላት አንድ ጊዜ ብቻ ደውለው ይዘጋሉ። ተመልሰው ከደወሉላቸው በ3 ሰከንድ ውስጥ በስልክዎ ላይ ያለውን የሰው ዝርዝር (Contact list) መውሰድ ይችላሉ፤ እንዲሁም በስልክዎ ላይ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃዎች ካሉ በቀላሉ ያገኟቸዋል። የሀገራት መለያ ኮዶች፦ • +375 - ቤላሩስ (Belarus) • +371 - ላቲቪያ (Latvia) • +381 - ሰርቢያ (Serbia) • +563 - ቫልፓራይሶ (Valparaiso) • +370 - ቪልኒየስ (Vilnius) • +255 - ታንዛኒያ (Tanzania) መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች፦ 1.ለእነዚህ ቁጥሮች አይመልሱ ወይም ተመልሰው አይደውሉ። 2.ማንኛውም ደዋይ በስልክዎ ላይ #90 ወይም #09 እንዲጫኑ ቢጠይቅዎት በፍጹም እንዳያደርጉት። ይህ ዘዴ የእርስዎን ሲም ካርድ (SIM card) ለመቆጣጠር፣ በእርስዎ ወጪ ስልክ ለመደወል እና እርስዎን ለወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ የሚጠቀሙበት አዲስ ሴራ ነው። ይህንን የጥሰት ሙከራ ለመከላከል ይህንን መልዕክት በተቻለዎት መጠን ለብዙ ጓደኞችዎ ያጋሩ (Forward ያድርጉ)!!! @Addis_News @Addis_News
Open in Telegramመግዛትም መሸጥም አሁን ቀላል ሆኗል! 📱🔥 FastMarket እነሆ! 🚗 መኪና 🏡 ቤት 👗 ልብስ 📱 ኤሌክትሮኒክስ 🛋️ የቤት እቃዎችና ሌሎችም! 💥 የራስዎን እቃ በነፃ ያስተዋውቁ! በቀላሉ ይሽጡ፣ በቀላሉ ይግዙ! 📲 FastMarketን አሁኑኑ ያውርዱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.fastmarket
Open in TelegramBOOM BOOM እያንበሸበሽን ነው በየቀኑ እስከ 100,000 ብር! ያሸንፉ!💰⚽️ 🎁 አሁኑኑ ትኬቶን ይቁረጡ🔥 ይመዝገቡ ጊዜ አያባክኑ መመዝገቢያ ሊንክ ይፍጠኑ ⬇️ Ahadu.Bets Ahadu.Bets Ahadu.Bets
Open in Telegramግብፅና ሱዳን የባሕር ጠረፍ ለሌላቸው ሀገራት የሚሰጥ የባሕር በር ተደራሽነትንና ቀይ ባሕርን ወታደራዊ ቀጠና የማድረግ ሙከራዎችን ውድቅ አደረጉ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል እድሪስ ትናንት ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም በካይሮ ባደረጉት ውይይትና ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የቀይ ባሕር አስተዳደር የባሕር ጠረፍ ሀገራት ብቻ መብት መሆኑን በመግለጽ የባሕር ጠረፍ ሀገራትን ሉዓላዊነት በሚጎዳ መልኩ የባሕር በር ለሌላቸው ሀገራት የሚሰጥ ተደራሽነትን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። ሁለቱ መሪዎች የባሕር መስመሩን ወታደራዊ ቀጠና ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎችን በጋራ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ከጦርነት በኋላ ለሚከናወነው የሱዳን መልሶ ግንባታ ቅድሚያ ለመስጠትና ፖለቲካዊ አጋርነታቸውን ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚና የልማት ፕሮጀክቶች ለመለወጥ ተስማምተዋል። ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ የሱዳን ዜጎች በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ እንዲሁም በግብፅ እስር ቤቶች የሚገኙ ሱዳናውያን ቀሪ የእስር ጊዜያቸውን በሀገራቸው እንዲጨርሱ የሚያስችል ዕቅድ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጥተዋል። የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል በበኩላቸው ሱዳን በአፍሪካ ሕብረትና በሌሎች አህጉራዊ ተቋማት ያላትን ተሳትፎ እንድትመልስ የግብፅን ድጋፍ የጠየቁ ሲሆን፣ ሁለቱ ሀገራት በቀይ ባሕር ጸጥታ ዙሪያ ከኤርትራና ከሶማሊያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ቅንጅት አጠናክረው መቀጠላቸው ተመላክቷል። @Addis_News @Addis_News
Open in Telegram