አንኽ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ "ሒሮግልይፊኮስ" ἱερογλυφικός ማለት "ቅዱስ ቅርፅ" ማለት ሲሆን የግብፃውያን የፊደል ገበታ"Hieroglyphs" በድንጋይ ላይ አሊያም በደንገል"Papyrus" ላይ የተጻፈ ነው፥ ይህ የፊደል ገበታ ከ 3250 ቅድመ ልደት እስከ 400 ቅድመ ልደት የነበረ ሲሆን ከግብፃውያን የፊደል ገበታ አንዱ አንኽ"Ankh" ነው። በግብፃውያን "አንኽ" ꜥnḫ ማለት "ሕይወት" ማለት ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው፥ በግብፃውያን ሥነ ተረት ጥናት"Egyptian mythology" "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የተመሳቀለ መስቀል "ሆረስ" የተባለው አምላክ "ለዳግማዊ ራምሴ ንጉሥ የሰጠው ሕይወት ነው" ተብሎ ይታመናል። "ሆረስ" የተባለው ጣዖት የመራባት፣ የእርሻ፣ የሞት እና የትንሣኤ አምላክ ከተባለው "ኦስሪስ" አባቱ እና የኦስሪስ ሚስት ከሆነችው ሴት አምላክ "አይሲስ" እናቱ የተወለደ ነው" ተብሎ ይታመናል። "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የእናትየው የአይሲስ የእጅ እንጥልጥ ነው፥ አንኽ በተለይ የግብፅ የሕይወት ምልክት እና ከሞት በኋላ ስለሚኖረው ሕይወት የሚያመለክት የጥንታዊ ግብጻውያን የጣዖት ምልክት ሲሆን የግብፃውያን አማልክት ብዙውን ጊዜ በቀኝ እጅ ይይዙት ነበር፡፡ "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ስርዋፅ ሆኖ የገባው በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት ሲሆን "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ በኃላ ላይ የአዲስ ኪዳን ብጥስጣሾች"Fragments" በሆኑት ደንገሎች ላይ ተጽፎ ይገኛል፥ ለምሳሌ፦ ደንገል 66 በ 150 ድኅረ ልደት ገደማ፣ ደንገል 45 በ 250 ድኅረ ልደት ገደማ እና ደንገል 75 250 ድኅረ ልደት ገደማ ልባሶቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት"Staurogram" ተደርጓል። ዋቢ ምንጭ ይመልከቱ፦ የብሪታኒካ መድብለ ዕውቀት(ኢንሳይክሎፔድያ) (1946)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 753 "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ሰርጎ ገብ በመሆን ዘው ብሎ ሲገባ በድርሳነ ዑራኤል፣ በፍካሬ ኢየሱስ፣ በራእየ ሲኖዳ፣ በራእየ ሳቤላ፣ በመጽሐፈ ምሥጢር እና በገድለ ፊቅጦር "ይመጣል" ተብሎ የሚጠበቀው "ቶ" የተባለው ንጉሥ "ቴዎድሮስ" ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው። የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 14 አንድምታ ላይ ስለ ቴዎድሮስ መምጣት ይመልከቱ! በግሪክ "ቴዎስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ድሮስ" δῶρος ማለት "ስጦታ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ቴዎ ድሮስ" θεό δῶρος ማለት "የአምላክ ስጦታ" ማለት ነው። በግሪክ ሥነ ተረት "ሲቡላ" Σίβυλλα መጻዒ ጊዜን የሚተነትን "ትንቢት" ሲሆን ግሪካውያን በግሪክ አማልክት መንፈስ፦ "ጥቁር ንጉሥ ከጥቁር አገር ይመጣል፥ ስሙም "ቴዎድሮስ" ነው" ብለው የተናገሩትን ምናባዊ ንጉሥ ነው፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ይህንን አስተምህሮት የቀየጠችው ከእነዚህ ዐረማዊ"Pagan" አስተምህሮት ነው። ፨ በመጀመር እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" አቆጣጠር ከ 1413 ድኅረ ልደት እስከ 1416 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የቀዳማዊ አጼ ዳዊት እና የንግሥት ጽዮን መንገሻ ልጅ "ወልደ አንበሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ቀዳማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው። ፨በመቀጠል እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር ከ 1811 ድኅረ ልደት እስከ 1860 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የደጅ አዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ እና የአትጠገብ ወንድ ወሰን ልጅ "ካሳ ኃይሉ" በፈረስ ስሙ "አባ ታጠቅ" በወታደራዊ ስሙ "መይሳው ካሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው። ፨ በመሠለስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ "ሣልሳዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ይመጣል፣ ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ ትሆናለች፣ የዓለም መንግሥታት በሙሉ ይታዘዙታል" ብለው ዛሬ ላይ ብዙኃኑ እየጠበቁ ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት እየሰማናቸው ካሉ የቆረፈዱ የምኞት ተረቶች መካከል "ቶ ንጉሥ የተባለ ኢትዮጵያን የሚገዛ ንጉሥ ይነግሣል" የሚለው ትርክት ከማኅበረ ቅዱሳን እስከ ፋኖ፣ ከጴጥሮሳውያን እስከ ሞዐ ተዋሕዶ፣ ከባልደራስ እስከ ኢትዮ 360 ያሉት ደሴታውያን የሚጠብቁት ይህንን ተስፋ ነው። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የ "ቶ" መስቀል እሳቤ ከግብፅ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ሲሆን የ "ቴዎድሮስ" እሳቤ ከግሪክ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ነው። እናንተ እነዚህ እሳቦት የምታራምዱ፣ የምታቀንቅኑ እና የምታስቀነቅኑ ክርስቲያኖች ሆይ! ከእናንተ በፊት በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ፦ 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ አምላካችን አሏህ የየተሳሳቱን የዐረማዊ ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች ከመከተል ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 1 |
| 7 h | 119 |
- After 6 hours119
- Total to date119








