Кабинет
Tiriyachen | ጥሪያችን

Tiriyachen | ጥሪያችን

Юзернейм
@tiriyachen
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики3 686
Просмотров на пост, 7 дн.114−65% к пред. 7 дн.
ERR3,08 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
31 окт. 2026 г.754
3 нояб. 2026 г.631
4 нояб. 2026 г.542
5 нояб. 2026 г.536
6 нояб. 2026 г.608
9 нояб. 2026 г.494
14 нояб. 2026 г.332
15 нояб. 2026 г.359
19 нояб. 2026 г.301
20 нояб. 2026 г.306
28 нояб. 2026 г.114

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры754
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02

    https://tiriyachen.org/ተውራት/

    Превью ссылки
    Просмотры631
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03

    በዚህ ስሌት የጎደለው በዚህ መልኩ ይሞላል፦ 1. ሚስት 100 × 3 ÷ 27 = 11111.11 2. ሴት ልጆች 100 × 16 ÷ 27 = 59259.26 3. አባት 100 × 4 ÷ 27 = 14814.81 4. እናት 100 × 4 ÷ 27 = 14814.81 ድምር= 11111.11 + 59259.26 + 14814.81 + 14814.81 = 100,000 ይሆናል። "24" በሒሣብ የክፍፍል"Fraction" ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት"Lowest Common Multiple(LCM) ሲሆን "27" ደግሞ ከፍተኛው የጋራ አካፋይ"Highest Common Factor(HCF) ነው፥ ⅛ ለሚስት፣ ⅔ ለሴቶች ልጆች፣ ⅙ ለአባት፣ ⅙ ለእናት ሲሆን፦ 1. 24 × ⅛ = 3 2. 24 × ⅔ = 16 3. 24 × ⅙ = 4 5. 24 × ⅙ = 4 ውጤት 27 ይሆናል። ይህንን ክፍፍል ስላናካፍል በሒሣብ ሕግ ትንሹ የጋራ ብዜት የሆነውን 24 መሠረት አርገን ከፍተኛው የጋራ አካፋይ 27 ስናገኝ ለጎዶሎ መሙያ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ" ብለዋል፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 85 ሐዲስ 53 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ክፍፍልን ለሚገባቸው አካፍሉ"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَلْحِقُوا الْفَرَائِضَ بِأَهْلِهَا ይህ የውርስ ክፍፍል ለመጀመሪያ ጊዜ በተግባ የዋለው በሥስተኛው ኸሊፋው በዑመር አል ኽጧብ"ረ.ዐ." ጊዜ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የሶሓባዎች ኢጅማዕ"Consensus" አለበት፥ ይህ ደግሞ ከአል-ኺላፈቱ አር-ሯሺዳህ የተገኘ ሡናህ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ"፦ "የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል-ኺላፈቱ አር-ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ" ብለውናል፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 12 አል-ዒርባድ እደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእኔ በኃላ ከእናንተ ማንም ቢኖር እና ብዙ ልዩነት ቢያይ የእኔን ሡናህ እና የተመሩ የአል-ኺላፈቱ አር-ሯሺዳህ ሡናህ ተከተሉ! በእርሷም ያዙና በእርሷ ላይ አጥብቁ! መጤ ነገርን አስወግዱ! መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው"። فَقَالَ الْعِرْبَاضُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ... فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلاَفًا كَثِيرًا فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الْمَهْدِيِّينَ الرَّاشِدِينَ تَمَسَّكُوا بِهَا وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الأُمُورِ فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلاَلَةٌ ‏"‏ የአል ኺላፈቱ አር ሯሺዳህ ሡናህ ደግሞ በረሡል የተደገፈ ሡናህ እንጂ መጤ ቢድዓህ ስላልሆነ የጎደሎ ውርስ በኢሥቲእዋል ሕግ እንዲህ ይፈታል። በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን"ረሂመሁሏህ" የተዘጋጀ ኪታብ "ተስሒሉል ፈራኢድ" تسهيل الفرائض ተመልከቱ! “አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎ አምላካችን አሏህ ለአህሉል ኩፍር ሂዳያውን ይወፍቃቸው! ለእኛም ኢሥቲቃማውን ይወፍቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ ወሠላሙ ዐለይኩም

    Текст
    Просмотры624
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры608
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#2117Текст

አንኽ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ "ሒሮግልይፊኮስ" ἱερογλυφικός ማለት "ቅዱስ ቅርፅ" ማለት ሲሆን የግብፃውያን የፊደል ገበታ"Hieroglyphs" በድንጋይ ላይ አሊያም በደንገል"Papyrus" ላይ የተጻፈ ነው፥ ይህ የፊደል ገበታ ከ 3250 ቅድመ ልደት እስከ 400 ቅድመ ልደት የነበረ ሲሆን ከግብፃውያን የፊደል ገበታ አንዱ አንኽ"Ankh" ነው። በግብፃውያን "አንኽ" ꜥnḫ ማለት "ሕይወት" ማለት ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው፥ በግብፃውያን ሥነ ተረት ጥናት"Egyptian mythology" "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የተመሳቀለ መስቀል "ሆረስ" የተባለው አምላክ "ለዳግማዊ ራምሴ ንጉሥ የሰጠው ሕይወት ነው" ተብሎ ይታመናል። "ሆረስ" የተባለው ጣዖት የመራባት፣ የእርሻ፣ የሞት እና የትንሣኤ አምላክ ከተባለው "ኦስሪስ" አባቱ እና የኦስሪስ ሚስት ከሆነችው ሴት አምላክ "አይሲስ" እናቱ የተወለደ ነው" ተብሎ ይታመናል። "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ የእናትየው የአይሲስ የእጅ እንጥልጥ ነው፥ አንኽ በተለይ የግብፅ የሕይወት ምልክት እና ከሞት በኋላ ስለሚኖረው ሕይወት የሚያመለክት የጥንታዊ ግብጻውያን የጣዖት ምልክት ሲሆን የግብፃውያን አማልክት ብዙውን ጊዜ በቀኝ እጅ ይይዙት ነበር፡፡ "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ስርዋፅ ሆኖ የገባው በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት ሲሆን "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ በኃላ ላይ የአዲስ ኪዳን ብጥስጣሾች"Fragments" በሆኑት ደንገሎች ላይ ተጽፎ ይገኛል፥ ለምሳሌ፦ ደንገል 66 በ 150 ድኅረ ልደት ገደማ፣ ደንገል 45 በ 250 ድኅረ ልደት ገደማ እና ደንገል 75 250 ድኅረ ልደት ገደማ ልባሶቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት"Staurogram" ተደርጓል። ዋቢ ምንጭ ይመልከቱ፦ የብሪታኒካ መድብለ ዕውቀት(ኢንሳይክሎፔድያ) (1946)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 753 "ቶ" ምልክት ያለው አንኽ ወደ ክርስትና ሰርጎ ገብ በመሆን ዘው ብሎ ሲገባ በድርሳነ ዑራኤል፣ በፍካሬ ኢየሱስ፣ በራእየ ሲኖዳ፣ በራእየ ሳቤላ፣ በመጽሐፈ ምሥጢር እና በገድለ ፊቅጦር "ይመጣል" ተብሎ የሚጠበቀው "ቶ" የተባለው ንጉሥ "ቴዎድሮስ" ሲሆን ምልክቱ "ቶ" ነው። የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቁጥር 14 አንድምታ ላይ ስለ ቴዎድሮስ መምጣት ይመልከቱ! በግሪክ "ቴዎስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ድሮስ" δῶρος ማለት "ስጦታ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ቴዎ ድሮስ" θεό δῶρος ማለት "የአምላክ ስጦታ" ማለት ነው። በግሪክ ሥነ ተረት "ሲቡላ" Σίβυλλα መጻዒ ጊዜን የሚተነትን "ትንቢት" ሲሆን ግሪካውያን በግሪክ አማልክት መንፈስ፦ "ጥቁር ንጉሥ ከጥቁር አገር ይመጣል፥ ስሙም "ቴዎድሮስ" ነው" ብለው የተናገሩትን ምናባዊ ንጉሥ ነው፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ይህንን አስተምህሮት የቀየጠችው ከእነዚህ ዐረማዊ"Pagan" አስተምህሮት ነው። ፨ በመጀመር እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" አቆጣጠር ከ 1413 ድኅረ ልደት እስከ 1416 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የቀዳማዊ አጼ ዳዊት እና የንግሥት ጽዮን መንገሻ ልጅ "ወልደ አንበሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ቀዳማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው። ፨በመቀጠል እንደ ኢትዮጵያ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር ከ 1811 ድኅረ ልደት እስከ 1860 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የደጅ አዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ እና የአትጠገብ ወንድ ወሰን ልጅ "ካሳ ኃይሉ" በፈረስ ስሙ "አባ ታጠቅ" በወታደራዊ ስሙ "መይሳው ካሳ" እራሱ "ያ ይጠበቀው ቴዎድሮስ ነኝ" ብሎ ትንቢቱ ሳይሳካ የቀረው ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ነው። ፨ በመሠለስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ "ሣልሳዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ይመጣል፣ ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ ትሆናለች፣ የዓለም መንግሥታት በሙሉ ይታዘዙታል" ብለው ዛሬ ላይ ብዙኃኑ እየጠበቁ ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት እየሰማናቸው ካሉ የቆረፈዱ የምኞት ተረቶች መካከል "ቶ ንጉሥ የተባለ ኢትዮጵያን የሚገዛ ንጉሥ ይነግሣል" የሚለው ትርክት ከማኅበረ ቅዱሳን እስከ ፋኖ፣ ከጴጥሮሳውያን እስከ ሞዐ ተዋሕዶ፣ ከባልደራስ እስከ ኢትዮ 360 ያሉት ደሴታውያን የሚጠብቁት ይህንን ተስፋ ነው። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የ "ቶ" መስቀል እሳቤ ከግብፅ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ሲሆን የ "ቴዎድሮስ" እሳቤ ከግሪክ ሥነ ተረት የተወሰደ ከንቱ ዝንባሌ ነው። እናንተ እነዚህ እሳቦት የምታራምዱ፣ የምታቀንቅኑ እና የምታስቀነቅኑ ክርስቲያኖች ሆይ! ከእናንተ በፊት በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ፦ 5፥77 «እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ! በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትን እና ከቀጥተኛው መንገድ የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ አምላካችን አሏህ የየተሳሳቱን የዐረማዊ ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች ከመከተል ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም

Открыть в Telegram
Просмотры119−71%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч1
7 ч119
  1. Через 6 часов119
  2. Всего сейчас119
#2115Фото
Просмотры108−73%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч1
7 ч108
  1. Через 6 часов108
  2. Всего сейчас108
#2114Текст

ተውራት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያ እና ብርሃን ያለባት ስትሆን አወረድን። إِنَّآ أَنزَلْنَا ٱلتَّوْرَىٰةَ فِيهَا هُدًۭى وَنُورٌۭ ۚ "ተውራት" ‌تَوْرَات⁩ የሚለው የዐረቢኛ ቃል፣ "ቶራህ" תּוֹרָה የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ኡራይታህ" אוֹרַיְתָא⁩ የሚለው የዐረማይስጥ ቃል፣ ኦሪት" የሚለው የግዕዝ ቃል ትርጉሙ "ሕግ" "መርሕ" "መመሪያ" ማለት ነው፥ "ተውራህ" تَوْرَاة⁩ ተብሎ በታእ መርቡጧህ እና "ተውራት" ‌تَوْرَات⁩ ተብሎ በታእ መፍቱሓህ ሲመጣ ልክ እንደ "ኢምረኣህ" امْرَأَة እና "ኢምረአት" امْرَأَت ልዩነት የለውም። "ተውራት" تَوْرَاة⁩ የሚለው ቃል በቁርኣን ላይ 18 ጊዜ በ 16 አንቀጽ ላይ ተጠቅሶ ይገኛል፥ ተውራት አምላካችን አሏህ በነቢዩላህ ሙሣ ላይ ያወረደው ወሕይ ነው፦ 5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያ እና ብርሃን ያለባት ስትሆን አወረድን። إِنَّآ أَنزَلْنَا ٱلتَّوْرَىٰةَ فِيهَا هُدًۭى وَنُورٌۭ ۚ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 20 አል በራእ ኢብኑ ዓዚብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ከአይሁድ ዐዋቂዎች አንዱን ጠሩትና፦ "ተውራትን ለሙሣ ባወረደለት አምልሃለው" አሉት"። عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم دَعَا رَجُلاً مِنْ عُلَمَاءِ الْيَهُودِ فَقَالَ ‏ "‏ أَنْشُدُكَ بِاللَّهِ الَّذِي أَنْزَلَ التَّوْرَاةَ عَلَى مُوسَى ‏"‏ ‏.‏ "ተውራትን ለሙሣ ባወረደለት አምልሃለው" የሚለው ይሰመርበት! "ተውራት ለሙሣ አልተሰጠም" የሚል የድፍረት ቃል እንዴት ደፍራችሁ ተናገራችሁ? አምላካችን አሏህ ለሙሣ ተውራትን የሰጠው በመለኮታዊ እጁ ጽፎ ነው፥ አምላካችን አሏህ "ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼን እና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት" በማለት ይናገራል፦ 7፥145 ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼን እና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ مَّوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 106 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- "አደም እና ሙሣ ተከራከሩ፥ ሙሣም፦ "አደም ሆይ! አንተ አባታችን ነህ፥ አዋረድከን ከጀነትም አስወጣኸን" አለው። አደምም፦ ሙሣ ሆይ! አሏህ አንተን በቀጥታ በማናገሩ መርጦሀል እንዲሁ "ተውራትን በእጁ ጽፎ ሰጥቶአል"፡፡ ታዲያ አሏህ እኔን ከመፍጠሩ ከአርባ ዓመት በፊት ቀድሞ በወሰነብኝ ነገር ትወቅሰኛለህን? አለው፡፡ አደም ሙሳን ረታው። عَنْ أَبَا هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ احْتَجَّ آدَمُ وَمُوسَى فَقَالَ مُوسَى يَا آدَمُ أَنْتَ أَبُونَا خَيَّبْتَنَا وَأَخْرَجْتَنَا مِنَ الْجَنَّةِ ‏.‏ فَقَالَ آدَمُ أَنْتَ مُوسَى اصْطَفَاكَ اللَّهُ بِكَلاَمِهِ وَخَطَّ لَكَ التَّوْرَاةَ بِيَدِهِ تَلُومُنِي عَلَى أَمْرٍ قَدَّرَهُ عَلَىَّ قَبْلَ أَنْ يَخْلُقَنِي بِأَرْبَعِينَ سَنَةً فَحَجَّ آدَمُ مُوسَى ‏"‏ ‏ "ተውራትን በእጁ ጽፎ ሰጥቶአል" የሚለው ይሰመርበት! እንዲህ ዓይነት የድፍረት ጥግ አይቼ እና ሰምቼ አላውቅም። አምላካችን አሏህ ይህንን መጽሐፍ አሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ይመሩ ዘንድ ሰጠው፦ 11፥110 ለሙሣ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ 2፥87 ሙሣንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ 23፥49 ሙሣን ነገዶቹ ይመሩ ዘንድ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ لَعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ 17፥2 ሙሣንም መጽሐፉን ሰጠነው፡፡ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፡፡" ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ" አልናቸውም፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُوا مِن دُونِي وَكِيلًا ሆን ብላችሁ ፈሣድን ለምታስፋፉ ሙፍሢዲን አምላካችን አሏህ ሂዳያውን ይስጣችሁ! እኛንም ከሙፍሢድ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም

Открыть в Telegram
Просмотры320−21%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#2112Текст

ቁረይሾች ለሙታን ሐውልት ሠርተው "እርዱን" ብለው ኢሥቲጋሣህ ሲያደርጉ ትልቁ ሺርክ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት መቃረቢያ ይሆኑ ዘንድ ተወሡል በማድረግ ትንሹ ሺርክ ውስጥ ተዘፍቀው ነበር፦ 46፥28 እነዚያም መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርገው የያዙዋቸው አይረዷቸውም ኖሯልን? በእርግጥ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ይህም ውሸታቸው እና በልማድ ይቀጥፉት የነበሩት ነው፡፡ فَلَوْلَا نَصَرَهُمُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ قُرْبَانًا آلِهَةً ۖ بَلْ ضَلُّوا عَنْهُمْ ۚ وَذَٰلِكَ إِفْكُهُمْ وَمَا كَانُوا يَفْتَرُونَ ስለዚህ "በእከሌ ይሁንብክ" በእከሊት ይሁንብክ" ብሎ በሙታን ሆነ በሕያዋን ሰዎች መመጀን ቢድዓህ ሲሆን ትንሹ ሺርክ ነው፥ ገፋ ካለ ግን ወደ ሙታን ሰዎች ኢሥቲጋሳህ ማድረግ ነውና ትልቁ ሺርክ ነው። ምክንያቱም ቁረይሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን እና የማይጠቅማቸውን ረዳቶች የያዙት ወደ አሏህ ማቃረብን እንዲያቃሩባቸው ነው፥ «እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» አሉ፦ 39፥3 እነዚያም ከእርሱ ከአሏህ ሌላ ረዳቶች የያዙት «ወደ አሏህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጂ ለሌላ አናመልካቸውም» ይላሉ፡፡ وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَا إِلَى اللَّهِ زُلْفَىٰ 10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን እና የማይጠቅማቸውን ያመልካሉ፡፡ «እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አሏህን በሰማያት እና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ "አሏህ ዘንድ በምልጃቸው ያቃርቡናል" ብለው ከተወሡል አልፈው ኢሥቲጋሳህ ሲያረጉ ያመልኳቸዋል። አሏህን በሰማያት እና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ስለሌለ አሏህ ቅርብ ነው፥ የለማኝን ጸሎት በለመነው ጊዜ ይቀበለዋል። ከአሏህ ሌላ የሚጠሩት ሙታን የእኛ ቢጤ ሲሆኑ ለአሏህ ባሮች ናቸው፥ ብንጠራቸው አይሰሙም፦ 2፥186 ባሮቼም ስለ እኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ 7፥194 እነዚያ ከአሏህ ሌላ የምትጠሯቸው ብጤዎቻችሁ ባሮች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ እስቲ ይመልሱላችሁ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ ሙታንን ኢሥቲጋሳህ ከሚደረግ ከሺርኩል አክበር እና በሙታን ተወሡል በማድረግ ከሚደረግ ከሺርኩል አስገር አሏህ ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ ጥሪያችን Tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም

Открыть в Telegram
Просмотры353−13%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#2111Текст

ተወሡል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ወደ እርሱ መቃረቢያን መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ "ተወሡል" تَوَسُّل የሚለው ቃል "ተወሠለ" تَوَسَّلَ ማለትም "ተቃረበ" "ተገናኘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መቃረቢያ" "መገናኛ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "መገናኛ ብዙኃን"Social media" እራሱ "አት ተዋሡል ኢጅቲማዒይ" التَّوَاصُل الْاِجْتِمَاعِيّ ይባላል። አምላካችን አሏህ ስለ ተወሡል እንዲህ ይለናል፦ 5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ወደ እርሱ "መቃረቢያን" መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ እዚህ አንቀጽ ላይ "መቃረቢያ" ለሚለው የገባው ቃል "ወሢላህ" وَسِيلَة ሲሆን ይህ መቃረቢያ ከኢማን በኃላ የሚሠራ "መልካም ሥራ" እንደሆነ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል። ለምሳሌ፦ ሶደቃህ መሶደቅ አሏህ ዘንድ መቃረቢያ ነው፦ 9፥99 ከአዕራቦች በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውን ምጽዋቶች አሏህ ዘንድ መቃረቢያዎች እና ወደ መልእክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አለ፡፡ ንቁ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ "አቃራቢ" ናት፡፡ وَمِنَ الْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَاتٍ عِندَ اللَّهِ وَصَلَوَاتِ الرَّسُولِ ۚ أَلَا إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ "ንቁ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ "አቃራቢ" ናት" የሚለው ይሰመርበት! ሶደቃህ አሏህ ዘንድ መቃረቢያ እና የመልእክተኛው ጸሎቶች መዳረሻም ነው። አምላካችን አሏህ በቁርኣን የገለጻቸው የተዋቡ ስሞች አሉት፥ በስሞቹ ተወሡል እንድናረግ ነግሮናል፦ 7፥180 ለአሏህ መልካም ስሞች አሉት፡፡ በእርሷም ጥሩት፡፡ وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَ እዚህ አንቀጽ ላይ "ጥሩት" ለሚለው የገባው ቃል "ኢድዑ-ሁ" ادْعُوهُ ሲሆን "ዱዓእ" دُعَآء በእርሱ ስሞች ማድረግ ተወሡል ነው። ወደ አሏህ ለመቃረብ አንድ በሕይወት ያለ ሙእሚንን "ዱዓእ አርግልኝ" ብሎ ማለት እራሱ ተወሡል ነው፦ 9፥103 ለእነሱም ጸልይላቸው! ጸሎትህ ለእነርሱ እርጋታ ነውና፥ አሏህ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ وَصَلِّ عَلَيْهِمْ ۖ إِنَّ صَلَاتَكَ سَكَنٌ لَّهُمْ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 5 አነሥ እንደተረከው፦ "ሰዎች ድርቅ በገጠማቸው ጊዜ ዑመር ኢብኑ ኸጣብ"ረ.ዐ." በአል ዐባሥ ኢብኑ ዐብዲል ሙጦሊብ ይቃረብ ነበር፥ "አሏህ ሆይ! ቀድሞ በነብያችን"ﷺ" ምክንያት ወደ አንተ "እንቃረብ" እና ታጠጣን ነበር፥ አሁን ደግሞ በነብያችን"ﷺ" አጎት ምክንያት ወደ አንተ "እንቃረባለንና" አጠጣን" ይል ነበር"። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ ـ رضى الله عنه ـ كَانَ إِذَا قَحَطُوا اسْتَسْقَى بِالْعَبَّاسِ بْنِ عَبْدِ الْمُطَّلِبِ فَقَالَ اللَّهُمَّ إِنَّا كُنَّا نَتَوَسَّلُ إِلَيْكَ بِنَبِيِّنَا فَتَسْقِينَا وَإِنَّا نَتَوَسَّلُ إِلَيْكَ بِعَمِّ نَبِيِّنَا فَاسْقِنَا‏.‏ "ቢ" بِ የምትባለው "ባ ሠበቢያህ" بَا سَبَبِيَّة ስትሆን "ምክንያት"Because" ማለት ናት፥ ለምሳሌ፦ "ቢ-"ኢማኒሂም" بِإِيمَانِهِمْ ማለት "በእምነታቸው ምክንያት" ማለት ሲሆን "ቢ" بِ እዚህ ላይ ምክንያት ናት፦ 10፥9 እነዚያ ያመኑ እና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው "በእምነታቸው ምክንያት" የገነትን መንገድ ይመራቸዋል፥ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ يَهْدِيهِمْ رَبُّهُم بِإِيمَانِهِمْ ۖ تَجْرِي مِن تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ "በእምነታቸው ምክንያት" የሚለው ይሰመርበት! ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ቢ-ነቢይና" بِنَبِيِّنَا ማለት "በነቢያችን ምክንያት" ማለት ነው። እዚህ ሐዲስ ላይ "እንቃረብ" ለሚለው የገባው ቃል "ነተወሠሉ" نَتَوَسَّلُ ሲሆን ነብያችን"ﷺ" በሕይወት እያሉ "ዱዓእ አርጉሉን" ብለው ተወሡል ያረጉ እንደነበር እና ከሞቱ በኃላ ግን በሕይወት ባለው በነብያችን"ﷺ" አጎት ይዋሠሉ እንደነበር እሙን እና ቅቡል ነው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን እሳቸው ከሞቱ በኃላ በእርሳቸው ተወሡል አለመደረጉ በራሱ በሞቱ የአሏህ ደጋግ ባሮች ተወሡል ማድረግ ቢድዓህ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። በመልካም ሥራ፣ በአሏህ ስም እና "ዱዓእ አርጉልን" በማለት በሕይወት ባሉ ደጋግ የአሏህ ባሮች ወደ አሏህ መቃረብ የሚቻል ሲሆን ነገር ግን በሞቱ የአሏህ ደጋግ ባሮችን "በእከሌ ይሁንብክ" ብሎ አሏህን መለመን ሆነ እነርሱን "ዱዓእ አርጉልን" "ድረሱልን" "እርዱን" ማለት ክልክል ነው፦ 17፥56 «እነዚያን ከእርሱ ሌላ የምትሏቸውን ጥሩ! ከእናንተ ላይ ጉዳትን ማስወገድን አይችሉም» በላቸው። قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِهِ فَلَا يَمْلِكُونَ كَشْفَ الضُّرِّ عَنكُمْ وَلَا تَحْوِيلًا እዚህ አንቀጽ ላይ "ጥሩ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢድዑ" ادْعُوا ሲሆን ከአሏህ ሌላ ወደ ሆኑ ማንነት ሆነ ምንነት ዱዓእ ቢደረግ ከእናንተ ላይ ጉዳትን ማስወገድን አይችሉም፥ እነዚያ እነርሱ የሚጠሯቸው ማንኛቸውም ወደ አሏህ መቃረቢያን ሥራን ይፈልጋሉ፦ 17፥57 እነዚያ እነርሱ የሚጠሯቸው ማንኛቸውም ወደ አሏህ በጣም ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን ሥራን ይፈልጋሉ፣ እዝነቱን ይከጅላሉ፣ ቅጣቱንም ይፈራሉ። የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ يَدْعُونَ يَبْتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ الْوَسِيلَةَ أَيُّهُمْ أَقْرَبُ وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ ۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحْذُورًا ወደ አሏህ መቃረቢያን ሥራን የሚፈልጉን አካላትን በገይብ መጥራት አምልኮ ሲሆን በሞቱ የአሏህ ደጋግ ባሮች ተወሡል ማድረግ "ሺርኩል አክበር" ሳይሆን "ሺርኩል አስገር" ነው፥ "ሺርኩል አክበር" شِرْك الأَكْبَرْ ማለት ከኢሥላም አጥር የሚያስወጣ "ትልቁ ማጋራት" ሲሆን "ሺርኩል አስገር" شِرْك الأَصْغَر ማለት ደግሞ ከኢሥላም አጥር የማያስወጣ "ትንሹ ማጋራት" ማለት ነው።

Открыть в Telegram
Просмотры306−24%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#2109Текст

ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4298 አቢ አድ-ደርዳእ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው"። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ فُسْطَاطَ الْمُسْلِمِينَ يَوْمَ الْمَلْحَمَةِ بِالْغُوطَةِ إِلَى جَانِبِ مَدِينَةٍ يُقَالُ لَهَا دِمَشْقُ مِنْ خَيْرِ مَدَائِنِ الشَّامِ ‏"‏ "ዲመሽቅ" دِمَشْق ማለት "ደማስቆ" ማለት ነው፥ "ጉጧህ" غُوطَة የሻም ደቡብ ምዕራብ ክፍል ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በሐዲሳቸው አሏህ ለዒሣ፦ "ከባሮቼ ውስጥ ማንም ሊዋጋላቸው የማይችለውን ሰዎች አውጥቻለሁና እነዚህን ሰዎች በደህና ወደ ተራራው ውሰዳቸው" እንደሚለው ተናግረዋል፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 134 አሏህ ለዒሣ፦ "ከባሮቼ ውስጥ ማንም ሊዋጋላቸው የማይችለውን ሰዎች አውጥቻለሁና እነዚህን ሰዎች በደህና ወደ ተራራው ውሰዳቸው" ይለዋል"። أَوْحَى اللَّهُ إِلَى عِيسَى إِنِّي قَدْ أَخْرَجْتُ عِبَادًا لِي لاَ يَدَانِ لأَحَدٍ بِقِتَالِهِمْ فَحَرِّزْ عِبَادِي إِلَى الطُّورِ የአሏህ ባሮች ከመሢሑ ጋር ወደ ተራራ መሰብሰባቸው ንጥቀት ነው፥ ይህ ነጥብ ኢሥላማዊ የዘመኑ ፍጻሜ ጥናትን"Islamic Eschatology" ዋቢ እና ታሳቢ ያደረገ ነጥብ ነው። አምላካችን አሏህ ከደጃል ፊትናህ ይጠብቀን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/tiriyachen ወሠላሙ ዐለይኩም

Открыть в Telegram
Просмотры460+14%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#2108Текст

ንጥቀት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 43፥61 እርሱም ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው፡፡ «በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِنَّهُ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَاتَّبِعُونِ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ "ሐርፓዞ" ἁρπάζω ማለት "ወሰደ" "ነጠቀ" ማለት ሲሆን "ንጥቀት"Rapture" ማለት ደግሞ "ውስደት" ማለት ነው፥ "መነጠቅ" ማለት "መወሰድ" ማለት ነው፦ ምሳሌ 2፥22 ኃጥኣን ግን ከምድር ይጠፋሉ፥ ዓመፀኞችም ከእርስዋ "ይነጠቃሉ"። ὁδοὶ ἀσεβῶν ἐκ γῆς ὀλοῦνται, οἱ δὲ παράνομοι ἐξωσθήσονται ἀπ᾿ αὐτῆς. "ይነጠቃሉ" ማለት "ይወሰዳሉ" ማለት ነው፥ ዓመፀኞች ከምድር "ይነጠቃሉ" ሲባል "ይወሰዳሉ" በሚል ከተረዳነው ዘንዳ መሢሑ ሲመጣ ሁለት ዓይነት ሰዎች በዚህ ዓለም ይሆናሉ፥ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል፦ ሉቃስ 17፥36 ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፥ አንዱ ይወሰዳል ሁለተኛውም ይቀራል። "እርሻው" ይህ ዓለም ነው፥ ማቴዎስ 13፥38 ተመልከት! እንደ ንስር አስተዋይ የሆኑ ሰዎች ወደ መሢሑ ይሰበሰባሉ፦ ሉቃስ 17፥37 መልሰውም፦ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፦ “አካል ወዳለበት በዚያ ንስሮች ይሰበሰባሉ" አላቸው። καὶ ἀποκριθέντες λέγουσιν αὐτῷ Ποῦ, Κύριε; ὁ δὲ εἶπεν αὐτοῖς Ὅπου τὸ σῶμα, ἐκεῖ καὶ οἱ ἀετοὶ ἐπισυναχθήσονται. መሰብሰቡ የሚሆነው መቼ ነው? መሰብሰቡ የሚሆነው ኢየሱስ ከመጣ በኃላ ነው፦ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፥1 ወንድሞች ሆይ! ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት እና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን እንለምናችኋለን። Ἐρωτῶμεν δὲ ὑμᾶς, ἀδελφοί, ὑπὲρ τῆς παρουσίας τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ καὶ ἡμῶν ἐπισυναγωγῆς ἐπ’ αὐτόν, 2ኛ ተሰሎንቄ 2፥2 በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት፦ “የጌታ ቀን ደርሶአል” ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም። εἰς τὸ μὴ ταχέως σαλευθῆναι ὑμᾶς ἀπὸ τοῦ νοὸς μηδὲ θροεῖσθαι μήτε διὰ πνεύματος μήτε διὰ λόγου μήτε δι’ ἐπιστολῆς ὡς δι’ ἡμῶν, ὡς ὅτι ἐνέστηκεν ἡ ἡμέρα τοῦ Κυρίου. የጌታ ቀን ከመድረሱ እና መሢሑ መጥቶ ከመሰብሰብ በፊት የጥፋት ልጅ ሐሣዌ መሢሕ"False Christ" ይመጣል፦ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፥3 ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና። የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ የጌታ ቀን አይደርስምና፥ ስለዚህ "የጌታ ቀን ደርሶአል" ብለው "ከሐሣዌ መሢሕ በፊት ንጥቀት አለ" የሚለው የፕሮቴስታንት ዘለሰኛ ትምህርት ድባቅ ገብቷል። ምክንያቱም መወሰዱ ወደ እርሱ ለመሰብሰብ ነው፦ 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥17 ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና "እንነጠቃለን"። ἁρπαγησόμεθα ἐν νεφέλαις εἰς ἀπάντησιν τοῦ Κυρίου εἰς ἀέρα· እርሱ የሚመጣው ከሰማይ ወደ ምድር ነው፥ "ኢየሱስ ከሐሣዌ መሢሕ በፊት መጥቶ ይወስደናል" የሚል ቂል ክርስቲያን መጽሐፉን በቅጡ እና በአግባብ ያላነበበ ነው። የፕሮቴስንታት አክራሪ ክርስቲያን"Christian Fundamentalist" የንጥቀት ትምህርት እንደ ጎርጎሮሳውያን"Gregorian" አቆጣጠር በ 1830 ድኅረ ልደት የተጀመረ ሲሆን ይህ የንጥቀት ትምህርት፦ "ቅድመ መከራዊ ንጥቀት"Pre Tribulational Rapture"፣ "መሀል መከራዊ ንጥቀት"Mid Tribulational Rapture"፣ "ድኅረ መከራዊ ንጥቀት"Post Tribulational Rapture" ተብሎ ለሦስት ይከፈላል። ፨ "ቅድመ መከራዊ ንጥቀት" ማለት "ከመከራው በፊት እና በመከራው ጊዜ ከሚመጣው ሐሣዌ መሢሕ በፊት ንጥቀት አለ" ብሎ የሚታመንበት ትምህርት ነው። ፨ "መሀል መከራዊ ንጥቀት" ማለት "በመከራው አጋማሽ ላይ ንጥቀት አለ" ብሎ የሚታመንበት ትምህርት ነው። ፨ "ድኅረ መከራዊ ንጥቀት" ማለት "ከመከራው በኃላ እና በመከራው ጊዜ ከሚመጣው ሐሣዌ መሢሕ በኃላ ንጥቀት አለ" ብሎ የሚታመንበት ትምህርት ነው። ታላቁ መከራ ማለት ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ነው፦ ማቴዎስ 24፥21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና። እኛ ሙሥሊሞች የጳውሎስን ንግግር ለእኛ መረጃ ለክርስቲያኖች ማስረጃ አርገን እንጠቀምበታለን እንጂ በጳውሎስ ሆነ በንግግሩ አናምንም፥ መለኮታዊ ቅሪት በኦሪት እና በወንጌል እንጂ በጳውሎስ ደብዳቤዎች ውስጥ የለም። በዲኑል ኢሥላም አል መሢሕ ዒሣ ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው፥ ሰዓቲቱ የትንሣኤ ቀን ስትሆን ያ ቀን መቃረቡ የዒሣ መምጣት ነው፦ 43፥61 እርሱም ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው፡፡ «በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِنَّهُ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَاتَّبِعُونِ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ "ታላቁ መከራ" በዲኑል ኢሥላም የመሢሑ ምጽአታዊ ትንቢት"Apocalyptic Prophecy" ውስጥ "አል መልሐመቱል ኩብራ" المَلْحَمَة الكُبْرَى ሲባል ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ታረጋለች፥ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ባደረገች ጊዜ ሐሳዌ መሢሕ ይመጣል፦ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4 ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በይቱል መቅዲሥ ሲለመልም የስሪብ ፍርስራሽ ትሆናለች፣ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል፣ ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ታረጋለች፣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ባደረገች ጊዜ አል ደጃል ይመጣል"። عَنْ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ عُمْرَانُ بَيْتِ الْمَقْدِسِ خَرَابُ يَثْرِبَ وَخَرَابُ يَثْرِبَ خُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ وَخُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ فَتْحُ قُسْطَنْطِينِيَّةَ وَفَتْحُ الْقُسْطَنْطِينِيَّةِ خُرُوجُ الدَّجَّالِ ‏"‏ "የስሪብ" يَثْرِب የመዲና ጥንታዊ ስም ነው፥ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። "ቁሥጦንጢኒያህ" قُسْطَنْطِينِيَّة ማለት "ቆስጠንጢኒያ"Constantinople" ማለት ነው፥ ቆስጠንጢኒያ ከ 306 እስከ 337 ድኅረ ልደት ሲገዛ በነበረው በሮሙ ቄሳር በቆስጠንጢኖስ ስም የተሰየመችው የአሁኗ ቱርክ ናት። በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው፦

Открыть в Telegram
Просмотры364−10%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи