Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 42 |
| 5 ч | 48 |
- Через 6 часов48
- Всего сейчас48

እኔ #በእግዚአብሔር_ፊት የምቆመው #ገብርኤል_ነኝ በቻናላናችን የሚሰጡ መንፈሳዊ ትምህርቶች መንፈሳዊ ምክሮች መንፈሳዊ መዝሙር መንፈሳዊ ጥያቄዎች መንፈሳዊ ስዕልዎች በየለቱ ስንክሳር
28 нояб. – 29 нояб.−2 (−0,1%)
| Дата | Подписчики |
|---|---|
| 28 нояб. 2026 г. | 3 590 |
| 29 нояб. 2026 г. | 3 588 |
По дню публикации
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 26 нояб. 2026 г. | 287 |
| 27 нояб. 2026 г. | 266 |
| 28 нояб. 2026 г. | 151 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 42 |
| 5 ч | 48 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 40 |
| 5 ч | 44 |
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞ [ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ] 🕊 † ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት † 🕊 በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች:: ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ [የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው] በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው:: ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር:: በዛው ልክ ደግሞ ገና በ፳ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል በውበቱም ደመ ግቡ በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል:: ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን [የጠላት] ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል:: የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው:: አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ፳፬ ክንድ ነበር:: ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው:: ክርስቶስ ተክዶ ጣዖት ቁሞ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው የክርስቲያኖች ደም ፈሶ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ:: ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ :- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት:: በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ:: በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን የጻፈ ያጻፈ ያነበበ ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል:: 🕊 † ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ † 🕊 ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ፶ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል:: ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ [አንያኑ] ይባላል:: ጣዖት አምላኪ ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው [መስፊያው] ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ [አታኦስ]" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር:: ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው:: ወዲያውም ደሙ ቁሞ ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው:: አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው:: ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ፷ ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት አድርጐ ሾመው:: ቅዱስ አንያኖስም ለ፲፪ ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ:: የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ ፻፲፰ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ ፻፲፯ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት:: አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት ፪. ቅዱስ አንያኖስ [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ ፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ ፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና ፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት " በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" [፩ዼጥ.፫፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 41 |
| 5 ч | 46 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 30 |
| 4 ч | 123 |
| 6 ч | 144 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 31 |
| 4 ч | 124 |
| 6 ч | 140 |
🕊 💖 🕊 [ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ] 🍒 🍒 [ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ] [ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ] 🌸 ♱ 🌸 [ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ] [ ክፍል አስር ] 💛 ድንቅ ትምህርት 💛 [ በመምህራችን ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] 🍒 🍒 ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ] 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊 👇
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 32 |
| 4 ч | 126 |
| 6 ч | 141 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 95 |
| 6 ч | 165 |
| 9 ч | 210 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 94 |
| 6 ч | 157 |
| 9 ч | 202 |
🍒 † 🍒 💖 [ ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ! ] 💖 🕊 💖 🕊 ❝ ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል ፥ ሕያውም ያደርገዋል ፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም። እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል ፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።❞ [መዝ.፵፩፥፩ ] 🌸 ♱ 🌸 ❝ እግዚአብሔር ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ አወቅሁ። ❞ [ መዝ.፻፵፥፲፪ ] 🌸 ♱ 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 89 |
| 6 ч | 155 |
| 9 ч | 203 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 90 |
| 5 ч | 138 |
| 8 ч | 181 |
የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት@ewketbirhanРелигия3,56 тыс.
የጎ/ሕ/ጤ/ሳ/ኮ ግቢ ጉባኤ /GC_GG@gc_gibigubaeРелигия3,53 тыс.
Tiriyachen | ጥሪያችን@tiriyachenРелигия3,69 тыс.
AS-HABULE YEMINE@ashabuleyamineРелигия3,49 тыс.
www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn@hawaztegegnРелигия3,71 тыс.
BibleProject - Amharic/አማርኛ@bibleprojectamharicРелигия3,45 тыс.
ፍሬ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት@frehaymanotssРелигия3,43 тыс.
አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ@christian930Религия3,79 тыс.