Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 42 |
| 5 ч | 48 |
- Через 6 часов48
- Всего сейчас48
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 42 |
| 5 ч | 48 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 40 |
| 5 ч | 44 |
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞ [ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ] 🕊 † ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት † 🕊 በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች:: ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ [የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው] በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው:: ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር:: በዛው ልክ ደግሞ ገና በ፳ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል በውበቱም ደመ ግቡ በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል:: ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን [የጠላት] ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል:: የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው:: አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ፳፬ ክንድ ነበር:: ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው:: ክርስቶስ ተክዶ ጣዖት ቁሞ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው የክርስቲያኖች ደም ፈሶ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ:: ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ :- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት:: በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ:: በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን የጻፈ ያጻፈ ያነበበ ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል:: 🕊 † ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ † 🕊 ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ፶ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል:: ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ [አንያኑ] ይባላል:: ጣዖት አምላኪ ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው [መስፊያው] ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ [አታኦስ]" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር:: ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው:: ወዲያውም ደሙ ቁሞ ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው:: አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው:: ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ፷ ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት አድርጐ ሾመው:: ቅዱስ አንያኖስም ለ፲፪ ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ:: የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ ፻፲፰ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ ፻፲፯ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት:: አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት ፪. ቅዱስ አንያኖስ [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ ፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ ፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና ፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት " በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" [፩ዼጥ.፫፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 41 |
| 5 ч | 46 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 30 |
| 4 ч | 123 |
| 6 ч | 144 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 31 |
| 4 ч | 124 |
| 6 ч | 140 |
🕊 💖 🕊 [ 🕊 ድምፀ ተዋሕዶ 🕊 ] 🍒 🍒 [ ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ። ] [ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ] 🌸 ♱ 🌸 [ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ] [ ክፍል አስር ] 💛 ድንቅ ትምህርት 💛 [ በመምህራችን ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] 🍒 🍒 ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ] 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊 👇
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 32 |
| 4 ч | 126 |
| 6 ч | 141 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 95 |
| 6 ч | 165 |
| 9 ч | 210 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 94 |
| 6 ч | 157 |
| 9 ч | 202 |
🍒 † 🍒 💖 [ ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ! ] 💖 🕊 💖 🕊 ❝ ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል ፥ ሕያውም ያደርገዋል ፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም። እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል ፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።❞ [መዝ.፵፩፥፩ ] 🌸 ♱ 🌸 ❝ እግዚአብሔር ለድሀ ዳኝነትን ለችግረኛም ፍርድን እንዲያደርግ አወቅሁ። ❞ [ መዝ.፻፵፥፲፪ ] 🌸 ♱ 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 89 |
| 6 ч | 155 |
| 9 ч | 203 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 90 |
| 5 ч | 138 |
| 8 ч | 181 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 87 |
| 5 ч | 132 |
| 8 ч | 174 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 88 |
| 5 ч | 133 |
| 8 ч | 176 |
🕊 💖 🕊 🩵 [ መዝሙረ ተዋሕዶ ] 🩵 🕊 💖 🕊 ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ንጹሕና የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሐሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በእናትነቷና በምልጃዋ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ያስተምረናል ፥ ፈሪሐ እግዚአብሔርንና ያጎናጽፈናል፡፡ 🕊 💖 🕊 ❝ ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። ❞ [ዳን.፱፥፳፩] ❝ በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ፥ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። ❞ [ዘጸ.፳፫፥፳] 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 3 ч | 92 |
| 5 ч | 142 |
| 8 ч | 194 |
#መልክአ_ገብርኤል #የአሸናፊና የኃይል መልአክ #ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ከፍጹም ጥፋት እድን ዘንድ ክንፍህን ጋርድልኝ። #ወደ_ድንግል የተላክ #ገብርኤል_ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ ምስራች ተናጋሪ #ገብርኤል1ሆይ፤ ሰላም ላንተ ይሁን። ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ አብሳሪ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የአካላዊ ቃልን የመጸነስ ብሥራት በማኀፀነ ማርያም ላሳደርክ ሰላም ላንተ ይሁን። #በመላአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ #ገብርኤል_ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን አሜን። #_ሰናይ___ቀን🙏 አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች •➢ 👇 ለማግኘት // 👇 @Enatachn_mareyam @Enatachn_mareyam
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 110 |
| 7 ч | 215 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 7 ч | 94 |
| 24 ч | 313 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 7 ч | 95 |
| 24 ч | 305 |
🕊 [ † እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊 † ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ † 🕊 † ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል:: እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ [ሰርግዮስ] ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር:: ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና:: በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው:: ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ:: ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ:: ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ:: በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት:: መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት ፬ [4] ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት:: ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት:: ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ፮ ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል:: 🕊 † ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ † 🕊 † ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል:: በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት:: ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና ፭ ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን [መታሠሩን] ሰማች:: ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ:: ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው:: ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ፭ ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ:: † አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት ፪. ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት ፫. ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ [የቅዱሱ ሚስትና ልጅ] ፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ [ልደቱ] [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ ፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ ፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም ፮. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ † "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" † [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 7 ч | 95 |
| 24 ч | 337 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 10 ч | 185 |
| 27 ч | 298 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 10 ч | 184 |
| 27 ч | 298 |
🕊 💖 🕊 🩵 [ ምክረ ቅዱሳን ] 🩵 ▷ " ኃይልህ የት ሄደ ! " [ 🍒 በቅዱሳን አባቶች አስተምህሮ 🍒 ] 🌸 ♱ 🌸 -▷ ❝ ጥበብን አግኝ ፤ ማስተዋልን አግኝ ፤ አትርሳም ፥ ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል። አትተዋት ፥ ትደግፍህማለች ፤ ውደዳት ፥ ትጠብቅህማለች። ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ከፍ ከፍ አድርጋት ፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች ፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። ❞ [ ምሳ.፬፥፭ ] « የተዘረገፈ ወንዝና የጠፋ ትኩረት ! 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊 👇
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 10 ч | 184 |
| 27 ч | 317 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 11 ч | 161 |
| 25 ч | 273 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 11 ч | 159 |
| 25 ч | 278 |
🍒 🍒 💖 [ የትዕቢት መጀመሪያ ! ] 💖 🕊 🕊 የትዕቢት መጀመሪያ [ ሲራክ.፲፥፲፪ ] ❝ ልጆቼ ! እንዲያውም ትዕቢት ከዝሙት ወይም ከማመንዘር በላይ እኛን ያቆሽሻል፡፡ ለምን ? ያላችሁኝ እንደ ኾነም ምንም እንኳን ዝሙት ንስሐ ካልገቡበት ሥርየተ ኃጢአት የሌለው በደል ቢሆንም በዝሙት የቆሸሸ ሰው ንስሐ ለመግባት ቅርብ ነው። በትዕቢት የታመመ ሰው ግን እንዲህ እንደ ዘማዊው ያለ ዓቅምን አያገኝም፡፡ ስለዚህ ትዕቢት እጅግ አደገኛ ደዌ ዘነፍስ ነው ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡ ከትዕቢተኛ ሰው በላይ ጎስቋላ ሰው የለም፡፡ የፈለገ ያህልም ብዕል [ ሀብት ] ፣ የዚህን ዓለም ዕውቀት ቢኖረውም ከትዕቢተኛ ሰው የባሰ ጎስቋላ ሰው የለም፡፡ በንግሥና ወንበር ቢቀመጥ ፣ በሰዎች ዘንድ እጅግ "የተከበረ" ቢኾንም ከዚህ ሰው በላይ ጎስቋላ ሰው የለም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፡፡ እስኪ ንገሩኝ ! የዚህን ከንቱ ደግሞም ሐላፊና ጠፊ ዓለምን ነገር ይዞ ከመታበይ በላይ ምን አላዋቂነት አለ? ነገ የሚጠወልገውን የመስከረም አደይ አበባን [የዚህ ዓለም ክብር] ይዞ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ነው ጎስቋላ? ሕልምን ይዞ እውኑን ዓለም ከሚያጣ ከዚህ ሰው በላይ ማን ጎስቋላ ሰው አለ ልትሉኝ ትችላላችሁ? አሁን በወርቅ አልጋ ላይ ስለተኛ ከሚታበይ ሰው [ በኋላ ግን እንደ ነዌ ከሚለምን ሰው ] በላይ ማን ድኻ አለ ልትሉኝ ትችላላችሁ? ❞ [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ] 🌸 ♱ 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 19 ч | 250 |
| 27 ч | 309 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 19 ч | 248 |
| 27 ч | 300 |
🕊 🌺 🕊 💛 [ 💖 ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ 💖 ] 💛 🕊 🌺 🕊 ❝ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ ፣ ቶማስና ማቴዎስ ፣ ታዴዎስና ናትናኤል ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ ፲፪ ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ❞ 🌸 ♱ 🌸 ❝ † አቤቱ በስምኽ የሰበኩ ፤ በታላቅ መከራ በረኀብና በጥም ፤ በብርድና በመራቆት ፤ በመውዛትና በመድከም ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ዘንድ ተፈርዶባቸው መከራን በመቀበል በምድር ኹሉ ውስጥ የቃልኽን መዝገብ ስለዘሩ ስለነዚኽ ደቀ መዛሙርትኽ ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ በእሳት በመከራ የተቀበለ አለ ፤ በጦርም የተወጋ አለ ፤ በሰይፍም የተቆረጠ አለ ፤ በመንኰራኲርም የተፈጨ አለ ፤ በደንጊያም የተወገረ ፤ በበትርም የተቀጠቀጠ አለ ፤ ስለነርሱ ብለኽ ማረኝ አስበኝም ፤ ስለሥቃያቸው ስለመቸገራቸውና ስለደማቸው ብለኽ የእኔን የአገልጋይኽን የዕዳ መጽሐፌን ቅደድ ፤ አሜን። ❞ † [ ተአምኆ ቅዱሳን ] 🕊 💖 🕊 [ እንኩዋን ለሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ] ምልጃውና ጸሎቱ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: † 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 19 ч | 247 |
| 27 ч | 299 |
፪ቱ ቅዱሳት አብረው እየዋሉ: አብረው እያደሩ በጾምና በጸሎት ቢጠመዱ ድንግል ማርያም እመቤታችን ተገለጠችላቸው:: ከልጇ ዘንድ አቅርባም አስባረከቻቸው:: ይህ ሁሉ ሲሆን የቅድስት አጥራስስ አባት ንጉሡ በሃገር አልነበረም:: ሲመለስ ግን የሆነውን ሁሉ አወቀ:: ሕዝቡን ሰብስቦ በአንዲት ልጁ አጥራስስና በወዳጇ ዮና ላይ በእሳት እንዲሞቱ ፈረደባቸው:: እሳቱ ብዙ እጥፍ ነዶ ሕዝቡ ሲያለቅስላቸው ፪ቱ ደናግል እርስ በርስ ተቃቅፈው ተሳሳሙ:: እየጸለዩም ወደ እሳቱ ተወረወሩ:: በዚያም ለፈጣሪያቸው ነፍሳቸውን ሰጡ:: እሳቱ ግን ልብሳቸውን እንኩዋ አላቀነበረውም:: አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ ሲል ቸርነቱን: ምሕረቱን ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ] ፪. ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ እንትያ [ሰማዕታት] ፫. ቅዱሳት ደናግል አጥራስስ ወዮና [ሰማዕታት] ፬. ቅዱስ አትናቴዎስ የዋሕ [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን ፪. አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ ፫. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ ፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ አርድእት] " እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር:: ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ:: አይታችሁትማል አለው:: ፊልዾስ :- 'ጌታ ሆይ ! አብን አሳየንና ይበቃናል' አለው:: ጌታ ኢየሱስም አለው :- 'አንተ ፊልዾስ ! ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል:: እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ: አብም በእኔ እንዳለ አመታምንምን?" [ዮሐ.፲፬፥፯] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
Открыть в Telegram🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ [ ✞ እንኩዋን ለቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ: ለቅዱስ ኤላውትሮስ እና ለደናግል አጥራስስ ወዮና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ] 🕊 † ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ † 🕊 እንደ አባቶቻችን ትርጉም 'ፊልዾስ' ማለት 'መፍቀሬ አኃው ወንድሞችን የሚወድ' ማለት ሲሆን ከ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው:: [ማቴ.፲፥፫] በዚህ ስም የሚጠራ ሐዋርያ ከ፸፪ቱ አርድእት ውስጥ ነበር:: እርሱም ጃንደረባውን ባኮስን ያጠመቀው ነው:: አንዳንዴ የ፪ቱ ታሪክ ሲቀላቀል እንሰማለን:: ለሁሉም ይህኛው ቅዱስ ፊልዾስ ቁጥሩ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት ሆኖ ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር:: በወቅቱ ገማልያል የሚሉት ክቡርና ምሑረ ኦሪት በርካታ ምሑራነ ኦሪትን አፍርቶ ነበር:: እንደ ምሳሌም ቅዱሳኑን "ዻውሎስን: ኒቆዲሞስን: ናትናኤልን: እስጢፋኖስንና የዛሬውን ሐዋርያ ቅዱስ ፊልዾስን" መጥቀስ እንችላለን:: ቅዱስ ፊልዾስ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው:: ኦሪትን ተምሮ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ 'መሲሕ ቀረ' እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ደረሰ:: ትክ ብሎ አይቶት "ተከተለኝ" አለው:: [ዮሐ.፩፥፵፬] ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት: ሁሉን ትቶ በመንኖ ጥሪት ተከተለው:: በዚህ ዓይነት ጥሪ መድኃኒታችን ቅዱስ ማቴዎስንም ጠርቶታል:: [ማቴ.፱፥፱] ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ሥራ አልፈታም:: ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል [ቀናተኛው ስምዖን] ሰበከለት እንጂ:: "ሙሴ በኦሪት: ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቸዋለሁ" አለው:: ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል:: [ዮሐ.፩፥፵፮] ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልዾስም መልሶ "ነዐ ትርአይ-ታይ ዘንድ ና" አለው:: ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ:: ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል:: በተለይ ደግሞ ጌታ የ፭ ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር:: እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ፪፻ ዲናር እንጀራ ብንገዛም አንዘልቀውም" ብሎ ነበር:: በሁዋላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ:: [ዮሐ.፮፥፭] በተለይ ደግሞ በሐዋርያት አበው መካከል ለጌታ እንደ እንደራሴ ሆኖ ያገለግል እንደ ነበርም ተጠቅሷል:: ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱና እንድርያስን ያናግሩ ነበር:: [ዮሐ.፲፪፥፳] አንድ ጊዜ ግን እስካሁን ሊቃውንትን የምታስደምም ጥያቄ ጠይቆ ነበር:: አጠያየቁ ደግሞ ፍጹም የዋሕ እንደ ሆነ ያሳያል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ አብ እየነገራቸው ሳለ ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ "እግዚኦ አርእነሁ ለአብ ወየአክለነ": ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል:: [ዮሐ.፲፬፥፰] ጌታችን ግን "ዘርእየ ኪያየ ርዕዮ ለአብ-እኔን ያየ አብን አይቷል" [ዮሐ.፲፬፥፱] ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩን: አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል:: ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ: ለ፵ ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: ቅዱስ መንፈሱን ከ፸፪ ልሳን ጋር ነስቶ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ [አፍሪካ] ደርሳዋለች:: ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው:: በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ መንጋው [ወደ ክርስትና በረት] ቀላቀለ:: ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ: ብርሃነ ክርስቶስን ሲያበራ: ነፍሳትንም ሲማርክ ቆየ:: ገድለ ሐዋርያት እንደሚለው የቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደ ሆነ ቢታወቅም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ መለየት አልተቻለም:: ዜናው ግን እንዲህ ነው:- በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ ሰበከ:: ብዙዎችንም አሳመነ:: ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት: ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት:: ከዚያም በእሳት እናቃጥላለን ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው:: በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ፫ ቀናት ጾሙ: ተማለሉ:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው: ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል:: 🕊 † ቅዱስ ኤላውትሮስ ሰማዕት † 🕊 ቅዱሱ ሰማዕትና ቅድስት እናቱ [እንትያ ትባላለች] የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ቅድስት እንትያ መልካም እናት ናትና ቅዱስ ኤላውትሮስን በሃይማኖት በሥርዓት አሳደገችው:: በ፲፯ ዓመቱ ዲቁናን ተሾመ:: በ፲፰ ዓመቱ ቅስና: በ፳ ዓመቱ ደግሞ ዽዽስናን ተሾመ:: ያን ጊዜ ሃገራቸው ሮም የግፍ ቦታ ነበረችና የቅዱሱ ዜና ሕይወት: ብርሃንነቱ: ስብከቱ: ንጹሕ ሕይወቱ በሃገረ ገዢው ዘንድ ተሰማ:: አንዱን መኮንን ጠርቶ "ሒድ አምጣው" አለው:: መኮንኑ ሲደርስ ቅዱስ ኤላውትሮስ እየሰበከ ነበርና በጣዕመ ስብከቱ ተማርኮ ከነ ተከታዮቹ አምኖ በዚያው ቀረ:: አገረ ገዢውም ሌላ መኮንን ልኮ አስመጣውና ቅዱሱን "ለምን የተሰቀለውን ታመልካለህ?" አለው:: ቅዱሱም መልሶ "ማስተዋል የተሳነህ! ቢገባህ ኑሮ የተቀለው እኮ ለእኔና ለአንተ ነው" አለው:: ሞት ተፈርዶበት ቅዱሱን ብዙ አሰቃይተው እሥር ቤት ሲጥሉት ርግብ መጥታ መገበችው:: እግሩን ቸንክረው በመንገድ ላይ ሲጐትቱት መልአክ ወርዶ ፈታው:: ወደ በርሃም ወሰደው:: ከጊዜያት በሁዋላ እንደ ገና ይዘው አምጥተው: ብዙ አሰቃይተው በዚህች ዕለት: ከእናቱ ቅድስት እንትያ ጋር በጦር እየወጉ ገድለዋቸዋል:: ሊቃውንትም የሰማዕታቱንና የሐዋርያውን ተጋድሎ እያደነቁ እንዲህ ጸልየዋል :- "ሰላም ለፊልዾስ ጽዑረ አባል በመቅሰፍት: ወለኤላውትሮስ ርጉዝ በብልኃ ኩናት: ምስለ እንትያ እባእ ኀበ ተርኅወ ገነት: ያሩጸኒ መዓዛሆሙ ወጼናሆሙ ዕፍረት: ለዝ ሐዋርያ ወለዝ ሰማዕት::" [አርኬ] 🕊 † ደናግል አጥራስስ ወዮና † 🕊 እሊህ ቡሩካት ሴት ወጣቶችም ምድራቸው ሮም ናት:: ቅድስት አጥራስስ የንጉሥ ልጅ ስትሆን ቅድስት ዮና ደግሞ የታላላቆች ልጅ ናት:: 2ቱ ቅዱሳት አንስት አይተዋወቁም ነበር:: ዮና ገና በልጅነቷ ክርስትናን አጥንታለች:: አጥራስስ ግን አባቷ ጣዖት አምላኪ በመሆኑ ቤት ሠርቶ: በወርቅ አንቆጥቁጦ ጣዖቶችን እንድታመልክ: ሰውም እንዳታይ አደረጋት:: እርሷ ግን ጣዖቱ እንደ ማይረባ ተመራምራ አውቃ ጣለችው:: "የማላውቅህ እውነተኛው አምላክ ተገለጽልኝ?" ስትልም ጸለየች:: ያን ጊዜ ቅዱስ መልአክ "ዮና የምትባል ሴት ታስተምርሽ" ስላላት አስፈልጋ አስመጣቻት:: ቅድስት ዮናም ክርስትናን ከጥንቱ ጀምራ አስተማረቻት::
Открыть в Telegram