Account
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

እኔ #በእግዚአብሔር_ፊት የምቆመው #ገብርኤል_ነኝ በቻናላናችን የሚሰጡ መንፈሳዊ ትምህርቶች መንፈሳዊ ምክሮች መንፈሳዊ መዝሙር መንፈሳዊ ጥያቄዎች መንፈሳዊ ስዕልዎች በየለቱ ስንክሳር

Username
@enatachn_mareyam
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers3,588−2 in 1 day
Avg views per post, 7d217last 7 days
ERR6.04%last 7 days

Subscribers, 30 days

Nov 28 – Nov 29−2 (−0.1%)

Show as table
DateSubscribers
Nov 28, 20263,590
Nov 29, 20263,588

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 26, 2026287
Nov 27, 2026266
Nov 28, 2026151

Most viewed this month

  1. 01

    🕊 [  † እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  †  ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ  †  🕊 † ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው:: ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው:: እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም:: እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል:: በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል:: እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ [ሰርግዮስ] ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር:: ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና:: በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው:: ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ:: ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ:: ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ:: በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት:: መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት ፬ [4] ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት:: ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት:: ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ፮ ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል:: 🕊  † ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ †  🕊 † ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል:: በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት:: ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና ፭ ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን [መታሠሩን] ሰማች:: ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ:: ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው:: ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ፭ ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ:: † አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [  † ኅዳር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት ፪. ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት ፫. ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ [የቅዱሱ ሚስትና ልጅ] ፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ [ልደቱ] [   †  ወርሐዊ በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት ፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ ፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ ፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም ፮. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ † "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" † [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

    Text
    Views337
    Forwards—
    Reactions6
    Comments—
  2. 02
    Views317
    Forwards—
    Reactions1
    Comments—
  3. 03

    No text

    Photo
    Views313
    Forwards—
    Reactions4
    Comments—
  4. 04

    No text

    Photo
    Views309
    Forwards—
    Reactions3
    Comments—

Latest posts

#24792Photo
Views48−78%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h42
5 h48
  1. After 6 hours48
  2. Total to date48
#24791Audio
Views44−80%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h40
5 h44
  1. After 6 hours44
  2. Total to date44
#24790Text

🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞ [ እንኩዋን ለኃያል ሰማዕት "ማር ቴዎድሮስ" እና "ቅዱስ አንያኖስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ] 🕊 † ቅዱስ ቴዎድሮስ ማር ሰማዕት † 🕊 በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች:: ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ [የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው] በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብፅ አሳደደችው:: ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር:: በዛው ልክ ደግሞ ገና በ፳ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል በውበቱም ደመ ግቡ በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል:: ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን [የጠላት] ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል:: የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው:: አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርበቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ፳፬ ክንድ ነበር:: ከነገር ሁሉ በሁዋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው:: ክርስቶስ ተክዶ ጣዖት ቁሞ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው የክርስቲያኖች ደም ፈሶ ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ:: ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ :- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት:: በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውሃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ:: በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን የጻፈ ያጻፈ ያነበበ ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው:: በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል:: 🕊 † ቅዱስ አንያኖስ ዘግብጽ † 🕊 ይህ ቅዱስ አባት ውለታው ከፍ ያለ ነውና በምድረ ግብጽ እጅግ ይከበራል:: በተለይ ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብሎ ለምዕመናን ያስረከበ አባት በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :- ወንጌላዊው ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ተመድቦ በፈቃደ እግዚአብሔር ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ በ፶ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: እስክንድርያ ከተማ በሜዲትራኒያን ባሕር ዳርቻ እንደ መኖሯም መጀመሪያ ወደ እርሷ ደረሰ:: ልክ ወደ ከተማ ሲገባ ገና አንደበቱ ለወንጌል ሳይከፈት እንቅፋት መትቶት ጫማው ተበጠሰ:: ያን ሁሉ በርሃ የቻለች ጫማ በእንቅፋት በመበጠሷ እያዘነ ወደ ጫማ ሰፊ ዘንድ ደርሶ "ሥራልኝ?" ይለዋል:: ይህ ጫማ ሰፊ አንያኖስ [አንያኑ] ይባላል:: ጣዖት አምላኪ ግን ደግሞ ቅንና ገር የሆነ ሰው ነበር:: "እሺ" ብሎ ሲሰፋለት መሳፈቻው [መስፊያው] ስቶ መሐል እጣቱን ስለ ወጋው "ኢታስታኦስ [አታኦስ]" ብሎ ጮኸ:: ትርጉሙም "አንድ አምላክ" ማለት ነበር:: ይህንን የሰማው ቅዱስ ማርቆስ ቀና ብሎ "ጌታየ ሆይ! ጐዳናየን ስላቀናህልኝ አመሰግንሃለሁ!" ብሎ ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ የአንያኖስን እጅ ቀባው:: ወዲያውም ደሙ ቁሞ ቁስሉም ድኖ እንደ ነበረው ሆነ:: በዚህ ተአምር ድንጋጤም ደስታም ቢሰማው "ማነህ አንተ?" ሲል ቅዱሱን ጠየቀው:: ወንጌላዊውም መልሶ "እኔ የክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ" አለው:: አንያኖስም "እባክህ ወደ ቤቴ እንሒድ" ብሎ ሐዋርያውን ጋበዘው:: እቤት ሲደርሱም ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር አስተናግደውት የሕይወትን ቃል ለመኑት:: ቅዱስ ማርቆስም ከስነ ፍጥረት እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ አስተምሯቸው አመኑ:: አጥምቆ ሥጋውን ደሙን አቀበላቸው:: ይህቺው የቅዱስ አንያኖስ ቤትም በምድረ ግብጽ የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቤትና ቤተ ክርስቲያን ሆነች:: ቅዱሱ ሐዋርያ በ፷ ዓ/ም አካባቢ በቅዱስ አንያኑ ቤት ሆኖ በርካቶችን አሳመነ:: በሰማዕትነት ከማረፉ በፊትም ቅዱስ አንያኖስን የምድረ ግብጽ ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት አድርጐ ሾመው:: ቅዱስ አንያኖስም ለ፲፪ ዓመታት የክርስቶስን መንጋ እያበዛ ተጋደለ:: ከሐዋርያው የተቀበለውን ንጹሕ ዘር ዘራ:: የድኅነት የምሥራቹንም አዳረሰ:: ይሔው ይህ መልካም ተክል ዛሬም ድረስ ሳይጠወልግ አለ:: የአሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ታውድሮስም ከቅዱስ ማርቆስ ፻፲፰ኛ ሲሆኑ ከቅዱስ አንያኖስ ፻፲፯ኛ ናቸው:: ቅዱሱ ለእኛ ኢትዮዽያውያንም የክህነት አባታችን ነው:: ይህች ቀንም ዕለተ ዕረፍቱ ናት:: አምላከ ቅዱሳን ክፉውን አርቆ ከበጐው ዘመን ያድርሰን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፳ [20] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ማር ቴዎድሮስ ኃያል ሰማዕት ፪. ቅዱስ አንያኖስ [ †  ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ ፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ ፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና ፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት " በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" [፩ዼጥ.፫፥፲፫] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

Open in Telegram
Views46−79%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h41
5 h46
  1. After 6 hours46
  2. Total to date46
#24789Photo
Views144−34%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h30
4 h123
6 h144
  1. After 1 hour30
  2. After 6 hours144
  3. Total to date144
#24788Audio
Views140−35%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h31
4 h124
6 h140
  1. After 1 hour31
  2. After 6 hours140
  3. Total to date140
#24787Photo

🕊                        💖                       🕊           [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]   🍒                                                    🍒 [  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]         [   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ] 🌸                         ♱                       🌸 [ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]                [   ክፍል አስር   ]           💛   ድንቅ ትምህርት  💛 [ በመምህራችን ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ] 🍒                                                    🍒 ❝ የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ] 🌸                                                  🌸                            †††                ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊                        💖                        🕊                              👇

Open in Telegram
Views141−35%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h32
4 h126
6 h141
  1. After 1 hour32
  2. After 6 hours141
  3. Total to date141
#24786Photo
Views210−3%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h95
6 h165
9 h210
  1. After 6 hours165
  2. Total to date210
#24785Audio
Views202−7%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h94
6 h157
9 h202
  1. After 6 hours157
  2. Total to date202
#24784Photo
Views203−6%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h89
6 h155
9 h203
  1. After 6 hours155
  2. Total to date203
#24783Photo
Views181−16%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h90
5 h138
8 h181
  1. After 6 hours138
  2. Total to date181

All posts

Connections