ለሁሉም ሼር በማድረግ አብረን እናገልግል 1000153401768 ቀበና መካነ/ሕ/አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ለበለጠ መረጃ 0911890696 ወይም 0913039824
Open in Telegram
www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn
ይህ የዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ telegram channel ነው። በዚህ ቻናል ➟ በየቀኑ አዳዲስ ዝማሬዎችን ➟ ቆየት ያሉና ነባር ዝማሬዎችን ➟ የተለያዩ አስተማሪ ፅሁፎችን ያገኛሉ። #ሊያድነን_ከሰማያት_የመጣው #የእግዚአብሔር_ልጅ_ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ይወደናል። @HawazTegegn @HawazTegegn
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 17, 2026 | 532 |
| Nov 26, 2026 | 180 |
Latest posts
ወበእንተ ኃጣውኢነ ውእቱ ተሰቅለ ዲበ ዕፅ በሥጋሁ ከመ ያውፅአነ እምኃጣውኢነ ወበጽድቁ ያሕይወነ። በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።— 1 ጴጥሮስ 2:25 እህቴ ዘማሪት በጸሎት ዝማሬ መላዕክትን ያሰማልን : ወገኖች ሁላችንም ክስር ባለው የእህታችን የዘማሪት በጸሎት YouTube channel ሊንክ እየገባን ይህን ድንቅ ዝማሬ እናዳምጥ እግዚአብሔርን ስለምሕረቱ እናመስግነው:: https://youtu.be/Oes8f8CpIG4?si=Q6c28Fk8bDFaC61n
Open in Telegramሳይገባኝ በምሥጋናህ አደባባይ ምሥክርህ አድርገህ አቆምከኝ : የዘመኔን ቁጥር ባሰላው ከውለታህ ብዛት ጋ ሊነጻጸር ከቶ አይችልም አምላኬ ሆይ ውለታህ ብዙ ነው:: ለእኔ ያላዳረግኸው ምን አለ?? አብረን እንዘምር ወገኖቼ
Open in Telegramያላንተ ክብር የለኝም || ኪዳነ ምሕረት ኪዳነ ኮነ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ተወዳጅ ዝማሬዎች :: ዜማ ሐዋዝ ሪከርዲንግስ ምርቃት Yalante kibr yelegnim https://youtu.be/1nn4lBP297w
Open in Telegramአትበሉ ግድ የላችሁም ዛሬ አንድ የስንፍና ሃሳብ ወደ አይምሮዬ ሲመጣ የገሰጸኝን ቅዱስ ቃል ልንገራችሁ : እንደ ሌላው ቀን ይሄም ቀን ያው ነው ምን ለየው የሚል ሃሳብ ሹክ አለብኝ : እግዚአብሔር የቀናትን ቁጥር “ቁጥር“ ብቻ አድርጎ አይደለም ያቀረበው ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጠን ሲቀርብ ነው አመቱን ቁጥር ብቻ : ዘመን መለወጫን እንደ ሌላው ቀን ቀን ብቻ የሚያደርግብን :: ቀናት የማይቆጠሩለት ጌታ ቀንን ቆጥሮ ዘመንን ለክቶ ሲሰራ አይተነዋል : አለማትን ከመፍጠሩ ጀምሮ በግዜ ልኬት ውስጥ የማይወሰነው ጌታ : ግዜን ግን ለክቶ እና ገደብም :ወሰንም :መቀያየርንም :ጸባይም ሰጥቶት በብርሃናት እና በተፈጥሮ ኡደት ቀምሮታል:: ቀንም ሆነ ማታም ሆነ አንድ ቀን እየተባለ በዘፍጥረት ያየነው ቁጥር በሰባተኛውም ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ ተብሎ ዘለአለማዊው አምላክ በተቆጠረ ቀን ውስጥ ስራውን ሲገልጥ አየነው:: ቀናት እና ዘመናት ለእግዚአብሔር የምህርትም የትድግናውም የባርኮቱም እንዲሁም የቁጣው መገለጫ መሳሪያ ሲሆኑ ብዙ ቦታዎች እናያለን :: አዲሱ ኪዳን አመተ ምሕረት ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ከንጽሕተ ንጹሃን ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ያድነን ዘንድ የቤዛነቱን ስራ ሲገልጥ ቀንን ተጠቅሞ ዘመናትን ቆጥሮ አመታትን መዝኖ ነው:: ዛሬ አንድ የስንፍና ሃሳብ ወደ አይምሮዬ ሲመጣ የገሰጸኝን ቅዱስ ቃል ልንገራችሁ : እንደ ሌላው ቀን ይሄም ቀን ያው ነው ምን ለየው የሚል ሃሳብ ሹክ አለብኝ : ግን እኮ እኔ በተለወጠ ማንነት እና እግዚአብሔርን በማስቀደም ክጀመርኩት ይህ ዘመን በእግዚአብሔር ቸርነት ልዩ ይሆናል አልኩኝ : እግዚአብሔር ከዘመናት ጋ በልዩነት ይሰራል እንዴ ግን ?? አዎ ግዜ አይለውጠውም እርሱን ነገር ግን ግዜን ይለውጠዋል አስታውሱ ወገኖቼ ጌታችን በትንቢት የተነገረውን ቃል ይፈጽም ዘንድ የተወደደችውን የጌታን አመት አለ :- ሉቃ4:17 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፡— የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። እኔም እንዲህ አልኩኝ የተወደደች የጌታ አመት ትሁንልን ለታሰርነው መፈታት : ተስፋ ለተራብን :ምህረት ለናፈቀን :ሠላምን ለተመኘን አይኖች ፍቅርን :ሠላምን :ጽድቅን : እናይ ዘንድ ያድለን: የተገፉ ካሳን ያጡ - ማግኘትን : የወደቁ - መነሳትን -ነፃነትን ያገኙ ዘንድ : ከኃጢአት እስራት ነጻ ወጥተንም - በንስሃ በክቡር ስጋው በቅዱስ ደሙ ታትመን የምንባረክበት እውነትም የተወደደችው የጌታ አመት ይሁንልን :: ዘመኑ ተለውጧል እኛም በተለወጠ ማንነት እንመላለስበት ዘንድ አሁን አንድ ብለን እንድንጀምረው የእግዚአብሔር ቸርነት ይድረስልን : የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ የቅዱሳን የጻድቃን የሰማዕታት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት አይለየን:: 01/01/2019 ዓመተ ምሕረት ታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ
Open in TelegramConnections
Similar channels
ውሉደ ብርሃን ሚድያ@weludebirhanReligion3.79K- አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ@christian930Religion3.79K
ኡስታዝ አቡየሕያ አብዱልዋሲዕ | قناة أستاذ أبي يحيى عبدالواسع@menhajadamaReligion3.87K
የጎ/ሕ/ጤ/ሳ/ኮ ግቢ ጉባኤ /GC_GG@gc_gibigubaeReligion3.53K
AS-HABULE YEMINE@ashabuleyamineReligion3.49K
Abdu & Hasu@abduftsemierReligion3.98K
URIM | ኡሪም@urim7Religion4.14K
𝐄𝐂𝐂𝐋𝐄𝐒𝐈𝐀 - 𝐓𝐔𝐁𝐄 ✞@ecclesia_tubeReligion3.29K