Account

Posts of www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn

newest first

#2056Link preview
Views532+49%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#2049Text

አትበሉ ግድ የላችሁም ዛሬ አንድ የስንፍና ሃሳብ ወደ አይምሮዬ ሲመጣ የገሰጸኝን ቅዱስ ቃል ልንገራችሁ : እንደ ሌላው ቀን ይሄም ቀን ያው ነው ምን ለየው የሚል ሃሳብ ሹክ አለብኝ : እግዚአብሔር የቀናትን ቁጥር “ቁጥር“ ብቻ አድርጎ አይደለም ያቀረበው ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጠን ሲቀርብ ነው አመቱን ቁጥር ብቻ : ዘመን መለወጫን እንደ ሌላው ቀን ቀን ብቻ የሚያደርግብን :: ቀናት የማይቆጠሩለት ጌታ ቀንን ቆጥሮ ዘመንን ለክቶ ሲሰራ አይተነዋል : አለማትን ከመፍጠሩ ጀምሮ በግዜ ልኬት ውስጥ የማይወሰነው ጌታ : ግዜን ግን ለክቶ እና ገደብም :ወሰንም :መቀያየርንም :ጸባይም ሰጥቶት በብርሃናት እና በተፈጥሮ ኡደት ቀምሮታል:: ቀንም ሆነ ማታም ሆነ አንድ ቀን እየተባለ በዘፍጥረት ያየነው ቁጥር በሰባተኛውም ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ ተብሎ ዘለአለማዊው አምላክ በተቆጠረ ቀን ውስጥ ስራውን ሲገልጥ አየነው:: ቀናት እና ዘመናት ለእግዚአብሔር የምህርትም የትድግናውም የባርኮቱም እንዲሁም የቁጣው መገለጫ መሳሪያ ሲሆኑ ብዙ ቦታዎች እናያለን :: አዲሱ ኪዳን አመተ ምሕረት ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁ እግዚአብሔር ወልድ ከእመቤታችን ከንጽሕተ ንጹሃን ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ያድነን ዘንድ የቤዛነቱን ስራ ሲገልጥ ቀንን ተጠቅሞ ዘመናትን ቆጥሮ አመታትን መዝኖ ነው:: ዛሬ አንድ የስንፍና ሃሳብ ወደ አይምሮዬ ሲመጣ የገሰጸኝን ቅዱስ ቃል ልንገራችሁ : እንደ ሌላው ቀን ይሄም ቀን ያው ነው ምን ለየው የሚል ሃሳብ ሹክ አለብኝ : ግን እኮ እኔ በተለወጠ ማንነት እና እግዚአብሔርን በማስቀደም ክጀመርኩት ይህ ዘመን በእግዚአብሔር ቸርነት ልዩ ይሆናል አልኩኝ : እግዚአብሔር ከዘመናት ጋ በልዩነት ይሰራል እንዴ ግን ?? አዎ ግዜ አይለውጠውም እርሱን ነገር ግን ግዜን ይለውጠዋል አስታውሱ ወገኖቼ ጌታችን በትንቢት የተነገረውን ቃል ይፈጽም ዘንድ የተወደደችውን የጌታን አመት አለ :- ሉቃ4:17 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፡— የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። እኔም እንዲህ አልኩኝ የተወደደች የጌታ አመት ትሁንልን ለታሰርነው መፈታት : ተስፋ ለተራብን :ምህረት ለናፈቀን :ሠላምን ለተመኘን አይኖች ፍቅርን :ሠላምን :ጽድቅን : እናይ ዘንድ ያድለን: የተገፉ ካሳን ያጡ - ማግኘትን : የወደቁ - መነሳትን -ነፃነትን ያገኙ ዘንድ : ከኃጢአት እስራት ነጻ ወጥተንም - በንስሃ በክቡር ስጋው በቅዱስ ደሙ ታትመን የምንባረክበት እውነትም የተወደደችው የጌታ አመት ይሁንልን :: ዘመኑ ተለውጧል እኛም በተለወጠ ማንነት እንመላለስበት ዘንድ አሁን አንድ ብለን እንድንጀምረው የእግዚአብሔር ቸርነት ይድረስልን : የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ የቅዱሳን የጻድቃን የሰማዕታት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት አይለየን:: 01/01/2019 ዓመተ ምሕረት ታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ

Open in Telegram
Views1,440+304%vs avg
Forwards—
Reactions25
Comments—
#2046Text

አዲስ አመት በረከት ነው ቁጥር መቀየር ብቻ አይደለም አብሮት ከእግዚአብሔር የሚሰጠን በረከት ብዙ ነው:: አመታት የማይቆጠሩለት አምላክ በግዜ ልኬት ውስጥ የማይመጠነው ንጉስ እርሱ ለሰው ልጆች የሚቆጠረውን አመት በስጦታ አበርክቶልናል አዎ በሚቆጠሩ አመታት የማይቆጠረውን የዘለአለም ሕይወታችንን ማረፊያ እናደላድል ዘንድ ይህን እድል ሰጥቶናል ሰው የነፃ ፈቃድ ባለመብት ነውና:: በዚህ አመት ፍፃሜ በአዲሱ አመት መባቻ እግዚአብሔር ደስ የሚል የአብሮነትን ቀን ለገሰን አዲስ አመት ከሰው ጋ ደስ ይላል : : እህቴ ዘማሪት የትም ወርቅ ወደ ዜማ ሐዋዝ ሪክርዲንግስ ለእንኳን አደረሳችሁ ምስጋና ከተወዳጅ የእህትማማች የዘማርያን ሕብረት ጋ መጥተው ነበር እጅግ ምንወደው ወንድም Bejai Naiker በተገኘበት ይህን አመት በምስጋና ጀምረነዋል:: ደስታ ሣቅ ደግነት አብሮነት ተስፋ በሞላበት መንገድ ይህን አመት ልንቀበለው ያልፈውን በምስጋና ሸኝተነዋል እንዳሰባችሁን እግዚአብሔር በመልካምነቱ ያስባችሁ እህቶቼ :: እናንተም በዚህ ያላችሁ ቤተሰቦቼ ሁላችሁም ቤት በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ በምስጋና የምትቀበሉትን ደስታ ይዞላችሁ ይመጣ ዘንድ ፀሎቴም ምኞቴም ነው:: የእግዚአብሔር ፍቅር የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፃድቃን የሰማእታት የቅዱሳን የመላዕክት ረድኤት በረከት አይለየን :: የአመት ሰው ይበለን :: ታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ::

Open in Telegram
Views1,080+203%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#2044Video
Views1,720+383%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—
#2042Text
Views1,430+302%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—
#2040Text

👉ቅዱሳን መላዕክት ስለእኛ ያውቃሉ? አዎ ! 👉ቅዱሳን መላዕክት ሊያስታውቁን ይችላሉ ? አዎ ! 👉ቅዱሳን መላዕክትን እግዚአብሔር ከሰጣቸው ግርማ እና ስልጣን የተነሳ በአክብሮት በፊታቸው እንሰግዳለን ወይ ? አዎ! እንደው በቅተን ቅዱሳን መላዕክትን ለማየት አንደርስም እንጂ በግርማቸው ቢገለጡ እንካን መስገድ በፍጥረታዊ ድፍረት እና አቅም መቆምም አንችልም 🫵🏽 ያው ያኔ ተገዶ ከመስገድ አሁን በፍቅር መስገድ በረከት አለው:: 👉ቅዱሳን መላዕክት ሊዳስሱን ሊቀርቡን ይችላሉ ወይ? አዎ👉👇👇 ዳንኤል 8 : 16 በኡባልም ወንዝ መካከል፡— ገብርኤል ሆይ፥ ራእዩን ለዚህ ሰው አስታውቀው ብሎ የሚጮኸውን የሰውን ድምፅ ሰማሁ። 17 እኔም ወደ ቆምሁበት ቀረበ፤ በመጣም ጊዜ ፈርቼ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም፡— የሰው ልጅ ሆይ፥ ራእዩ ለፍጻሜ ዘመን እንደ ሆነ አስተውል፡ አለኝ። 18 ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ። ቅዱስ ገብርኤል ሆይ የእግዚአብሔርን የፈቃዱን ምስጢር እናውቅ እናስተውል ዘንድ ቅረበን: የጌታ መልዓክ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ የሚለው ድምፅህ ዛሬም በምንወድህ ልጆችህ ልቡና ላይ ያስተጋባል: በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም እኛን ወዳጆችህን አስበን : እንኳን የአምላክ ባለሟል የንጉሥ አጋዥ ያኮራል የለ? እሳቱን ስታበርድ ሠማዕታትን ስታጸና ሰምተን ተጽናንተናል : ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣን የእግዚአብሔርን የፈቃዱን ምስጢር ገልጠህላቸዋልና:: መጋቤ ኃዲስ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን አስታውቀኸናል አሁንም ቅዱስ ስሙን በልባችን ዘወትር አትምልን : ለተቀበሉት በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ ተብሎ እንደተጻፈልን በእምነት ጸንተን እንድንቆም ተራዳኢነትህ ይደግፈን:: ዳንኤል 9:21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። 22 አስተማረኝም፥ ተናገረኝም እንዲህም አለ፡— ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ። ገብርኤል ብሂል ብዕሲ ወአምላክ እምሃበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ (ቅዱስ ያሬድ ማሕሌተ ጽጌ) ትርጉም:- ገብርኤል ማለት ሰው እና አምላክ ማለት ነው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መልዕክተኛ ማለት ነው:: ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላክኸው ቅዱሱ መልዓክ ዳንኤልን እንደዳሰስከው እኛንም ዳስሰን አቤቱ ተናገረንም ማስተዋል እና ጥበብን ስጠን:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ይገለጣልና ገብርኤል የእግዚአብሔር ኃይል / ገብርኤል ሰውእና አምላክ ( የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምስጢረ ሥጋዌ ገልጧልና) ገብርኤል (እግዚአብሔር ብርታቴ ነው) :: እንኳን አደረሳችሁ የሊቀ መልዓኩ የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ለሁላችን ይድረሰን:: ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ታናሽ ወንድማችሁ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ 19/11/2018 ዓ.ም

Open in Telegram
Views1,460+310%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—
#2038Text

ዛሬ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቅዱሳን ሐዋርያትን የሰማዕትነት ክብር የምታስበው ከስብከታቸው ቃል : ከሕይወት ምስክርነታቸው : ለእግዚአብሔር ከተሰጠው ዕጹብ ማንነታቸው ጋር ነው:: ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ዓለም ሁሉ ይሰማ ያምን ዘንድ እስከ ሞት ድረስ ታምነው መስክረዋል:: የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት መፈክር ሳይሆን እውነተኛ የሕይወት መሰጠት እና ራስን አሳልፎ ለእግዚአብሔር የማስረከብ እንደሆነ አስተምረውናል :: በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርና በሰይፍ አንገቱ የተቀላውን ቅዱስ ጳውሎስን እንዲሁም ቁልቁል የተሰቀለውን ቅዱስ ጴጥሮስን በሌሊት ቤተክርስትያን እንዲህ ስትል ቅዱስ ያሬድ በጻፈው ድንቅ ቃል በፍቅር ስታወሳቸው አድራለች :- ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስለ መዓዛሁ ቅድው። ቃለ ደምክሙ ሐዋርያ ዘእግሩ ከዋው። ትርጉም:- የሐዋርያት የደማችሁ ድምፅ የእግሩ ኮቴ (የስብከቱ ጉዞ) : የተቀደሰ መዓዛው ከነበረው ውበት ጋር በልቤ ውስጥ ተመላለሰ: 🔶ደማቸው ክርስቶስን ያስታውሰናል ስለ ስሙ ነው የተሰውት:: 🔶ደማችው ስብከታቸውን ያስታውሰናል እንደ ሚታረድ በግ ተቆጠርን ብለው እንደተናገሩ ሞትን በዝምታ እምነታቸውን ደግሞ በአንክሮ ቃል ወደ አለም ሁሉ አስተጋብተዋልና :: 🔶ደማቸው የኮቴ ድምፅ አለው ቅድስናን ያውጃል 🔶ደማቸው መአዛ አለው ክርስቶስን ለብሰውታልና የዓለም ብርሃን የሆናችሁ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ዛሬም ምልጃችሁ እና ጸሎታችሁ ለእኛ ለልጆቻችሁ ይድረሰን:: እናንተ የክርስቶስ ሙሽሮች በስብክታችሁ አምነን በስሙ ተጠምቀናል ዛሬ በእምነታችን እንዳንደክም ምልጃ እና በረከታችሁን እናገኝ ዘንድ ደጅ እንጠናለን:: እናንተ በሰይፍ በሞታችሁ ክርስቶስን አከበራችሁ እኛ በሕይወት እያለን በምቾት መሃል ለምንባዝን ጸጋችሁ መንገዳችንን ያቅናልን:: ይህች ቀን እጅግ የከበረች ናትና ሞታችሁን ሳይሆን በክርስቶስ ሕያው መሆናችሁን ደግሞም በተሰጣችሁ ቃልኪዳን ልጆቻችሁ ለሆንን ለእኛ ምልጃ ጸሎታችሁ እንዳለን እያሰብን የሃዘን ሳይሆን የደስታን እንባ በአይኖቻችን አቅርረን : የስብክታችሁ መዓዛ የሆነውን መአዛ ቅዱሳን ኢየሱስ ክርስቶስን በደማችሁ መፍሰስ ያከበራችሁትን በምስጋና በፊቱ እንቆማለን:: ዛሬም በሃገራችን በኢትዮጵያ ያሉ ሰማዕታትን የእናንተን ዋጋ ያገኙ ዘንድ በረክታችሁ በምድራችን ላይ ይደር:: እናንተ ሰማዕታት ብርሃናተ ዓለም ሆይ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ብርሃን አብርታችሁልናልና አሁን በብርሃን ነን እንጂ ጨለማ አይጨልምብንም:: ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ሐምሌ 05 2018 ከታናሽ ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ

Open in Telegram
Views1,850+420%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—