Account
URIM | ኡሪም

URIM | ኡሪም

ለሞተልን መኖር | ብርሀንን ማብራት | ለምፅአት መዘጋጀት 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15 ¹⁵ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። ሁሉን ለወንጌል ብቻ በልባችን እርሱ ያስብ በአንደበታችን እርሱ ያውራ። Creator- @Kaleabkasaye

Username
@urim7
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers4,143
Avg views per post, 7d97−48.6% vs prev 7d
ERR2.35%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 29, 2026332
Nov 3, 2026277
Nov 6, 2026389
Nov 7, 2026305
Nov 8, 2026279
Nov 10, 2026254
Nov 14, 2026200
Nov 15, 2026194
Nov 17, 2026175
Nov 22, 2026117
Nov 23, 202697
Nov 24, 202679

Most viewed this month

  1. 01

    ቤተልሄም የሰው ልጅ በህይወቱ ሊኖረው ከሚገባው መሰረታዊ ነገር መሀከል አንዱ አና ዋነኛው ትእግስት ነው። የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል እንዲል የሀገሬው ባህል መቸኮል ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ከብዙ ያጎድላል ብዙም ያከስራል። ለሚታገስ ደግሞ ትእግስት ፍሬ አላት የሚገርመው እና በጣም የሚደንቀው ነገር አብዛኛው ሰው በትእግስት ውስጥ ያለውን መልካም ፍሬ መመልከት አለመቻሉ ነው። ካስተዋልን ተፈጥሮ እንኳን የይድረስ የይድረስ አይደለም የተፈጠረው በእርግጥም የምናመልከው አምላክ ሁሉን በአንዴ ካለመኖር ወደመኖር ካለ መታየት ወደ መታየት ማምጣት የሚችል አምላክ እንደሆነ ባምንም እርሱ እራሱ አንድ ሁለት እያለ እስከ ሰባተኛው ቀን ነው ሁሉን የደመደመው ሌሎች ሌሎች ብዙ ምሳሌዎችን ብናነሳ ለሁሉም ነገር የራሱ ጊዜ እንዳለው እንረዳለን። የዘመኔ በሽታ ግን መቸኮል ሆነና ነገሩ ብዙ ነገሮች ተበላሽተውብናል ብዙ ነገሮች መስመር ስተውብናል አክስረውናል አጉድለውናል አለፍ ሲልም ብዙ አሳጥተውናል። እኔም በዘመኔ በዚሁ በሽታ ከተጠቁት መሀል ነበርኩ አንድን ነገር ፈረንጆች እንደሚሉት (Overnight) ማግኘት የምመኝ መመኘት ብቻ ሳይሆን እንደዛ ለማድረግ የምጣጣር የምታትር አይነት ሰው ነበርኩ። በተፈጥሮዬ በጣም ችኩል ከመሆኔ የተነሳ በልጅነት ወራቶቼ ላይ የአመቱ አልያም የ ሴሚስተሩ ማጠቃለያ ፈተና ሲሰጥ ከሁሉም ቀድሞ ለመውጣት ሳላነብ በግምት መልስ አስገባ እንደነበረ ብዙ ነገሮች በመቸኮሌ እንዳበላሸው ትዝታዎቼ ናቸው። ረጋ ያለ ቅቤ ይወጣዋል እኔ ጋር አይሰራም ቅቤው ይቅር ባይ ነኝ ይህ እንግዲህ ከልጅነት አብሮኝ ያደገ መጥፎ ምግባሬ ነው። የሚያስተምር የሚገስፅ ጌታ ነው እና እኔንም ጌታ በህይወቴ መታገስን አስተማረኝ ቆይቶ መጠበቅን ሹክ አለኝ ብዙ ባልጠብቅም ከተማርኳት ከጥቂቷ ግን እነሆ ልበላቹ በእስራኤል ምድር ቤተልሄምን የመሰለ ለምለም ምድር አልነበረም ከስሙ ትርጓሜ እንኳ እንደምንረዳው የእንጀራ ቦታ የመብል ቦታ የምግብ ቦታ ተብሎ ይጠራል ታዲያ ይህ ቦታ መሳፍንት በሚገዙበት እየተቀያየሩ በሚነግሱበት ሰአት አዋጅ መጣ ረሀብ ቸነፈር ነገሰበት የእንጀራ ቦታ ተብሎ የሚጠራው ቤተልሄም እንኳን እንጀራ ሊሰጥ ቀርቶ እንጀራ ፈላጊ ሆኖ ተገኘ። ይህኔ ነው ከአይሁድ ወገን የሆኑ የቤተልሄም ነዋሪዎች ቤተሰብ ታሪክ የሚጀምረው የአቤሜሌክ ቤተሰብ አይሁዳዊ ቢሆኑም ምንም እንኳ የእስራኤልን አምላክ ቢያመልኩም ረሀብ ሲበረታ ችግር ሲፀና ግራ መጋባት ሲደራራበብ ያስቸኩላል ትኩረት ይነሳል። የጅብ ችኩልም ቀንድ ይነክሳል እና ነው ነገሩ አቤሜሌክ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ እንጀራ ፍለጋ ከነበረበት የበረከት ሀገር ከተባለች ለጊዜው ግን ረሀብ ከነገሰባት ቤተልሄም እንጀራ አገኛለው እራሴንም ቤተሰቤንም አተርፋለው ብሎ ወዳሰበበት ሞአብ የሄደው። ግና ሞአብ እንዳሰበው ያልሆነለት አቤሜሌክ ረሀብ ችግር ሞት ሽሽት የሄደባት ሞአብ እራሷ ገደለችው አቤሜሌክ ከሞት ሸሽቶ ሞአብ ቢረግጥም የፈራው ሞት ግን በሞአብ አልቀረለትም። አቤሜሌክ በውሳኔው በመሳቱ ከመቆያ ስፍራው በመውጣቱ የራሱን ብቻ ሳይሆን የቤተሰቡን ህይወት አበላሸ የአቤሜሌክ ልጆች ሞቱ ኑሀሚንን ብቻዋን ከምራቶቿ ጋር እንድትቀር አለፍ ሲልም ከደረሰበት መከራ የተነሳ በእግዚአብሄር ላይ ምሪት እንድታነሳ አደረጋት አስተውሉ ይህ ሁሉ የሆነው ከቤተልሄም በመውጣታቸው ነው። በጣም የሚገርመው ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ቤተልሄም ተጎበኘች ይህንንም ኑሀሚን አቤሜሌክን እንዲሁም ሁለቱን ልጆቿን ካጣች ቡሀላ ወሬው ደረሳት እጅግ ልብ ሰባሪ ነገር ገጠማት ኑሀሚንም ማራ በሉኝ እስከምትል ደረሰ በጌታዋ ልቧ ተቆጣ ለምን ከተባለ ከ ቤተልሄም በመውጣቷ። ህይወት ሲቸኮልባት አትወድም በተለይ ደግሞ ለኪዳን ህዝብ እግዚአብሄርን ከማድመጥ ከመስማት ውጪ ሌላ ምንም መፍትሄ የለም የኪዳን ህዝብ ጉዞው አካሄዱ በሙሉ የሚቃኘው በጌታው ድምፅ ነው። በግ ከእረኛው ውጪ ተስፋም ህይወትም ምሪትም የለውም በግ እረኛውን ካልሰማ እጣ ፈንታው የተኩላ እራት መሆን ነው ለዚህም ነው ጌታችን እና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ ያለው። ቤተልሄም ቢያመንም ብንታምም የምንቆይበት እግዚአብሄርን የምንጠብቅበት ስፍራችን ነው። አዎ በእርግጥ ረሀብ አለ በእርግጥ ሁኔታው ግራ ያጋባል በእርግጥ የሞት ድምፅ ያንዣባል ግን በእርግጠኝነት እመጣለው ያለን ጌታ በሞአብ ሳይሆን በዚያው ባለን በቤተልሄም መምጣቱ አይቀርምና ቤተልሄም ሆነን እንጠብቀው በእርግጥም ያወራን የተናገረን ጌታ በጊዜው ቃሉን ይጠብቃል በጊዜው ይደርስልናል። አብዛኞች ከበረከት ለምን ጎደሉ ብለን ከጠየቅን ሞአብ ሄደው ነው። የአብዛኞቻችን ችግር አለመረጋጋት በቤተልሄም አለመቀመጥ ነው። በዘመኔ ከኔም ተሞክሮ በክርስትናም ከቆየሁባቸው አመታቶች የተማርኩት ትልቁ ትምህርት መቆየት የሚል ነው። የማይቆይ ሰው አይቀበልም የማይታገስ ሰው የቸኮለለትን ያንኑ ነው የሚወርሰው የታገሰ ግን ጌታውን የጠበቀ ግን ጌታው ያሰበለትን ጌታው ያቀደለትን ያንን ያገኛል። ለአንድ ሰው ብቻ አጋሩት😊😁 @Urim7

    Text
    Views389
    Forwards—
    Reactions6
    Comments—
  2. 02
    Views332
    Forwards—
    Reactions7
    Comments—
  3. 03
    Views305
    Forwards—
    Reactions6
    Comments—
  4. 04
    Views279
    Forwards—
    Reactions3
    Comments—

Latest posts

#3377Text

Forwarded from GK's Journey

ሠላሳ ብር ይጎዳኛል። ከሦስት ዓመት ተኩል ተልዕኮው ማጋባደጃ ሰሞን የተከሰተ ክስተት ነው። ለሰው ልጆች ነፍሱን መሥዋዕት አድርጎ በፈቃዱ ሊሰጥ የነበረበት ወቅት ነው። ሳምንቱ እልፍ ክውኖች የተፈጸሙበት ነበር። ሊወለድ ያለ ካለ ምጥ እንዳይሆን ሁሉ ከመስቀሉም በፊት ተሸክሞ የቻላቸው መስቀሎች የነበሩትም ያህል ይሰማኛል። ይከተሉት ዘንድ ከተመረጡቱ ዐሥራ ሁለቱ መሃል አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ ነው። ማንም ይህን ስም ሲሰማ የጌታዬ ጠላት፣የአምላኬ ነጋዴ እያለ እየቀጸለ መውቀሱና መተቸቱን እናውቀዋለን። የይሁዳ ክህደት የዋለ ያደረ ቢሆንም ከዚያም ዘመን የተቀዱ ይሁዳዎች መብዛታቸው ግን አልተስዋለም። ቆም ብዬ ዐስብና ደግሞም ለአፍታ ኢየሱስን በመከተል ጓዳናዬ እርምጃዬን እገታና "የእውነትም ተከታዪ ነኝ?" ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። ረቡኒ ብዬ ብጣራው ከእግሩ ስር ልማር ብቀመጥም፥ ከእርምጃው ፈለጉን ልከተል ከኋላው ባዘግምም ... አንዳንዴ ግን የእርሱ የመምህሬ ነጋዴ ሆኜ እገኛለሁ። በእርሱ ያገኘሁትን ብቻ ሳይሆን እርሱንም ስሸጠው እገኛለሁ። ከፍላጎቱ ይልቅ ፍላጎቴ ይገንብኛል። ከፈቃዱ ምሪት ይልቅ የልቤ ዐሳብ ይገዛኛል። ጥዬው የተከተልኩት መረቤ ከእልፍ ጉዞ በኋላ ወደ ኋላ ያስናፍቀኛል። ስለ እኔው ትርፍና ለሥጋዬ ድሎት ስልማ "ሠላሳ ብር ኢየሱሴን መሸሸጥ እኔኑ የገንዘቡ መጠን ይጎዳኛል" ... እደራደርበታለሁ! "በጣም አስወደድከው! ኧረ ቀንስልኝ! ደግሞ ለዚህም! እያልኩ ኢየሱስን ከእኔው የገዛ ምኞት፣ከሐሰት ጉጉትና ከሽንገላ ስራዬ አሳንሼው እቆጥራለሁ። ከእንግዲህ ይሁዳ ላይ ጣቴን አልቀስርም። በይሁዳ ውስጥ እልፍ ይሁዳነቴን ተምሬያለሁ። ከራሴ ተማክሬ ከሠላሳውም አንሶብኝ ኢየሱስን አይቼዋለሁ። ውርደቱስ ለእኔ በገዛ ራሴ ተመርቼ ጌታዬን ነጋዴ ለሆንኩት። በጸጸት ነፍሴን ከማጠፋት፥ በንስሃ ሳልመለስ ከደጁ ርቄ እንዳልቀር ማስተዋልን እማጸናለሁ። @gkjourney1

Open in Telegram
Views94−54%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#3373Photo
Views175−15%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—

All posts

Connections