
ግጥም 🇪🇹
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ ግጥም እና የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።🙏🙏🙏 👏👏👏👏👏👏 ግጥሞቻችሁን ለመላክ እንዲሁም ለአስተያየት ይችን ይጠቀሙ @kidus15👍 ግሩፓችንን ይቀላቀሉ @kidapoimgroups
Latest posts
ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️✍️ ብዕር ባስለቀሰው የቅኔ ፊደላት እምባህን አብሰህ ቀን እስኪያልፍ ቢያለፋም የከፋው ገፅህን በፈገግታ አልብሰህ ወርቅ ማንነትህ በመዳብ የቃኙት ክብርህን ባይለካም ጠቢብ ካደላበት የውስጥህን ዓለም ህሊናህ ባይረካም ከፅናት ማህደር ጠብቀህ ያኖርከው ጥበብ ቢገነፍል የእውነት ልብ እንዳይሞት ስጋ ይንገላታል ነፍስ ዋጋ ሲከፍል
Open in Telegram( ያሬዳዊ ግጥም ) ያሬድ ከበደ ፖለቲካ አይደለም ✍️✍️✍️✍️ ትዝታ አንቺ ሆዬ በባቲና አምባሰል ቃኝተህ አፈ ሙዙን ከዘመነ ጊልዶ አሻግረህ እንድናይ ዘመነ ካሙዙን ሰምና ወርቅ ቅኔ ህልምም ይሁን ቅዠት ነውና እንደ ፈችው የፓርላማን አባል ከእቅልፉ ቀስቅሳ ጥበብ ከጠራችው በቀን ሶስት ጊዜ ባስማት የሚመግብ እስኪሰጠው መሪ የፖለቲካን መልክ በከፊልም ቢሆን መቀየር ከቻለ አንድ አቀናባሪ የነ እከሌን ዘፈን ሲሰማ ለኖረ ዳባ ለባሽ ጆሮ ምን ቢሰቀጥጥም መንግስት ዜማ ካለው ላድማጭ ነፃነት ሲል ህዝብ ይፅፋል ግጥም
Open in TelegramMy teacher Teacher I have no word You are the best in all the world ####### From the explanation To the description ####### From the experiment To the excitement ####### From the example To the collection of sample ####### You are the first not the last Your speech make us fast ####### May God give us another chance To thanks live in balance ✍pharez
Open in Telegramያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️✍️ ታሳ ጋሞ 😭😭😭😭😭 😭😭😭😭😭😭 እንደ ሐምሌ ወራት የሀዘን ጥል አጥልቶ ከጋሞ ሰማይ ስር ሞትም ከነ ጓዙ እያጉረመረመ ቁልቁል ጣት ሲቀስር መቼም አንዳንድ ቀን ሰኔና ሰኞ አይነት እንደ ገጠመ እጣው ሰው ፈልጌ ብሄድ ዛሬ ግን ሰው አጣው አውድማውን ብቃኝ በሬ'ሳላይ መጣው ታዲያ በዚህ መሀል,,,,, ያየሁትን ሁሉ ውስጤ አላምን አለኝ ደስታን የሚሰጥ ህዝብ በሀዘን ሲቀበለኝ ትህትና ፍቅራቸው መልካምነታቸው እጅጉን የበዛ እንደ ባህል ወጉ ፈትሎና ሸምኖ ሚያለብሰው ድንጉዛ ዛሬ ምን ገጠመው ቅን ልቡ ሲሰበር በሀዘን ስንክሳር ጌታ ሆይ እባክህ በቶሎ ታረቀን ይላል የጋሞ ህዝብ ቀንጥሶ እርጥብ ሳር
Open in Telegramያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️ " " እኔ በፊትህ መቆሞ ባልችልም በፅድቅ ሚዛን እየፀፀታት ልቤ ተሰብራ በርጠሚዎስን ከንቱ ይመስል ዛሬ ካልሆነ ብዬ ማስቸግር አይኔ ካልበራ ከምኞት ይልቅ ፈቃድህ ሆኖ ትፈፅመው ዘንድ እስከምታደል ምርኩዝ ጨብጬ ጭፍን ስራመድ ዳር ዳሩን እንጂ ባላይም ገደል ጥውልግ ተስፋዬን አለምልመኸው ከወደኩበት እንደተነሳው እንደ መፃጉ እልፍ ውለታህን ቀለል አድርጌ ስለምረሳው ከተሳሳቱ እርምጃዎቼ ቀናውን መንገድ በል ምራኝና የእውነት አቅጣጫን አንተ ጠቢብ ሆይ ታምር የሰሩ ውብ እጆችህን በራሴ ላይ ጫን
Open in Telegram፡ ሆነሽ ሳለ ቆንጂዬ ልጅ 'ምታሳሳ 'ምትወደድ ቢኖርሽም አፍቃሪ ልብ መልካም ሀሳብ ቀና መንገድ ወትሮ እኔን መንከባከብ ባይታክትሽ ማስደሰቱ እውነት እውነት እልሻለሁ ማፍቀር ላልችል ደከምሽ እቱ እያሰብኩኝ የሆንሽውን እየታየኝ ውበት መልክሽ ያለሽን ግልፅ ፅኑ አቋም የሚደነቅ ፀባይ ልክሽ እየጣርኩኝ ላለማጣት ካንቺ ደጃፍ እግሬ እንዳይቀር ላይሆንልኝ ደከምኩ እንጂ አይቻልም ታግሎ ማፍቀር Join 👇👇👇👇 https://t.me/getmtg
Open in Telegram






