Account
የሶላ ደብዳቤ

የሶላ ደብዳቤ

ጣዕመ #ግጥሞች #ደብዳቤዎች #ድርሰቶች #ወጎች ፤ አነቃቂ ፅሁፎች ለዛ ባለው አቀራረብ አዋዝተን እናቀርባለን። ኑ ከጥበብ ማዕዳችን እንቋደስ ... << ነገ ላይ ቀድሞ የሰፈረ የለም ፤ ተስፋ እስካለ ግን መኖር መልካም ነው >> #መፃፍ_ይቀጥላል ( ሶላ እንደፃፈው ) @Mel_akuM21 ግጥም የኪነጥበባት ሁሉ የደም ጠብታ ነው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

Username
@ammelakuletters
Category
Art
Country
EthiopiaEthiopia
Created
, 8 years
Subscribers1,123
Avg views per post, 7d—last 7 days
ERR17.19%30-day average

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 2, 2026218
Nov 4, 2026168

Latest posts

#5895Link preview

<< ግራ እጄ እና ቀለበት ጣቷ... >>        ደራሲ ፦ ሶላ ✍ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዛሬ ደግሞ አርፍዳለች ... ካወኳት ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የሚያረፍድ ሰው አልወድም ስትለኝ አልነበር ...ወይስ ለሷ ማርፈድ ማለት ቀድማ ስትገኝ ብቻ ነው ! ... መቅረት የሚሉት ነገር ስላለ በማርፈዷ አላማረርኩም... እኔን ያስጨነቀኝ ምን እንደምጋብዛት ነው ... አስተናጋጁ ያመጣልኝን አንድ ማኪያቶ ለ45 ደቂቃ ሳቆይ Takeaway እንዳልለው ፈርቶ ይሆን እጄን ልታጠብ ብዬ እንዳልሮጥ ብቻ አስተያየቱ ደስ አይልም ... አሁን የትኛው የአማኑኤል ታማሚ ነው ለማኪያቶ እጄን ታጥቤ ልምጣ የሚል ! ... አይኑ ስላስፈራኝ ልጋብዛት ያሰብኩትን ማኪያቶ እንዲደግመኝ አዘዝኩት ... ምን ሲቆላኝ ነው ላግኝህ ስትለኝ እሽ ያልኳት ?  አስተናጋጁ ያቀረበልኝን ልጎነጭ ጎንበስ ስል << የማያልፍለት ድሀ ሀብታም ይጋብዛል ! >> ብላ  በፈገግታ ዲዛይን በተሰራልኝ ማኪያቶ ላይ ስትስቅ ምስሏ ታየኝ ... ከፈገግታው ዲዛይን ስር የሚታየው ነጭ ወተት ጥርሷን ስለሚመስል ማኪያቶውን ሳይሆን እርሷን ያመጣልኝ መሰለኝ .   ሰዓታት አርፍዳ መጣች ... ላቅፋት ሁለት እጄን ስሰድ ቀኝ እጄን ጨብጣ የጉንጯን ከንፈር ከጉንጬ አሳሳመች ... የድርሻውን ስላጣ ግራ እጄ ቅር ቢለውም ሌላ ቀን እምደማስቀድመው ስነግረው ተረጋጋ ... እርሷ ግን መረጋጋት አልቻለችም  ... አስር ጊዜ ፀጉሯን ትፈትላለች ... ለአጭር ሰከንድ ታየኝ እና ለደቂቃ ግራ ጣቶቿን ታየዋለች ... አዲስ ጥፍር ቀለም ገዛች እንዴ እያልኩ አይኗን ተከትዬ ጣቷ ላይ ማፍጠጥ ጀመርኩ ... አዲስ ነገር አልታይ አለኝ ... አስተናጋጁ ሊታዘዛት ሊመጣ ሲል በእጇ ምልክት መለሰችው .... ቀለበት ጣቷን እየዳበሰች በድንገት ካፏ << ላገባ ነው >> የሚል ቃል አወጣች ... ጋብቻ የሞት ጥላ ስለሚመስለኝ ደነገጥኩ ... ጨርሼ ስላልሰማዋት ነው እጂ ስለ ጊልዶ ዘፈን ነው የምታወራው ብዬ ራሴን ላረጋጋ ሞከርኩ  ... ደገመችው << አልሰማከኝም ላገባ ነው እያልኩህ ነው ! >> << ሰምቼሻለሁ >> << እና ምን ይዘጋሀል >> ( ያገባችን መስሏት ልትጨቃጨቀኝ ነው እንዴ? ) << ማንን እንደምታገቢ ግራ ቢገባኝ ነው >> ቀጠልኩና << ልጁ ግን ማነው ?>> አልኳት << አታውቀውም ! >> << ስለማላውቀውማ ነው የጠየኩሽ ! >> ስላት ፊቷን ወደ ካፌው በረንዳ ወርውራ አንድ ወጣት ጠቆመችኝ ... ጀርባውን አየሁት .... በልጅነታችን በጭቃ እንደምንሰራው ብይ የተድቦለቦለ 4በ4 የሆነ አጭር ነገር ነው ... በጣም ከማጠሩ የተነሳ እሷ ያደረገችውን ሂል ጫማ እንኳን ቢጫማ ወገቧ ላይ አይደርስም ... የኋላውን ገፅ ካየሁ በኋላ የፊተኛው ገፁን መገመት ጀመርኩ ከኋላ በኩርኩም ቢባል የሚረግፍ ትልልቅ አይን ፣ እንደ እኔ ከችግር የሚሰፋ አገጭ ፣ የድሮ የቴሌቪዥን ጀርባ የሚመስል ቦርጭ ያለው ሆኖ ታየኝ ... ከሀሳቤ ስመለስ ማውራቷን አንዳላቆመች አስተዋልኩ . << ወጌን ሳላይ ፤ ሳላገባ እድሜዬ እኮ ሊሄድ ነው >> << ከዚህ በላይ >>  ብላት ታንቀኛለች  ...  መልስ አልሰጠዋትም ... ደግማም አልጠየቀችም .... ከካፌው ጫጫታ በዝምታ የምንተነፍሰው አየር ወደ ጆሮዬ ይወርዳል ... የትዝታዋን ካሴት መታ መታ አድርጌ ከፈትኩ ... ድንገት መናገሯ እንጂ ለማግባት መውሰኗ ስህተት መስሎ አልታየኝም .... ሳቋ እና ስትስቅ የሚሰምጠው ጉንጫ ፤ ጨዋታዋ ፤ ቁም ነገሯ ፤  ደስ ይለኝ ነበር ... ዳሩ ግን ፍቅር ጋር  አይደርስም . << ዝም አልክ ምነው ?>> አለች ከንፈሯን ጣል አድርጋ << ይገርማል አንድ ምሽት  የህይወታችንን አቅጣጫ ለወጠች ማለት ነው ?>> አልኳት << ይገርማል አይደል  ህይወት  ግራ ነች >> አለችኝ በአንድ ምሽት ሀሳቧን ምን እንዳስቀረው መጠየቅ አልፈለኩም ፤  እንድትቀይርም አልጠብቅም << ይህቺ ምሽት ባትኖርስ በእኔ እና አንቺ መሀል ምን ይፈጠር ነበር ?>> አልኳት << አላውቅም ፤ ህይወት እና ነገ እኮ አይታወቁም !>> ብላ በመስኮቱ ማዶ አይኗን አሻግራ ተመለሰች ... አይኗን ታዘብኩ . << መቼም አይናችንን ጨፍነን የምናልመው እና ስንገልጥ የምኖረው ለየቅል ነው ... እኔ ገና አልነቃሁም ፤  አንቺ ግን ስለነቃሽ መኖር መጀመር አለብሽ >> አልኳት በውስጤ ... ቀና ብላ ስታየኝ ውስጤን የሰማችው መስሎኝ ፈገግ አልኩላት . የእርሷንም የእኔንም እጆች አየሁ ... ቀኝ እጆቻችን ላይ የሰላምታችን አሸራዎች ተቀርፀዋል .... የተቀሩትን እጆቻችንን አስተዋኩ ፤ የኔ ግራ እጅ  ለሰላምታ ይናፍቃል ... የሷ ቀለበት ጣት ግን አዲስ ደስታ ፤ ህይወት እና የነገን የተስፋ ይናፍቃል ... ህይወት ግራ አይደለች << የሱንስ አላውቅም ... አንቺ ግን ዛሬ  ያረፈድሽው የሰርጌ ቀን እስኪደርስ ልለማመድ ብለሽ ነው ?>> አልኳት ፤ ሶስታችንም አንድ ላይ ሳቅን ፤ አስተናጋጁ ግን ተኮሳትሮ እንዳየኝ ነበር .     እኔም እንዳንተ አላዘንኩም ሄጄ ልበለው ? ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨     #ስላነበባችሁት_ከልብ_አመሰግናለሁ https://t.me/Ammelakuletters #Repost / መስከረም 2014 / ( ፅሁፎቼ እንደኔ የናፈቃችሁ push me as u can ) @mel_akuM21

Open in Telegram
Views218+13%vs avg
Forwards1
Reactions5
Comments0
#5894Text

Forwarded from 📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ

Real story #101 ዛሬም በስራ ጉዳይ መሸብኝ እና ታክሲ አጥቼ አጎቴ ጋር አሳድረኝ ልለው ደወልኹ...         ...ስልኩ ጠራ... አጎቴ አነሳው (አጎቴ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው...) : "ልጅ ሶፎንያስ የጌታ ሰላም ይብዛልህ እንደምን አለህ?" መልሴን አልጠበቀም "ምነው በዚህ ሰዓት ደወልኽ በሰላም ነው?" እኔ : "አዎ አጎቴ በሰላም ነው መሸብኝና ለእናንተ አካባቢ ቅርብ ስለኾንኹ መጥቼ ለማደር ላስፈቅድህ ነው..." አጎቴ : "ቤትህ አይደለም ምን ታስፈቅደኛለህ ? በጌታ ሰላም ና ።" መልሱ ፈገግ እያሰኘኝ ስልኩን ዘጋውት እና ወደቤታቸው ሄድኹ። ቤታቸው ስደርስ ቤቱን ደመቅመቅ አድርጎት ጠበቀኝ...ደስ አለኝ...አጎቴም ሲያየኝ ደስ አለው "ሸምግለህ የለ እንዴ ልጅ ሶፎንያስ ሃሃሃ በጌታ መንፈስ ተመርተህ እቤቴ መጣህ..." "ታክሲ አጥቼ ነው አጎቴ " አለኹት ከፈገግታ ጋር ድንገት መምጣቴን ለመንገር..."ቢኾንም ጌታ ካልፈቀደው የሚኾን የለም..." አለኝ ንግግሬን አቋርጦ እንድቀመጥ እየጋበዘኝ... ቡና ተፈልቶ ቴሌቪዥን መመልኽት እንደጀመርን አስታውሳለሁ...በቴሌቪዥን መስኮት የጦር አውሮፕራኖች እየታዩም ነበር...አጎቴ ወሬውን ትክዝ ብሎ "አለም ላይ ያሉት ኃያላን ሀገራት ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ እናሸንፈዋለን ብለው ነው ጦራቸውን የሚያደራጁት ..." ብሎ እንደዠመረ አስታውሳለሁ...ነገር ግን በየት በኩል መፅሐፍ ቅዱስ ገልጦ ከዘፍጥረት ዠምሮ መተንተን እንደዠመረ አላስታውስም...አኹን የእስራኤላውያን ታሪክ ላይ ደርሰናል...እስከ ነገ ጌታ ከፈቀደ አዲስ ኪዳን እንደርሳለን...አጎቴ ደስ በሚል Energy እያብራራ ነው...እኔ እንቅልፍ እያማለለኝ ነው በዚህ ሰዓት ምንም ቢለኝ እስማማለሁ...ሲነጋ ግን የሐይማኖት አቋሜን አስቀምጬ ነው የምወጣው... በጌታ ሰላም- ሰላም እደሩ #repost ©ሶፊ

Open in Telegram
Views448+132%vs avg
Forwards1
Reactions5
Comments0
#5892Photo

Forwarded from Sami fashion

1800

Open in Telegram
Views682+253%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments0
#5890Photo

Forwarded from 1137439312:AAGumjHJ7pzA6vrrfVMlKoqTUsCs59GySrg

No text

Open in Telegram
Views856+344%vs avg
Forwards0
Reactions—
Comments—
#5888Text
Views352+82%vs avg
Forwards5
Reactions5
Comments0
#5887Text
Views925+379%vs avg
Forwards8
Reactions—
Comments0
#5886Text
Views806+318%vs avg
Forwards2
Reactions10
Comments0

All posts

Connections