ፍቅርተ ክፍል 18❤ ወደ እቤት ገባሁኝ እናም ቁጭ አልኩ ከላይ አቤል እየመጣ እንደሆነ የሚያሳየኝ የጫማ ኮቴ ሰማሁ ያው ሲያስጨንቀኝ ነበረውን ነገር ሊነግረኝ አይደል ደስ እያለኝ ማንጋጠጤን ቀጠልኩ ሲመጣ ግን አፈርኩኝ እንዴ ቆይ ትንሽ ነገር ደረብ አድርጎ አይመጣም እንዴ አይኔ እኮ ከደረቱ መንቀል አልቻለም እንዴ ቆይ እንደዚህም የሚያምር ደረት አለ ወይ ሲክስ ፓክ እራሱ አለው ጎዶሎ ሳይሆን ሙሉ ሲክስ ፓክ ልክ ወደ እኔ እየቀረበ ሳመጣ ግን አይኔን ሰበር አረኩት አቤልም ሳቅ እያለ << ቆየ ሁብሽ አይደል ትንሽ ሪላክስ ላድርግ ብዬ ነው ምን የሚጠጣ ላምጣልሽ>> አለኝ እኔስ መቆየቱ አልታየኝም ነበር ውጪ ላይ ከ ጠንባዛው ዘበኛ ጋር እያወራሁ ጊዜው ሲሄድ አልተሰማኝም ነበር ደሞ የምን የሚጠጣ ነው አልኮል ነገር ነው የሚለኝ እያልኩ እያሰብኩ <<ፍቅር ዛሬ ምን ሆነሻል አስደበርኩሽ አይደል እሺ ምን ልቀጣ>> አለኝ እኔም በፍጥነት እኔ ጋር ሁን ሰው ያስፈልገኛል ታስፈልገኛለህ በቃ አሁን በብቸኝነት ስሜት ውስጥ እየተሰቃየ ነው አለው አልከኝ የታለህ እዚህ የምን እንደመጣሁ እራሱ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለህም ቆይ ምን አይነት ሰው ነህ ልለው ብዬ አሰብኩና መልስ ብዬ ምንም ብቻ የምጠይቅህን በስርአት መልስልኝ አልኩት እሱም የቀድሞውን ፈገግታ በከንፈሩ እየሸፈነ << እሺ አልኮል ነገር አምሮኛል ይዤ ልምጣ >> ብሎ ተነሳ እኔም እሺ ብዬው እዛው ቁጭ ባልኩበት እንባዬ ይፈሱ ጀመረ ጓደኞቼ እንኳን ለምን ይሄን ሁሉ ቀን ቀረሽ አላሉኝም በቃ ዝም ብለውኛል ቤተሰቦቼ ያላወሩኝ ነገር የደበቁኝ ነገር እንዳለ ውስጤን ይሰማኛል የሆነ የሚከብድ ነገር እንደሆነ ውስጤን ታውቆኛል አቤልም መጣ ቶሎ ብዬ እንባዬን ጠረኩትና ማውራት ጀመርን <<ልቅዳልሽ ?>>አለኝ እኔም መጨነቅ ስለደከመኝ ምን አልባት ካስረሳኝ በሚል ጠማማ ሀሳብ እሺ አልኩት እየቀዳልኝ ወሬውን ቀጠልኩ አቤል? ስለው <<ወዬ ፍቅር >> አለኝ አቤል ትምህርት ሲዘጋ ወደ እቤት እመለሳለዋ አልኩትኝ እሱም ትንሽ ፈገግታ እያሳየኝ << አትመለሺም ፍቅር ከዚህ በውሀላ እዚሁ ነው የምትኖሪው እንኪ ጠጪ>> ብሎ መጠጫውን ሰጠኝ እኔም ነገሩ ጭራሽ ግራ እያጋባኝ እንዴ ቆይ ቤተሰቦቼስ እነሱንስ አላገኝም እንዴትስ ሆኖ ነው ነው ወይስ እዚህ አንተ አለህ አልኩት ድምጼን ከፍ እያረኩ መጣሁበት መሰል በትኩረት እያየኝ ወደ እኔ አጠገብ መጥቶ ተቀመጣ መጀመሪያ ላይ እኔ ከነበርኩበት ፊለፊት በነበረ ሶፋ ላይ ሲሆን አሁን ደሞ ከ አጠገቤ ይገኛል አትኩሮ በሚያማምር አይኖቹ እያየኝ <<የኔ ፍቅር ታውቂያለሻ እንደስምሽ ፍቅር የሆንሽሴት እንደሆንሽ >> አለኝ የቅድሙ ቁጣዬ ለፍቅርና ለመረጋጋት ቦታ ሲለቅለት ይታወቀኛል አቤት አይኖቹ እኮ የጉድ ነው አይወራም እኔም የምለው እየጠፋኝ አትቀልድ ባክህ አሁን የጠየኩህን መልስልኝ ብዬ እኔም ባላሰብኩት እሱም ባላሰበው መንገድ አንስቼ መጠጡን ቅጥም አረገኩት እኔም ሰውነቴን በሙሉ ንዝር ሲያደርገኝ ያው ጠጥቼ ስለማላውቅ እኮ ነው እሱም እንደ መደንቀጥ እያለ << እንዴ ፍቅር ቀስ ብለሽ ጠጪ እንጂ እንደዚህ እኮ አይጠጣም>> አለኝ ምንም አላልኩትም ነበር አሁንም ቀን አይኑ ከአይኖቼ ሳይነቅል ስንተያይ ቆየን ጥያቄውስ ካላችሁኝ ተውኩት በቃ እረሳው አሁንማ እሱም ተመቸው መሰለኝ ወደ እኔ መቅረቡን አጧጧፈው እኔም ደንገጥ እያልኩኝ ለመሸሽ እሞክራለሁ ያው አንድ እርምጃ ስቀርበው እሱ ሁለት አረገው ከዛ እኔ ዜሮ ሁንኩኝ እሱም ዜሮ ስሆን ገባሁና << ፍቅር ካልተመቸሽ እንተኛ >> አለኝ እንደው ምን አይነት ቅልብልብ እንደሆንኩ ምንም ነው የማይገባኝ ሰው ትንሽ ይረጋጋል እኔ በቀጥታ አብረን ነው የምንተኛው እረ ደፋር አልፈልግም ብቻዬን ነው የምተኛው አልኩትና የቀዳልኝን መጠጥ መልሼ በአንድ አፍ ጭልጥ አርጌ ተነሳሁ ገርሞታል በጣም አቤል በአግርሞት የማረገውን እያየ የማወራውን ያዳምጠኛል ልነሳ ስል ግን አዞረኝና..... ይ....ቀ...ጥ....ላ...ል❤
Open in Telegram
🕯️የህላዌ ብዕር✍️
🖋️የህላዌ ብዕር🕯 ስሜት በቃል… ቃልን በብዕር… ✨ እንኳን ደህና መጡ! ✍️ መፃፍ ውስጤ ነው… ስሜትን በቅኔ፣ ትዝታን በወግ፣ ሕይወትን በገጠመኝ፣ ምናብን በልቦለድ እተርካለሁ። 🌿 ወግ • 🌸 ግጥም • 🕰️ ገጠመኝ 📖 አጭርና ረዥም ልቦለድ ስለ፦❤️ ፍቅር • 🕊️ ሐዘን • ✨ ትዝታ • 🌱 ሕይወት ሁሉንም ታገኛላችሁ… አንዳንዱን ታነባላችሁ፤ አንዳንዱን ደሞ በልባችሁ ታነቡታላችሁ። 🖤
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 20, 2026 | 357 |
| Nov 21, 2026 | 415 |
| Nov 22, 2026 | 438 |
| Nov 23, 2026 | 335 |
| Nov 24, 2026 | 100 |
| Nov 25, 2026 | 144 |
Most viewed this month
- 01Views834Forwards—Reactions19Comments—
- 02Views536Forwards—Reactions30Comments—
- 03Views389Forwards—Reactions21Comments—
- 04Views367Forwards—Reactions19Comments—
Latest posts
ከሞተች በኋላ ከሚበላው ምስጡ አካሏን ቀብራችሁ ልቧን ለኔ ስጡ ቆርጬ ረብርቤ ላድርገው መሰላል ልቧ ብዙ ነገር መሸከም ይችላል (እምዬ😍)
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 116 |
| 3 h | 207 |
| 5 h | 289 |
- After 1 hour116
- After 6 hours289
- Total to date289
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 14 |
| 4 h | 79 |
| 7 h | 135 |
- After 6 hours135
- Total to date135
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 1 h | 37 |
| 2 h | 73 |
| 4 h | 90 |
- After 1 hour37
- After 6 hours90
- Total to date90
Views growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 6 h | 51 |
| 24 h | 206 |
- After 6 hours51
- After 24 hours206
- Total to date206
"እናትሽም እንዳልሽው አድርጋ ነበር ነገር ግን ሁሉንም መጥተው ገደሏቸው፤ለእኛም ይሄ መንገድ አይጠቅመንም ያልኩሽ ሁላችንንም እንዳይገድሉን ነው፤በዚህ በቀል ውስጥ በጭራሽ ፖሊስ የሚባል ነገር አይገባም።" "አዎ ልክ ነህ ታድያ ምን ልናደርግ ነው?" "እቅዳችንን ለማውጣት ብዙ ጊዜ ይፈጃል፤ግን እቅዳችንን እያሰብን ጎን ለጎን ሌላ ነገር እንድናደርግ አስቢያለሁ።" "ምንድነው ያሰብከው?" "እኔ አንቺ እና እህትሽ ራሳችንን መከላከል መሰልጠን አለብን።" "እ?ራሳችንን መከላከል ማለት?" "እኔ በእግሬ ለመሄድ መታከም አለብኝ፤እናንተ ሁለታችሁ ደግሞ ሽጉጥ መተኮስ፣ካራቴ ቦክስ እና ቴኳንዶ መሰልጠን፣ዋና መዋኘት፣ወታደር የሚሰለጥናቸው ስልጠናዎችን መሰልጠን እና መኪና በፍጥነት መንዳት.....ግን መኪና መንዳት ሁለታችሁም ትችላላችሁ ብዬ አስባለሁ።"አላት። "አይ አጎቴ መኪና መንዳት ሁለታችንም አንችልም።" "እ?እስካሁን አትችሉም?እሺ እህትሽ መኪና ስላልነበራት ነው አንቺ ግን መቻል ነበረብሽ።" "እኔ ለምን እስካሁን እንዳልቻልኩ አላውቅም፤ለምንድነው ባለመቻሌ ጥፍተኛ የምታደርጉኝ?" "ጥፋተኛ ስለሆንሽ ነው ጥፋተኛ ነሽ ያልኩሽ።" "ቆይ አሁን እህቴ ስልጠናውን መሰልጠን አለባት፤ግን ምን ብለን ነው የምናስረዳት? እንዴት ነው እሺ የምትለን?" "እህትሽን በትንሽ ነገር ማሳመን ካልቻልሽ እንዴት ነው እነዛ ሰዎች ፊት የምትቆሚው?" "እነዛ ሰዎች ለኔ ጠላቶቼ ናቸው እሷ ግን ብቸኛ እህቴ ናት እሷን ማጣት አልፈልግም።" "ብቸኛ እህትሽን ላለማጣት ከፈለግሽ ከዚህ በቀል መውጣትሽ ብቻ በቂ ነው።" "አታስብ አጎቴ!እኔ ስልጠናውን እንድትወስድ እህቴን አሳምናታለሁ።" "ጥሩ...ግን ተጠንቀቂ መጠርጠር የለባትም።" "እሺ አትጠረጥረኝም።"አለችው። ክፍል-16 በቅርቡ ይቀጥላል... ❤💌🔁
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 70 |
| 24 h | 226 |
- After 6 hours70
- After 24 hours226
- Total to date226
"አጎቴ!አንተም እንደእኔ የወላጆቼን ገዳይ ለመበቀል ትፈልጋለህ?" "እ....እ?በቀል?" "አዎ ገዳዮቹን መበቀል አትፈልግም?እኔ ግን በጣም እፈልጋለሁ።" "እየውልሽ የኔ ልጅ በቀል እንደምታስቢው ቀላል አይደለም፤በዛ ላይ የወላጆችሽን ገዳዮች በጣም ሀይለኛ ሰዎች ናቸው።" "የእኔ በቀል ከእነሱ ሀይል የሚያንስ ነው የሚመስልህ አጎቴ?" "ለሀያ አመታቶች ስለእነሱ ሳጣራ ነበር ግን ነገሮች ቀላል አይደሉም።" "ከሀያ አመት በፊት የጀመርከውን ከባድ ነው ብለን መተው አንችልም።" "ቃል የኔ ልጅ ትናንት ከእህትሽ ጋር ያወራሽውን እረስተሽ ነው?እህትሽ ስለበቀል እንኳን ስታወሪ ከሰማችሽ ድጋሚ እህቷ እንደማትሆኚ ነግራሽ ነበር አይደል፤ቆይ ስለ መንታ እህትሽ አታስቢም?" "ለእህቴ በቀላችንን ከጨረስን በኋላ እናስረዳታለን፤ስለዚህ እህቴን እርሳት እና በቀላችንን እንጀምር።" "እህትሽ ብትሰማ ምን ሊፈጠር ነው?ያለፈውን እርሺ እና ስለ ወላጆችሽ ምትክ ስለብቸኛ እህትሽ ብቻ አስቢ።" "አጎቴ በዚህ ነገር ባታግዘኝ ብቻዬን ማድረጌ አይቀርም እውነቴን ነው።" "ኡፍፍፍ አንቺ ልጅ በቃ አቁሚ ይኼንን በቀል ለኔ ተይው አንቺን ችግር ውስጥ መክተት አልፈልግም፤አንቺ እኮ የአደራ ልጄ ነሽ።" "እሺ አንተ ባታግዘኝም እኔ በራሴ አደርገዋለሁ፤በቀሌን እበቀላለሁ።" ብላው ከተቀመጠችበት ተነሳች እና ልትወጣ የቢሮው በር ላይ ስትደርስ፦ "ነይ በቃ አሁን እናውራ።"አላት አጎቷ ኢያሱ። "የምናወራው ስለ በቀላችን ብቻ ከሆነ ነው የምመጣው አጎቴ።" "እሺ አልኩሽ አሁን ነይ እና ተቀመጪ።" "ሌላ ምክር አልፈልግም የምናደርገውን ነገር ነው የምናወራው።"ብላ ተመልሳ ተቀመጠች። "ምን አይነት ደረቅ ልጅ መሆንሽን ታውቂያለሽ? " "አዎ አውቃለሁ!አሁን ወደ ጉዳያችን እንግባ።" "እሺ!...እንደነገርኩሽ ለሀያ አመታት ነበር ስለገዳዮቹ ማጣራት የጀመርኩት እና አሁን ስለ እነሱ አጣርቼ ጨርሼአለሁ፤አሁን በምን መልኩ እንደምንጀምር ደግሞ በጣም ጥሩ እቅድ እያወጣሁ ነው።" "ታድያ ስለ እነሱ ለሀያ አመታት ያጣራኸው ነገር ምንድን ነው?" "እነዚህ ሰዎች ከተማችን ውስጥ ያሉ ማደጎ ቤቶች ውስጥ ከ14-18 አመት ያሉ ሴቶች ልጆችን ሴተኛ አዳሪዎች ያደርጓቸዋል ከዛ እድሜያቸው ከፍ ሲል ሁለት ምርጫዎች ይሰጧቸዋል፤አንደኛው ምርጫቸው በዚሁ ስራቸው ፀጥ ብለው እየሰሩ እንዲኖሩ ነው።ሁለተኛው ደግሞ መሞት እና የሰውነት አካል ክፍላቸውን አውጥተው በውድ ዋጋ መሸጥ ነው፤ነገር ግን ሴቶቹ በጣም ጥሩ ደንበኞች እና ገቢ የሚያስገኙ ከሆነ አደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በዛ ቆሻሻ ስራ ውስጥ ብዙ አመት እንዲሰሩ ያደርጓቸዋል።"አላት። "በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው።" "አልጨረስኩም!ሌላኛው ስራቸው ቀናቸው ያለፉ ምርቶችን እውነተኛ አስመስለው መሸጥ፣አደንዛዥ እፅ እና የጦር መሳሪያዎችን እያስመጡ በድብቅ መሸጥ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ስራዎቻቸው ናቸው፤የሰውን ገንዘብ አታለው መውሰድ፣ሰው መግደል ለነሱ በጣም ቀላል ከሚባሉት ስራዎች ውስጥ ይመደባሉ።" "አሁን ታድያ እቅድህ ምንድን ነው?" "እስካሁን ስለ ስራቸው ስለአለቆቻቸው እና ስለሰራተኞቻቸው ፀባይ አጣርቻለሁ፤ግን ስለእቅዱ ገና አላሰብኩም።በጣም ውስብስብ ነው ብዙ ጊዜ ያስፈልገናል።"አላት። "እኔ ጥሩ ሀሳብ አለኝ።ለምን ያለንን ማስረጃዎች ይዘን ክስ አንመሰርትም ከዛ እስር ቤት ለዘላለም ይኖራሉ።" "እሱ መንገድ ለኛ በቀል አይሆንም።" "ለምን አይሆንም?እንደውም ቀላል መንገድ ነው፤እነዚህ ሰዎች ለዘለአለም ያለ ነፃነት ይኖራሉ።"
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 48 |
| 24 h | 178 |
- After 6 hours48
- After 24 hours178
- Total to date178
"እ..እ ስልኬን ክፍልሽ ውስጥ እረስቼው መጣሁ፤በቃ ቶሎ ይዤ ልምጣ አንቺ እዚሁ ጠብቂኝ።"አለች አዲስ። "እሺ ቶሎ በይ።"አለቻት ቃልኪዳን። አዲስ ኪዳንም ወደ ቃል ኪዳን ክፍል ሄደች እና የናሆምን ልብስ በያዘችው ቦርሳ ውስጥ አደረገችው እና ወደ ቃል ኪዳን ተመለሰች፤እነሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ።ቤታቸው ከደረሱ በኋላ ወደ ሶፋው ሄዱ እና ተቀመጡ። "ነገ እናት እና አባቴ ጋር እሄዳለሁ፤ እንዴት እንደሆኑ ማየት እፈልጋለሁ።"አለች አዲስኪዳን። "እሺ።" "አብረሽኝ አትመጭም?" "ከጠዋት ትምህርት አለኝ እንጂ አብረን እንሄድ ነበር።" "ሙሉ ቀን እዛ ነው የምውለው፤ ትምህርት ስትጨርሺ ከሰአት ነይ።" "ካልደከመኝ ቀጥታ እመጣለሁ።" "እሺ አሁን ወደ አልጋችን እንሂድ ጠዋት እንገናኛለን ደህና ደሪ።" ብላት ወደ ክፍሏ ሄደ፤ቃል ኪዳንም ወደ አልጋዋ ሄደች እና ተኛች፤በህልሟ አንድ ጭንብል ያደረገ ሰውዬ እናቷን ኤልዳናን እያሯሯጣት ነበር በያዘው ሽጉጥ ከጀርባዋ በሽጉጥ ተኩሶ ይመታታል ከዛ በጣም እየጮኸ ይስቃል።ቃል ኪዳንም በርግጋ ከእንቅልፏ ተነሳች፤ስትነሳ ጠዋት ሆኖ ነበር፤አዲስ ኪዳንም ጠዋት ተነስታ ለእሷ እና ለእህቷ ቁርስ አዘጋጅታ እና አብረው ይበሉ ነበር። "ምን ሁነሽ ነው ፊትሽ ከብዶታል፤ ደህና ነሽ?"አለች አዲስ ኪዳን ቃልኪዳንን እያየች። "ደህና ነኝ ምናልባት በደንብ አልተኛሁ ይሆናል።" "ቁርስ ስትበይ ቀለል ይልሻል።"አለቻት በደንብ እንድትበላላት። "እኔ መቼ ነው ግን ቁርስ የምሰራልሽ?"አለች ቃልኪዳን። "አንድ ቀን ትሰሪልኛለሽ።"አለች አዲስኪዳን። "ደግሞ የምትሰሪው ምግብ በጣም ይጣፍጣል፤እናንተ ቤት በቆየሁበት ቀናት ምግብ መስራት እንደማትችይ ነበር የሰማሁት፤ግን በጣም ጎበዝ አብሳይ ነሽ።"አለቻት ምግቡን በደንብ ባትበላም እንደወደደችው እንድታውቅላት። "አዎ.....እኔ ምግብ የሚባል መስራት አልችልም።"አለች አዲስኪዳን። "ይኼን የምበላውን ታድያ ማን ሰርቶት ነው?አንቺ አይደለሽ የሰራሽው?"አለች ቃልኪዳን ወደ ምግቡ እየጠቆመቻት። "በጣም ብዙ ጊዜ የሰራሁበት ምግብ ቤት አለ እዛ የሚሰሩት ምግብ በጣም አሪፍ ነው፤አሁን የምንበላው ቁርስ ከዛ ምግብ ቤት ነው ያዘዝኩት እንጂ እኔ አልሰራሁትም።"አለች አዲስኪዳን። "እ...እ?ከምርሽን ነው?" "እውነቴን ነው።እኔ ምግብ መስራት አልችልም፤ጨው እና ስኳርን መለየት እንኳን አልችልም።"አለች አዲስ። "ገባኝ! እኔም ማብሰል አልችልም ግን ጨው እና ስኳርን መለየት እችላለሁ።" "ጨው እና ስኳር መለየትሽ አንድ ጥሩ ነገር ነው፤ቆይ ስኳር ነው ጨው ነው የሚመረው?"አለች አዲስ ኪዳን። "ጨው ነው።ግን እኔም አንቺም ምግብ መስራት ካልቻልን ሁሌ የውጭ ምግብ እያዘዝን ልንበላ ነው?" "ምግብ የሚሰራልን ሰው መቅጠር እንችላለን።" "ጥሩ ሀሳብ ነው እኔ የማውቃት ሼፍ አለች እሷን ላናግራት እችላለሁ።"አለች ቃልኪዳን። "ስለእሱ አንቺ ታውቂያለሽ እንደሚሆን አድርጊው።"አለች አዲስኪዳን። "እሺ።በቃ ልሂድ እንዳይረፍድብኝ እንገናኛለን በቃ ቻው።" ብላት ሄደች።አዲስ ኪዳንም ወደ አሳዳጊዎቿ ጋር ሄደች፤ቃል ኪዳን ወደ ትምህርት ቤት ደርሳ ክፍል ውስጥ ሆና ያየችው ህልም ትዝ እያላት ሀሳብ ይዟት ይሄዳል፤የመበቀል ፍላጎቷ እጅግ እየበዛ መጣ።ያየችው ህልም በጣም ይመላለስባት ነበር በተለይ በህልሟ ውስጥ እናቷን ከገደለ በኋላ እየጮኸ ሲስቅ የነበረው ሰውዬ ድምፅ በጣም ይሰማት ነበር፤ትምህርቱ እንዳለቀ ቀጥታ ከክፍል ትወጣ እና ወደ አጎቷ ኢያሱ ትሄዳለች።ወደቢሮው ገብታ ከፊቱ ያለው ወንበር ጋር ተቀመጠች። "እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልጅ!...ደግሞ ዛሬ ብቻሽን ነው የመጣሽው እንዴ?እህትሽ የት ናት?...ምን ሁነሽ ነው የተናደድሽው?ችግር አለ እንዴ?...ቃል!ለምንድነው የምጠይቅሽን የማትመልሽልኝ?የሆንሽው ነገር አለ?ንገሪኝ!"አላት ኢያሱ የቃልኪዳን ሁኔታ አስተውሎ።
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 37 |
| 24 h | 151 |
- After 6 hours37
- After 24 hours151
- Total to date151
ሀይል ምእራፍ -2 ክፍል-15 ደራሲ፦ቪክቶሪ ወደቤታቸው ሄደው ከገዙት ልብሶች መረጡ እና ለማታ እራት ተዘጋጁ።የእራቱ ሰአት ሲደርስ ወደ ቃል ኪዳን አሳዳጊ ቤተሰቦች ቤት ሄዱ።የቃል ኪዳን አሳዳጊ ቤተሰቦች የሳሎኑ በር ላይ ሆነው ሊቀበሏቸው ቆሙ፤እነሱም አዲስ ኪዳንን እና ቃል ኪዳንን በአይናቸው ለይተው ማወቅ አልቻሉም።ኤፍራታም ሁለቱንም በደንብ ተመለከተቻቸው እና ወደ ቃል ኪዳን ዞረች እና፦ "አዲስ ኪዳን እንኳን ደህና በሰላም ወደ ቤታችን መጣሽ፤ስላየንሽ በጣም ደስ ብሎናል።እኔ የቃል ኪዳን ታላቅ እህት ኤፍራታ እባላለሁ።"አለቻት። "ለምንድነው እንደ አዲስ ሰው የምታይኝ እህቴ?እኔ ቃል ኪዳን ነኝ።መንታ እህቴ አዲስ ኪዳን ማለት እሷ ናት።"ብላ ወደ አዲስ ዞር አለች። "እውነትሽን ነው?በጣም ትመሳሰላችሁ ለዛነው እናንተን መለየት ያቃተኝ፤እንኳን ደህና መጣሽ አዲስ ኪዳን።"አለች ኤፍራት ወደ አዲስ ኪዳን እየተመለከተች። "አመሰግናለሁ።"አለች አዲስ። "እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልጅ ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል።"አላት አቶ አለማየሁ ለሰላምታ እጁን እየዘረጋላት። "ሁላችሁንም ስላገኘኋችሁ በጣም ደስ ብሎኛል፤ አመሰግናለሁ።"አለች እና ሰላምታውን በአክብሮት ተቀበለች። "ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል ልጄ፤እዚህ አትቁሙ ወደውስጥ እንግባ እና እንጫወት።"አለቻቸው ፀሀይ። ሁሉም ተሰብስበው ወደ ሳሎን ሄዱ እና ሶፋ ላይ ተቀምጠው ያወሩ ነበር።ራት ሲቀርብ ወደ ጠረጴዛው ሄዱ እና መብላት ጀመሩ። "አዲስ!ያኔ እማዬ ልትሰጠን መጀመሪያ እዚህ ቤት ነበር የመጣነው።አሳዳጊ ቤተሰቦቼ ደግሞ ሁለታችንንም ለማሳደግ ፈልገው ነበር።"አለቻት ቃልኪዳን። "አዎ በሰአቱ እንደዛ አስበን እናታችሁ አናግረናት ነበር ነገር ግን እናታችሁ አልተስማማችም ነበር።"አለ አቶ አለማየሁ። "ልታሳድጉኝ በመፈለጋችሁ በጣም አመሰግናለሁ፤ግን እማዬ የግድ እኔ እና መንታ እህቴን መለያየት ነበረባት።እናታችን ምክንያት አላት።"አለች አዲስኪዳን። "ኤፍራታን ከወለድን በኋላ ሌላ ወንድ ልጅ ደግመን ወልደን ነበር ግን ድንገት ህይወቱ አለፈብን፤በዛ ምክንያት ቃልዬ ስትመጣ ግን ለኛ የልጃችን ሞት ማስረሻ ሆነችን።"አለች ፀሀይ በወንድ ልጇ ሞት አዘን ብላ። "በጣም አዝናለሁ፤የኔ አሳዳጊዎች ዶክተር መውለድ እንደማይችሉ ነግራቸው፤እነሱ ልጅ በጣም በሚፈልጉበት ሰአት ነበር እኔን ያገኙኝ።"አለች አዲስኪዳን። "በቃ አሁን ስላለፈው ነገር ትተን ምግባችንን እንብላ።"አለች ቃልኪዳን። እነሱም እራታቸው ከበሉ በኋላ ወደቤታቸው ሊሄዱ ተሰነባበቱ። "ስለሁሉም ነገር በጣም አመሰግናለሁ።"አለቻቸው አዲስ ኪዳን። "ምንም ችግር የለውም የሚያስፈልግሽ ነገር ሁሌም በራችን ላንቺ ክፍት ነው።"አለቻት ፀሀይ። "እሺ በጣም አመሰግናለሁ።" "አዲስ አንዴ ወደ እኔ ክፍል ሄደን አንዳንድ የምፈልጋቸውን እቃዎች ይዘን እንሂድ።"አለቻት ቃል ኪዳን። "እሺ እንሂድ።" አለቻት እና ወደ ቃል ኪዳን ክፍል ሄዱ።ቃል ኪዳንም የምትፈልጋቸውን እቃዎች መሰብሰብ ጀመረች፤አዲስ ኪዳን ደግሞ የቃል ኪዳን አልጋ ላይ ተቀመጠች። "የማግዝሽ ነገር አለ?"አለቻት አዲስ እህቷ የጠፋባት ነገር ያለ ይመስል ቁምሳጥኗን ስትመሰቃቅለው እያየች። "እቃዎቼን ልሰብስባቸው እና ታያይዢኛለሽ።"አለች ቃልኪዳን። "እሺ፤ቤተሰቦችሽ በጣም ጥሩ ሰው ናቸው።በህይወቴ እንደቤተሰቦችሽ አይነት ጨዋ ሀብታም አይቼ አላውቅም።" "ስለወደድሻቸው ደስ ብሎኛል።"አለች ቃልኪዳን ቁምሳጥኗን እየመነቃቀረች። አዲስ ኪዳንም እህቷ ልብሷን ስትፈልግ ዝም ብላ ትመለከታት ነበር፤ቃል ኪዳንም ከምፈልገው ልብሶች መሀከል የወንድ ኮት ታገኛለች። "እ...እ?የማን ነው ልብስ?የወንድ ኮት እኔ ልብሶች ጋር ምን ይሰራል?"አለች ኮቱን ለአዲስኪዳን እያሳየቻት። አዲስ ኪዳን ኮቱን ስትመለከት የመጀመሪያ ቀን ናሆም ጋር በተገናኘችበት ምሽት ላይ ወክ እያደረጉ የራሱን ኮት አውልቆ ያለበሳት ኮት መሆኑ ትዝ አላት። "የማነው?ደግሞ የሆነ ሰው ላይ አይቼዋለሁ መሰለኝ።"እያለች የማን እንደሆነ ለማስታወስ ሞከረች። "እ..እ ምናልባት የአባትሽ ይሆናል።"አለች አዲስ ኪዳን የናሆም መሆኑ ትዝ እንዳይላት። "እስኪ ተመልከችው.....በዚህ ልብስ አባቴን አስቢው፤እሱ እንደዚህ አይነት ልብስ አይለብስም።ቆይ ቆይ እስኪ ማን ለብሶት ነበር ያየሁት?ማስታወስ አለብኝ።ማን ነበር?"አለች ድጋሚ ለማስታወስ እየሞከረች። "ቃል አሁን እየመሸ ነው እሱን ተይው እና ቶሎ ብለን ወደ ቤታችን እንሂድ።"አለች አዲስ ነገሩን እንድትተወው ለማድረግ። "ልክ ነሽ በቃ ጨርሻለሁ እንሂድ።" አለቻት እና የናሆምን ልብስ አልጋው አስቀመጠችው እና ከክፍሉ ወጥተው ትንሽ እንደተራመዱ አዲስ ኪዳን የናሆምን ልብስ ልትወስድ እና ልትሰጠው ታስባለች።
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 7 h | 66 |
| 24 h | 215 |
- After 6 hours66
- After 24 hours215
- Total to date215
Connections
Similar channels
ግጥም የልብ ድምፅ@yenegitiem21Art2.2K
Латун ✍️Стихи✍️ Любовь@latunlyubovzArt1.26K
my CRT dreams@mycrtdreamsArt1.26K
Творческий апокалипсис💥@creative_apocalypseeArt1.26K
Вечерний ветер | Марина Битокова@marie_bitokArt1.26K
Маяк@space_mayakArt1.26K
kóchiz: Not Found 404@k0chizArt1.26K
Ростовский Кремль@roskremlArt1.26K
Mentioned by
ጥቀርሻ🧠🗣@tkersha1 mentionLatest post