"እናትሽም እንዳልሽው አድርጋ ነበር ነገር ግን ሁሉንም መጥተው ገደሏቸው፤ለእኛም ይሄ መንገድ አይጠቅመንም ያልኩሽ ሁላችንንም እንዳይገድሉን ነው፤በዚህ በቀል ውስጥ በጭራሽ ፖሊስ የሚባል ነገር አይገባም።"
"አዎ ልክ ነህ ታድያ ምን ልናደርግ ነው?"
"እቅዳችንን ለማውጣት ብዙ ጊዜ ይፈጃል፤ግን እቅዳችንን እያሰብን ጎን ለጎን ሌላ ነገር እንድናደርግ አስቢያለሁ።"
"ምንድነው ያሰብከው?"
"እኔ አንቺ እና እህትሽ ራሳችንን መከላከል መሰልጠን አለብን።"
"እ?ራሳችንን መከላከል ማለት?"
"እኔ በእግሬ ለመሄድ መታከም አለብኝ፤እናንተ ሁለታችሁ ደግሞ ሽጉጥ መተኮስ፣ካራቴ ቦክስ እና ቴኳንዶ መሰልጠን፣ዋና መዋኘት፣ወታደር የሚሰለጥናቸው ስልጠናዎችን መሰልጠን እና መኪና በፍጥነት መንዳት.....ግን መኪና መንዳት ሁለታችሁም ትችላላችሁ ብዬ አስባለሁ።"አላት።
"አይ አጎቴ መኪና መንዳት ሁለታችንም አንችልም።"
"እ?እስካሁን አትችሉም?እሺ እህትሽ መኪና ስላልነበራት ነው አንቺ ግን መቻል ነበረብሽ።"
"እኔ ለምን እስካሁን እንዳልቻልኩ አላውቅም፤ለምንድነው ባለመቻሌ ጥፍተኛ የምታደርጉኝ?"
"ጥፋተኛ ስለሆንሽ ነው ጥፋተኛ ነሽ ያልኩሽ።"
"ቆይ አሁን እህቴ ስልጠናውን መሰልጠን አለባት፤ግን ምን ብለን ነው የምናስረዳት? እንዴት ነው እሺ የምትለን?"
"እህትሽን በትንሽ ነገር ማሳመን ካልቻልሽ እንዴት ነው እነዛ ሰዎች ፊት የምትቆሚው?"
"እነዛ ሰዎች ለኔ ጠላቶቼ ናቸው እሷ ግን ብቸኛ እህቴ ናት እሷን ማጣት አልፈልግም።"
"ብቸኛ እህትሽን ላለማጣት ከፈለግሽ ከዚህ በቀል መውጣትሽ ብቻ በቂ ነው።"
"አታስብ አጎቴ!እኔ ስልጠናውን እንድትወስድ እህቴን አሳምናታለሁ።"
"ጥሩ...ግን ተጠንቀቂ መጠርጠር የለባትም።"
"እሺ አትጠረጥረኝም።"አለችው።
ክፍል-16 በቅርቡ ይቀጥላል...
❤💌🔁