"አፈርነት" አፈርነት ውርደት፡ አፈርነት ጭቃ ለምንም ቁም ነገር፡ የማይሆን ለእቃ አፈር..... እንኳንስ ሊያቅራራ፡ እንኳንስ ሊኮራ ተረግጦ መኖር ነው፡ ሁሌም የ'ሱ ስራ። እግዜሩ አፈርን ፡ ከምድር ወሰደና ሰው አድርጎ ፈጠረ ፡ ነፍሱን ሰጠና አፈር ሰው ነው ሰውም አፈር ነው... አዳምና አፈር ፡ ሁለቱም አንድ ነው አዳምም አፈር ፡ አፈርም አዳም ነው ለአፈርና ለአዳም ፡ ልዩነት ለ'ነሱ እግዜሩ የሰጠው ፡ የእሱ እስትንፋሱ፤ አፈር ተከፋፍሎ... አሜሪካ ነጭ አፈር ፈረንጆች ቀይ አፈር ቻይና ቢጫ አፈር እኛ ጥቁር አፈር ትዕቢትን ጀመረ ፡ ረሳና የማንነቱን ነገር ማንስ ቀርቦ ይንገር፡ እንደ ሆነ አፈር። አፈሩ ቢኮራ ፡ አፈሩ ቢተብት ቢረሳ የራሱን ፡ የጭቃነት ሕይወት እኔን አይገርመኝም ፡ እኔ አላደንቅም አፈር አፈር ነውና ፡ በአፈር አይተብትም አፈር ቢሰባ ቢወፍር ፡ በትዕቢት ቢወጠር የትም አያደርሰውም፡ ይመለሳል ወደ አፈር። By Æmanuel Negash (abu) @getem @getem @getem
Open in Telegram
ግጥም ብቻ 📘
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Oct 29, 2026 | 13,450 |
| Nov 3, 2026 | 11,700 |
| Nov 5, 2026 | 11,100 |
| Nov 7, 2026 | 11,700 |
| Nov 13, 2026 | 7,730 |
| Nov 14, 2026 | 8,150 |
| Nov 16, 2026 | 6,763 |
| Nov 18, 2026 | 5,360 |
| Nov 26, 2026 | 426 |
Most viewed this month
- 01Views15.2KForwards—Reactions159Comments—
- 02Views11.7KForwards—Reactions100Comments—
- 03Views11.7KForwards—Reactions49Comments—
- 04Views11.7KForwards—Reactions101Comments—
Latest posts
⁰ "ራስ አባይ" ⁰ ◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈ ⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰₀⁰ ውሃ ሆነን ፣ ከምድር ተነን እንደገና ፣ ነፅተን ጠለን የተያየን ፣ ደመና ላይ ያለ ቀለም ፣ ከላይ ሰማይ ልንያያዝ ፣ የዘረጋነው ጉሙን ጭልም ፣ ሲያደርገው ጣለን ካለም ፣ አፈር ገሉ አንድም ከቀይ ፣ ከጥቁሩ ምድር ስትዞር ፣ የወደቅነው ከጥቁሩ ፣ ከቀዩ ነው ውሃ ገባው ፣ የአፈር አመል ሁሉን 'ሚበላ ፣ ማይዳበል ወንዝ ሆነን ፣ ብንሞክረው የማይጠራ ፣ ባህሪ ነው። ያ መልክ አልባ ፣ ውብ መልካችን ደፍርሶብን ፣ ዓለማችን አንድም ቀይ አባይ ፣ ሆንን ጥቁር አባይ እንዳልነበርን ፣ ጭሱን አባይ ሆኖ ራስ አባይ... ተገናኘን ፣ ይዞን አዘን ባንድ ወንዝ ፣ ተያይዘን ባፈር ቀለም ፣ ደፈራርሰን አለያይቶ ፣ አፈሰሰን ለመያያዝ ፣ ተዘርግተን ተላለፍን ፣ ተሳስተን። አባል ስተን... By ናትናኤል_አበበ @getem @getem @getem
Open in Telegramምኞቴን ግታልኝ : አርገኝ እንዳ መናኝ፣ ትናንት የጠየኩህ ሊጥለኝ ከሆነ : እንኳንም አልቀናኝ። By Abebaw Hailu @getem @getem @paappii
Open in Telegramያልሄድንባቸዉ መንገዶች ያላወቅናቸዉ እዉነቶች መኖር ስንጀምር ያላየችን እናት ደርሰንለት ያልመረቀን አባት ከኛ አልፈን የምናተርፋቸዉ ነፍሶች ሳቃችንን ማየት ያለባቸዉ ምቀኛዎች……… ገና አሉ……….. በኛ ፈጣሪ ሲመሰገን ድንቅ እኮነዉ ቆመዉ ሲሉ እንዴት ሆነላት ሲባባሉ እግዚአብሔር የሚጠራበት ስሙ የሚከብርበት ጐጆ ቀልሰን እኔ ና አንተ የምንኖረዉ የምናየዉ ህይወት አለን……….. By ትዝታ ወልዴ @getem @Tizita21
Open in Telegramነገረ ሥራዋ እንደ እስትንፋስ ዓይነት ----------------------------------------- ለአፍታ ብዘነጋሽ ፥ ለጋነቴን ፈጀሁ ጠዋት ረስቼሽ ፥ ማታውኑ አረጀሁ፡፡ መልዐከ ሞት መጣ ... ቆመ ... ከቤቴ በር ፡ ለካ አንቺን መናፈቅ ያለመልም ነበር። By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
Open in Telegram"በሰው ዓለም" ------------------------- ባየነው ልክ አደርን። በሰማነው ልክ ኖርን። ከዚያስ?...ከዚያማ... "አዲስ ነገር የለም?" ብለን ጠየቅን አሁንም! እንዲያሳዩን ጠበቅን። አለማወቅ አወቅን። አዎን አዲስ ነገር የለም። ካልፈጠርነው የኛን ዓለም አዲስ-ነገር-የለም!! by ናቲ @getem @getem @getem
Open in Telegramአዝማሪ ቤት አፍሮ ፥ ፀሎት ሥቆም የሚያንጎራጉረኝ ፤ ግራ -ገብ ነብሴ ነው፣ ከሠው ፣ ከአምላክ የለያየኝ By sostkilo @getem @getem @paappii
Open in Telegramእንደዉ ባጋጣሚ በድንገት አግኝቼህ፤ ምኑንም ሳያዉቀዉ ቀልቤ ተረታልህ፤ ንግግርህ መሐል ሳቅህን ስሰማ፤ መጥፋት ያሰኘኛል ከልብህ ከተማ፤ በዉስጥህ ያለዉን በቅጡ ባላዉቅም፤ አንተኑ ከመዉደድ ፍጹም አልቦዝንም፤ የመጣህ ሲመስለኝ...... ከልቤ ላስገባህ በራፌን ከፍቼ፤ እጠብቅሃለዉ ተስፋን ተሞልቼ፤ ደግሞ ተመልሰህ ጓዝህን ሸክፈህ፤ ወደ መጣሁበት ሊሂድ ትለኛለህ፤ አንተማ..... አይታክትህ መሄድ መምጣት፤ መመላለስ በሰዉ ሕይወት፤ እኔ ልጅት..... በመሐል ቤት ተሰቃየሁ፤ ላንተ ብዬ ሰላም አጣሁ፤ መሻትህን አላዉቅ የገጠመኝ ፍርጃ፤ የልብህ ቋጠሮ ምን እንደሆን እንጃ፤ እንጃ.......... እናልህ አለሜ....... በደመነፍስ ሆነህ ባገኘኸዉ መንገድ፤ እግርህ ወደ መራህ አትምጣ ለመሄድ። ✍️ዔደን ታደሰ @Ediwub @getem @getem
Open in Telegram----------°--------°--------- አያስደንቅም የሚንጋጋው ሰው: አውቃለሁና ውጥኑን ሁሉ እንዳልጨረሰው! የፈለገውን ነክቶ ይተዋል፣ በምን ጽናቱ ይፈፅመዋል?፨ ወከባ መሐል፧ የመረጠውን መጥጦ ሲጥለው፡ ወኔ ቢስነት ሲያልፈሰፍሰው፡ የኔ አጀብታ የኔ ፈገግታ:- ያ'ለመሠልቸት የፍቅር ክንድሽ፤ (እስካሁን ድረስ እኔን መውደድሽ!) ----------°--------°--------- [ዓለም] @mypoems396 @getem @getem @getem
Open in Telegramተዳፍኖ እንደ ፈገገ፣ ----------------------------- ቁልቁል ተቀብሮ እንዳደገ፣ ፍሬ እንዳንዠረገገ፣ እንደ ስውር ቅድስና፣ እንዳልተጮኸለት ዝና፣ ትንሽ መሆን ግዝፈት አለው፤ ያ ለ መ ታ የ ት ውበት ነው። By Ze B Der @getem @getem @paappii
Open in Telegram






