🧠🫀 እኔ እና ቁርአን Part 77 እኔ :- "ያ ረቢ... አንዳንዴ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ሳስበው ውስጤ በፍርሃት ይርዳል። ቀናት፣ ወራትና ዓመታት እንደ ጀት እየበረሩ ነው፤ ድንገት 'እገሌ ሞተ' ሲባል ስሰማ ልቤ ክው ይላል። ለጥቂት ደቂቃዎችም ቢሆን ዱንያ ትጨልምብኛለች። ግን ደግሞ ወዲያውኑ ረስቼው ተመልሼ በሶሻል ሚዲያ፣ በቲክቶክ፣ በስልክ እና በዘፈን ዓለም ውስጥ እሰምጣለሁ። ከሁሉም በላይ እንቅልፍ የሚነሳኝና የሚያስጨንቀኝ ነገር ግን... 'እውነት አሁን ሞት ቢመጣብኝ አላህን ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ?' የሚለው ጥያቄ ነው። 😢 ለዚህች ጠፊ ዱንያ ስኬት፣ ጥሩ ስራ ለመያዝ፣ ገንዘብ ለማግኘትና 'ህይወቴን ለመቀየር' ብዬ ሌት ተቀን 'Plan' አወጣለሁ፣ እለፋለሁ፤ ለማይቀረው የቀብር ቤቴና #ለአኺራዬ ግን ምንም ያዘጋጀሁት ስንቅ የለኝም። ጌታዬ ሆይ! ሞት ድንገት ቢቀድመኝ በምን ፊትና በምን ስራዬ ነው አንተን የምገናኘው? 🥺 የልቤ መድረቅና መዘናጋት በጣም አስፈርቶኛል... እውነት አሁንም ተመልሼ የምስተካከልበት ጊዜ ይኖረኝ ይሆን?" ቁርአን :- > كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ ተደቡር :- ታውቃለህ ሀቢቢ... አንተ በወጣትነት ጉልበትህ ተማምነህ በዱንያ ፕላን፣ በህልም እና በሩጫ ተጠምደህ 'ገና ወጣት ነኝ፣ ብዙ ጊዜ አለኝ፣ ሳረጅ እስተካከላለሁ' እያልክ ራስህን ስታታልል፣ አላህ ግን በዙሪያህ ባሉ ጓደኞችህ ሞት የማይቀረውን እውነት ፊት ለፊት እያሳየህ ነው... كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ "(ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት!)" ይልሃል። አስተውል! አላህ "ሁሉም ሰው ይሞታል" አላለም፤ "ቀማሽ ናት (ዛኢቀቱል መውት)" ነው ያለው። ልክ ምግብ ስትቀምስ ጣዕሙ እንደሚታወቅህ ሁሉ፣ እያንዳንዳችን የሞትን ጽዋ መቅመሳችን የማይቀር #እውነታ ነው። ዛሬ ጀናዛ የምትሸኘው አንተ ነህ፤ ነገ ደግሞ በሰዎች ትከሻ ላይ ሆነህ ወደ ቀብር የምትሸኘው አንተው ራስህ ነህ። ያ "በዱንያ ስኬት እና ብር ተታልዬ አኺራዬን ረሳሁት" የሚለው ስጋትህ ትልቅ ማንቂያ ነው። አላህ እኮ የዱንያን እውነተኛ ማንነት ሲነግርህ:- وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ (ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም) እያለ remind ያረገሃል። ዱንያ Fake ነች! ዛሬ የምትሮጥለት ዝና፣ ብር እና ውበት ቀብርህ አፍ ላይ ጥሎህ ይመለሳል። አብሮህ ጨለማው ቀብር ውስጥ የሚገባው ሶላትህ፣ ቁርአንህ፣ ሰደቃህ እና ንጹህ ልብህ ብቻ ነው። Look... ዛሬ "እውነተኛው ስኬት Success ምንድን ነው?" ብለህ ስትጠይቅ፣ አላህ ትክክለኛውን #የስኬት ትርጉም እንዲህ ብሎ ይሰጥሃል:- فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ "(ከእሳትም የተራቀና ጀነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ / ተሳካለት!)" "ፈቀድ ፋዝ" (በእርግጥ ተሳካለት!) የሚለውን ቃል ልብ ብለህ አስተውለውማ...♡♡ በወጣትነትህ የምትለፋለት ትልቅ ቤት መስራት፣ ዘመናዊ መኪና መንዳት ወይም ሚሊየነር መሆን አይደለም እውነተኛው ስኬት፤ ትልቁና የመጨረሻው 'Achievement' ከጀሀነም እሳት ተርፎ ጀነት መግባት ነው! 🫰🏽🤍 Habibi... እስትንፋስህ እስካለ ድረስ "ረፍዷል" የሚባል ነገር የለም። አሁን ይህንን እያነበብክ መሆንህ ራሱ አላህ የሰጠህ ሌላ 'Second Chance' ነው። ዛሬውኑ ስንቅህን ማዘጋጀት ጀምር፤ ሶላትህን አስተካክል፣ የበደልከውን ይቅርታ ጠይቅ፣ ወደ ጌታህ ተመለስ—ሞት በሩን ሳያንኳኳ በፊት ለመገናኘት ተዘጋጅ! 🙌🏽 🍂 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 561 |
| 5 h | 778 |
| 7 h | 799 |
- After 1 hour561
- After 6 hours799
- Total to date799








