Account
ወርቃማ ንግግሮች

ወርቃማ ንግግሮች

ለአስተያየት.. @Golden_SpeechBot 🍂

Username
@golden_speech
Category
Religion
Country
EthiopiaEthiopia
Subscribers13,785
Avg views per post, 7d528−59.4% vs prev 7d
ERR3.83%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Oct 31, 20261,650
Nov 3, 20261,590
Nov 6, 20261,130
Nov 7, 20261,665
Nov 10, 20261,370
Nov 12, 20261,350
Nov 15, 20261,300
Nov 16, 20261,250
Nov 22, 2026732
Nov 24, 2026528
Nov 25, 2026322

Most viewed this month

  1. 01

    አላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር.. አንተ ሽንፈት አድርገህ የምትቆጥረው ሁሉ ወደ ትክክለኛ መስመርህ የመመለሻ ጉዞ ነው። የሰው ልጅ ሊዋረድ አይወድቅም። የቱ ጋር መቆም እንዳለበት ቦታውን ሊያውቅ ነው የሚወድቀው። ለሩሕያው የማይመጥነውን ሸክም ሊያቃልል ነው የሚወድቀው። በሕይወት ትልቁ ጦርነት ከሰው ጋር አይደለም። ሰዎች የምንወደውን እና የምንጠላውን፣ የምንደብቀውንና ግልጽ የምናወጣውን ሀሳብና ስሜት የሚያንጸባርቁ ምስል ከሳች መስታዎቶች ናቸው። እውነተኛው ጦርነት ግን በውስጥ ነው የሚካህደው። የተደበቀ እውነትና እምነት እያለን ፍርሀታችን ጎልቶ ይታያል። ሩሐችን በንጽህናዋ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ማደግን ስትሻ የነፍስያ ስሜት ፍላጎታችን ወደምድር ትስበናለች። በዚህ መሀል ከራሳችን ጋር በምናደርገው የውስጥ ግብግብና ትግል ውስጥ ነው የእኛ እውነት ያለው። ስብራት የሚመስልህ ሁሉ በአላህ እይታ አንተን የማንጻት ጅማሮ ነው። የአላህ ሒክማ/ጥበብ የሰው ልጅ ተሰብሮ እንዲቀር አይፈቅድም። ባይሆን የጌትነቱ ሒክማ ባሪያው በስብራቱ ምክንያት እንዲበስል ይሻል። ልቡ እንዲመለከት፣ አዕምሮው እንዲነጻ፣ ሩሕያው ቀድሞ በእርሱ አክናፍ ወደነበረችበት ቅድስና እንድትመለስ ይሻል። ለዚህ ነው ቁስል አንዱ የእነጻ ክፍል የሆነው። ክስረት የመማሪያና መረዳት መንገድ፣ ሕመም የእውነተኛው መዳን በር ክንቻር የሆው። የመክፈቻ ቁልፉ ትዕግስትና ጽናት ነው። የመድህን ጎዳናው የሚገለጠው በሩ ሲከፈት ነው። ቅድሚያ ወደ ራስህ ስትመለስ ወደ አላህ ትመለሳለህ። ወደ አላህ ስትመለስ የጠፋውን አቅምህን መልሰህ ታገኛለህ። ያኔ ነገሮችን በፍርሀትህ መጠን ሳይሆን ክስተቱ በሚገባው ብቻ በልኩ መመልከት ትጀምራለህ። የዘገየው ሁሉ እንዳላጣሀው፣ ያጣሀውም ያንተ እንዳልነበር ይገባሀል፣ የተሰበረውም ሁሉ አንተ መልካም መስሎህ ልታገኘው የተመኘኽው ግን የማታየው የሆነን ቆሻሻ አላህ እያስወገደልህ እንደነበር ይገለጥልሀል። ስትበስል ምናልባት ስሜትህን የሚረዳህ እንጂ የሚጠግንህ ፍለጋ አትኳትንም። ለመስተካከልህ አቅጣጫ የሚጠቁምህ አጽናኝ አድርገህ የምትንጠለጠልበት ሰው አይኖርም። በሮችን አታንኳኳም። ይልቁን አላህ ላንተ ያለው የስኬት በር ይከፈት ዘንድ የሚቆረቆረው/የሚንኳኳው በእጅ ሳይሆን በንጹህ ቀልብ መሆኑን አስረግጠህ ታውቃለህ። በዚህ ጊዜ ብቻ.. ሽንፈት ትምህርት መሆኑን ትረዳለህ። ውድቀትም የመነሳትና የከፍታ ጅማሮ መሆኑ ይገለጥልሀል። አላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር! #دكتور #مصطفى_محمود "واعلم أن ما أصابك لم يكن ليخطأك، وأن ما أخطأك لم يكن ليصيبك، رفعة الأقلام وجفة الصحف.. وأن مع العسر يسرى، إجن العسل ولا تخسر الخلية / ያገኘህም ሆነ የሳተህ ጸጋም ሆነ ፈተና ወትሮም ሊያገኝህ አለያም ሊስትህ የተወሰነ እንዳልነበር እወቅ። ከችግርም ጋር ገር ነገር እንዳለ አስታውስ። ማሩን ቁረጥ ቀፎውን ግን አትስበር!። Hamudi Hamudi

    Text
    Views1.87K
    Forwards—
    Reactions14
    Comments—
  2. 02

    ደሴ ከተማ ላይ የተፈፀመ አስነዋሪ ድርጊት‼️ በትላንትናው እለት በደሴ ከተማ ከ130 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውንና የዛውያው ሸይኽ ሸይኽ ሲራጅ ቡሰይሪ ይባሉ የነበሩ ለ 111 አመት የኖሩ ብዙ ደረሳዎችን ያፈሩ ቀብራቸውም ከመስጂዱ 100ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ዛዉያ በርካታ ደረሶችና ህፃናት እውቀት የሚቀስሙበት ታዋቂውን የአማን አንባ ዛውያ ከ45 በላይ ህፃናት በአሁኑ ሰአት ቁርአን እየቀሩበት የሚገኘውን ዛውያ ኢላማ ያደረገ እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ድርጊት ተፈፅሟል። የደሴ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ በሆነው በአሸናፊ አለማየሁ ትዕዛዝ እና በኮማንደር ሰይድ አስፈፃሚነት በበርካታ ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ታጅበው ወደ ስፍራው በመግባት ታፔላዎችን ነቃቅለው፣ኬንዳውን ገነጣጥለው ይህ ቦታ ለሌላ ሃይማኖት ተሰጥቷል በማለት የአላህ ቃል የሆነውን ታላቁን ቁርአን ኮማንደር ሰይድ በርግጫ በማለት ዛውያችሁን ሂዳችሁ ፈልጉ እያለ እየዛተ በምትመለከቱት መልኩ እንድቀደድና እንድበታተን አድርጎታል። በጣም የሚያናድደውና የሚያሳቅቀው ከአንድ የከተመዋ የፀጥታ መሪ የማይጠበቅ አሰቃቂ ድርጊት የተፈጸመው የተቀደሰው የአላህ ቃል (ቁርአን) በኮማንደር ሰይድ የጫማ እርግጫ እንዲረገጥና እንዲቀደድ መደረጉ ነው። ገና ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ህፃናት ላይ ክላሽና ስናይፐር አስደቅነው፣ መሳሪያ አቀባብለው በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያለቅሱና እንዲፈሩ ተደርጓል። አካባቢው ላይ የሚገኙ ሰላማዊ ሰዎችንና የኮሚቴ አባላትን በመደብደብና በማሰር መብታቸው ተገፈፏል። ህዝቡም በታሪካዊ ይዞታዎቹ መነጠቅና በልጆቹ ላይ በደረሰው እንግልት በእንባና በሐዘን ላይ ይገኛል። የደሴ ከተማ መጅሊስ ሆይ‼️ በምትመሩት ከተማና በማታስተዳድሩት የሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የጥንት አያቶቻችን የዕውቀትና የኢባዳ ( ይዞታዎች እንዲቀሙ፣ የአላህ ቃል በግልጽ እየተረገጠና እየተቀደደ ገና በለጋ ዕድሜ ላይ በሚገኙ ህፃናት ላይ የጦር መሳሪያ እየተደቀነባቸው ይህ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጸም ዝምታችሁ እስከ መቼ ነው? የደሴ ከተማ ብልፅግና ከእንግዲህ ከአቅማችሁ በላይ ሆኗል እንጂ ይህን ግፍ እያያችሁ በዝምታ ማለፍ አልነበረባችሁም። ካልሆነላችሁና ይህንን መከላከል ካልቻላችሁ ጉዳዩን ለፌደራል ብልፅግናና ለመንግስት አካላት አሳውቁ ይህ ካልሆነም ህዝብንና ሃይማኖትን መጠበቅ ካልተቻለ ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቡ። ክቡር ከንቲባ አቶ ዱባለ ሆይ‼️ በደሴ ከተማ ላይ ተሰግስጎ ህዝቡን ከህግና ከመንግስት ጋር ለማጋጨት፣ ማህበረሰቡን የሚያማርርና አብሮነቱን የሚያናጋ አጥፊ ተግባር እየፈጸመ ያለውን የደሴ ከተማ የብልፅግና ፅህፈት ቤት አካሄድ እንዴት እየተመለከቱት ነው? በከተማዋ ሰላምና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ሃላፊነት የተሰጠው አካል ራሱ የህዝብን መብትና የዕምነት ተቋማት የሚጥስ ከሆነ ከንቲባው ዝምታ ምን ሊባል ይችላል? ህዝባችን የጥንት አያቶቹን አሻራና የልጆቹን የእምነት ነፃነት የሚነፍግ ማንኛውንም ኢ-ህገ-መንግስታዊና ግፈኛ ድርጊት አጥብቆ ይቃወማል። የከተማው አስተዳደርና የሚመለከታቸው አካላት ይህንን አሳሳቢ ችግር ወዲያውኑ አጣርተው የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ አበክረን እንጠይቃለን።

    Text
    Views1.78K
    Forwards—
    Reactions15
    Comments—
  3. 03

    ጥንቃቄ🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯 ከጎሮ ሰሚት 72 ባለው መንገድ ያለው ከባድ ሌብነት ዛሬ በራሴ ላይ ያጋጠመኝን ላጋራችሁ🎯🎯 ዛሬ ቢሮ ስብሰባ ስለነበረኝ 1:30 አካባቢ ወጥቼ ከቦሌ መድሀኒያሌም በጎሮ ሰሚት 72 ወደ አያት እያመራሁ ነው። እስከሰሚት መንገዱ ሰላም ነበር። ልክ ሰሚትን አልፌ ወደ 72 ድልድይ እየሄድኩ በጣም ተዘጋግቷል እንደምንም ድልድዮን አለፍኩኝ ወዲያውኑ ያጋጠመኝ ከባድ የዘረፋ ተግባር ከኋላዬ ባለ መኪና ክላክስና በኔም ጉልበት ከመዘረፍ ተርፌአለሁ። ነገሩ እንደዚህ ነው ልክ ድልድዮን እንዳለፍኩ በግምት በግራም በቀኝም ከ100 የማያንሱ መኪኖች እስከ ኖክ ማደያው ተሰልፈው ይንፏቀቃሉ። እኔም ከፊቴ ያለውን ሲኖ ትራክ እየተጠነቀቅኩ አሽከረክራለሁ ከመቅስፈት በኔ በኩል አንድ ወጠምሻ ጎረምሳ የመኪናዬን በር ከፍቶ እንድ እብድ እየጮኸ ሰው ገጭቼ እንደመጣሁ ሰውየው ደም በደም ሆኖ እንዴት ትተኸው ትሄዳለህ እያለ በሚያስደነግጥ ድምፅ ይጮሀል። ወዲያውኑ ሌብነት እንደሆነ ስለገባኝ በሩን ለመዝጋት መታገል ጀመርኩኝ እንደምንም ስታገለው እጄ ላይ ያለውን ሰዐት ለመበጠስ ሲሞክር ታግዬ በሩን ዘጋሁት። ለካ በተቃራኒው ያለውን በር እኔ እዚህ ስታገል ሌላው ሌባ በሩን ከፍቶ ስልኬን ሊወስድ ሲል ከአጠገቤ የነበረው መኪና ክላስክ በመንፋት ሊገጨው ሲል በሩን ከፍቶ ወደ ድልድዩ ውስጥ ሮጠ። በኔ በኩል ያለውም እንደዛው ወደ ድልድ ሮጦ ገባ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በግምት 500 ሜትር የማይሞላ ቦታ የ72 ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አቅራቢያ ነው። በጣም ጩኸቱ ስላስደነገጠኝ ወደፊት ሄጄ ከተረጋጋሁ በኋላ ወደ ፖሊስ ጣቢያው በመሄድ የደረሰብኝን አስረዳሁ ነገር ግን በአሳፋሪ መልኩ ከፖሊስ በማይጠበቅ ስነስርአት የተለመደ ተግባር እንደሆነ ነግረው አቃለው ሸኙኝ። የኔ ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ እኔስ ተረፍኩኝ ከኔ በኋላ ያሉ አሽከርካሪዎች የኔ እድል እንዳይገጥማቸው ለማሳወቅ እና ሌቦቹ ድልድዩ ውስጥ ስላሉ እንዲከታተሉ ለማሳሰብም ጭምር ነበር። ይህ ሁሉ የሆነው ከምሽቱ 2:00 ሰዐት አካባቢ ሲሆን ቦተው በሰውና በህንፃ የተሞላ ፖሊስ ጣቢያም አጠገቡ ያለ መሆኑ የሌቦቹን ድፍረት አደገኛ ያደርገዋል። በኔ የደረሰ አይድረስባችሁ። መኪናችሁን ሁሉም በር መዘጋቱን አረጋግጡ። ሞባይላችሁን በኪሳችሁ ካልሆነ ደግሞ መቀጫጫችሁ ስር እግራችሁ መሀል አድርጉ። ሴቶች ቦርሳችሁን የማይታይ ቦታ ወይም የኋላ ኪስ ውስጥ አስቀምጡት። በፍጹም በር እንዳትከፍቱ የፈለገ ቢጮህባችሁ። እንጠንቀቅ አሽከርካሪዎች እንዲህ ከይነት ሌብነት ስናይ እንረዳዳ እንደጋገፍ። ከፎስቡክ ሰፈር ከጠቀማችሁ ተጠንቀቁበት

    Text
    Views1.65K
    Forwards—
    Reactions15
    Comments—
  4. 04

    --- *🇨🇳 ከቻይና በቀጥታ - ለንግድዎ!* ጓንግዙ ውስጥ ነኝ! እርስዎ ለንግድዎ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ከቻይና በቀጥታ ማዘዝ ይችላሉ! ✅ የህፃናት ልብስ ✅ የሴቶች ቀሚስ / አባያ / ካፍታን ✅ ጫማ / ቦርሳ / ሻንጣ ✅ የቤት እቃዎች ✅ የሞባይል መለዋወጫ / ኤሌክትሮኒክስ ✅ የፀጉር እቃዎች / ኮስሜቲክስ *ለምን ከእኛ?* 🔥 የፋብሪካ ዋጋ - ያለ ደላላ 🔥 በመጀመሪያ ፎቶ እና ቪዲዮ እንልክልዎታለን 🔥 እርስዎ ከመረጡ በኋላ ነው የሚገዛው 🔥 ወደ አዲስ አበባ በአየር እና በባህር እንልክልዎታለን *እንዴት ማዘዝ ይቻላል?* 1. የሚፈልጉትን ፎቶ ይላኩልን 2. ዋጋ እና የትራንስፖርት ወጪ እንነግርዎታለን 3. ከተስማሙ በኋላ እቃዎን እንገዛለን 📍 አድራሻ: Guangzhou, China *ዛሬውኑ ይዘዙ! እቃዎን እኛ እንጠብቅልዎታለን!* #ከቻይና #ጅምላ #Guangzhou #ኢትዮጵያ_ንግድ #Abaya #ቀሚስ --- *ለ Story / Status - አጭር ስሪት:* > በቻይና - ጓንግዙ ውስጥ ነኝ 🇨🇳 > ለንግድዎ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ማዘዝ ይችላሉ! > ቀሚስ፣ የህፃናት ልብስ፣ ጫማ፣ ቦርሳ፣ ኤሌክትሮኒክስ.. > የፋብሪካ ዋጋ! ፎቶ ይላኩልኝ ዋጋውን እነግርዎታለሁ! --- ከቻይና ጓንግዙ እቃ ማዘዝ ይፈልጋሉ? 🇨🇳 ቀሚስ፣ አባያ፣ የህፃናት ልብስ፣ ጫማ - ሁሉም በፋብሪካ ዋጋ! ~ @Golden_SpeechBot DM አድርጉኝ! ~ @Golden_SpeechBot

    Text
    Views1.46K
    Forwards—
    Reactions5
    Comments—

Latest posts

#10362Photo
Views322−72%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#10360Text

በነገራችን ላይ… አብዛሃኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ፤ ጌታቸው ሺፈራው የሚባለው ግለሰብ ሰሞኑን የያዘው ውንጀላ ከጀርባው ያዘለውን ሴራ በቅጡ አልተረዳም። 🖊 ይህ ልጅ እንደተለመደው ጎንደር አላባቢ በሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያን ሽፋን እስራኤል ከገባ ከ3 አመታት ጀምሮ፣ በተለይም ዜግነት ለማግኘት ብሎ ለመወደድ ብዙ አጀንዳ ከጀርባ ተረክቧል። ይሄውም ኦርቶዶክሱንና ሙስሊሙን ማጋጨት ነው። ለዚህም ሲባል ሰሞኑን እያደረ እንዳለው፤ በፌዴራል ደረጃ ሳይቀር እውቅና ኖሮት በተለያዩ የክልል ከተሞችም አባላትን እያዋቀረ የሚገኘውን የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አባላት ፎቶ ከፌስቡክ ገፃቸው ላይ እየወሰደ፤ ልክ ተደብቀው ጦር ሲሰለጥኑ ያገኛቸው ይመስል ለዚህ የዋህ መንጋ «ተጠንቀቋቸው፣ ግብፅ ያባረረችው ሙስሊም ብራዘርሁድ አባላት ናቸው!…» እያለ ይፖስታል። 🔗 የኛዎቹ ኦርቶዶክስ ነን ባይ ቂሎች ደግሞ፤ ብዙዎቻቸው ሙስሊም ጠልነት ወትሮውንም የሚያጠናውታቸው ስለሆኑ በደስታ ያራግቡለታል። እንኳን ለርሱ ለዋናዋ እስ•ራኤል ራሱ የሚያራግቡ ናቸው። እርሷ ግን እነርሱ ሞተው እንኳ አብረዋት እንዲቀበሩ አትፈቅድም፣ ወታደሮቿም የእየ•ሱስን ሐውልት ጆሮ ግንዱን እያሉ በሊባኖስ ሲያፈራርሱ ነበር። ጌታቸውን የላከው አይ•ሁዳዊ ቡድን የሚፈልገው፤ ጌታቸው የንጹሐን ሙስሊሞችን ፎቶ እየፖሰተ ሲወነጅል፤ እኛም በርሱ ልክ ለመራመድ ሲባል በየ አካባቢው የሚገኝን በሺዎች የሚቆጠር ኦርቶዶክሳዊ አደረጃጀት ፎቶ እየፖሰትን የሆነውንም ያልሆነውንም በሽ°ብር እንድንፈርጅ ነው። እኛ ግን አናደርገውም። ምክንያቱም፦ 1️⃣ እምነታችን ውሸትን አይፈቅድም። በእልህና በስሜት ተነሳስተን ድንበር እንድናልፍ አልተፈቀደልንም። 2️⃣ ከወንጀሉ ነጻ የሆኑትን ሁሉ በጅምላ ለመፈረጅ የሚያበቃን አንዳችም ምክንያት የለም። ምክንያቱም በወንጀሉ የተነከሩ፤ እንኳን ከአማኙ ከዋና ዋና ቄሳውስቶች ስላሉ፤ በቪድዮም ጭምር ማስረጃ እያቀረብን… ፍርዱን ለአስተዋዮች እንተወዋለን። 🔽 ስለዚህ የኦርቶዶክስ ወገኖቻችን ሆይ! አንድ ቀን ሲደብረን… ሰሞኑን እየዘረዘርን ያለውን ሺህ አደረጃጀታችሁን ወደ ሌላ ፍረጃ እንዳንወስደው ከፈለጋችሁ፤ በዚያ ግለሰብ ፖስት ስር ስትሸለጠለጡ እንዳላገኛችሁ። ተናግሪያለሁ! እርሱ እኛን የማጋጨት ተልዕኮ ስላለው፤ ህልሙ ስለሚሳካለት «ተው! ታስመታናለህ!» ብትሉት እንኳ አይሰማችሁም። ምክንያቱም መመታታችሁን ይፈልጋል። ግን ችግሩ የማይገባችሁ የእግዜር በጎ°ች ናቸው! ግራ ቀኙን ያላመዛዘነ ዝም ብሎ ጭፍን ጥላቻና ባዶ ስሜት ብቻ! ወደ አዕምሯችሁ ትመለሱ ዘንድ ምክሬ ነው‼ አሊያ…

Open in Telegram
Views552−52%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#10358Text

በአማራ ክልል የሚገኙ 68 የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ተቋማትና አደረጃጀቶች‼ ============================= (ከባሕር ዳር እስከ ጎንደር፣ ከጎጃም እስከ ወሎ፣ ከሰሜን ሸዋ እስከ ዋግ ኽምራ፣ ከዞን ከተሞች እስከ ወረዳዎች!) || ✍️ ልክ የተዋህዶ ልጆች በይፋና በህቡዕ እንደተደራጁት ሁሉ፤ የሙስሊም ወጣቶች በኃይማኖታቸው፣ በትምህርት፣ በበጎ አድራጎትና በማኅበራዊ አገልግሎት ዙሪያ መደራጀት መብታቸው ነው። ወጣቶች በጋራ መቆማቸው፣ ፎቶ መነሳታቸው ወይም የካውንስል አባል መሆናቸው ብቻ የሽብርተኝነት ማስረጃ አይደለም። በወንጀል የተሳተፈ ማንም ሰው በማስረጃ ሊጠየቅ ይገባል። ነገር ግን በሃይማኖት ማንነት ብቻ የጅምላ ውንጀላ ማቅረብ ፍትሕ አይደለም። የመደራጀት ነፃነት ለሁሉም፤ ተጠያቂነትም ለሁሉም በተመሳሳይ የሕግ ሚዛን! 🖊 አንድ የሙስሊም ወጣት ካውንስል መቋቋም በዚህ ልክ ስጋት ሆኖባቸው ስም ለሚያጠፉ አካላት፤ ትናንት በጨረፍታ ካየናቸው 61+ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከሚገኙ ማህበራት ባሻገር፤ ስም ዝርዝራቸው ብቻ ያለኝን በአንድ ክልል በአማራ ክልል ብቻ የሚገኙትን በከፊል ዝም ዝርዝራቸውን ልጋብዛችሁ። 1. የማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል — ባሕር ዳር። 2. የማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል — ጎንደር። 3. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ታቦር ማእከል — ደቡብ ጎንደር። 4. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል — ምሥራቅ ጎጃም። 5. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል — ሰሜን ሸዋ። 6. የማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል — ደቡብ ወሎ። 7. የማኅበረ ቅዱሳን ወልዲያ ማእከል — ሰሜን ወሎ። 8. የማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል — አዊ። 9. የማኅበረ ቅዱሳን ፍኖተ ሰላም ማእከል — ምዕራብ ጎጃም። 10. የማኅበረ ቅዱሳን ሰቆጣ ማእከል — ዋግ ኽምራ። 11. የማኅበረ ቅዱሳን ከሚሴ ማእከል — ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን። 12. የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ባሕር ዳር። 13. የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት — ባሕር ዳር። 14. የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጉባኤ — ባሕር ዳር። 15. የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ ጉባኤ — ባሕር ዳር። 16. የጎንደር ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ጎንደር። 17. መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ኤስድሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 18. ደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 19. የጎንደር ፋሲል ግቢ ጉባኤ — ጎንደር። 20. የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ — ደብረ ማርቆስ። 21. የደሴ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ደሴ። 22. የደሴ ማእከል የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል — ደሴና ኮምቦልቻ። 23. የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ደብረ ብርሃንና አካባቢው። 24. የማኅበረ ቅዱሳን ሽንዲ ወረዳ ማእከል — ምዕራብ ጎጃም። 25. የማኅበረ ቅዱሳን ቻግኒ ወረዳ ማእከል — አዊ። 26. የማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ወረዳ ማእከል — ደሴ። 27. የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት — ባሕር ዳር። 28. ወረታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ወረታ፣ ፎገራ። 29. የጎንደር መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤያት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 30. አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ጎንደር። 31. ደባርቅ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ደባርቅ፣ ሰሜን ጎንደር። 32. እስቴ መካነ ኢየሱስ የመጻሕፍት ጉባኤ — እስቴ፣ ደቡብ ጎንደር። 33. እብናት ደብረ አሜን ተክለሃይማኖት የሐዲሳት ጉባኤ — እብናት፣ ደቡብ ጎንደር። 34. ጣና ቂርቆስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት — ጣና ሐይቅ አካባቢ። 35. ሐይቅ እስጢፋኖስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ — ሐይቅ፣ ደቡብ ወሎ። 36. ሞጣ ጊዮርጊስ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ሞጣ፣ ምሥራቅ ጎጃም። 37. ቢቸና ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ቢቸና፣ ምሥራቅ ጎጃም። 38. መልዕልተ አድባራት ቅዱስ ማርቆስ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት — በመጻሕፍት ድጋፍ ማውጫ የተጠቀሰ። 39. ጨጎዴ ሐና የቅኔ ጉባኤ ቤት — ጨጎዴ። 40. ፍኖተ ሰላም የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ፍኖተ ሰላም፣ ምዕራብ ጎጃም። 41. በልበሊት ኢየሱስ የቅዳሴ ጉባኤ ቤት — በልበሊት። 42. ቆቦ ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሐዲሳት ጉባኤ — ቆቦ፣ ሰሜን ወሎ። 43. ፍላቂት ቅዱስ ገብርኤል የሐዲሳት ጉባኤ — ፍላቂት። 44. ወለህ ማርያም የሐዲሳት ትርጓሜ ጉባኤ — ወለህ። 45. ወለህ ወይብላ ቅድስት ማርያም የሐዲሳት ትርጓሜ ጉባኤ — ወለህ ወይብላ። 46. መርጡለ ማርያም ጉባኤ ቤት — መርጦለ ማርያም፣ ምሥራቅ ጎጃም። 47. ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ዋሸራ፣ ጎጃም። 48. ተድባበ ማርያም የቅኔ ጉባኤ — ተድባበ ማርያም። 49. አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — አበራ። 50. ቁራ አንበሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ቁራ አንበሳ። 51. ቆማ ፋሲለደስ የቆሜ ዜማ ጉባኤ — ቆማ። 52. ፀጉር ሚካኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ፀጉር ሚካኤል። 53. እርግ ዋሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — እርግ ዋሻ። 54. ድንቢሶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ድንቢሶ። 55. የፋርጣ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 56. የላይ ጋይንት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 57. የፎገራ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 58. የምዕራብ እስቴ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 59. የታች ጋይንት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 60. የምሥራቅ እስቴ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 61. የደብረ ታቦር ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 62. የእብናት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 63. የስማዳ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 📌 ከላይ ያሉት 68 ስሞች የተለያዩ የማኅበር ማእከላት፣ የሰንበት ት/ቤቶች፣ የግቢ ጉባኤያት፣ የአብነት ጉባኤ ቤቶችና የቤተ ክህነት መዋቅሮች ናቸው። ስም ዝርዝራቸው የሌለኝ አያሌ አደረጃጀቶች እንደሚኖሩ መገመት ቀላል ነው። ታዲያ የነዚህን ማኅበራት አባላት ፎቶ ዝም ብሎ በመፖሰት በአክራሪነት መፈረጅ ተገቢ ነው ትላላችሁ⁉️ ተው! እረፉ‼ || t.me/MuradTadesse

Open in Telegram
Views732−36%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#10357Photo
Views1,250+9%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#10356Photo
Views1,300+13%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#10355Text
Views1,350+18%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#10354Text
Views1,370+19%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#10353Text

አላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር.. አንተ ሽንፈት አድርገህ የምትቆጥረው ሁሉ ወደ ትክክለኛ መስመርህ የመመለሻ ጉዞ ነው። የሰው ልጅ ሊዋረድ አይወድቅም። የቱ ጋር መቆም እንዳለበት ቦታውን ሊያውቅ ነው የሚወድቀው። ለሩሕያው የማይመጥነውን ሸክም ሊያቃልል ነው የሚወድቀው። በሕይወት ትልቁ ጦርነት ከሰው ጋር አይደለም። ሰዎች የምንወደውን እና የምንጠላውን፣ የምንደብቀውንና ግልጽ የምናወጣውን ሀሳብና ስሜት የሚያንጸባርቁ ምስል ከሳች መስታዎቶች ናቸው። እውነተኛው ጦርነት ግን በውስጥ ነው የሚካህደው። የተደበቀ እውነትና እምነት እያለን ፍርሀታችን ጎልቶ ይታያል። ሩሐችን በንጽህናዋ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ማደግን ስትሻ የነፍስያ ስሜት ፍላጎታችን ወደምድር ትስበናለች። በዚህ መሀል ከራሳችን ጋር በምናደርገው የውስጥ ግብግብና ትግል ውስጥ ነው የእኛ እውነት ያለው። ስብራት የሚመስልህ ሁሉ በአላህ እይታ አንተን የማንጻት ጅማሮ ነው። የአላህ ሒክማ/ጥበብ የሰው ልጅ ተሰብሮ እንዲቀር አይፈቅድም። ባይሆን የጌትነቱ ሒክማ ባሪያው በስብራቱ ምክንያት እንዲበስል ይሻል። ልቡ እንዲመለከት፣ አዕምሮው እንዲነጻ፣ ሩሕያው ቀድሞ በእርሱ አክናፍ ወደነበረችበት ቅድስና እንድትመለስ ይሻል። ለዚህ ነው ቁስል አንዱ የእነጻ ክፍል የሆነው። ክስረት የመማሪያና መረዳት መንገድ፣ ሕመም የእውነተኛው መዳን በር ክንቻር የሆው። የመክፈቻ ቁልፉ ትዕግስትና ጽናት ነው። የመድህን ጎዳናው የሚገለጠው በሩ ሲከፈት ነው። ቅድሚያ ወደ ራስህ ስትመለስ ወደ አላህ ትመለሳለህ። ወደ አላህ ስትመለስ የጠፋውን አቅምህን መልሰህ ታገኛለህ። ያኔ ነገሮችን በፍርሀትህ መጠን ሳይሆን ክስተቱ በሚገባው ብቻ በልኩ መመልከት ትጀምራለህ። የዘገየው ሁሉ እንዳላጣሀው፣ ያጣሀውም ያንተ እንዳልነበር ይገባሀል፣ የተሰበረውም ሁሉ አንተ መልካም መስሎህ ልታገኘው የተመኘኽው ግን የማታየው የሆነን ቆሻሻ አላህ እያስወገደልህ እንደነበር ይገለጥልሀል። ስትበስል ምናልባት ስሜትህን የሚረዳህ እንጂ የሚጠግንህ ፍለጋ አትኳትንም። ለመስተካከልህ አቅጣጫ የሚጠቁምህ አጽናኝ አድርገህ የምትንጠለጠልበት ሰው አይኖርም። በሮችን አታንኳኳም። ይልቁን አላህ ላንተ ያለው የስኬት በር ይከፈት ዘንድ የሚቆረቆረው/የሚንኳኳው በእጅ ሳይሆን በንጹህ ቀልብ መሆኑን አስረግጠህ ታውቃለህ። በዚህ ጊዜ ብቻ.. ሽንፈት ትምህርት መሆኑን ትረዳለህ። ውድቀትም የመነሳትና የከፍታ ጅማሮ መሆኑ ይገለጥልሀል። አላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር! #دكتور #مصطفى_محمود "واعلم أن ما أصابك لم يكن ليخطأك، وأن ما أخطأك لم يكن ليصيبك، رفعة الأقلام وجفة الصحف.. وأن مع العسر يسرى، إجن العسل ولا تخسر الخلية / ያገኘህም ሆነ የሳተህ ጸጋም ሆነ ፈተና ወትሮም ሊያገኝህ አለያም ሊስትህ የተወሰነ እንዳልነበር እወቅ። ከችግርም ጋር ገር ነገር እንዳለ አስታውስ። ማሩን ቁረጥ ቀፎውን ግን አትስበር!። Hamudi Hamudi

Open in Telegram
Views1,870+63%vs avg
Forwards—
Reactions14
Comments—

All posts

Connections