በአልጄሪያ የተጀመረው የፈጅር ሰላት ቻሌንጅ ወደ ተለያዩ ሙስሊም ሀገራት በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። «የፈጅር ወንዶች» የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ቻሌንጅ ከተጀመረ 10 ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በሙስሊም ሀገራት ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል። ቻሌንጁ ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት በላይ የሆኑ ሕፃናትን ለፈጅር ሰላት በመቀስቀስ ወደ መስጅድ ይዞ የመሄድ ሲሆን፣ መነሻውን በ6 ሕፃናት ቢያደርግም አሁን ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ሕፃናት ተቀላቅለውታል። የፈጅር ወንዶች ቻሌንጅ በሀገራችን ኢትዮጵያም ለመተግበር እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የቻሌንጁ ተሳታፊዎች ወደ መስጊድ ሲሄዱና ሲመለሱ የተቀረጸ ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋራሉ።
Открыть в Telegram
ወርቃማ ንግግሮች
ለአስተያየት.. @Golden_SpeechBot 🍂
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 31 окт. 2026 г. | 1 650 |
| 3 нояб. 2026 г. | 1 590 |
| 6 нояб. 2026 г. | 1 130 |
| 7 нояб. 2026 г. | 1 665 |
| 10 нояб. 2026 г. | 1 370 |
| 12 нояб. 2026 г. | 1 350 |
| 15 нояб. 2026 г. | 1 300 |
| 16 нояб. 2026 г. | 1 250 |
| 22 нояб. 2026 г. | 732 |
| 24 нояб. 2026 г. | 528 |
| 25 нояб. 2026 г. | 322 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры1,87 тыс.Пересылки—Реакции14Комментарии—
- 02Просмотры1,78 тыс.Пересылки—Реакции15Комментарии—
- 03Просмотры1,65 тыс.Пересылки—Реакции15Комментарии—
- 04Просмотры1,46 тыс.Пересылки—Реакции5Комментарии—
Новые посты
በነገራችን ላይ… አብዛሃኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ፤ ጌታቸው ሺፈራው የሚባለው ግለሰብ ሰሞኑን የያዘው ውንጀላ ከጀርባው ያዘለውን ሴራ በቅጡ አልተረዳም። 🖊 ይህ ልጅ እንደተለመደው ጎንደር አላባቢ በሚገኙ ቤተ እስራኤላዊያን ሽፋን እስራኤል ከገባ ከ3 አመታት ጀምሮ፣ በተለይም ዜግነት ለማግኘት ብሎ ለመወደድ ብዙ አጀንዳ ከጀርባ ተረክቧል። ይሄውም ኦርቶዶክሱንና ሙስሊሙን ማጋጨት ነው። ለዚህም ሲባል ሰሞኑን እያደረ እንዳለው፤ በፌዴራል ደረጃ ሳይቀር እውቅና ኖሮት በተለያዩ የክልል ከተሞችም አባላትን እያዋቀረ የሚገኘውን የሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አባላት ፎቶ ከፌስቡክ ገፃቸው ላይ እየወሰደ፤ ልክ ተደብቀው ጦር ሲሰለጥኑ ያገኛቸው ይመስል ለዚህ የዋህ መንጋ «ተጠንቀቋቸው፣ ግብፅ ያባረረችው ሙስሊም ብራዘርሁድ አባላት ናቸው!…» እያለ ይፖስታል። 🔗 የኛዎቹ ኦርቶዶክስ ነን ባይ ቂሎች ደግሞ፤ ብዙዎቻቸው ሙስሊም ጠልነት ወትሮውንም የሚያጠናውታቸው ስለሆኑ በደስታ ያራግቡለታል። እንኳን ለርሱ ለዋናዋ እስ•ራኤል ራሱ የሚያራግቡ ናቸው። እርሷ ግን እነርሱ ሞተው እንኳ አብረዋት እንዲቀበሩ አትፈቅድም፣ ወታደሮቿም የእየ•ሱስን ሐውልት ጆሮ ግንዱን እያሉ በሊባኖስ ሲያፈራርሱ ነበር። ጌታቸውን የላከው አይ•ሁዳዊ ቡድን የሚፈልገው፤ ጌታቸው የንጹሐን ሙስሊሞችን ፎቶ እየፖሰተ ሲወነጅል፤ እኛም በርሱ ልክ ለመራመድ ሲባል በየ አካባቢው የሚገኝን በሺዎች የሚቆጠር ኦርቶዶክሳዊ አደረጃጀት ፎቶ እየፖሰትን የሆነውንም ያልሆነውንም በሽ°ብር እንድንፈርጅ ነው። እኛ ግን አናደርገውም። ምክንያቱም፦ 1️⃣ እምነታችን ውሸትን አይፈቅድም። በእልህና በስሜት ተነሳስተን ድንበር እንድናልፍ አልተፈቀደልንም። 2️⃣ ከወንጀሉ ነጻ የሆኑትን ሁሉ በጅምላ ለመፈረጅ የሚያበቃን አንዳችም ምክንያት የለም። ምክንያቱም በወንጀሉ የተነከሩ፤ እንኳን ከአማኙ ከዋና ዋና ቄሳውስቶች ስላሉ፤ በቪድዮም ጭምር ማስረጃ እያቀረብን… ፍርዱን ለአስተዋዮች እንተወዋለን። 🔽 ስለዚህ የኦርቶዶክስ ወገኖቻችን ሆይ! አንድ ቀን ሲደብረን… ሰሞኑን እየዘረዘርን ያለውን ሺህ አደረጃጀታችሁን ወደ ሌላ ፍረጃ እንዳንወስደው ከፈለጋችሁ፤ በዚያ ግለሰብ ፖስት ስር ስትሸለጠለጡ እንዳላገኛችሁ። ተናግሪያለሁ! እርሱ እኛን የማጋጨት ተልዕኮ ስላለው፤ ህልሙ ስለሚሳካለት «ተው! ታስመታናለህ!» ብትሉት እንኳ አይሰማችሁም። ምክንያቱም መመታታችሁን ይፈልጋል። ግን ችግሩ የማይገባችሁ የእግዜር በጎ°ች ናቸው! ግራ ቀኙን ያላመዛዘነ ዝም ብሎ ጭፍን ጥላቻና ባዶ ስሜት ብቻ! ወደ አዕምሯችሁ ትመለሱ ዘንድ ምክሬ ነው‼ አሊያ…
Открыть в Telegramበአማራ ክልል የሚገኙ 68 የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ተቋማትና አደረጃጀቶች‼ ============================= (ከባሕር ዳር እስከ ጎንደር፣ ከጎጃም እስከ ወሎ፣ ከሰሜን ሸዋ እስከ ዋግ ኽምራ፣ ከዞን ከተሞች እስከ ወረዳዎች!) || ✍️ ልክ የተዋህዶ ልጆች በይፋና በህቡዕ እንደተደራጁት ሁሉ፤ የሙስሊም ወጣቶች በኃይማኖታቸው፣ በትምህርት፣ በበጎ አድራጎትና በማኅበራዊ አገልግሎት ዙሪያ መደራጀት መብታቸው ነው። ወጣቶች በጋራ መቆማቸው፣ ፎቶ መነሳታቸው ወይም የካውንስል አባል መሆናቸው ብቻ የሽብርተኝነት ማስረጃ አይደለም። በወንጀል የተሳተፈ ማንም ሰው በማስረጃ ሊጠየቅ ይገባል። ነገር ግን በሃይማኖት ማንነት ብቻ የጅምላ ውንጀላ ማቅረብ ፍትሕ አይደለም። የመደራጀት ነፃነት ለሁሉም፤ ተጠያቂነትም ለሁሉም በተመሳሳይ የሕግ ሚዛን! 🖊 አንድ የሙስሊም ወጣት ካውንስል መቋቋም በዚህ ልክ ስጋት ሆኖባቸው ስም ለሚያጠፉ አካላት፤ ትናንት በጨረፍታ ካየናቸው 61+ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከሚገኙ ማህበራት ባሻገር፤ ስም ዝርዝራቸው ብቻ ያለኝን በአንድ ክልል በአማራ ክልል ብቻ የሚገኙትን በከፊል ዝም ዝርዝራቸውን ልጋብዛችሁ። 1. የማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል — ባሕር ዳር። 2. የማኅበረ ቅዱሳን ጎንደር ማእከል — ጎንደር። 3. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ታቦር ማእከል — ደቡብ ጎንደር። 4. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል — ምሥራቅ ጎጃም። 5. የማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል — ሰሜን ሸዋ። 6. የማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል — ደቡብ ወሎ። 7. የማኅበረ ቅዱሳን ወልዲያ ማእከል — ሰሜን ወሎ። 8. የማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል — አዊ። 9. የማኅበረ ቅዱሳን ፍኖተ ሰላም ማእከል — ምዕራብ ጎጃም። 10. የማኅበረ ቅዱሳን ሰቆጣ ማእከል — ዋግ ኽምራ። 11. የማኅበረ ቅዱሳን ከሚሴ ማእከል — ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን። 12. የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ባሕር ዳር። 13. የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት — ባሕር ዳር። 14. የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጉባኤ — ባሕር ዳር። 15. የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግ ግቢ ጉባኤ — ባሕር ዳር። 16. የጎንደር ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ጎንደር። 17. መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ኤስድሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 18. ደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 19. የጎንደር ፋሲል ግቢ ጉባኤ — ጎንደር። 20. የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ — ደብረ ማርቆስ። 21. የደሴ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ደሴ። 22. የደሴ ማእከል የግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል — ደሴና ኮምቦልቻ። 23. የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት — ደብረ ብርሃንና አካባቢው። 24. የማኅበረ ቅዱሳን ሽንዲ ወረዳ ማእከል — ምዕራብ ጎጃም። 25. የማኅበረ ቅዱሳን ቻግኒ ወረዳ ማእከል — አዊ። 26. የማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ወረዳ ማእከል — ደሴ። 27. የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት — ባሕር ዳር። 28. ወረታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ወረታ፣ ፎገራ። 29. የጎንደር መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤያት ትምህርት ቤት — ጎንደር። 30. አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ጎንደር። 31. ደባርቅ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ደባርቅ፣ ሰሜን ጎንደር። 32. እስቴ መካነ ኢየሱስ የመጻሕፍት ጉባኤ — እስቴ፣ ደቡብ ጎንደር። 33. እብናት ደብረ አሜን ተክለሃይማኖት የሐዲሳት ጉባኤ — እብናት፣ ደቡብ ጎንደር። 34. ጣና ቂርቆስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት — ጣና ሐይቅ አካባቢ። 35. ሐይቅ እስጢፋኖስ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤ — ሐይቅ፣ ደቡብ ወሎ። 36. ሞጣ ጊዮርጊስ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ሞጣ፣ ምሥራቅ ጎጃም። 37. ቢቸና ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ቢቸና፣ ምሥራቅ ጎጃም። 38. መልዕልተ አድባራት ቅዱስ ማርቆስ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት — በመጻሕፍት ድጋፍ ማውጫ የተጠቀሰ። 39. ጨጎዴ ሐና የቅኔ ጉባኤ ቤት — ጨጎዴ። 40. ፍኖተ ሰላም የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤ ቤት — ፍኖተ ሰላም፣ ምዕራብ ጎጃም። 41. በልበሊት ኢየሱስ የቅዳሴ ጉባኤ ቤት — በልበሊት። 42. ቆቦ ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሐዲሳት ጉባኤ — ቆቦ፣ ሰሜን ወሎ። 43. ፍላቂት ቅዱስ ገብርኤል የሐዲሳት ጉባኤ — ፍላቂት። 44. ወለህ ማርያም የሐዲሳት ትርጓሜ ጉባኤ — ወለህ። 45. ወለህ ወይብላ ቅድስት ማርያም የሐዲሳት ትርጓሜ ጉባኤ — ወለህ ወይብላ። 46. መርጡለ ማርያም ጉባኤ ቤት — መርጦለ ማርያም፣ ምሥራቅ ጎጃም። 47. ደብረ ምዕራፍ ዋሸራ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ዋሸራ፣ ጎጃም። 48. ተድባበ ማርያም የቅኔ ጉባኤ — ተድባበ ማርያም። 49. አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — አበራ። 50. ቁራ አንበሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ቁራ አንበሳ። 51. ቆማ ፋሲለደስ የቆሜ ዜማ ጉባኤ — ቆማ። 52. ፀጉር ሚካኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት — ፀጉር ሚካኤል። 53. እርግ ዋሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — እርግ ዋሻ። 54. ድንቢሶ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቅኔ ጉባኤ ቤት — ድንቢሶ። 55. የፋርጣ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 56. የላይ ጋይንት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 57. የፎገራ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 58. የምዕራብ እስቴ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 59. የታች ጋይንት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 60. የምሥራቅ እስቴ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 61. የደብረ ታቦር ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 62. የእብናት ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 63. የስማዳ ወረዳ ቤተ ክህነት መዋቅር — ደቡብ ጎንደር። 📌 ከላይ ያሉት 68 ስሞች የተለያዩ የማኅበር ማእከላት፣ የሰንበት ት/ቤቶች፣ የግቢ ጉባኤያት፣ የአብነት ጉባኤ ቤቶችና የቤተ ክህነት መዋቅሮች ናቸው። ስም ዝርዝራቸው የሌለኝ አያሌ አደረጃጀቶች እንደሚኖሩ መገመት ቀላል ነው። ታዲያ የነዚህን ማኅበራት አባላት ፎቶ ዝም ብሎ በመፖሰት በአክራሪነት መፈረጅ ተገቢ ነው ትላላችሁ⁉️ ተው! እረፉ‼ || t.me/MuradTadesse
Открыть в Telegram#ተጠንቀቁ ⚠️ ትናንት እንዴት ስራ ቦታ ድረስ መጦ እንዳጭበረበረ እዩ ብቻ 🤔 መጀመሪያ cosmotics አስመረጠችውና ገዛ ...ግን አልከፈለም ከዛ ቀጠለና አቢሲኒያ ባንክ ብር ላስልክ #cash ካለሽ የዶድራንቱን ሂሳብ ቀንሰሽ ስጭኝ ። ምን ያህል ነው ያለሽ ሲላት ትንሽ ነው ስትለው እሽ ያለውን ብቻ ስጨኝ ብሎ ቅብል። ከዛ ስልኳን ተቀብሎ የሱን ቁጥር #BAO ብሎ #save ያደርጋል ... ከዛም የምታዩትን text 150,000 birr ገባላት ማለት ኖው 😭 mobile banking wrong password ደጋግሞ ነክቶ #block አስደርጎባታል b.c እሷ ገብታ #check እንዳታደርግበት and then ቀሪውን አውጥተሽ ጠብቂኝ በኋላ በዚህ ሳልፍ #ዶድራንቱ ጋር እወስዳለሁ ብሎ እብስ አለ ማለት አይደል።
Открыть в Telegramሸይኽ ዐብዱልለጢፍ አረፉ‼ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የፈትዋ ጉዳዮች ዋና ሰብሳቢ ሸኽ አብዲለጢፍ ሸረፈዲን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሸይኽ ዐብዱልለጢፍ በወሎ ኬሚሴና ሌሎች አካባቢዎች እድሜቸውን ሙሉ በዳዕዋ እና በኢልም ስርጭት ሲተጉ የቆዩት ነበሩ። የሸይኽ ዐብዱልለጢፍ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ህዳር 6 በአዲስ አበባ ኮልፌ ሙስሊሞች መካነ መቃብር ከዙሁር ሰላት በኋላ ይፈጸማል።ለእሳቸው ጀነትን ፍርደውስ ለቤተሰቡ ሰብሩን ይወፍቃቸው።
Открыть в TelegramПереслано из ኢህሳን jobs Advertising 🌱
በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ የሚገኘዉ ሰላም መስጅድ ኡስታዝ ይፈልጋል (አስቸኳይ) 1 የማስቀራት ልምድ ያለው 2. ኢስላማዊ አደብ የተላበሰ 3.ኪታብ የማስቀራት አቅም ያለዉ 4 ከሰዎች ጋር ተግባቢነት ያለዉ ብዛት:- 1ወንድ ደሞዝ:- በስምምነት ቅጥር በቋሚነት በዚህ ያናግሩን በቴሌግራም @Jilaluebest ለመደወል 0925417548 አስቸኳይ ነው
Открыть в TelegramПереслано из ኢህሳን jobs Advertising 🌱
ኢህሳን jobs Advertising የሰራ ማስታወቂያ የሚለቀቅበት ቻናል ከስራ ማስታወቂያ በተጨማሪ የሚሸጥ ያገለገለ እቃ ኖሯችሁ ገዢ ማግኘት ለተቸገራችሁ የሚሸጠውን እቃ እናስተዋውቃለን በቻናሉ እንለቃለን✅ 👍 @ihsan_1213 👍 @ihsan_1213 ✅🔡🔡🔡🔡🔡🔡🔡 ❤️https://t.me/ihsan_jobs ✅https://t.me/ihsan_jobs
Открыть в Telegramአላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር.. አንተ ሽንፈት አድርገህ የምትቆጥረው ሁሉ ወደ ትክክለኛ መስመርህ የመመለሻ ጉዞ ነው። የሰው ልጅ ሊዋረድ አይወድቅም። የቱ ጋር መቆም እንዳለበት ቦታውን ሊያውቅ ነው የሚወድቀው። ለሩሕያው የማይመጥነውን ሸክም ሊያቃልል ነው የሚወድቀው። በሕይወት ትልቁ ጦርነት ከሰው ጋር አይደለም። ሰዎች የምንወደውን እና የምንጠላውን፣ የምንደብቀውንና ግልጽ የምናወጣውን ሀሳብና ስሜት የሚያንጸባርቁ ምስል ከሳች መስታዎቶች ናቸው። እውነተኛው ጦርነት ግን በውስጥ ነው የሚካህደው። የተደበቀ እውነትና እምነት እያለን ፍርሀታችን ጎልቶ ይታያል። ሩሐችን በንጽህናዋ ወደ ሰማይ ከፍ ብላ ማደግን ስትሻ የነፍስያ ስሜት ፍላጎታችን ወደምድር ትስበናለች። በዚህ መሀል ከራሳችን ጋር በምናደርገው የውስጥ ግብግብና ትግል ውስጥ ነው የእኛ እውነት ያለው። ስብራት የሚመስልህ ሁሉ በአላህ እይታ አንተን የማንጻት ጅማሮ ነው። የአላህ ሒክማ/ጥበብ የሰው ልጅ ተሰብሮ እንዲቀር አይፈቅድም። ባይሆን የጌትነቱ ሒክማ ባሪያው በስብራቱ ምክንያት እንዲበስል ይሻል። ልቡ እንዲመለከት፣ አዕምሮው እንዲነጻ፣ ሩሕያው ቀድሞ በእርሱ አክናፍ ወደነበረችበት ቅድስና እንድትመለስ ይሻል። ለዚህ ነው ቁስል አንዱ የእነጻ ክፍል የሆነው። ክስረት የመማሪያና መረዳት መንገድ፣ ሕመም የእውነተኛው መዳን በር ክንቻር የሆው። የመክፈቻ ቁልፉ ትዕግስትና ጽናት ነው። የመድህን ጎዳናው የሚገለጠው በሩ ሲከፈት ነው። ቅድሚያ ወደ ራስህ ስትመለስ ወደ አላህ ትመለሳለህ። ወደ አላህ ስትመለስ የጠፋውን አቅምህን መልሰህ ታገኛለህ። ያኔ ነገሮችን በፍርሀትህ መጠን ሳይሆን ክስተቱ በሚገባው ብቻ በልኩ መመልከት ትጀምራለህ። የዘገየው ሁሉ እንዳላጣሀው፣ ያጣሀውም ያንተ እንዳልነበር ይገባሀል፣ የተሰበረውም ሁሉ አንተ መልካም መስሎህ ልታገኘው የተመኘኽው ግን የማታየው የሆነን ቆሻሻ አላህ እያስወገደልህ እንደነበር ይገለጥልሀል። ስትበስል ምናልባት ስሜትህን የሚረዳህ እንጂ የሚጠግንህ ፍለጋ አትኳትንም። ለመስተካከልህ አቅጣጫ የሚጠቁምህ አጽናኝ አድርገህ የምትንጠለጠልበት ሰው አይኖርም። በሮችን አታንኳኳም። ይልቁን አላህ ላንተ ያለው የስኬት በር ይከፈት ዘንድ የሚቆረቆረው/የሚንኳኳው በእጅ ሳይሆን በንጹህ ቀልብ መሆኑን አስረግጠህ ታውቃለህ። በዚህ ጊዜ ብቻ.. ሽንፈት ትምህርት መሆኑን ትረዳለህ። ውድቀትም የመነሳትና የከፍታ ጅማሮ መሆኑ ይገለጥልሀል። አላወቅክም እንጂ አላህ የጠፋህን እየመለሰልህ ነበር! #دكتور #مصطفى_محمود "واعلم أن ما أصابك لم يكن ليخطأك، وأن ما أخطأك لم يكن ليصيبك، رفعة الأقلام وجفة الصحف.. وأن مع العسر يسرى، إجن العسل ولا تخسر الخلية / ያገኘህም ሆነ የሳተህ ጸጋም ሆነ ፈተና ወትሮም ሊያገኝህ አለያም ሊስትህ የተወሰነ እንዳልነበር እወቅ። ከችግርም ጋር ገር ነገር እንዳለ አስታውስ። ማሩን ቁረጥ ቀፎውን ግን አትስበር!። Hamudi Hamudi
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
Mujib Amino Z islam@mujibbinislamРелигия13,8 тыс.
Orthodox picture ✝@orthodox_photoРелигия14 тыс.
የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)@sultan_54Религия13,3 тыс.
EQUIP Media/Mamusha Fenta@mamusha_fentaРелигия14,4 тыс.
ISLAM IS UNIVERSITY@islamisuniverstiy_public_groupРелигия13,2 тыс.
ABU MUSLIM A-DUROOS@abumuslimalarsiРелигия13 тыс.
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡@ibrahim_furiiРелигия15,1 тыс.
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸@hamdquanteРелигия12,2 тыс.