Кабинет
ISLAM IS UNIVERSITY

ISLAM IS UNIVERSITY

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው 📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው አስተያየት👇 t.me/AnuSeu

Юзернейм
@islamisuniverstiy_public_group
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики13 186
Просмотров на пост, 7 дн.—за 7 дней
ERR7,96 %в среднем за 30 дней

Новые посты

#9571Текст

🏅🏅🏅ለማስታወስ ያህል🏅🏅🏅       ✍🏼አሚር ሰይድ 🟢 ነቢዩ ﷺ  አንድ ጉዳይ ያስጨነቃቸው እንደሆነ ያሀዩ ያቀዩሙ ቢረህመቲከ አስተጊስ፡፡ ይሉ ነበር፡፡ 🟡 ነቢዩ ﷺየሆነ ነገር ያሳሰባቸው ያስጨነቃቸዉ እንደሆነ ራሳቸውን ወደ ሰማይ ቀና በማድረግ ሱብሀነሏህ አልዐዚም ይላሉ፡፡ 🔴 ጠንከር ያለ ዱዓዕ ማድረግ ሲፈልጉም ያ ሐይዩ ያ ቀይዩሙ ይሉ ነበር፡፡ 🟢ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- አንድ የተጨነቀ ሰዉ ጭንቀቱን የምታቀልለት ዱአ ልጠቁማችሁ ነብዩ የኑስ በዓሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሆኖ ጌታውን የጠራበት ፡-ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነዟሊሚን አንድ ሙስሊም ይሄን ዱዓ ካደረገ፡ አላህ ለዱዓዉ ምላሽ ይሰጠዋል ብለዋል 🟡ሰዉ ወይም ሲፈራ የሚባል ☞አሏሁመ ኢና ነጅአሉከ ፊኑሁሪሂም ወነኡዙ ቢከ ሚን ሹሩሩሂም 🔴 የሆነ ቦታ ላይ ሲቀመጡ አኡዚ ቢከሊማቲላሂ ታማ ሚንሸሪ ማኸለቅ 🟢ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-ጠዋትና ማታ ሐስቢየሏሁ ላ ኢላሀ አላሁወ ዐለይሂ ተወከልቱ ወሁወ ረቡል ዐርሽል ዐዚም ሰባት ጊዜ ያለ ሰው ከዱነያም ሆነ ከአኺራ ጉዳይ ያሳሰበውን ሁሉ አላህ ይበቃዋል።ብለዋል 🟡 አቡሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-ሲነጋና ሲመሽ 100ጊዜ ሱበሀነሏህ ወቢሀምዲሂ ያለ እንደርሱ ወይ ከእሱ በላይ ይህን ቃል ያለ ሲቀር ሌላ ሰዉ ከእርሱ የላቀ ደረጃ ይዞ በዕለተ ቂያማ አይመጣም(ሙስሊም) 🔴 ጃቢር እንዳስተላለፉት ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ሱብሀነሏህ ወቢሀምዲሂ ያለ ጀነት ዉስጥ የተምር ዛፍ ትተከልለታለች(ቲርሚዚ) 🔷 ነብዩﷺ ለአንዱ ሱሀባ እንዲህ አሉት:- የመግሪብ ሶላትን እንዳጠናቀቅክ ሰባት ጊዜ አሏሁመ አጅርኒ ሚነናር፡አላህ ሆይ ከእካት ጠብቀኝ በል፡፡እሷን ብለህ በዚያ ለሊት የሞትክ እንደሆነ ከሷ መጠበቅ ይፃፍልሀል፡፡ ☞ሱብሒ ስትሰግድም ይህንኑ በል፡፡ያንኑ ቀን የሞትክ እንደሆነ ከጀሀነም እሳት መጥጠበቅ ይፃፍልሀል፡፡ 🔶 ነብዩﷺእንዲህ ብለዋል ከሱብሂ ሶለት ቡሀላ መስገጃዉ ላይ ሶላት እንደሚሰግደዉ እግሮቹን አቆላልፎ ላኢለሀኢለሏህ ወህደሁ ላሸሪከለሁ ለሁልሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ዩህይ ወዩሚቱ ወሁወ አላኩሊሸይኢን ቀዲር ያለ ☞10ወንጀል ይሰረዝለታል ☞10ደረጃ ከፍ ይላል ☞ከሸይጧን ይጠበቃል ☞ከእለቱ መጥፎ ነገር መከላከያ ይሆነዋል ብለዋል Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры1 0500%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#9570Текст

🎖🎖 #ዉሸታም_ሁኖ_እስኪመዘገብ_ድረስ🎖🎖                  ✍🏼አሚር ሰይድ ⚡️⚡️ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሰው ሁልጊዜ ይዋሻል፣ ውሸትንም ይፈልጋል፣ እስከመጨረሻም በአላህ ዘንድ ውሸታም ሆኖ እስኪመዘገብ ድረስ።” በዚህ ዘመን ስንቶቻችን ይሆን እለት በዕለት ዉሏችን በዉሸት ሁኖ ኑሯችን ዉሸት ሁኖ ዉሸታም ተብለን በአላህ ቤት የተመዘገብነዉ??? አሏህ ሱወ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ብሏል፡- وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ “የውሸትን ንግግር ራቁት።” (ሱረቱል ሐጅ 30) ☞إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي مَنْ هُوَ كَاذِبٌ كَفَّارٌ “አላህ ውሸታምና ክህደተኛ የሆነን ሰው አይመራም።” (ሱረቱዝ ዙመር 3) 💚 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ስለ ዉሸት አስቀያሚነት ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:- ወንድምህ የምታወሪውን ነገር እውነት ነው ብሎ አምኖ እየተቀበለህ አንተ ግን ስትዋሽው ከዚህ በላይ ክህደት የለም፡፡"ብለዋል 💛 በሌላ ንግግራቸው የመናፍቅ ምልክቶች ሶስት መሆናቸውን ጠቅሰው ከእነዚያ ውስጥ አነዱ ሲናገር የሚዋሽ መሆኑን ገልጸዋል። ቡሀሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ነብዩ ﷺእንዲህ ብለዋል፡- «إِيَّاكُمْ وَالْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وَإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ» “ከውሸት ተጠንቀቁ፤ ውሸት ወደ ኃጢአት ይመራል፣ ኃጢአትም ወደ እሳት ይመራል።” ❤️ ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ የዉሸት ከባድነትን ሲገልፁ እንዲህ ብለዋል - "አንድ ሰው በሚዋሽበት ጊዜ ከድርጊቱ መግማት የተነሳ መላዕክት አንድ ማይል ያክል ከእርሱ ይርቃሉ በእርግጥ ውሸት የሚገማ ነገር ነው:: መላዕክት እንደዚያ ተጸይፈዉ የሚርቁት ከሆነ አላህን ምን ያህል ያስከፋዋል? ልብ በሉ ይህን ዋሾ ሰው መላዕክት የሚርቁት _ ከሆነ እርሱን የሚቀርቡት እነማን ናቸው? ያለጥርጥር ሰይጣናት ናቸው የሚሆኑት፡፡  ሰይጣናት ይቀርቡትና እነርሱ እንደሚፈልጉት እያደረጉ ይጫወቱበታል፡፡ የነቢዩ ﷺ ባልደቦች እንደመሰከሩት "የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ዘንድ ከመዋሸት የበለጠ የተጠላ ባህሪ የለም ዋሾው ሰው ተፀፅቶ እስኪመለስ ድረስ'' ብለዋል፡፡ 🔰🔰 ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦ «እውነትን ያዙ፤ እውነት ወደ በጎነት ይመራል፣ በጎነትም ወደ ጀነት ይመራል። ከውሸት ተጠንቀቁ፤ ውሸት ወደ ኃጢአት ይመራል፣ ኃጢአትም ወደ እሳት ይመራል።» ብሀዋል.... በዚች የትንኝ ክንፍ በማትመዝን የዉሸት አለም ኑሮን ህይወትን ትዳርን በዉሸት የተሞላ ማድረግ ለነገ የአኼራ የኪሳራ ካርድ ዱንያ ላይ ባንቆርጥ መልካም ነዉ፡፡ እስኪ ትናንት ከተናገርካቸዉ ከዋልክባቸዉ...ስትነግድ ከዋልክ በዉሸት ነዉ ስታግባባ ስትሸጥ የዋልከዉ??? ጓደኛህ ጋር ስትዉል ስታወሩ ወይ ስታወሪ የዋልሽዉ እዉነት ነዉ ወይስ ዉሸት?? ብቻ ቀን በቀን ያለንን ዉሎ የትናንትን መርምረን የዛሬና የመኖር እድል ከአላህ ከተሰጠ ደግሞ የነገን ህይወት ከዉሸት ለመራቅ እንሞክር....ነገ ከአላህ እድል ካልተሰጠ ዛሬ ዉሸት ስንገበይ ስናወራ ዉለን የህይወት ካርዷ ብትቆረጥ ዉሸታችንን ይዘን ቀብር ገብተን አላህ ፊት ብንቀርብስ ብለን አስበንዋል ............??????❔⁉️ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры2 300+119%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#9568Текст

ሴትና መፅሀፍ! Women is a book of everyday’s edition ሴት ....መነኩሴና ህፃን ካልሆነ በቀር ፍቅር ያላስያዘችውና አቅሉን ያላሳተችው ወንድ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ብዙ ወንድ ህይወቱ የሚባለሸዉ ነገሮች የሚምታቱበት ሴት ታፈቅረኛለች ብሎ ያፈቀረ ጊዜ ነዉ ...ሴትን አፍቅራታለሁ እንጂ ታፈቅረኛለች ማለት ራስን መሸወድ ነው ነገ ከነገ ወዳ የሚፈጠረዉን ብናቅ ኑሮ ዛሬ ማፍቀራችን ስህተት መሆኑን እንገነዘብ ነበር...ችግሩ የምናቀዉ ነገ ከነገ ወዳ የተወሰም ብዙም አመታት ቡሀላ ከረፈደ ከረፈደ ከረፈደ ከረፋፈደ ቡሀላ ነዉ!!! ፍቅር ለአፍቃሪዉም ለተፈቃሪዉም ሚዛናዊ አይደለም የሚወዱት ጋር ለመኖር ፍቅር .............??? ✈ ሶቅራጦስ የሚስቱ ዛፒቴ ጭቅጭቅ መፈላሰፊያ መንገዱ ፍልስፍና የጀመረበት እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ✈አነስታይንን ስለሴት ምንነት ግራ ያጋባችው ሚስቱ ማሊቫ ነበረች፡፡ ✈ ሌላኛው ስለሴት ዕድሜውን ሙሉ የተመራመረውና ሴትነትን እንዲህ ነው ብሎ ጠቅልሎ መደምደም ያልቻለው የሥነልቦና ባለሞያው ፍሮይድም የሴት ነገር እንቆቅልሽ ሆኖበት ነው ሕይወቱ ያለፈው፡፡ ሴቶችን እድሜ ልኩን ተመራምሯቸዉ ሳያቃቸዉ ነዉ የሞተዉ ✈ ኒቼም ስለሴት ብዙ ብሏል፡፡ ✈ ሾፐንሐወርም እናቱ ስላገለለችው ለሴት ያለው አመለካከት ጥሩ አይደለም፡፡ ♦ ሴትነት ማለት ሴቶቹ ለራሱ በደንብ የማያውቁት ልዩ ሚስጥር ነው፡፡ ☞ መፅሐፍን መላልሰሽ /መላልሰህ በማንበብ ትረጂው/ትረዳዉ ይሆናል፤ ሴት ግን  ሳታገባም አግብታም ሆነ ወልዳ ከብዳም ማንነቷን መረዳት ከባድ ነው፡፡ ☞ መፅሐፍት አይለዋወጡም፤ ሴቶች ግን በነበሩበት አይቆዩም፡፡ ☞ ሴትን ከስስ ገላዋ በላይ ማንነቷን ማወቅ ያጓጓል፡፡ ☞ሴቶች አሁን መልአክ፤ በኋላ ሰይጣን የመሆን ሀይል አላቸዉ፡፡ ስሜታችን ተለዋዋጭ፤ ሃሳባችን ተቀያያሪ፤ ዓመላቸዉ የማይጨበጥ ነው፡፡     አንዳንድ መፅሀፍ ልክ እንደሴት ፍቅር ሁሌ ካላየሁትና ካላነበብኩት ያሰኛል፡፡ የወደድከዉ መፅሀፍ ባነበብከዉ ቁጥር የልብ ደስታ ይሰጥሀል፡፡ ለዚህ ነው ስብሐት ዛዚ በተባለው የትርጉም መፅሐፉ፡- ‹‹በሕይወታችን ከጥቂት ሴቶች ጋር ብቻ ፍቅር እንደሚይዘን፤ በንባባችንም ከጥቂት መፃሀፍት ጋር ብቻ ፍቅር ይይዘናል፡፡ ይሄ ማለት በድብርት ወይም በብስጭት ሰዓት ላይ ስንሆን ይህንኑ ደጋግመን ያነበብነውን መፅሐፍ የሆነ ገፅ ከፍተን ማንበብ እንጀምራለን፡፡ ንባባችን ሲቀጥል ቀስበቀስ ሳይታወቀን ድብርታችን እየለቀቀን ይሄድና ንባባችን የሙጥኝ መሆኑ አልፎ የመዝናናትና የመደሰት ይሆናል፡፡›› የሚለው፡፡     ሴት በየጊዜው ህትመቷ የሚሻሻል መፅሐፍ (Women is a book of everyday’s edition) ነችና ዕለት ዕለት መነበብ አለባት፡፡ አንብቧቸዉ!! የቀን በቀን ልዩነት ዉጤት ናቸዉ ትናንት ሌላ ዛሬ ሌላ ነገ ደግሞ.......??? እንጃ ምን እንደሚሆኑ አታቃቸዉም ሌላ ..... ====================================== ====================================== ዑመር ቢን ኸጧብ رضي الله عنه  ሴቶች ሶስት አይነት ናቸዉ ይላሉ #አንደኛዋ  ገራገር፣ ምቹ፣ ቁጥብና ጥብቅ የሆነች ሙስሊም ሴት ነኝ። አፍቃሪም፣ ተፈቃሪም፣ ማህፀነ ለምለም የሆነች ሴት። ባሏ ሲቸገር ከጎኑ የምትቆም፣ አብሽር ያልፋል እያለች የምታጠናክር፣ ይገባሃል፣ የእጂህን ነው ያገኘኸው፣ ደግ ሆነሃል፣ ኧረ ሲያንስህ ነው በማለት በመከራው ላይ ሌላን መከራ የማትደራርብ አይነት ሴት። የዚች አይነት ሴት በጣም ጥቂት ናቸውና ማግኘቱም ከባድ ነው። #ሁለተኛዋ አይነት ሴት: ቁጥብና ጥብቅ ሙስሊም ሴት ነች። ባይሆን ግን ልጅ ከመውለድ ያለፈ ምንም ሚና የላትም። (ይችም ለክፉ አትሰጥም።) #ሶስተኛዋ ሴት አመለ ክፉ መከራና ቅማል የሆነች ሴት ነች። ከራስ ላይ የማትወርድ፣ በአንገት ላይ የተጠመጠመች ማነቆ፣ በእጅ ላይ የገባች የመከራ ካቴና፣ ራቂ ቢሏት የማትርቅ፣ አብረሽ ኑሪ ብለው ቢተዋት ሰላም የማትሰጥ፣ አላህ ፈተናን ለፈለገበት ባሪያው የሚሰጣት፣ አላህ ካልሆነ በስተቀር የማያስወግዳት አይነት የፈተና ሸክም የሆነች ሴት። {ሙሰነፍ ኢብኑ አቢ ሸይባ} Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры3 720+254%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#9567Текст

🎖🎖 #በጥበብ_የተሞሉ_ንግግሮች ✍አሚር ሰይድ ⭐️ አቡ በክር አስ-ሲድ-ዲቅ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል ☞ለሞት ጓጓ፤ ሕይወትን ይሰጥሀልና፡ ☞ነፍስን አሳምር፤ ሰዎች ላንተ ያሳምሩልሀልና። ☞በልብ ድርቀት እንጂ እንባ አልደረቀም፡፡ ☞በኃጢአቶች ብዛት እንጂ ቀልቦች አልደረቁም፡፡ ብለዋል ⭐️ዑመር አል-ፋሩቅ (ረ.ዐ) ይህን ብለዋል ☞ሚስጥሩን የደበቀ ሰው አማራጩ በእጁ ነው። ☞ሦስት ነገሮች በወንድምህ ደረት ውስጥ ውዴታሀን ያፀኑልሀል፦ ➊በሰላምታ መጀመር፣ ➋ለርሱ መጅሊስን ማስፋትና ➌ እርሱ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ በሆኑ ስሞች እርሱን መጥራት ብለዋል ⭐️ ዑስማን ቢን አፋን እንዲህ ብለዋል፡- አራት ነገሮች ውጪአቸው ሲታይ ትሩፋት ሲሆን ውስጣቸው ሲታይ ደግሞ ግዴታ ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ➊ ከደጋግ ሰዎች ጋር መቀላቀል ትሩፋት ሲሆን ነገር ግን በነርሱ መመራት ግዴታ ነዉ፡፡ ➋ ቁርአንን ማንበብ ትሩፋት ሲሆን ነገር ግን በርሱ መሥራት ግዴታ ነው። ➌ ቀብርን መጎብኘት ትሩፋት ሲሆን ለርሱ መሰናዳት ለቀብር መዘጋጀት ግን ግዴታ ነው። ➍ የታመመን ሰው መጠየቅ ትሩፋት ሲሆን ተግሳፅን መውሰድ ግን ግዴታ ነው። ብለዋል፡፡ ⭐️ ዐሊይ ቢን አቢ ጣሊብ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- ☞ የታገለ ሰው አሸነፈ፡፡ ንፉግ የሆነ ሰውም ተዋረደ፡፡ ከሰዎች ሁሉ በጣም ቸሩም ይሰጠኛል ብሎ ከርሱ ለማይከጅል ሰው የሰጠው ነው። ☞ ዓመቱ የተለያየ ሆኖ ሲዞር አይቻለሁ ....... ሀዘንም ሆነ ደስታ አይዘወትርም፡፡ ☞ ንጉሣን በርሱ ውስጥ ቤተ መንግስትን ገንብተዋል ....ንጉሳን ሆነ ቤተ-መንግስቱ ግን ኋላ ቀሪዎች አልሆኑም። ☞አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲል የወደደህ ሰዉ ያንን ጥቅም ሲያጣብህ ወዲያዉኑ ተሰላችቶ ይተዉሀል ☞ይቺ አለም ህልም ናት፡ መጭዉ አለም ንቃት ነዉ፡፡እኛ ደግሞ በመካከላቸዉ በህልም ቅዠት ዉስጥ እንገኛለን ☞የማጣትም ሆነ የመጎዳት ዋናዉ ምክንያት ግዴለሽነት ባህሪ ነዉ ☞አላህ ዘንድ ያለዉን ደረጃ ለማወቅ የፈለገ ሰዉ እርሱ ለአላህ ብሎ የሚያደርገዉን ነገር ይመልከት ☞አንዳንድ ጊዜ የማግኘት ተስፋ ወደ ማጣት፡የማትረፍ ተስፋ ወደ መክሰር ያመጣል ☞ልማድ ጠንካራ ሀይል ነዉ በድብቅ አንድን ነገር የለመደ ሰዉ በአደባባይ ያጋልጠዋል ☞የዋህ ብሎ ማለት አንድ ጉድጓድ ወስጥ ሁለቴ የወደቀ ነዉ ☞በእሱና በአላህ መካከል ያለዉን ነገር ያስተካከለ አላህ በርሱና በሰዎች መካከል ያለዉን ነገር ያስተካክልለታል ☞በራስ ስራ መኮፈስ ራስን በራስ የሚደረግ ምቀኝነት ነዉ ☞አላህ የሰጠዉን ነገርወዶ የተቀበለ ባላገኘዉ ነገር አያዝንም ☞ምላስ አዉሬ ነዉ መረን ከለቀቀ ይናከሳል ወዘተ ሁሉንም አሏህ ኸይር ስራቸዉን ይቀበላቸዉ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры3 080+193%к среднему
Пересылки—
Реакции20
Комментарии—
#9566Текст

🎖🎖✋ #ሰላምታህ_የሰላም_ይሁን✋🎖🎖                      ✍🏼አሚር ሰይድ ወዳጄ ሆይ! አሁንም ወደፊትም ልብህን አፅዳ፡፡ ደስተኛ ሕይወት ትኖራለህ፡፡ ቀለል ብሎህ ውለህ ታድራለህ፡፡ እፎይ ብለህ ትተኛለህ። አዎን ውስጥህን አፅዳ፡፡ ☞ በውስጥህ እየተራገምክ በአንደበትህ አትመርቅ። ☞ በልብህ እያጉረመረምክ በንግግር አታታልል፡፡ ሠላምታህ የሠላም ይሁን፡፡ ቃልህ የፍቅር ይሁን፡፡ ከአሽሙርና ከማሽሟጠጥ ተጠንቀቅ። ☞ ወዳጄ ሆይ በነገር እየወጋህ  አትሸንግል፡፡ የጎሪጥ እያወራህ አታስመስል፡፡ የቱን ያህል ብትበደልም በወንድምህ ላይ የጥላቻ ክስ አትመስርት፣ በባልንጀራህ ላይ የውሸት ፋይል አትክፈት፤ በጓደኛህ ላይ የግፍ ጦር አታንሳ፡፡ ☞ ጠላትን የመጠንቀቁ ነገር እንዳለ ሆኖ ስለሰው መልካም ነገር እንጂ አታስብ፡፡ ጥሩ በማሰብህ ትክክል ከሆንክ ጥሩ ምንዳ ታገኛለህ።መጥፎ አስበህ ከሆነ ደግሞ በመጥፎ ጥርጣሬ ወንጀል ላይ ትወድቃለህ። ⚡️⚡️ከሰዎች መካከል እንዲሁ ከመሬት ተነስተው በውስጣቸው ለያንዳንዱ የሰው ልጅ የመገምገሚያ ኬላዎችንና የፍተሻ ጣቢያዎችን የሚያቋቁሙ አሉ፡፡ ይህች አጭር እድሜያችን ለዚህ ሁሉ የምትበቃ አይደለችም። በመሆኑም እጅግ ውድ የሆነው እድሜህን፣ እጅግ አጭር የሆነችውን ጊዜህን ውድ ለሆነው ፍቅር እንጂ ርካሽ ለሆነው ጠላትነት መስጠት የለብህም ሐቢቢ…፡፡ ☞ ወዳጄ ሆይ! ውስጥህ የጥላቻና የተንኮል ወደብ የሆነ እንደሆነ፣ በምድር ላይ ቆይታህ ሴራ ብቻ የምትጎነጉን ከሆነ በገዛ እጅህ መርዝ እየተጋትክ መሆነን እወቅ፡፡ ይቅር ባይነትና ትእግስት ጠላትን ለመጋፈጥ ትልቁ መሳሪያ ሆኖ ሣለ ቸኩለህ በደል የምትፈፅም ከሆነ ሽንፈትን እንጂ ድልን እትጎናፀፍም፡፡ ውድቀት እንጂ ስኬት አታገኝም፡፡ ሀቢቢ በጉልበትህ፣ በገንዘብህና በወገኖችህ ከምትተማመነውና ከምትታገዘው በላይ በይቅርታና ትእግስት በማድረግህ አላህ (ሱ.ወ) የበለጠ ያግዝሃል። ✏️ህልም አለኝ ከሚለዉ ሙሀመድ ሰይድ መፅሀፍ የተዘጋጀ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры2 740+161%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#9565Текст

📕📕 ሐሰነ ልአ-በስሪ አላህ አዛኝ ነዉ ብለዉ ለሚዘነጉ ሰዎች ይሄን ምክር ጀባ ብለዉ አልፈዋል፡-    “ምህረት እናገኛለን በሚል አጉል ምኞት ተሞልተው አንዳች በጎ ስራ ሳይኖራቸው ከዱንያ ዓለም የወጡ ሰዎች አሉ። እንዲህም ሲሉ ራሳቸውን ያታልላሉ፡-በታላቁ ጌታዬ ላይ በጎ ጥርጣሬ አለኝ። በጎ ስራዬ በዛም አነሰም ግድ የለኝም። በግርጥም እንዲህ የሚል ሰው ዋሽቷል። ምክንያቱም በጌታው ላይ በጎ ጥርጣሬ በርግጥ ቢኖረው ኖሮ ስራውን ያሳምር ነበርና። አላህ (ሱ ወ) እንዲህ ይላል። { وَذَ ٰ⁠لِكُمۡ ظَنُّكُمُ ٱلَّذِی ظَنَنتُم بِرَبِّكُمۡ أَرۡدَىٰكُمۡ فَأَصۡبَحۡتُم مِّنَ ٱلۡخَـٰسِرِینَ } “ይህም ያ በጌታችሁ የጠረጠራችሁት ጥርጣሪያችሁ አጠፋችሁ። ከከሳሪዎቹም ኾናችሁ ( ይባላሉ) ። (ፉሲለት23) 📒📒 በተጨማሪ ደግሞ የሕያ ኢብን ሙዓዝ እንዲህ ይላሉ፡- ☞ከሽንገላ ሁሉ ትልቁ ሽንገላ ራስን መሸንገል ነው፤ ይቅርታን ተስፋ በማድረግ ያለ ምንም ፀፀት በወንጀል ላይ ለረጅም ጊዜ መቆየት ነው፤ ☞አላህን ያለመታዘዝ ወደ አላህ መቃረብን መመኘት ነው፤ ☞የጀሀነም ዘርን ዘርቶ የጀነትን አዝርዕት መጠባበቅ ነው፤ ☞ወንጀል ላይ ተዘፍቆ አላህን የታዘዙ የአላህ ባሮች የሚገቡበትን ጀነት መመኘት ነው፤ ☞ስራ ሳይሰሩ ደመወዝን መጠበቅ ነው፤ በአጠቃላይ ከኸይር ስራ ሙሉ ለሙሉ ርቆ በአላህ ላይ ከንቱ ምኞት መመኘት ነው።” 📗📗አቡ ሓሚድ አል-ገዛሊ በመደጋገም ይሄን ዱዓ ያደርጉ ነበር፦ “ጌታዬ ሆይ! የማይሰሩትን ከሚናገሩ ሰዎች አታድርገን፤ ከሚሰሙ ግን ከማይቀበሉ ሰዎች አትደምረን፤ይሉ ነበር ❤️❤️❤️ ዛሬ የጁምአ ለይል ነዉ ዱንያዉም እንዲሰምር አኼራዉም እንዲያምር ነገ የቀብሩ ጥበት እንዲሰፋ የቀብሩ ጨለማ እንዲበራ... ነፍስያችንን ለመግራት ከቆሻሻ ነፍስያ ለመንጣት ...ነፍስያ ለመግራት ምክንያት እንዲሆነን... የዛ ቀን ጥም በሚበረታበት ሀዉድ በእጃቸዉ ከምንጠጣዉ እንዲያደርገን አላህ እሱን ወዶ ሁሉን ያስወደደዉ ለከዉኑ አይነታ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሶለዋት እናዉርድ { إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَـٰۤىِٕكَتَهُۥ یُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِیِّۚ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَیۡهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسۡلِیمًا } አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡(አል አህዛብ 56) ሶሉ አለል ሀቢብ ሰይዲና ሙሀመድﷺﷺ💚💚💚 🌙✨መልካም ኸሚስ ምሽት 🌙✨ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ 💚💚💚💚💚 ®Amir seid Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры2 790+166%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#9563Текст

🔥🔥 #ያቺ_የምትንቀለቀል_እሳት🔥🔥 ✍🏼 አሚር ሰይድ    ዐሊይ አቡጧሊብ ከዕለታት አንድ ቀን ኩመይል ከሚባል ሰዉ ጋር  ወደ መቃብር ቦታ አመሩ፤ እዚያ እንደ ደረሱም እንዲህ አሉ፡- "...እናንተ የመቃብር ነዋሪዎች ሆይ! እናንተ አካላችሁ ወደ ብናኝ የተቀየረ ሰዎች ሆይ እናንተ የብቸኝነት ባለቤቶች ሆይ! ..እናንተ ዘንድ ያለው ዜና ምን ይሆን? እኛ ዘንድ ያለዉ ዜና ☞ ንብረታችሁ ለወራሾች ተከፋፍሏል ☞ ልጆቻችሁ የቲሞች  ሆነዋል፤ ☞አሳዳጊ አልባ ሆነው ቀርተዋል፤ ☞ሚስቶቻችሁን ሌሎች ሰዎች አግብተዋል። ይህ እኛ ጋ ያለው ዜና ነው፤ እናንተ ጋ ያለው ዜና ምን ይሆ?!" ይህንን ካሉ በኋላ ወደ እኔ ዘወር ብለው፦ “አንተ ኩመይል ሆይ .... ሙታኑ መልስ እንዲሰጡ ቢፈቀድላቸው ኖሮ ' #ከስንቅ_ሁሉ_በላጩ_አላህን_መፍራት_ነው!' የሚል ምላሽ ይሰጡን ነበር።” አሉኝ። ዐሊይ ይህንን ተናግረው ተንሰቅስቀው አለቀሱ😢። አስከተሉና እንዲህ ሲሉ ምክራቸውን ለገሱኝ፦ “ኩመይል ሆይ! መቃብር የስራ ሳንዱቅ ነው፤ ውስጡ ያለውን ዜና የምታውቀው የሞትክ ዕለት ነው።” (ሐያቱ ሶሐባ፤ ካንደህለዊይ) ⚡️⚡️⚡️ ከቀብር ቡሀላ ያለዉ ህይወት እና የጀሀነም እሳት  ያሳሰባቸዉ ዑመር ኢብን ዐብደል አዚዝ ..ከዕለታት በአንድ ሌሊት  ሰዎች በተሰበሰቡበት የአል-ለይል ምዕራፍን አነበቡ:- { وَٱلَّیۡلِ إِذَا یَغۡشَىٰ (1 ) وَٱلنَّهَارِ إِذَا تَجَلَّىٰ (2) وَمَا خَلَقَ ٱلذَّكَرَ وَٱلۡأُنثَىٰۤ (3) إِنَّ سَعۡیَكُمۡ لَشَتَّىٰ (4) فَأَمَّا مَنۡ أَعۡطَىٰ وَٱتَّقَىٰ (5) وَصَدَّقَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ (6) فَسَنُیَسِّرُهُۥ لِلۡیُسۡرَىٰ (7) وَأَمَّا مَنۢ بَخِلَ وَٱسۡتَغۡنَىٰ (8) وَكَذَّبَ بِٱلۡحُسۡنَىٰ (9)  فَسَنُیَسِّرُهُۥ لِلۡعُسۡرَىٰ (10) وَمَا یُغۡنِی عَنۡهُ مَالُهُۥۤ إِذَا تَرَدَّىٰۤ (11) إِنَّ عَلَیۡنَا لَلۡهُدَىٰ (12) وَإِنَّ لَنَا لَلۡـَٔاخِرَةَ وَٱلۡأُولَىٰ (13) فَأَنذَرۡتُكُمۡ نَارࣰا تَلَظَّىٰ (14) } “በሌሊቱ እምላለሁ፤  በፅልመቱ ፍጡራንን በሚሸፍን  ጊዜ፣ በቀኑም በገተለፀ ጊዜ፣.......... የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው)  (አል ለይል፡ 1-14) ዑመር “የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው)::" የሚለውን የምዕራፉን ክፍል ሲያነቡ እንባ ተናነቃቸው። አንቀፁን ማጠናቀቅ አልቻሉም። ድጋሚ ወደ ምዕራፉ መጀመሪያ ክፍል ተመለሱ። ማንበባቸውንም ቀጥለው “የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ በላቸው ።" የሚለው አንቀፅ ላይ ሲደርሱ አሁንም ይንሰቀሰቁ ጀመር😢። ይህችን አንቀፅ ማለፍ አልቻሉም። በመጨረሻም ምዕራፉን ትተው ሌላ ምዕራፍ ማንበብ ጀመሩ። ✏️ነገ ወይ ዛሬ ሞት እያለና ...ያቺ የምትንቀለቀል እሳት እኛን ምን ያህል አሳስቦን ለይለ ተነስተን አልቅሰናል??ምን ያህል ሰደቃ ሰጥተናል??ምን ያህል የሰዉ ሀቅ ላይ ጠንቃቃ ሁነናል?? ግን እኛ የምንኖረዉ አኗኗር ቆም ብለን አስበንዋል?? ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺሁላችሁም እንዳኗኗራችሁ ትሞታላችሁ እንዳሟሟታችሁ ትቀሰቀሳላችሁ ያሉንን ሀዲስ ምን ያህል አስተንትነንዋል?? 🎖🎖 ወሀብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- ብልህ የሆነ ሰው ከአራት ጊዜያቶች መዘናጋት የለበትም:: ➊ ከአላህ ጋርተገልሎ ጉዳዩን ለሱ የሚነግርበት ጊዜ፣ ➋ስለ አጠቃላይ ሁኔታው ራሱን የሚመረምርበት ጊዜ፣ ➌ስለ እውነት ብለው ጥፋቱንና እንከኑን ከሚነግሩት ጓደኞቹ ጋር የሚገለልበት ጊዜ እና ➍ከራሱ ነፍስ ጋር ብቻውን ተገልሎ የሚያምራት እና የምትፈልገውን ነገር ከሷ የሚያቅበበት ጊዜ፡፡ እነኚህ ሰዓታት ለነዚያ የትንሳኤ ቀን ሰዓታት ያግዙታል፡፡ ቀልቡንም ያበሩለታል፡፡ ብልህ ሰው በሶስት ነገሮች ላይየዘወትር ትኩረቱን ያደርጋል፡- ▶️ ለነፍሱ የሚሰንቅበት ጊዜያት፣ ▶️ ለምድር ላይ ኑሮው የሚሰራበት ጊዜያት እና ▶️ ሐራም ባልሆነ ነገር ላይ የሚዝናናበት ጊዜያት፡፡ ብልህ የሆነ ሰው ያለበትን ዘመን ሁኔታ የሚያውቅ፤ ምላሱን የሚጠብቅ፣ አጠቃላይ ሁኔታውን የሚመረምር መሆን ይኖርበታል፡፡ ብለዋል Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры2 980+184%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#9562Текст

👐 #አለይከ_ረበና_ቢሁስኒል_ሂታሚ             ✍ አሚር ሰይድ      “ግብፅ ውስጥ አንድ ሰው ነበር ይባላል። ይህ ሰው የመስጂድ ሙአዚን በመሆኑና ከጀመዓ ሶላት ባለመጥፋቱ ይታወቃል። ከዕለታት በአንዱ ቀን  እንደተለመደው አዛን ለማለት ወደ ሚናራ ይወጣል። ከሚናራው ስር የሚኖር የአንድ ክርስቲያን ግለሰብ ቤት ይገኛል። ይህ ሙአዚን ዓይኑን ወደ ቤቱ ሲወረወር የባለቤቱን ሴት ልጅ ይመለከታል። በውበቷ በእጅጉ በመፈተኑ አዛን ማለቱን ትቶ ከሚናራው ወረደ። ወደ ቤቷም አመራ። በሩን አንኳኳ። ምን ፈልገህ ነው?' ስትል ጠየቀችው። 'የፈለግኩት አንቺን ነው' ሲል መለሰ። ልጅቱም: 'ለምን ፈለግከኝ?' ስትል ጠየቀችው። እርሱም: "ልቤን ተቆጣጥረሽዋል፤ ልቦናዬን ሰልበሽዋል' ሲል መለሰ። ልጅቱም 'ለዝሙት ፈቃደኛ አይደለሁም' አለችው። ሰውዬውም:-ላገባሽ ዝግጁ ነኝ” አላት። "አንተ ሙስሊም ነህ፤ እኔ ደግሞ ክርስቲያን:: አባቴ አንተን እንዳገባ ፈቃደኛ አይሆንም”አለችዉ "ክርስቲያን እሆናለሁ” የሚል ነበር የሰውዬው መልስ። እርሷም፡- "ይህንን ማድረግ ከቻልክ እኔም ሚስትህ እሆናለሁ” ስትል ፈቃደኝነቷን ገለፀች። ከዚያም ሰውዬው እርሷን ለማግኘት ባለው ከፍተኛ ጉጉት ምክኒያት እምነቱን ቀየረ። ከቤተሰቦቿ ጋርም መኖር ጀመረ። ጋብቻውን በፈፀመበት ሰሞን ወደ ጣሪያ ላይ ወጣ። ከጣሪያዉም ድንገት ወደቀና ህይወቱ አለፈች😔። ይህ ሰው ዲኑን አጣ። እርሷንም አላገኘ። ከአጨራረስ ክፋት ደጋግመን በአላህ እንጠበቃለን!!። ለዚህም ነው የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የሚከተለውን ምክር ጀባ ብለዉናል፦ “አጨራረሱን ሳትመለክቱ በአንድ ሰው ስራ አትደነቁ።' ( አጥ-ጦበራኒ) Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры3 020+188%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#9561Текст

🏅🏅#የጀመአና_ሶላትና_እኛስ??🏅🏅            ✍🏽 አሚር ሰይድ     ዓይነ ስውር የነበረው ኢብኑ ኡሙ መክቱም ሰይዲና ሙሀመድ ﷺን በቤቱ እንዲሰግድ ፈቃድ ጠየቀ።   ..ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉት፦ هَلْ تَسْمَعُ النِّدَاءَ بِالصَّلَاةِ؟ "የሶላትን ጥሪ (አዛን) ትሰማለህ?" "አዎ" ባለ ጊዜ "እንግዲያ ጥሪውን ተቀበል ወደ መስጊድ መጥተህ ስገድ አሉት 🟢🟢.....ዛሬ ላይ ከኔ ጀምሮ ጀመአ ሶላት ለመስገድ አይናችን እያየ ግን ልባችን ጨልሟል፡፡ ለአይነ ስዉሩ ኢብኑ መክቱም እቤቱ እንዲሰግድ ፍቃድ ያላገኘዉ የእኛ እቤት ለመስገድ ማን ፍቃድ እንደሰጠንና ለፍረዱ ቀን ምን አይነት ኡዙር እንደምንሰጥ ግራ ያጋባል ወገን፡፡ ታዳ የበፊት ምርጥ ትዉልዶች ለጀመአ ሶላት ያላቸዉ ክብር የተወሰኑትን በዱንያ ያሳለፉትን ሀል ስናወሳ ✏️ ታዋቂው የሐዲሥ ሊቅ ቢሽር ኢብን አል-ሐሰን “አሱ ሶፍፊይ” - የሚል ቅፅል ስም ነበራቸው። ለሀምሳ ዓመታት ያህል የመጀመሪያው ሶፍ አምልጧቸው አያውቅም ነበር። ✏️ በተመሳሳይ መልኩ ኢብራሂይም ኢብን መይሙን ይወሳሉ። የአንጥረኝነት ባለሙያ ነበሩ። መዶሻቸውን አንስተው እያለ አዛን ከሰሙ ባለበት ያቆሙት ነበር። ✏️ የሶሪያው ዋነኛ ዳኛ ሱለይማን ኢብን ሀምዘተል መቅዲሲይ እንዲህ ይላሉ፦ "የግዴታ ሶላቶችን ብቻዬን የሰገድኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። እነርሱን ሶላቶች በርግጥ እንዳልሰገድኳቸው ይሰማኛል።” ይህንን ሲሉ እድሜያቸው ወደ ዘጠና ተቃርቦ ነበር። ✏️✏️ የቡኻሪና የሙስሊም መምህር የነበሩት ዑበይደላህ ኢብን ዑመር አልቀዋሪይሪ እንዲህ ይተርኩልናል፦ “የዒሻእ ሶላት ጀመዓ አምልጦኝ አያውቅም ነበር፡፡ አንዲት ሌሊት እንግዳ ቤቴ አረፈ። እርሱን በማስተናገድ ተጠመድኩ፡፡ የዒሻ ጀማዓ ሶላት አለፈኝ። በስራ ከተማ ውስጥ ያሉ መስጅዶችን እየዞርኩ ጀመዓ ፍለጋ ማሰንኩ። ሁሉም መስጅዶች ጀመዓ ተሰግዶ መስጅዶቹም ተዘግተዋል። ወደ ቤቴ ተመለስኩ። ለራሴ እንዲህ እልኩ። ሶላተል ጀመዓ በተናጠል ከሚሰገድ ሶላት በሃያ ሰባት ደረጃ እንደሚበልጥ በሐዲስ ተነግሯል።' የዒሻእ ሶላትን ሀያ ሰባት ጊዜ ሰገድኩ። ከዚያም ተኛሁ። በህልሜ ሰዎች ጋር የፈረስ ውድድር እያደረግኩ ተመለከትኩ። ፈረሴን በፍጥነት እጋልባለሁ፤ ግን ልደርስባቸው አልቻልኩም ከነርሱ መካከል አንዱ ወደኔ ዘወር አለና፦ 'ፈረስህን አታድክመው፤ ልትደርስብን አትችልም።' አለኝ። 'ለምን?' እልኩት። 'እኛ ዒሻእን በጀመዓ ሰግደናል፤ አንተ ግን ብቻህን ነው የሰገድከው' አለኝ። በከፍተኛ ሃዘንና ጭንቀት ላይ ስሆን ከእንቅልፌ ነቃሁ።" ብለዉ ጀመአ ሶላት ያለፈባቸዉን ይቆጫሉ... እኛስ የጀመአ ሶላት ጋር ያለን ቁርኝነት ምን ያህል እንደሆነ ራሳችንን ብንፈትለሽ መልካም ነዉ Join👇👇 t.me/IslamisUniverstiy_public_group   t.me/IslamisUniverstiy_public_group

Открыть в Telegram
Просмотры3 800+262%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#9560Текст
Просмотры3 400+224%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—

Все посты

Связи