በዘሪሁን ግርማ የተጻፈው "ሚዲያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን" የተሰኘው መጽሐፍ ዶክመንተሪ ሐሙስ ማታ በኢቫንጀሊካል ሚዲያ ኔትወርክ ቲቪ ይጠብቁን
Открыть в Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው። "ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 13 нояб. 2026 г. | 2 950 |
| 16 нояб. 2026 г. | 2 780 |
| 19 нояб. 2026 г. | 2 320 |
| 25 нояб. 2026 г. | 924 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры2,95 тыс.Пересылки—Реакции9Комментарии—
- 02Просмотры2,78 тыс.Пересылки—Реакции14Комментарии—
- 03Просмотры2,32 тыс.Пересылки—Реакции16Комментарии—
- 04Просмотры924Пересылки—Реакции13Комментарии—
Новые посты
ሸክላዉ በእግዛብሔር እጅ የተሰኘ በቄስ ይተፋ ጎበና ህይወት ታሪክ እና አገልግሎት ዙሪያ የተጻፈ መጽሐፍ ሊመረቅ ነዉ ህዳር 9ቀን2019 ዓ .ም ሸክላዉ በእግዛብሔር እጅ የተሰኘ በቄስ ይተፋ ጎበና ህይወት ታሪክ እና አገልግሎት ዙሪያ በቄስ እሰይ ሞሬሳ የተጻፈ መጽሐፍ ምርቃት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል። መጽሐፉን የጻፋት ቄስ እሰይ ሞሬሳ ዋና አላማዉ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሰጡ እና ለዚህ ትዉልድ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ለማስተማር እንደሆነ ገልጸዉ የሸክላዉ ባለቤት እግዚብሔር ስራ ላይ ያተኮረዉ ይህ መጽሐፍ 7ምዕራፎች በ267 ገጾች የተዋቀረ እንደሆነ ገልጸዋል። በመግለጫዉ ላይም የተገኙት የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ፕሬዝዳንት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያን ታሪክም ጭምር መሆኑን ገልጸዉ ለትዉልዱ ብሎም ለሀገር ትልቅ ጥቅም እንዳለዉ አክለዋል። በኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ 22 አብይ ጉባኤ በሚካሔድበት ወቅት ህዳር 17 ቀን2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ በመካነኢየሱስ ሴሚነሪም እንደሚመረቅም ተነግሯል። በአማረኛ የተጻፈዉ ይህ መጽሐፍ ወደ ኦሮምኛም የተተረጎመ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተቁሟል። ለኢቫንጀሊካል ዜና ሩት ዋቅጅራ
Открыть в Telegramየመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ “የሕይወት ሚዛን”መጽሐፍ ተመረቀ ሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም በመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ የተጻፈው “የሕይወት ሚዛን”የተሰኘው መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በቦሌ አጥቢያ ጉባኤ ተመረቀ። በመጽሐፉ ምረቃ ላይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት እና የሰርክል ተቋም መሥራች የሆኑት ፓስተር ጽድቁ አብዶ፣ የተለያዩ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ የጸሐፊው ወዳጆችና የመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ ቤተሰቦች ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ላይ ፓስተር ጽድቁ አብዶ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ “የሕይወት ሚዛን”የተሰኘውን መጽሐፍ አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል። የመጽሐፉ ደራሲ መጋቢ ዮሐንስ ሞገስ በበኩላቸው፣ መጽሐፉ ስለ ግል ሕይወት፣ ስለ ቤተሰብ፣ ስለ ቤተክርስቲያንና ስለ አገር የሚያስፈልገውን የሕይወት ሚዛን በመጠበቅ እንዴት መኖር እንደሚቻል የሚያስተምር መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ለመጽሐፉ ዝግጅት 20 አመታት የፈጀባቸውን ጊዜና የጽሑፍ ሂደቱን አብራርተዋል። በሌላ በኩል ፓስተር ቢንያም መጽሐፉን ደሳው የክርስቲያን መሪነት በውስጥ ከሚገኝ የሕይወት መሠረት የሚመነጭ መሆኑን አስመልክተው፣ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ሚዛኑን ጠብቆ መኖር እንደሚገባው አስተምረዋል። “የሕይወት ሚዛን”መጽሐፍ ምረቃ በእምነት፣ በግል ሕይወት፣ በቤተሰብና በአገልግሎት ዘርፎች ሚዛናዊ ኑሮን ለመገንባት መሆኑ ተገልጾዋል።
Открыть в Telegramለወንጌላውያን የሚዲያ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ተካሄደ የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሙያዎች ማኅበር ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ስልጠና በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል ተካሂዷል። ስልጠናው የሚዲያ ባለሙያዎች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና፣ ክርስቲያናዊ የሚዲያ አጠቃቀም፣ ተግባቦት እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንት በሆኑት ፓስተር ሰንበቶ ባሼ ጸሎት የተከፈተ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ደረጀ ታፈሰ በደረጉት ንግግር የሚዲያ ባለሙያዎች ስለ ወንጌል ሲሉ ለሚከፍሉት መስዋዕትነት ዋጋቸውን የማይረሳ ታማኝ ጌታ እንዳለ በመግለጽ የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ደራሲ ጋዜጠኛ፣ ተመራማሪ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ በሰጡት ስልጠና ባለሙያዎች በሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የኅብረቱ የሰላምና አድቮኬሲ ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ሂርጳሳ በበኩላቸው የሚዲያ ባለሙያዎች ለሀገር ሰላም መስፈን ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል። በመጨረሻም የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ወንድም ዘሪሁን ግርማ ስልጠናው የወንጌል አገልግሎትን ለማስፋትና ሰላምን ለማስፈን ሰፊ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ ለስልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረገው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምስጋና አቅርበዋል። በቤተልሔም ደረጀ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የወንጌል አማኞች ድምፅ t.me/evangelicalmedia 📞251 998870672 ላይ ያገኙናል
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸@hamdquanteРелигия12,2 тыс.
#KALTUBE@kaltubeРелигия11,8 тыс.
ABU MUSLIM A-DUROOS@abumuslimalarsiРелигия13 тыс.
ISLAM IS UNIVERSITY@islamisuniverstiy_public_groupРелигия13,2 тыс.
የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)@sultan_54Религия13,3 тыс.
ወርቃማ ንግግሮች@golden_speechРелигия13,8 тыс.
Mujib Amino Z islam@mujibbinislamРелигия13,8 тыс.- Orthodox picture ✝@orthodox_photoРелигия14 тыс.