👂ይደመጥ‼️ 📖{فَدَعَا رَبَّهُ أَنِّي مَغْلُوبٌ فَانتَصِرْ} {"እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ" ሲል ጌታውን ተጣራ፡፡} 👆ስለዚች አንቀፅ አጠር ያለ ዳሰሳ!! https://t.me/hamdquante
Открыть в Telegram
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ 👇🏾👇🏾👇🏾 @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል 👉🏿 @hamdquante_bot👈🏿
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 21 нояб. 2026 г. | 2 280 |
| 22 нояб. 2026 г. | 1 862 |
| 23 нояб. 2026 г. | 1 753 |
| 24 нояб. 2026 г. | 1 675 |
| 25 нояб. 2026 г. | 1 320 |
| 26 нояб. 2026 г. | 446 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры2,28 тыс.Пересылки—Реакции16Комментарии—
- 02Просмотры2,06 тыс.Пересылки—Реакции37Комментарии—
- 03Просмотры2,05 тыс.Пересылки—Реакции16Комментарии—
- 04Просмотры1,99 тыс.Пересылки—Реакции9Комментарии—
Новые посты
✍️ ክስተቱ የሚተርከው ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ነው……… የተቡክ ዘመቻ ጊዜ ነብዩﷺ ገንዘብ እንድናዋጣ አዘዙን። እንደ አጋጣሚ ሆነና በጊዜው እጄ ላይ የሆነች ሳንቲም ነበረች፤ ሁኔታው ተመቸኝና "እንደው አቡበክርን በልጬ የምገኝበት ቀን ካለ ዛሬ ነው" ብዬ ከንብረቴ ግማሹን ይዤ ወደ ረሱልﷺ መጣሁኝ። የአላህ መልእክተኛﷺ «ለቤተሰብህ ምን አስቀረህላቸው?» ሲሉኝ "አምሳያውን አስቀርቼላቸዋለሁ" አልኳቸው። ወድያው አቡበክር ሲዲቅ ያለው ንብረቱ ሙሉውን ተሸክሞ መጣ። ረሱልﷺ «ለቤተሰብህ ምን አስቀረህላቸው?» ሲሉት; "አላህና መልእክተኛውን አስቀርቼላቸዋለሁ" አላቸው። በዚህ ጊዜ……… "ወላሂ አቡበክርንማ በምንም ነገር ልቀድመው አልችልም አልኩኝ" ይላል። ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/hamdquante
Открыть в Telegram🔖 በመካ የባርነት ገበያ ከመሸጥ ጀምሮ <እስከ> በሰብር እና በየቂን የተገነባ የኢማን አርኣያነት!! ገና በህፃንነቱ ነበር በጠላት ተማርኮ የወሰደው። የወሰዱት ሰዎች ወደ ቅድስቲቷ ከተማ መካ ወስደው በባርነት ሸጡት። የመካ ነዋሪ የነበረችዋ ኡሙ አንማር አል-ሁዛዒያ የተባለች ሴት ለሽያጭ ከቀረቡ ባሮች መሃል መርጣ ገዛችው። እሷም የዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ረዲየላሁ አንሁ አባት የሆነው የዐውፍ ቢን ዐብዱ ዐውፍ አል-ዙህሪ የቅርብ ወዳጅ ነበረች። አባቱ ኢብኑ አረት ቢን ጀንደላ የቢን ሳዕድ ልጅ ሲሆን: ከተሚም ጎሳ ቅርንጫፎች አንዱ ከሆነው ከበኒ ሳዕድ ቢን ዘይድ መናት ነበር፤ ከኹዛዓ ጎሳም ነው ተብሏል። 👇 👉አንጋፋው ሰሓብይ ኸባብ ኢብኑ አረት‼️ ኸባብ በጃሂሊያ ዘመን ሰይፍ በማምረት ሥራ ይሠራ ነበር። በዚህ ጥበብም የተካነ ነበር። ነቢዩ ሙሐመድﷺ ልቡን ለማቀራረብ ይቀርቡትና አብረውት ይቀመጡ ነበር። ከዚያም አላህ ልቡን ለእስልምና ከፈተለት፤ ወደ እስልምና ቀድመው ከገቡት የመጀመሪያ ሰዎችም አንዱ ሆነ። ነቢዩﷺ ወደ ዳሩል አርቀም ቤት ከመግባታቸው በፊት ነው የሰለመው። ቅድሚያ ከሰለሙ ስድስት ሰዎች እሱ ስድስተኛው ነበር። እስልምናን ከተቀበሉት በቅደም ተከተል ሃያኛው ነበርም ተብሏል። ኸባብ እስልምናውን በግልጽ ባወጣ ጊዜ ከሙሽሪኮች ከባድ በደል ደረሰበት። ሃይማኖታቸውን ትተው ከእስልምና እንዲወጡ በመካ መኳንንቶች ስቃይ ከደረሰባቸው ደካሞች መካከል አንዱ ነበር። ሙሽሪኮች እሳት ያነዱና ጀርባው በሙቀቱ እስኪበሰል ድረስ በላዩ ላይ ያስቀምጡበታል። ከዚያም መሬት ላይ ይጥሉትና ከእነሱ አንዱ መጥቶ ደረቱ ላይ ይወጣና እንዳይንቀሳቀስ ይረግጠው ነበር። ስቃዩ በዚህ ብቻ አላቆመም፤ ገዢው የነበረችው ኡሙ አንማር በእሳት የጋለ ብረት ወስዳ ራሱ ላይ ታስቀምጥበታለች። በዚህም ሕመሙንና ስቃዩን ትጨምርበታለች። የሚደርስበት ስቃይ በበረታበት ጊዜ ወደ ነቢዩﷺ ሄዶ የደረሰበትን መከራ ጠቅሶ ፈረጅ እንዲመጣለት እገዛም እንዲጠይቁለት ነገራቸው። ነቢዩﷺ «አላህ ሆይ! ኸባብን እርዳው» ብለው ዱዐ አደረጉለት። ከዚያ በኋላ ኡሙ አንማር ራሷ ላይ በከባድ በሽታ ተፈተነች፤ ከሕመሙ ብዛት እንደ ውሻ እያላዘነች ትጮኻለች። ለህመሟ ህክምና ስታጠያይቅ በእሳት መተኮስ መድኃኒቷ እንደሆነ ተነገራት። ለዚህም ራሷን በጋለ ብረት የሚተኩሳት ሰው ያስፈልጋት ነበር፤ ከዝያም ኸባብ ራሱ እንዲያክማት ተደረገና የጋለውን ብረት እያመጣ አናቷ ላይ ያስቀምጥባት ነበር። /ብድር በምድር እንደሚሉት/ 📍ሙጃሂድ የተባለው ሊቅ እስልምናቸውን ይፋ ያደረጉ የመጀመሪያዎቹን ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡- "እስልምናቸውን ይፋ ያደረጉ የመጀመሪያዎቹ የአላህ መልዕክተኛﷺ፣ አቡ በክር፣ ኸባብ፣ ሱሃይብ፣ ቢላል፣ ዐማር እና የዐማር እናት ሱመያ ናቸው። የአላህ መልዕክተኛﷺ አላህ በአጎታቸው በአቡ ጣሊብ ጠበቃቸው፤ አቡ በክር ደግሞ በጎሳው ጠበቀው። ሌሎቹን ግን የመከራ ዓይነት አቀመሷቸው፤ በጋለ ብረት በፀሐይ ላይ አቀለጧቸው፤ ከብረቱና ከፀሐዩ ሙቀት የተነሳ አላህ የሻውን ያህል ድካምና ስቃይ ደረሰባቸው።" ኸባብ ረዲየላሁ ተዓላ አንሁ በስቃይ ፊት ለትዕግሥትና ለጽናት ምሳሌ ነበር። የደረሰበት ስቃይ ቢበረታም ከእምነቱ አልተመለሰም፤ የሙሽሪኮችን ጥያቄም አልተቀበለም። 📍ዓሚር አል-ሻዕቢ ኸባብ ላይ የደረሰበትን ስቃይ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡- "ኸባብ ታገሰ፤ ከሓዲዎች የጠየቁትንም አልሰጣቸውም። የጀርባው ሥጋ እስኪወልቅ ድረስ ጀርባውን በጋሉ ድንጋዮች አቃጠሉት።" ሙሽሪኮች ከሙቀቱ ብዛት የጀርባውን ሥጋ እስኪወልቅ ድረስ የኸባብ ጀርባ ላይ የጋሉ የተቃጠሉ ድንጋዮች ያስቀምጡ ነበር። ይሁንና ስቃዩ ምንም ያህል ቢደርስ እስልምናውን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በሃይማኖቱ ጸንቶ ቆየ። ከሙሽሪኮች ጋር ከገጠሙት ክስተቶች መካከል; በመካ ሰይፍ በማምረት ላይ በነበረበት አንድ ቀን ለዐስ ቢን ዋኢል አስ-ሰህሚ ሰይፍ ሠራለት። ሠርቶ ሲጨርስ ዋጋውን ሊጠይቀው ወደ እሱ ሄደ። ዐስ ገንዘቡን መክፈል እምቢ አለ። ገንዘቡን ሊሰጠው ከፈለገ በሙሐመድﷺ መካድ እንዳለበት ነገረው። ኸባብም በጽናትና በእርግጠኝነት እንዲህ ሲል መለሰለት፡- "አንተ ሞተህ ተመልሰህ እስክትቀሰቀስ ድረስ በሙሐመድﷺ አልክድም!!" አለው። ዐስም በማላገጥ እንዲህ አለው፡- "ከተቀሰቀስኩ በኋላ ገንዘብ ይኖረኛል፤ ያኔ እከፍልሃለሁ።" ኸባብም ወደ ነቢዩﷺ ሄዶ የተባባሉትን ነገራቸው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ቁርኣን አወረደ፡- 📖﴿أَفَرَأَيْتَ الَّذِي كَفَرَ بِآيَاتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالًا وَوَلَدًا أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِنْدَ الرَّحْمَنِ عَهْدًا كَلَّا سَنَكْتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُ مِنَ الْعَذَابِ مَدًّا وَنَرِثُهُ مَا يَقُولُ وَيَأْتِينَا فَرْدًا﴾ ኸባብ ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ የተሸከመው የስቃይ መጠን ታላቅ መሆኑን ከሚያሳዩ ነገሮች ውስጥ; በዑመር ቢን አል-ኸጧብ የኸሊፋነት ዘመን አንድ ቀን ዑመር በመካ ከሙሽሪኮች ስለደረሰበት ነገርና በእስልምናው ምክንያት ስለደረሰበት የስቃይ ዓይነቶች ጠየቀው። ኸባብም፡- "የምእመናን መሪ ሆይ! ጀርባዬን ተመልከት" አለና ጀርባውን ከፈተለት። ዑመር ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ የኸባብ ጀርባውን ባየ ጊዜና እሳቱ በአካሉ ላይ የተወውን የስቃይና የተቃጠለ ምልክት በተመለከተ ጊዜ ባየው ነገር ተደነቀና "ዛሬ ያየሁት ዓይነት አይቼ አላውቅም" አለ። ኸባብም የደረሰበትን ጽናት በማብራራት እንዲህ ሲል መለሰለት፡- "እሳት አነደዱብኝ፤ ያነደዱብኝ እሳት የጀርባዬ ስብ (ቅባት) ቢያጠፋው እንጂ ሌላ ነገር አላጠፋውም ነበር። የንግግሩ ትርጉም፦ ሙሽሪኮች እሳት አቀጣጥለው በሙቀቱ ሲያሰቃዩት ከጀርባው ላይ ስቡ እስኪቀልጥ ድረስ እንደሆነና ከቃጠሎው ብርታት የተነሳ ከአካሉ በፈሰሰው ስብ እንጂ እሳቱ እንዳልጠፋ ነው። አላህ ለሙስሊሞች ሂጅራን (ስደትን) ከፈቀደ በኋላ ኸባብ ከሚቅዳድ ቢን ዐምር ጋር ወደ መዲና ተሰደደ፤ በኩልሱም ቢን አል-ሀድም ቤትም አረፉ። ከዚያም ነቢዩ በኸባብ እና በጀብር ቢን ዐቲቅ መካከል የወንድማማችነት ትስስር አደረጉ። ኸባብ ከአላህ መልዕክተኛﷺ ጋር በሁሉም ጦርነቶችና ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል። እስልምናን ከመደገፍና በሁኔታዎቹ ከመሳተፍም ወደ ኋላ አላለም። የአላህ መልዕክተኛﷺ እስኪሞቱ ድረስ በጂሃድ እየተሳተፈ አብሯቸው ዘልቋል። ከነቢዩﷺ ሞት በኋላ የእስልምና ፍቱሓት እንቅስቃሴ ሲጀመር፤ የመንግሥቱም ግዛት ሲሰፋ፧ ኸባብ ቢን አረት ወደ ኩፋ ተዛውሮ እዚያ ተቀመጠ። በሰላሳ ሰባተኛው ዓመተ ሂጅራ ኸባብ በኩፋ ሞተ፤ ዕድሜውም ሰባ ሦስት ዓመት ነበር። ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ ሰገደበት። በኩፋ እምብርት የመጀመሪያ የተቀበረው ሰሓብይ እሱ ሆነ። በሞተ ጊዜ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ በእስልምናው የደረሰበትን በመግለጽ ደረጃውንና ቦታውን የሚያሳዩ ታላላቅ ቃላት ተናገረለት። እንዲህም አለ፡- "አላህ ለኸባብ ይዘንለት፤ በውዴታው ሰለመ፣ በታዛዥነት ተሰደደ፤ ሙጃሂድ ሆኖ ኖረ፤ በአካሉም የተለያዩ ሁኔታዎች ተፈተነ፤ አላህም ምንዳውን አያስቀርበት!!" 🤲አላህ ከረሱልﷺ እና ዕንቁ ባልደረቦቻቸውጋ በጀነት ያጎራብተን🤲 ✍አቡ ሙስሊም ሐምዱ ቋንጤ!! https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio 👆 👇 https://t.me/hamdquante
Открыть в TelegramПереслано из Unknown
💥🗣️የመጨረሻ ጥሪ🗣️💥 🕋 ወደ ተቀደሰው ቤት አብረን እንጓዝ 🤖1️⃣2️⃣ተኛ ዙር ልዩ የዑምራ ፓኬጅ🎁 ከተወዳጁ የለምለም ትራቭል ጋር ወደ መካና መዲና የማይረሳ የዒባዳ ጉዞ ይቀላቀሉ ⭐ወስን💻 🕋 ሁለት ጁሙዐዎችን በሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች 🌄አስደሳችና የተለየ ቆይታ በሐረመይን በኢማን፣ በኢባዳና በመንፈሳዊ ደስታ የተሞላ ጉዞ 🗓 የጉዞ ቀን 📥📥📥 🟢 ከረጀብ🥰እስከ🥰🥰 🟢ታህሳስ🥰እስከ🥰🥰 🟢December🥰🥰to🥰🥰 የምዝገባ ጊዜው ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል ዕድሉ አያምልጥህ ዛሬውኑ ተመዝገብ 0911674580 0911904297 0978333346 📍አድራሻ ቤተል ሚና ሞል 2ተኛ ፎቅ https://t.me/Yelemlem_travel
Открыть в Telegram✍ በቻልከው ልክ ከብዙ ሰዎች ጋ ላለመተዋወቅ ሞክር; የቂያማ ቀን የምትዋረድበት ነገር ቢገጥምህ ቢያንስ የሚያውቁህ ሰዎች ብዙ አይሆኑም!! https://t.me/hamdquante
Открыть в Telegram📖{فَخَسَفْنَا بِهِ وَبِدَارِهِ الْأَرْضَ} የዚህች አንቀፅ ማብራሪያ!! https://t.me/hamdquante/11426
Открыть в Telegram✍ ቢሽር ቢን ሓሪስ……… 📍አንድም ዱንያን አብዝቶ የሚወድ የለም; ሞትን ቢጠላ እንጂ!! 📍አንድም አላህን መገናኘት የሚወድ የለም; ዱንያ ላይ ቸልተኛ ቢሆን እንጂ!! https://t.me/hamdquante
Открыть в Telegram✍ በክር ቢን ዐብዱላህ አል_ሙዘኒ……… በዕድሜ ከእሱ የሚበልጡ አባቶች ሲያይ; "ይህ ከእኔ በበለጠ ረዥም ዓመታት አላህን መገዛት የቻለ ሰው ነው: ከእኔ እሱ ይሻላል!!" በዕድሜ ከእሱ የሚያንሱ ልጆች ሲያይ; "እኔ ከእሱ በበለጠ ረዥም ዓመታት ወንጀል እየሰራሁ ኖሬያለሁ: እሱ ከእኔ ይሻላል!!" ይል ነበር። https://t.me/hamdquante
Открыть в Telegram✍ የዱንያ እና የአኼራ ምሳሌያቸው እንደ ምስራቅ እና ምዕራብ ነው; ወደ አንደኛው በተጠጋኸው ልክ: ከሌላኛው ትርቃለህ። ዱንያ ማለት፦ ጅምሯ መከራ፤ መጨረሻዋ ጠፊ፣ ሐላልዋ ሂሳብ፣ ሐራምዋ እሳት፣ ሀብታሙ የሚፈተንባትና ደሀው የሚያዝንባት ሀገር ናት። /ኢማም ሐሰን አል_በስሪ/ https://t.me/hamdquante
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC@egbccРелигия12,2 тыс.
#KALTUBE@kaltubeРелигия11,8 тыс.
ABU MUSLIM A-DUROOS@abumuslimalarsiРелигия13 тыс.
ISLAM IS UNIVERSITY@islamisuniverstiy_public_groupРелигия13,2 тыс.
የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)@sultan_54Религия13,3 тыс.
ወርቃማ ንግግሮች@golden_speechРелигия13,8 тыс.
Mujib Amino Z islam@mujibbinislamРелигия13,8 тыс.
Orthodox picture ✝@orthodox_photoРелигия14 тыс.