Кабинет

Посты канала 🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸

сначала новые

#11432Текст
Просмотры417−72%к среднему
Пересылки—
Реакции9
Комментарии—
#11431Текст

🔖    በመካ የባርነት ገበያ ከመሸጥ ጀምሮ <እስከ> በሰብር እና በየቂን የተገነባ የኢማን አርኣያነት!!   ገና በህፃንነቱ ነበር በጠላት ተማርኮ የወሰደው። የወሰዱት ሰዎች ወደ ቅድስቲቷ ከተማ መካ ወስደው በባርነት ሸጡት።  የመካ ነዋሪ የነበረችዋ ኡሙ አንማር አል-ሁዛዒያ የተባለች ሴት ለሽያጭ ከቀረቡ ባሮች መሃል መርጣ ገዛችው። እሷም የዐብዱረሕማን ቢን ዐውፍ ረዲየላሁ አንሁ አባት የሆነው የዐውፍ ቢን ዐብዱ ዐውፍ አል-ዙህሪ የቅርብ ወዳጅ ነበረች።    አባቱ ኢብኑ አረት ቢን ጀንደላ የቢን ሳዕድ ልጅ ሲሆን: ከተሚም ጎሳ ቅርንጫፎች አንዱ ከሆነው ከበኒ ሳዕድ ቢን ዘይድ መናት ነበር፤ ከኹዛዓ ጎሳም ነው ተብሏል። 👇 👉አንጋፋው ሰሓብይ ኸባብ ኢብኑ አረት‼️ ​  ኸባብ በጃሂሊያ ዘመን ሰይፍ በማምረት ሥራ ይሠራ ነበር። በዚህ ጥበብም የተካነ ነበር። ነቢዩ ሙሐመድﷺ ልቡን ለማቀራረብ ይቀርቡትና አብረውት ይቀመጡ ነበር። ​  ከዚያም አላህ ልቡን ለእስልምና ከፈተለት፤ ወደ እስልምና ቀድመው ከገቡት የመጀመሪያ ሰዎችም አንዱ ሆነ። ነቢዩﷺ  ወደ ዳሩል አርቀም ቤት ከመግባታቸው በፊት ነው የሰለመው። ቅድሚያ ከሰለሙ ስድስት ሰዎች እሱ ስድስተኛው ነበር። እስልምናን ከተቀበሉት በቅደም ተከተል ሃያኛው ነበርም ተብሏል። ​  ኸባብ እስልምናውን በግልጽ ባወጣ ጊዜ ከሙሽሪኮች ከባድ በደል ደረሰበት። ሃይማኖታቸውን ትተው ከእስልምና እንዲወጡ በመካ መኳንንቶች ስቃይ ከደረሰባቸው ደካሞች መካከል አንዱ ነበር።    ሙሽሪኮች እሳት ያነዱና ጀርባው በሙቀቱ እስኪበሰል ድረስ በላዩ ላይ ያስቀምጡበታል። ከዚያም መሬት ላይ ይጥሉትና ከእነሱ አንዱ መጥቶ ደረቱ ላይ ይወጣና እንዳይንቀሳቀስ ይረግጠው ነበር። ​   ስቃዩ በዚህ ብቻ አላቆመም፤ ገዢው የነበረችው ኡሙ አንማር በእሳት የጋለ ብረት ወስዳ ራሱ ላይ ታስቀምጥበታለች። በዚህም ሕመሙንና ስቃዩን ትጨምርበታለች። ​   የሚደርስበት ስቃይ በበረታበት ጊዜ ወደ ነቢዩﷺ ሄዶ የደረሰበትን መከራ ጠቅሶ ፈረጅ እንዲመጣለት እገዛም እንዲጠይቁለት ነገራቸው።    ነቢዩﷺ «አላህ ሆይ! ኸባብን እርዳው» ብለው ዱዐ አደረጉለት። ​   ከዚያ በኋላ ኡሙ አንማር ራሷ ላይ በከባድ በሽታ ተፈተነች፤ ከሕመሙ ብዛት እንደ ውሻ እያላዘነች ትጮኻለች። ለህመሟ ህክምና ስታጠያይቅ በእሳት መተኮስ መድኃኒቷ እንደሆነ ተነገራት። ​  ለዚህም ራሷን በጋለ ብረት የሚተኩሳት ሰው ያስፈልጋት ነበር፤ ከዝያም ኸባብ ራሱ እንዲያክማት ተደረገና የጋለውን ብረት እያመጣ አናቷ ላይ ያስቀምጥባት ነበር። /ብድር በምድር እንደሚሉት/ 📍ሙጃሂድ የተባለው ሊቅ እስልምናቸውን ይፋ ያደረጉ የመጀመሪያዎቹን ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡-    "እስልምናቸውን ይፋ ያደረጉ የመጀመሪያዎቹ የአላህ መልዕክተኛﷺ፣ አቡ በክር፣ ኸባብ፣ ሱሃይብ፣ ቢላል፣ ዐማር እና የዐማር እናት ሱመያ ናቸው። የአላህ  መልዕክተኛﷺ አላህ በአጎታቸው በአቡ ጣሊብ ጠበቃቸው፤ አቡ በክር ደግሞ በጎሳው ጠበቀው። ሌሎቹን ግን የመከራ ዓይነት አቀመሷቸው፤ በጋለ ብረት በፀሐይ ላይ አቀለጧቸው፤ ከብረቱና ከፀሐዩ ሙቀት የተነሳ አላህ የሻውን ያህል ድካምና ስቃይ ደረሰባቸው።" ​  ኸባብ ረዲየላሁ ተዓላ አንሁ በስቃይ ፊት ለትዕግሥትና ለጽናት ምሳሌ ነበር። የደረሰበት ስቃይ ቢበረታም ከእምነቱ አልተመለሰም፤ የሙሽሪኮችን ጥያቄም አልተቀበለም። 📍​ዓሚር አል-ሻዕቢ ኸባብ ላይ የደረሰበትን ስቃይ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፡-    "ኸባብ ታገሰ፤ ከሓዲዎች የጠየቁትንም አልሰጣቸውም። የጀርባው ሥጋ እስኪወልቅ ድረስ ጀርባውን በጋሉ ድንጋዮች አቃጠሉት።"    ሙሽሪኮች ከሙቀቱ ብዛት የጀርባውን ሥጋ እስኪወልቅ ድረስ የኸባብ ጀርባ ላይ የጋሉ የተቃጠሉ ድንጋዮች ያስቀምጡ ነበር። ይሁንና ስቃዩ ምንም ያህል ቢደርስ እስልምናውን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን በሃይማኖቱ ጸንቶ ቆየ። ከሙሽሪኮች ጋር ከገጠሙት ክስተቶች መካከል;    በመካ ሰይፍ በማምረት ላይ በነበረበት አንድ ቀን ለዐስ ቢን ዋኢል አስ-ሰህሚ ሰይፍ ሠራለት። ሠርቶ ሲጨርስ ዋጋውን ሊጠይቀው ወደ እሱ ሄደ። ዐስ ገንዘቡን መክፈል እምቢ አለ። ገንዘቡን ሊሰጠው ከፈለገ በሙሐመድﷺ መካድ እንዳለበት ነገረው። ​  ኸባብም በጽናትና በእርግጠኝነት እንዲህ ሲል መለሰለት፡- "አንተ ሞተህ ተመልሰህ እስክትቀሰቀስ ድረስ በሙሐመድﷺ አልክድም!!" አለው። ​ዐስም በማላገጥ እንዲህ አለው፡- "ከተቀሰቀስኩ በኋላ ገንዘብ ይኖረኛል፤ ያኔ እከፍልሃለሁ።" ​  ኸባብም ወደ ነቢዩﷺ ሄዶ የተባባሉትን ነገራቸው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከተለውን ቁርኣን አወረደ፡- 📖​﴿أَفَرَأَيْتَ الَّذِي كَفَرَ بِآيَاتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالًا وَوَلَدًا ۝ أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِنْدَ الرَّحْمَنِ عَهْدًا ۝ كَلَّا سَنَكْتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُ مِنَ الْعَذَابِ مَدًّا ۝ وَنَرِثُهُ مَا يَقُولُ وَيَأْتِينَا فَرْدًا﴾ ​  ኸባብ ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ የተሸከመው የስቃይ መጠን ታላቅ መሆኑን ከሚያሳዩ ነገሮች ውስጥ;    በዑመር ቢን አል-ኸጧብ  የኸሊፋነት ዘመን አንድ ቀን ዑመር በመካ ከሙሽሪኮች ስለደረሰበት ነገርና በእስልምናው ምክንያት ስለደረሰበት የስቃይ ዓይነቶች ጠየቀው። ​ኸባብም፡- "የምእመናን መሪ ሆይ! ጀርባዬን ተመልከት" አለና ጀርባውን ከፈተለት። ​  ዑመር ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ የኸባብ ጀርባውን ባየ ጊዜና እሳቱ በአካሉ ላይ የተወውን የስቃይና የተቃጠለ ምልክት በተመለከተ ጊዜ ባየው ነገር ተደነቀና "ዛሬ ያየሁት ዓይነት አይቼ አላውቅም" አለ። ​    ኸባብም የደረሰበትን ጽናት በማብራራት እንዲህ ሲል መለሰለት፡-   "እሳት አነደዱብኝ፤ ያነደዱብኝ እሳት የጀርባዬ ስብ (ቅባት) ቢያጠፋው እንጂ ሌላ ነገር አላጠፋውም ነበር። የንግግሩ ትርጉም፦     ሙሽሪኮች እሳት አቀጣጥለው በሙቀቱ ሲያሰቃዩት ከጀርባው ላይ ስቡ እስኪቀልጥ ድረስ እንደሆነና ከቃጠሎው ብርታት የተነሳ ከአካሉ በፈሰሰው ስብ እንጂ እሳቱ እንዳልጠፋ ነው። ​  አላህ ለሙስሊሞች ሂጅራን (ስደትን) ከፈቀደ በኋላ ኸባብ  ከሚቅዳድ ቢን ዐምር ጋር ወደ መዲና ተሰደደ፤ በኩልሱም ቢን አል-ሀድም ቤትም አረፉ። ከዚያም ነቢዩ በኸባብ እና በጀብር ቢን ዐቲቅ መካከል የወንድማማችነት ትስስር አደረጉ። ​  ኸባብ ከአላህ መልዕክተኛﷺ ጋር በሁሉም ጦርነቶችና ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል። እስልምናን ከመደገፍና በሁኔታዎቹ ከመሳተፍም ወደ ኋላ አላለም። የአላህ መልዕክተኛﷺ እስኪሞቱ ድረስ በጂሃድ እየተሳተፈ አብሯቸው ዘልቋል። ​   ከነቢዩﷺ ሞት በኋላ የእስልምና ፍቱሓት እንቅስቃሴ ሲጀመር፤ የመንግሥቱም ግዛት ሲሰፋ፧ ኸባብ ቢን አረት ወደ ኩፋ ተዛውሮ እዚያ ተቀመጠ። ​  በሰላሳ ሰባተኛው ዓመተ ሂጅራ ኸባብ በኩፋ ሞተ፤ ዕድሜውም ሰባ ሦስት ዓመት ነበር። ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ተዓላ ዐንሁ ሰገደበት። በኩፋ እምብርት የመጀመሪያ የተቀበረው ሰሓብይ እሱ ሆነ። ​   በሞተ ጊዜ ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ በእስልምናው የደረሰበትን በመግለጽ ደረጃውንና ቦታውን የሚያሳዩ ታላላቅ ቃላት ተናገረለት። እንዲህም አለ፡- ​   "አላህ ለኸባብ ይዘንለት፤ በውዴታው ሰለመ፣ በታዛዥነት ተሰደደ፤ ሙጃሂድ ሆኖ ኖረ፤ በአካሉም የተለያዩ ሁኔታዎች ተፈተነ፤ አላህም ምንዳውን አያስቀርበት!!" 🤲አላህ ከረሱልﷺ እና ዕንቁ ባልደረቦቻቸውጋ በጀነት ያጎራብተን🤲 ✍አቡ ሙስሊም ሐምዱ ቋንጤ!! https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio 👆 👇 https://t.me/hamdquante

Открыть в Telegram
Просмотры534−64%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#11429Фото
Просмотры643−57%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#11424Текст
Просмотры1 720+14%к среднему
Пересылки—
Реакции34
Комментарии—
#11423Текст
Просмотры1 740+16%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#11420Текст

🔖   ነብዩ ሙሳﷺ እየፈሩና ዙሪያቸውን እየተጠባበቁ፣ ስንቅ ሳይኖራቸው፣ መጓጓዣ እንስሳ ሳይኖራቸው፣ ሌላው ቀርቶ ከአሸዋ ግለት የሚከላከልላቸው ጫማ እንኳ ሳይኖራቸው፞፧    በወቅቱ በምድር ላይ ካሉ ነገሥታት ሁሉ እጅግ ኃያል በነበረው ፊርዐውን ከተላለፈባቸው ግልጽ የሞት ፍርድ እየሸሹ ከግብፅ ወጡ። ​  በስነ-ልቦና መበታተን፣ በርሀብ ስቃይ፣ በባይተዋርነት ስሜትና በጠላት ስቃይ ፍራቻ ላይ ሆነው ወደ መድየን ውሃ ደረሱ።    እዚያም በእረኞች ግርግር መሃል በአቅም ማነስ ምክንያት በጎቻቸውን ወደ ውሃው እንዳይጠጉ የሚከለክሉ ሁለት ደካማ ሴቶችን ተመለከቱ; ​ሙሳ፦ "ራሴን ልርዳ፤ እኔ እንግዳ ነኝ፤ ተሳዳጅ ነኝ፤ በረሃብም እየሞትኩ ነው" ሳይሉ     በጀግንነትና በጨዋነት ተነሳስተው ምስጋናም ሆነ ገንዘብ ሳይጠብቁ ለሴቶቹ በጎች ውሃ አጠጡላቸው። ከዚያም፦ 📖{فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰ إِلَى الظِّلِّ فَقَالَ رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ}   {ለሁለቱም አጠጣላቸው፡፡ ከዚያም ወደ ጥላው ዘወር አለ፡፡ "ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ" አለ፡፡} ​የዚህን ሥነ-ምግባር ምስጢር አስተውል………    የፍላጎታቸው ዝርዝር አላቀረቡም፤ "ቤት እፈልጋለሁ፤ ደህንነቴ እንዲጠበቅ እፈልጋለሁ፤ ሚስት እፈልጋለሁ፤ ሲሳይ እፈልጋለሁ" አላሉም። ይልቁንስ;     በሰዎች ፊት ራሳቸውን አከበሩና ድህነታቸውን ሁሉ በፈጣሪ ደጃፍ ላይ ጣሉ!! ​ውጤቱስ ምን ሆነ?? አትልም??…………    በጥቂት ሰዓታት ብቻ... የዓመታት ሸክም ሁሉ በአንድ ውይይት ተፈታ። 📖{فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ قَالَتْ إِنَّ أَبِي يَدْعُوكَ لِيَجْزِيَكَ أَجْرَ مَا سَقَيْتَ لَنَا}    {ከሁለቱ አንደኛይቱም በሐፍረት የምትሄድ ሆና መጣችው፡፡ "አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል" አለችው፡፡} ደህንነታቸው ተጠበቀ፦ 📖{فَلَمَّا جَاءَهُ وَقَصَّ عَلَيْهِ الْقَصَصَ قَالَ لَا تَخَفْ ۖ نَجَوْتَ مِنَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ}    {ወደ እሱ በመጣና ዜናውን በእርሱ ላይ በተረከለት ጊዜ "አትፍራ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ድነሃል" አለው፡፡}   መጠለያ፤ ለዓሥር ዓመታት የሚቆይ ክቡር ሥራን፤ መልካም ሚስትንም አገኙ። ከዚያም ይህ ሁሉ በነቢይነት ማዕረግና የዓለማትን ጌታ በማነጋገር ክብር ተደመደመ!! ​ የአንተም ፈረጅ እንዲፋጠን ከፈለግክ………    እጅግ በተቸገርክበት ወቅት እንኳ ለአላህ ባሮች መልካም ዋል፤ በጉልበትህ የሚደረግ ምጽዋትና ለደካሞች ማዘን የተዘጉ በሮች መክፈቻ ቁልፎች ናቸው!! ​   ከዚያም በመተናነስ ጥላ ሥር ውደቅ፣ ከፍጡራኑ ማንንም አትለምን። በየቂን ልብ እንዲህ በል፦ 📖{رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ} https://t.me/hamdquante

Открыть в Telegram
Просмотры1 860+24%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#11419Текст
Просмотры1 720+14%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#11418Фото
Просмотры2 060+37%к среднему
Пересылки—
Реакции37
Комментарии—
#11417Текст
Просмотры2 050+36%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#11415Превью ссылки
Просмотры1 380−8%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#11413Фото

✍    የወንድነት መገለጫዎች በቁርኣን……… 🚩ኛ, ውስጣዊም ይሁን ውጫዊ ንፅህና መጠበቅ፦ 📖{فِيهِ رِجَالٌۭ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا۟ ۚ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُطَّهِّرِينَ} {በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ፤ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡]        [አል_ተውባ:¹⁰⁸] 🚩ኛ, አስቸጋሪ በሆኑ ጊዜያቶች ሀላፍትና መሸከም፦ 📖{وَجَآءَ مِنْ أَقْصَا ٱلْمَدِينَةِ رَجُلٌۭ يَسْعَىٰ قَالَ يَٰقَوْمِ ٱتَّبِعُوا۟ ٱلْمُرْسَلِينَ}   {ከከተማይቱ ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፡ "ወገኖቼ ሆይ! መልእክተኞቹን ተከተሉ" አለ፡፡}        [ያሲን:²⁰] 🚩ኛ، የገቡትን ቃል መሙላት፦ 📖{مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ رِجَالٌۭ صَدَقُوا۟ مَا عَٰهَدُوا۟ ٱللَّهَ عَلَيْهِ} {ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አሉ፡፡}       [አል_አህዛብ:²³] 🚩ኛ, እውነትን መከተል እና እውነት መናገር፦ 📖{وَقَالَ رَجُلٌۭ مُّؤْمِنٌۭ مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَكْتُمُ إِيمَٰنَهُۥٓ أَتَقْتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّىَ ٱللَّهُ} {ከፊርዓውን ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ኣማኝ ሰው "ሰውየውን ከጌታችሁ በተኣምራቶች በእርግጥ የመጣለችሁ ሲሆን "ጌታዬ አላህ ነው" ስለሚል ትገድላላችሁን?" አለ።}       [አል_ጋፊር:²⁸] 🚩ኛ, አማላይ ነገሮች ሲገጥሙ መፅናት፦ 📖{رِجَالٌۭ لَّا تُلْهِيهِمْ تِجَٰرَةٌۭ وَلَا بَيْعٌ عَن ذِكْرِ ٱللَّهِ}   {አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ወንዶች።}           [አል_ኑር:³⁷] 🚩ኛ, ጀግንነት እና ቸርነት፦ 📖{فَسَقَىٰ لَهُمَا ثُمَّ تَوَلَّىٰٓ إِلَى ٱلظِّلِّ} {ለሁለቱም አጠጣላቸው፡፡ ከዚያም ወደ ጥላው ዘወር አለ፡፡}          [አል_ቀሰስ:²⁴] 🚩ኛ, የቤተሰብ ሀላፍትና መሸከም፦ 📖{ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍۢ وَبِمَآ أَنفَقُوا۟ مِنْ أَمْوَٰلِهِمْ}   {ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡}        [አል_ኒሳእ:³⁴] 👌ወንድ ሁን!! https://t.me/hamdquante

Открыть в Telegram
Просмотры2 280+52%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—