📩 ቁርኣንን በምትሸምድበት ጉዞ ውስጥ መድከምና መሰላቸት ኢኽላስ እንደሌለህ ማሳያ አይደለም። ይህ በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥም ተፈጥሯዊ ሁኔታ ነው። 🔹 እንደገና ተነሳ! 🔹 ነፍስህን በትጋት ታገል! 🔹 ተነሳሽነትህን አድስ! 🔹 ከቁርኣን ባልደረቦችህ ጋር ተደጋገፉ! 💎 የልፋትህ ውጤት በአንድ ጊዜ ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ እየተከታተለ ይመጣል። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
የቻናሉ ትኩረትና ዓላማ: – √ ቁርዓንን በማየት(በነዘር)መቅራት ለማይችሉ እገዛና ድጋፍ ማድረግ። እንዲሁም በተጨማሪ በኡስታዝ ኢብራሒም የሚሰጡ:– √ የተጅዊድ √ የቁርአን ሐለቃ √ እና የተለያዩ ደርሶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው። 🏖 ለአስተያየት☞ @AbuHiba1 ወይም☞ @Ibrohalka_botይጠቀሙ!!
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 11 нояб. 2026 г. | 3 115 |
| 12 нояб. 2026 г. | 3 407 |
| 13 нояб. 2026 г. | 3 810 |
| 15 нояб. 2026 г. | 3 580 |
| 18 нояб. 2026 г. | 2 730 |
| 19 нояб. 2026 г. | 2 890 |
| 20 нояб. 2026 г. | 2 570 |
| 21 нояб. 2026 г. | 2 220 |
| 23 нояб. 2026 г. | 1 650 |
| 24 нояб. 2026 г. | 1 340 |
| 25 нояб. 2026 г. | 977 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры4,09 тыс.Пересылки—Реакции63Комментарии—
- 02Просмотры3,81 тыс.Пересылки—Реакции68Комментарии—
- 03Просмотры3,65 тыс.Пересылки—Реакции—Комментарии—
- 04Просмотры3,58 тыс.Пересылки—Реакции63Комментарии—
Новые посты
ለቁርኣን ያለህ ውዴታ እውነተኛ ቢሆን ኖሮ ለእርሱ የሚሆን ጊዜ ትመድብ ነበር! እንግዲህ ቁርኣንን ለማንበብ የወሰንከው በዕለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ በየትኛው ሰአት ነው? ከ24 ሰዓታት ውስጥ ለቁርኣን አንድ ሰዓት ወይም ግማሽ ሰዓት መመደብ እንኳን ያቅትሃልን?! ለሌሎች ነገሮች ጊዜ እያገኘህ ለቁርኣን ግን ጊዜ ማጣት እንዴት ይሆናል? http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram〰〰〰〰〰〰 🔖ሪያዱ ሷሊሒን ✅٨-كتاب الفضائل باب فضل قيام رمضان وهو التراويح 🎤ክፍል:- 96 🔖ሐዲስ ቁጥር:–1187 የትምህርቱ አቅራቢ:–ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን https://t.me/ibrahim_furii/7787 የኪታቡ ፒዲኤፍ👆 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram🌿 ወላጆችሽ በቁርኣን እንዲኮሩብሽ አድርጊ! አንዲት እህት እንዲህ ትላለች፦ «ቁርኣንን ለመሐፈዝ ያነሳሳኝና የበለጠ ትጋት የፈጠረልኝ ነገር የቂያማ ቀን ቁርኣንን የሸመደዱ ሰዎች ወላጆቻቸውን የክብር ዘውድ ሲያለብሷቸው እነርሱም በደስታና በሐሴት ሲሞሉ በአዕምሮዬ በተደጋጋሚ ማሰቤ ነው። ከዚያም ወላጆቼ እነዚያን ልጆች ሲመለከቱና ከልጆቻቸው መካከል አንድም ቁርኣንን የሀፈዘ እንደሌለ በማሰብ ሲቆጩ በአዕምሮዬ አስብ ነበር። ስለዚህም የአላህን መጽሐፍ ለመሐፈዝ ወሰንኩ በዚያ ቀን ደስታን ለወላጆቼ ለማጎናጸፍም ቁርጠኛ ውሳኔ ወሰንኩ። 🌸 ለወላጆችህ ልታበረክት ከምትችላቸው ታላላቅ ውለታዎች አንዱ ቁርኣንን መሐፈዝና በእርሱ መስራትና፣ መኖር መቻል ነው። 📖 ቁርኣንን በቃላችን እንሸመምድድ ለራሳችንም ለወላጆቻችንም የመልካም ሥራ ምንጭ እንሁን። የቁርኣን ሒፍዝህን የሚያግዙ ጠቃሚ ምክሮችንና ተግባራዊ ዘዴዎችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን JOIN ይበሉ። http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram📚የዑምደቱል አሕካም ደርስ ~ 📌 ደርስ ቁጥር፦ 35 📖باب اللباس 🔖ሐዲስ ቁጥር:‒392 🎙 የትምህርቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን የኪታቡ pdf ፋይል ለማግኘት👇 https://t.me/ibrahim_furii/8339 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramአንድ ሰው ለጓደኛው እንዲህ አለው፦ «እገሌ በጆሮህ ሲንሾካሾክ አየሁት፤ ለመሆኑ ምን አለህ?» ጓደኛውም፦ «ምስጢር ትጠብቃለህ?» ሲል ጠየቀው። ሰውየውም፦ «አዎ» አለ። ጓደኛውም፦ «እኔም እንደዚሁ ነኝ!» አለው። ~ምስጢር መጠበቅ የሥነ-ምግባር እና የታላቅነት መገለጫ ነው የተነገረንን ሁሉ ለሌላ ማውራት ተገቢ አይደለም። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramቁርኣንን ይዘህ ብቻህን በጉዞህ የቀጠልክ ወዳጄ ሆይ! ~ ከጎንህ የሚያበረታታህ ቤተሰብም ሆነ ጓደኛ ባታገኝ ጥረትህን የሚያደንቅና ጉዞህን የሚያበረታታ ሰው ባይኖርም ዓለማዊ ጉዳዮችንና የሶሻል ሚዲያን ወከባ ወደ ጎን ትተህ፣ ከቁርኣን ጋር ያለህን ጉዞ በትጋት የቀጠልክ ወዳጄ ሆይ! በፀጥታ ውስጥ ትታገላለህ ሌሊቱ ሲያሸልብ ሰዎች በእንቅልፍ ላይ ሳሉ አንተ ግን ከአልጋህ ተነስተህ ለመሐፈዝና ለሙራጃዓ ጊዜህን ትሰጣለህ። ማንም ሳያይህ ማንም ሳያበረታታህ በትዕግሥትና በፅናት ጥረትህን ትቀጥላለህ። ነገር ግን ውድ ወዳጄ! አንድ ታላቅ እውነት አትርሳ! ከቁርኣን ጋር ያለህ ጉዞ በሰዎች ዘንድ የማይታወቅ ቢሆንም በአላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ውድና የማይቋረጥ ነው። የነቢዩ ﷺ ይህንን ብሥራት አልሰማህምን? «اقْرَؤُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لِأَصْحَابِهِ» «ቁርኣንን አንብቡ እርሱ የቂያማ ቀን ለባልደረቦቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።» ~ስለዚህ ዛሬ ብቻህን ብትመስልም አትዘን የምታደርገው ጥረት ከንቱ አይደለም። ሌሊት የምታሳልፈው ጊዜ የምትሸመድደው አንቀጽ የምትደጋግመው ገጽና ለቁርኣን የምትከፍለው ድካም ሁሉ በአላህ ፈቃድ ታላቅ ፍሬ ይኖረዋል። ከቁርኣን ጋር ያለህን ጉዞ አታቋርጥ በትዕግሥት ቀጥል በኢኽላስ ጽና በቁርኣንም ሕይወትህን አሳምር። እስከ መጨረሻው ተጓዝ! 🤲 አላህ ከቁርኣን ባልደረቦች በቀንና በሌሊት የሚያነቡት፣ የሚሸመድዱትና የሚተገብሩት ሰዎች ያድርገን። آمين يا رب العالمين. t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramሴት ልጅ የዲን እውቀት ካጣች ባሏን ታደክማለች፣ ልጆቿን ታበላሻለች፣ ኡማውንም ታጠፋለች። ባል የዲን እውቀት ከሌለው ደግሞ አርአያነቱ ይወድቃል፣ በሴቷ ላይ ይበድላል፣ ቤቱንም ያፈርሳል። ቤተሰብ የሚቃናው— ሁለቱም በእውቀትና በቅንነት አብረው ሲቆሙ ብቻ ነው። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramሰዎች ላይ አታላግጥ ክብራቸውንም አታሳንስም! ምክንያቱም ነገ የአንተ ሁኔታ ምን እንደሚሆን አታውቅምና። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram⛔ ልብ በሉ! እና ተጠንቀቁ! ▪️ ጥንቃቄ ምንም የሚያስከፍል ነገር የለውም ቸልተኝነት ግን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። ▪️ አባት ባዕድ ወንዶች ወደ ቤቱ እንዳይገቡ በመጠንቀቅ የቤቱን በር በሴት ልጆቹ እንዲሁም በባለቤቱ ላይ ይዘጋል። ▪️ ነገር ግን እነዚያ እንግዶች በፌስቡክና በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች አማካኝነት በየዕለቱ ወደ ቤቱ እየገቡ መሆናቸውን ይዘነጋል! ▪️ ስለዚህ አባቶች ሆይ! በአብዛኞቹ የሙስሊሞች ቤቶች ውስጥ ሾልኮ የገባውን ይህን ታላቅ አደጋ ተገንዝባችሁ ልጆቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ጠብቁ! ▪️ በእነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ምክንያት ስንት የፍቺ ችግሮች፣ ከሃላል ውጭ የሆኑ ግንኙነቶች፣ ሴት ልጆችን በምስጢራቸው ማስፈራራትና በገንዘብ መጠቀም የመሳሰሉ ብዙ ችግሮች ስንመለከት ቆይተናል! ▪️ ስለዚህ አባቶች ሆይ! ተጠንቀቁ፤ የቤተሰባችሁን ጉዳይ በቸልተኝነት አትተዉ! ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْؤُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ» «ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ ሁላችሁም ስለምትጠብቁት ኃላፊነት ተጠያቂ ናችሁ።» 🤲 አላህ ደህንነትንና ከክፉ ነገሮች መጠበቅን ይወፍቀን። አሚን! http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
EQUIP Media/Mamusha Fenta@mamusha_fentaРелигия14,4 тыс.
Mahibere Kidusan@eotcmkРелигия16,1 тыс.
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት@finotehiwottРелигия16,3 тыс.
Orthodox picture ✝@orthodox_photoРелигия14 тыс.
Mujib Amino Z islam@mujibbinislamРелигия13,8 тыс.
ወርቃማ ንግግሮች@golden_speechРелигия13,8 тыс.
የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)@sultan_54Религия13,3 тыс.
ISLAM IS UNIVERSITY@islamisuniverstiy_public_groupРелигия13,2 тыс.