📩 ቁርኣንን በምትሸምድበት ጉዞ ውስጥ መድከምና መሰላቸት ኢኽላስ እንደሌለህ ማሳያ አይደለም። ይህ በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ የሚያጋጥም ተፈጥሯዊ ሁኔታ ነው። 🔹 እንደገና ተነሳ! 🔹 ነፍስህን በትጋት ታገል! 🔹 ተነሳሽነትህን አድስ! 🔹 ከቁርኣን ባልደረቦችህ ጋር ተደጋገፉ! 💎 የልፋትህ ውጤት በአንድ ጊዜ ሳይሆን፣ ቀስ በቀስ እየተከታተለ ይመጣል። t.me/ibrahim_furii
Открыть в TelegramПосты канала 𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
ለቁርኣን ያለህ ውዴታ እውነተኛ ቢሆን ኖሮ ለእርሱ የሚሆን ጊዜ ትመድብ ነበር! እንግዲህ ቁርኣንን ለማንበብ የወሰንከው በዕለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ በየትኛው ሰአት ነው? ከ24 ሰዓታት ውስጥ ለቁርኣን አንድ ሰዓት ወይም ግማሽ ሰዓት መመደብ እንኳን ያቅትሃልን?! ለሌሎች ነገሮች ጊዜ እያገኘህ ለቁርኣን ግን ጊዜ ማጣት እንዴት ይሆናል? http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram〰〰〰〰〰〰 🔖ሪያዱ ሷሊሒን ✅٨-كتاب الفضائل باب فضل قيام رمضان وهو التراويح 🎤ክፍል:- 96 🔖ሐዲስ ቁጥር:–1187 የትምህርቱ አቅራቢ:–ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን https://t.me/ibrahim_furii/7787 የኪታቡ ፒዲኤፍ👆 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram🌿 ወላጆችሽ በቁርኣን እንዲኮሩብሽ አድርጊ! አንዲት እህት እንዲህ ትላለች፦ «ቁርኣንን ለመሐፈዝ ያነሳሳኝና የበለጠ ትጋት የፈጠረልኝ ነገር የቂያማ ቀን ቁርኣንን የሸመደዱ ሰዎች ወላጆቻቸውን የክብር ዘውድ ሲያለብሷቸው እነርሱም በደስታና በሐሴት ሲሞሉ በአዕምሮዬ በተደጋጋሚ ማሰቤ ነው። ከዚያም ወላጆቼ እነዚያን ልጆች ሲመለከቱና ከልጆቻቸው መካከል አንድም ቁርኣንን የሀፈዘ እንደሌለ በማሰብ ሲቆጩ በአዕምሮዬ አስብ ነበር። ስለዚህም የአላህን መጽሐፍ ለመሐፈዝ ወሰንኩ በዚያ ቀን ደስታን ለወላጆቼ ለማጎናጸፍም ቁርጠኛ ውሳኔ ወሰንኩ። 🌸 ለወላጆችህ ልታበረክት ከምትችላቸው ታላላቅ ውለታዎች አንዱ ቁርኣንን መሐፈዝና በእርሱ መስራትና፣ መኖር መቻል ነው። 📖 ቁርኣንን በቃላችን እንሸመምድድ ለራሳችንም ለወላጆቻችንም የመልካም ሥራ ምንጭ እንሁን። የቁርኣን ሒፍዝህን የሚያግዙ ጠቃሚ ምክሮችንና ተግባራዊ ዘዴዎችን ለማግኘት ወደ ቻናላችን JOIN ይበሉ። http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram📚የዑምደቱል አሕካም ደርስ ~ 📌 ደርስ ቁጥር፦ 35 📖باب اللباس 🔖ሐዲስ ቁጥር:‒392 🎙 የትምህርቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን የኪታቡ pdf ፋይል ለማግኘት👇 https://t.me/ibrahim_furii/8339 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramአንድ ሰው ለጓደኛው እንዲህ አለው፦ «እገሌ በጆሮህ ሲንሾካሾክ አየሁት፤ ለመሆኑ ምን አለህ?» ጓደኛውም፦ «ምስጢር ትጠብቃለህ?» ሲል ጠየቀው። ሰውየውም፦ «አዎ» አለ። ጓደኛውም፦ «እኔም እንደዚሁ ነኝ!» አለው። ~ምስጢር መጠበቅ የሥነ-ምግባር እና የታላቅነት መገለጫ ነው የተነገረንን ሁሉ ለሌላ ማውራት ተገቢ አይደለም። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramቁርኣንን ይዘህ ብቻህን በጉዞህ የቀጠልክ ወዳጄ ሆይ! ~ ከጎንህ የሚያበረታታህ ቤተሰብም ሆነ ጓደኛ ባታገኝ ጥረትህን የሚያደንቅና ጉዞህን የሚያበረታታ ሰው ባይኖርም ዓለማዊ ጉዳዮችንና የሶሻል ሚዲያን ወከባ ወደ ጎን ትተህ፣ ከቁርኣን ጋር ያለህን ጉዞ በትጋት የቀጠልክ ወዳጄ ሆይ! በፀጥታ ውስጥ ትታገላለህ ሌሊቱ ሲያሸልብ ሰዎች በእንቅልፍ ላይ ሳሉ አንተ ግን ከአልጋህ ተነስተህ ለመሐፈዝና ለሙራጃዓ ጊዜህን ትሰጣለህ። ማንም ሳያይህ ማንም ሳያበረታታህ በትዕግሥትና በፅናት ጥረትህን ትቀጥላለህ። ነገር ግን ውድ ወዳጄ! አንድ ታላቅ እውነት አትርሳ! ከቁርኣን ጋር ያለህ ጉዞ በሰዎች ዘንድ የማይታወቅ ቢሆንም በአላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ውድና የማይቋረጥ ነው። የነቢዩ ﷺ ይህንን ብሥራት አልሰማህምን? «اقْرَؤُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لِأَصْحَابِهِ» «ቁርኣንን አንብቡ እርሱ የቂያማ ቀን ለባልደረቦቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።» ~ስለዚህ ዛሬ ብቻህን ብትመስልም አትዘን የምታደርገው ጥረት ከንቱ አይደለም። ሌሊት የምታሳልፈው ጊዜ የምትሸመድደው አንቀጽ የምትደጋግመው ገጽና ለቁርኣን የምትከፍለው ድካም ሁሉ በአላህ ፈቃድ ታላቅ ፍሬ ይኖረዋል። ከቁርኣን ጋር ያለህን ጉዞ አታቋርጥ በትዕግሥት ቀጥል በኢኽላስ ጽና በቁርኣንም ሕይወትህን አሳምር። እስከ መጨረሻው ተጓዝ! 🤲 አላህ ከቁርኣን ባልደረቦች በቀንና በሌሊት የሚያነቡት፣ የሚሸመድዱትና የሚተገብሩት ሰዎች ያድርገን። آمين يا رب العالمين. t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramሴት ልጅ የዲን እውቀት ካጣች ባሏን ታደክማለች፣ ልጆቿን ታበላሻለች፣ ኡማውንም ታጠፋለች። ባል የዲን እውቀት ከሌለው ደግሞ አርአያነቱ ይወድቃል፣ በሴቷ ላይ ይበድላል፣ ቤቱንም ያፈርሳል። ቤተሰብ የሚቃናው— ሁለቱም በእውቀትና በቅንነት አብረው ሲቆሙ ብቻ ነው። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramሰዎች ላይ አታላግጥ ክብራቸውንም አታሳንስም! ምክንያቱም ነገ የአንተ ሁኔታ ምን እንደሚሆን አታውቅምና። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram⛔ ልብ በሉ! እና ተጠንቀቁ! ▪️ ጥንቃቄ ምንም የሚያስከፍል ነገር የለውም ቸልተኝነት ግን ከባድ ዋጋ ያስከፍላል። ▪️ አባት ባዕድ ወንዶች ወደ ቤቱ እንዳይገቡ በመጠንቀቅ የቤቱን በር በሴት ልጆቹ እንዲሁም በባለቤቱ ላይ ይዘጋል። ▪️ ነገር ግን እነዚያ እንግዶች በፌስቡክና በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች አማካኝነት በየዕለቱ ወደ ቤቱ እየገቡ መሆናቸውን ይዘነጋል! ▪️ ስለዚህ አባቶች ሆይ! በአብዛኞቹ የሙስሊሞች ቤቶች ውስጥ ሾልኮ የገባውን ይህን ታላቅ አደጋ ተገንዝባችሁ ልጆቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ጠብቁ! ▪️ በእነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ምክንያት ስንት የፍቺ ችግሮች፣ ከሃላል ውጭ የሆኑ ግንኙነቶች፣ ሴት ልጆችን በምስጢራቸው ማስፈራራትና በገንዘብ መጠቀም የመሳሰሉ ብዙ ችግሮች ስንመለከት ቆይተናል! ▪️ ስለዚህ አባቶች ሆይ! ተጠንቀቁ፤ የቤተሰባችሁን ጉዳይ በቸልተኝነት አትተዉ! ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْؤُولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ» «ሁላችሁም ጠባቂዎች ናችሁ ሁላችሁም ስለምትጠብቁት ኃላፊነት ተጠያቂ ናችሁ።» 🤲 አላህ ደህንነትንና ከክፉ ነገሮች መጠበቅን ይወፍቀን። አሚን! http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram— ለልብህ የሹክሹክታ ጥሪ "ከቁርዓን ጋር ያለህን ልዩ ትስስር ለመገንባት የግድ መርከዝ መግባት ወይም ተቋም መቀላቀል አይጠበቅብህም፤ ... የሚያስፈልግህ ነገር ቢኖር አንድ ቁርዓን፣ ጠንካራ የሆነ ኡስታዝ እና ያንተ ቁርጠኛ ልብ ብቻ ነው 🌱 ታዲያ ከአላህ ንግግር ጋር የምታደርገውን ጉዞ መቼ ነው የምትጀምረው? አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም፤ ታዲያ ራስህን አታስተካክልም...!" t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramቁርኣንን በመሸምደድ መንገድ ላይ እስካለህ ድረስ፣ በጽናት ቀጥል! አላህ ለዚህ ታላቅ ፀጋ መርጦሃልና፤ ወዳጄ ሆይ! የምትጓዘውን መንገድ እስክትጨርስ ድረስ አትቁም! የአላህን ኪታብ የመጨረሻውን ፊደል እስክትሸመድድ ድረስ፤ የቂያማ ቀንም፦ «አንብብ፣ ደረጃህንም ከፍ አድርግ፣ በዱንያ ላይ ታነብ እንደነበረውም በዝግታና በማስተንተን አንብብ» የሚባልበትን ደረጃ እስክትደርስ ድረስ ጥረትህን አታቋርጥ። ደረጃህም የሚወሰነው በምታነባት የመጨረሻ አንቀጽ ነው። ነገር ግን ሁልጊዜ ከፊትህ ማስቀደም ያለብህ አንድ ታላቅ ጉዳይ አለ፦ ኢኽላስ (ለአላህ ብቻ ብሎ መሥራት)። መጀመሪያ ኢኽላስ ከዚያም ቁርአንን መሸምደድና በእርሱ መሥራት! t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram〰〰〰〰〰〰 🔖ሪያዱ ሷሊሒን ✅٨-كتاب الفضائل باب فضل قيام الليل 🎤ክፍል:- 95 🔖ሐዲስ ቁጥር:–1160 የትምህርቱ አቅራቢ:–ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን https://t.me/ibrahim_furii/7787 የኪታቡ ፒዲኤፍ👆 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramየወንድምህን ንግግርና ሀሳብ ካልተረዳህ… መጥፎ ከመጠርጠር ይልቅ ጠይቀው፤ ምን ማለት እንደፈለገ አረጋግጥ! ሸይጣን የወንድምህን ንግግር እንዲተረጉም አትፍቀድ! ብዙ አለመግባባቶች የሚጀምሩት ከመጥፎ ግምት ነው መፍትሔያቸው ግን በመጠየቅና በማብራራት ውስጥ ነው። t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegramእስካሁን ቁርአንን በቃልህ መሀፈዝ ያልጀመርክ ወንድሜ ሆይ! ምን እየጠበቅክ ነው? በአላህ ይሁንብኝ! የቁርአን አንቀጾችን ይዛ ከመኖር የተራቆተች ሕይወት ምንኛ ባዶ ናት! ቁርአንን መሀፈዝ ስትጀምር ግን ሕይወትህ የተለየ አቅጣጫ ትይዛለች፤ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም በአላህ እገዛ በእርካታ፣ በመረጋጋትና በሰላም የተሞላ ሕይወት ትኖራለህ! ከቁርአን ጋር ስትኖር ዱንያ በዓይንህ ታንሳለች ምኞትህና ዓላማህ ግን ከፍ ይላሉ! 📖 ቁርአንን የመሀፈዝ ጉዞህን ዛሬውኑ ጀምር! http://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram👈 ወየ ውልህ! በወጣትነትህ የምትፈጽመው ኢባዳ ይህን ያህል ብቻ ነውን?! እንግዲያስ በእርጅናህ ዘመን ምን ልታደርግ ነው?! @ibrahim_furii
Открыть в Telegram〰〰〰〰〰〰 🔖ሪያዱ ሷሊሒን ✅٨-كتاب الفضائل باب فضل صلاة الضحى وبيان أقلها وأكثرها وأوسطها.... 🎤ክፍል:- 94 🔖ሐዲስ ቁጥር:–1139 የትምህርቱ አቅራቢ:–ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን https://t.me/ibrahim_furii/7787 የኪታቡ ፒዲኤፍ👆 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в TelegramПереслано из ኢህሳን jobs Advertising 🌱
በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ የሚገኘዉ ሰላም መስጅድ ኡስታዝ ይፈልጋል (አስቸኳይ) 1 የማስቀራት ልምድ ያለው 2. ኢስላማዊ አደብ የተላበሰ 3.ኪታብ የማስቀራት አቅም ያለዉ 4 ከሰዎች ጋር ተግባቢነት ያለዉ ብዛት:- 1ወንድ ደሞዝ:- በስምምነት ቅጥር በቋሚነት በዚህ ያናግሩን በቴሌግራም @Jilaluebest ለመደወል 0925417548 አስቸኳይ ነው
Открыть в Telegram🌿በሒፍዝ ላይ አትቸኩሉ፤ አትሰልቹም! የቁርአን ሒፍዝ ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ ቢረዝምም አትሸነፉ። የዚህ ጉዞ መዳረሻ የአላህን ቃል በልባችሁ የመሸከም ታላቅ ክብር ነው። አንድን ጁዝእ ለመሸምደድ አንድ ወር ቢፈጅባችሁስ? ምን አጣችሁ? ምንም! ከዚያ ይልቅ በትጋታችሁና በጥረታችሁ ምንዳን ታገኛላችሁ። አንድን አስፈላጊ ነገር አትርሱ የቁርአን ሒፍዝ ወቅት በሕይወታችሁ ውስጥ ካሉ እጅግ ውድና ጣፋጭ ጊዜያት አንዱ ነው። ስለዚህ ቢከብድም ቢዘገይም በዚህ ጉዞ በምታሳልፉት እያንዳንዱ ቅጽበት ተደሰቱ። ፍጥነት ሳይሆን ቀጣይነት፤ ብዛት ሳይሆን ጥራት፤ መጨረስ ብቻ ሳይሆን በቁርአን መኖር ነው ዋናው! t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram📚የዑምደቱል አሕካም ደርስ ~ 📌 ደርስ ቁጥር፦ 34 📖باب الصيد 🔖ሐዲስ ቁጥር:‒382 🎙 የትምህርቱ አቅራቢ፦ ኡስታዝ ኢብራሒም ኸይረዲን የኪታቡ pdf ፋይል ለማግኘት👇 https://t.me/ibrahim_furii/8339 🌐https://t.me/ibrahim_furii
Открыть в Telegram