#ተሰውፍ ስም ብቻ አይደለም ከስያሜው በፊት የኖረ እውነት ነው! ብዙ ሰዎች ተሰውፍ ከዘመናት በኋላ የተወለደ ይመስላቸዋል፤ ሆኖም ጠበብት የሚያረጋግጡት እውነት የተሰውፍ እውነተኛ መሠረት ማለትም የልብን ማጥራት፣ ከነፍስ ጋር መታገል እና ወደ አላህ መመለስ የነብይነት ጥሪ እምብርት ራሱ መሆኑን ነው። ኢብን ኸልዱን በ“ሙቀዲማቸው” ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “የእነዚህ ሰዎች መንገድ… የሰሐቦች እና የታቢዒዮች መንገድ ነበር”፤ ከሰለፎችም አስተላልፈው ተሰውፍ ማለት “ነፍስን ማሠልጠን እና ተፈጥሮን ከመጥፎ ባሕርያት በመመለስ ወደ መልካም ባሕርያት እንደ ዙህድ (ዓለማዊነትን በልብ ውስጥ አለመያዝ)፣ ሕልም (ትዕግሥትና ገርነት)፣ ሰብር (ጽናት)፣ ኢኽላስ (ቅንነት) እና እውነተኝነት ማምጣት ነው” ብለዋል። እውነት ነው “ሱፊያ” የሚለው ቃል በነብዩ (ﷺ) ዘመን አልነበረም፤ ነገር ግን ትርጉሙ የእስልምና ራሱ በጣም የጠራ እና የተጣራ መልክ ነበር። ኢማም ጁነይድ አልባግዳዲ (ቁዲሰ ሲረሁ) እንዲህ ብለዋል፦ “ይህ ዕውቀታችን ማለትም ተሰውፍ ከመልዕክተኛው (ﷺ) ሐዲሥ ጋር የተሳሰረ ነው”፤ እንዲሁም “መንገዳችን በቁርአን እና በሱና የተገደበ ነው፤ ቁርአን ያላነበበ እና ሐዲሥ ያልጻፈ በመንገዳችንና በጠሪቃችን ሊከተሉት አይገባም” ብለዋል። ስለዚህ ሱኒ ተሰውፍ በሃይማኖት ውስጥ አዲስ በር አይደለም፤ ይልቁንም ጅብሪል ነብዩን (ﷺ) ስለ እርሱ የጠየቃቸው የ“ኢሕሳን” እውነት ስም ነው፦ “አላህን እንደምታየው አድርገህ ማምለክ ነው”። ሱፍዮቹ ይሕን ጥበብ ነው በተለያየ መንገድ የኖሩት፤ ሁሉም የተጎነጩት ከአንድ ምንጭ ነው። ከውስጣቸው የፈነዳላቸው በረከት ግን ቁጥር ሥፍር የለውም። ሳናውቃቸው አውቀናቸዋል ከማለት ጥድፊያ ይመልሰን! ሰላም ለይል ♥
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 22 |
| 3 h | 121 |
- Total to date121








