Account

Posts of Best kerim

newest first

#2556Photo

#ተሰውፍ ስም ብቻ አይደለም ከስያሜው በፊት የኖረ እውነት ነው! ብዙ ሰዎች ተሰውፍ ከዘመናት በኋላ የተወለደ ይመስላቸዋል፤ ሆኖም ጠበብት የሚያረጋግጡት እውነት የተሰውፍ እውነተኛ መሠረት ማለትም የልብን ማጥራት፣ ከነፍስ ጋር መታገል እና ወደ አላህ መመለስ የነብይነት ጥሪ እምብርት ራሱ መሆኑን ነው። ኢብን ኸልዱን በ“ሙቀዲማቸው” ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “የእነዚህ ሰዎች መንገድ… የሰሐቦች እና የታቢዒዮች መንገድ ነበር”፤ ከሰለፎችም አስተላልፈው ተሰውፍ ማለት “ነፍስን ማሠልጠን እና ተፈጥሮን ከመጥፎ ባሕርያት በመመለስ ወደ መልካም ባሕርያት እንደ ዙህድ (ዓለማዊነትን በልብ ውስጥ አለመያዝ)፣ ሕልም (ትዕግሥትና ገርነት)፣ ሰብር (ጽናት)፣ ኢኽላስ (ቅንነት) እና እውነተኝነት ማምጣት ነው” ብለዋል። እውነት ነው “ሱፊያ” የሚለው ቃል በነብዩ (ﷺ) ዘመን አልነበረም፤ ነገር ግን ትርጉሙ የእስልምና ራሱ በጣም የጠራ እና የተጣራ መልክ ነበር። ኢማም ጁነይድ አልባግዳዲ (ቁዲሰ ሲረሁ) እንዲህ ብለዋል፦ “ይህ ዕውቀታችን ማለትም ተሰውፍ ከመልዕክተኛው (ﷺ) ሐዲሥ ጋር የተሳሰረ ነው”፤ እንዲሁም “መንገዳችን በቁርአን እና በሱና የተገደበ ነው፤ ቁርአን ያላነበበ እና ሐዲሥ ያልጻፈ በመንገዳችንና በጠሪቃችን ሊከተሉት አይገባም” ብለዋል። ስለዚህ ሱኒ ተሰውፍ በሃይማኖት ውስጥ አዲስ በር አይደለም፤ ይልቁንም ጅብሪል ነብዩን (ﷺ) ስለ እርሱ የጠየቃቸው የ“ኢሕሳን” እውነት ስም ነው፦ “አላህን እንደምታየው አድርገህ ማምለክ ነው”። ሱፍዮቹ ይሕን ጥበብ ነው በተለያየ መንገድ የኖሩት፤ ሁሉም የተጎነጩት ከአንድ ምንጭ ነው። ከውስጣቸው የፈነዳላቸው በረከት ግን ቁጥር ሥፍር የለውም። ሳናውቃቸው አውቀናቸዋል ከማለት ጥድፊያ ይመልሰን! ሰላም ለይል ♥

Open in Telegram
Views121−58%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h22
3 h121
  1. Total to date121
#2555Text
Views207−27%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h76
3 h145
6 h207
  1. After 1 hour76
  2. After 6 hours207
  3. Total to date207
#2552Photo
Views208−27%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h68
7 h208
  1. After 1 hour68
  2. After 6 hours208
  3. Total to date208
#2551Video
Views175−39%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h60
7 h175
  1. After 1 hour60
  2. After 6 hours175
  3. Total to date175
#2550Photo
Views301+5%vs avg
Forwards—
Reactions15
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
8 h104
26 h301
  1. After 6 hours104
  2. After 24 hours301
  3. Total to date301
#2549Link preview
Views259−9%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
16 h195
26 h259
  1. After 24 hours259
  2. Total to date259
#2548Text
Views256−10%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#2547Photo
Views251−12%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#2546Video
Views313+10%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#2545Photo
Views313+10%vs avg
Forwards—
Reactions9
Comments—
#2544Photo
Views292+2%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—
#2542Photo
Views297+4%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#2540Text

#ሕልም ማለት ይህ ነው! የእኛ አይነቱ የተወሰነ ዳዕዋ አድርጎ ዝነኛ ይኾናል። ምንም ሳይሰራ በሾው ሊያብድ ይደርሳል። አንድ መድረሳ ወይም ትምህርተ ቤት ሳይከፍት አገረ ይያዝ ይላል። አንዳንድ የዳዕዋ እንቅስቃሴ ታሪኮችን ስታነብ ብናኝ እንደኾንን ይገባሀል። ወይም የኾነ ውስጣችንን ካሰረው አደገኛ ድህነት፣ የከተሜነትን ሾው ወጥቶልን እስኪበቃ መታገስ ይኖርብን ይኾናል። ይህን የምለፈልፈው የሚገባህ ተከታዩን ጽሁፍ ስታነበው ነው። ጀመረ ኢንዶኔዥያዊው የእስልምና ሊቅና የሃይማኖት ተሐድሶ አራማጅ ኬ.ኤች. አህመድ ዳህላን (1868–1923) እ.ኤ.አ. ህዳር 18 ቀን 1912 በዮግያካርታ፣ ኢንዶኔዥያ ውስጥ «ሙሐመዲያ» የተሰኘውን ድርጅት መሠረቱ። በራሳቸው መኖሪያ ቤት ውስጥ በትንሽ የትምህርት እንቅስቃሴ የተጀመረው ይህ ውጥን ውሎ አድሮ በሀገሪቱ ካሉ ትላልቅ እስላማዊ ድርጅቶች አንዱ ለመሆን በቅቷል። አህመድ ዳህላን ንቅናቄውን የመሠረቱት ኢስላማዊ ትምህርትን፣ ሃይማኖታዊ ግንዛቤንና ማኅበራዊ በጎ አድራጎትን ለማስፋፋት ነበር። እንደሚነገረው የመጀመሪያው ትምህርት ቤት በቤታቸው ውስጥ በምትገኝ አንዲት አነስተኛ ክፍል ውስጥ በስምንት ተማሪዎች ብቻ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህም ትምህርትን ለሰፊው ማኅበረሰብ ተደራሽ የማድረግ ራዕያቸውን የሚያንጸባርቅ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1923 ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ ሙሐመዲያ በተከታታይ አመራሮችና በአባላት ትውልዶች መስፋፋቱን ቀጠለ። ድርጅቱ በትምህርት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችና በሰብአዊ አገልግሎቶች ላይ ያተኮሩ ተቋማትን በመላው ኢንዶኔዥያ ገንብቷል። እ.ኤ.አ. በህዳር 2023 ይፋ በተደረገው ኦፊሴላዊ መረጃ መሠረት፣ ሙሐመዲያ እና ተጓዳኙ የ "አይሺያህ" ንቅናቄ 83 ዩኒቨርሲቲዎችን፣ 53 ኮሌጆችን እና 36 ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በአጠቃላይ 172 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ያስተዳድሩ ነበር። በተጨማሪም 122 ሆስፒታሎችን፣ 231 ክሊኒኮችን እና 5,345 ትምህርት ቤቶችንና መድረሳዎችን ያንቀሳቅሱ ነበር። የማኅበራዊ በጎ አድራጎት መረቡም በተመሳሳይ እጅግ ሰፊ ነው። የድርጅቱ የ2023 መረጃዎች እንደሚያሳዩት 1,012 የማኅበራዊ ተቋማትን (የወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያዎችንና ሌሎች የበጎ አድራጎት ማዕከላትን ጨምሮ) እንዲሁም 440 ኢስላማዊ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን መዝግቧል። እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2024 የሙሐመዲያ ዋና ጸሐፊ አብዱል ሙእቲ በአንድ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ባቀረቡት የተሻሻለ መረጃ መሠረት፣ ድርጅቱ 167 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ 126 ሆስፒታሎች፣ 5,346 የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማት፣ 630 የወላጅ አልባ ሕፃናት ማሳደጊያዎች እና ከ20,000 በላይ የመዋዕለ ሕፃናት ትምህርት ቤቶች እንዳሉት ገልጸዋል። እነዚህ አኃዞች ድርጅቱ ባለፉት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ የትምህርትና የሰብአዊ አገልግሎት ሥራዎቹን እንዴት እያስፋፋ እንደመጣ ያሳያሉ። እንደ 2023ቱ የድርጅቱ መረጃ ከሆነ፣ ዛሬ ሙሐመዲያ በሁሉም የኢንዶኔዥያ 35 ግዛቶች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በ30 ሀገራትም ቅርንጫፎች አሉት። ሥራዎቹ ከመማሪያ ክፍሎችና ከሆስፒታሎች ባለፈ ማኅበራዊ ድጋፍን፣ የማኅበረሰብ ልማትንና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ ተልዕኮዎችን ያካትታሉ። በመሆኑም ከአንድ ምዕተ ዓመት በፊት በአህመድ ዳህላን የተመሠረተው ይህ ድርጅት ከትሑት አጀማመሩ እጅግ በመላቅ፣ በትምህርት፣ በጤና አጠባበቅ እና በማኅበራዊ በጎ አድራጎት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያገለግል ታላቅ መረብ ለመሆን በቅቷል። ይህ ሪፖርት በሙሐመዲያ ኦፊሴላዊ ሕትመቶች እና በአመራሮቹ በተሰጡ መግለጫዎች ላይ የተመሠረተ ነው። የተቋማቱ አኃዞች የተጠቀሱት መረጃዎቹ ይፋ በተደረጉበት ጊዜ መሠረት ሲሆን በጊዜ ሂደት ሊለዋወጡ ይችላሉ። የድርጅቱ አጠቃላይ ስኬቶች የተገኙት በአህመድ ዳህላን ብቻ ሳይሆን ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ በዘለቀ የጋራ ጥረት ነው። በሐገራችን እንዲህ አይነት ወንዶች የማይፈጠሩት ለምንድነው? ዳዒ ማለት እንዲህ ኡመት ውስጥ ሕልሙን የሚያሰራጭ እንጂ ለኡማው የሐብታም ቁጥር የሚጨምር አይደለም። በጎ አድራጎት ማሕበራት የሚመሰረቱት የመሥራቾችን ኪስ ለማደለብ ሳይኾን የምር ማሕበረሰብን ለመቀየር ነው። ይህ ገብቶን የምንሰራበት ጊዜ ይናፍቀኛል። "የእኔ ሕልም ይህ ብቻ ነው!" የሚል ዳዒ/ዓሚል አላህ ይቀስቅስልን!

Open in Telegram
Views279−2%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#2538Text

Forwarded from Best kerim

#ማስታወሻ_ለዊርድ_ተጠቃሚዎች የተደራጀ የዒልም ካሪኩለም፣ ተሰዉፍን ለማለማመድ የሚያስመች የተደራጀ የአዝካር፣ የሰለዋትና የዱዓ ዊርዶች ያለውን ግለሰብ ኾነ ተቋም አድንቁ እንጂ አታዳክሙ። የመውሊድ ኪታቦች በቅጡ ተጽፈውና ታትመው ማንም እንዲጠቀማቸውና እንዲሰራጩ ምንም ባለተሰራበት ሁኔታ የተደራጁ ተቋማትንና ግለሰቦችን መንካት ፍጹም የኾነ ቂላቂልነት ነው። የሐበሻ መውሊዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በግለሰቦች ላይ ተንጠንልጥሎ እየቀረ ነው። ሙሉ የሐበሻ መውሊዶች በድምጽም ኾነ በኪታብ ደረጃ ተቀድተው ማስቀመጥ ላይ የሚሰራ የተደራጀ #ሐሪማ ከተማ ውስጥ አላየሁም። በየመሳጂዱ ባሉ ቀዲሞች ይህን ተርቲብ እንደ ዐዲስ ማነቃቃት ያስፈልጋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አውራድና፣ ሰለዋት በዐለምዐቀፍ ደረጃ የሚታወቁ የሐገራችን ሊቃውንቶችም የሚያውቋቸውን የሚጠቀሙ ሰዎች ስታዩ ማናናቅ ልክ አይደለም። ለምሳሌ፦ እነ ተንቢህ፣ ቡርዳ፣ ደላኢለል ኸይራት፣ የእነ ኢማም ነዋዊንና የሻዚሊን መሠረት ተደርገው የተዘጋጁ ዊርዶችና ሰለዋቶች አሉ። ከዚህም ውጭ በርካታ ቁርኣንና ሐዲስን መሠረት ያደረጉ፣ ቀደምት አንጋፋ ዐለምዐቀፍ መሻኢኾችን መሠረት ያደረጉ ዝግጅቶችም አሉ። እነዚህን ኹሉ መጠቀሙ እጅግ ጤናማና መለመድ ያለበት ተግባር ነው። ለምሳሌ እኔ ከቅርብ አመታት ወዲህ ለ 24 ሰአት ዊርድ የምጠቀመው ኪታብ ታላቁ የመኒው ሸይኽ ዑመር ሐቢብ (አላህ ይጠብቃቸው) የሰበሰቡትን "አልኹላሳ" የተሰኘውን ነው። በውስጡ በቁርኣን ሐዲስ ላይ የመጡ አዝካሮችን፣ ቀደምት ሊቃውንቶች እንደ ነወዊይ የመሳሰሉ ሰዎች የሚጠቀሟቸውን ዚክሮች ሰብስበው የያዙበት ኪታብ ነው። ይህን ኪታብ በማላመድ ደረጃ ትልቁ ባለውለታዬ ሸይኽ ዐዲል ሸሪፍ ናቸው። (አላህ ይጠብቃቸው) ሸይኽ ዐዲል ላለፉት ጥቂት አመታት በሩቅም በቅርብ ርቀትም ተዋውቄ ሰምቻቸዋለሁ። አንድም ቀን የሰው ስም አንስተው ሲያወሩ ገጥመውኝ አያውቅም፣ ሸይኽ ዐዲል ስለ አንጋፋው የሐበሻ ዐሊም ሐጅ ዘይኑና ሌሎች በቀጥታ ተርቢያ አግኝቶባቸው የሐረር ሊቃውንቶች፣ ስለ ሸይኽ ሸሪፍ ሲያወራ እና ስለእነርሱ ያለውን ሐያእ ለተረዳ ሰው የሐበሻ ሊቃውንት ዋጋ ምን እንደኾነ ከእርሱ ትማራለህ። በቅርብ ጊዜ የታተመውን የሸይኽ ታጁዲን (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ኪታብ በመድረሳው ለረጅም ጊዜ ለሰዎች ያቀራ ነበር። በእያንዳንዱ የሰለዋት ሐድራና መውሊዶቹ ላይ ለሐበሻ ሊቃውንቶች የሚያደርጋቸውም ዱዓዎች ይደንቀኛል። በሙሰላው ላይ ለ 24 ሰአት የሚለቀቁ የአምስቱም ወቅቶች አዝካሮች፣ ሳምንታዊ የቡርዳ (ሰለዋት)፣ በየወቅቱ የሚቀሩ ሲራዎች (ሰለዋቶች) ለበርካቶች የልብ መድሐኒት መኾን የቻለ ድንቅ ዓሊም ናቸው። አንድ ጊዜ ስለ ሐጂ ዘይኑ ሲያወሩ ምን አሉ መሰለህ " ሐጂ ዘይኑ ማለት የቀን የላኢላሀ ኢለላህ ዊርዳቸው በ ሺዎች ነበር" ሲል ቁጥሩን ስሰማው ለመቀበል ቸግሮኝ ነበር። በኃላ አንድ ቪድዮ ላይ የሐጂን የእጅ ጣት ሳየው ተጣሞ አየሁት ምንድነው ይህ ስል ደጋግመው ሙስበሐ የያዙበት እጅ ነው አላሉኝም! ላ ኢላሀ ኢለላህ! ያ ሪጃለላህ ሰዎች ስለ እነዚህ ሰዎች ዝም ብለን ብናወራ ነው የሚሻለው ♥

Open in Telegram
Views214−25%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#2537Photo
Views294+3%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
48 h270
66 h294
  1. Total to date294
#2536Photo
Views345+21%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#2535Photo
Views367+29%vs avg
Forwards—
Reactions12
Comments—
#2534Photo
Views414+45%vs avg
Forwards—
Reactions13
Comments—
#2533Photo

ትንሽ የምትመስለው ዓይን ታላቁንና ግዙፉን ዓለም በቀላሉ የመያዝና የማየት አቅም ከተሰጣት፤ አላህ የፈጠረው ልብም ከሚገጥመው ሐዘንና ችግር በላይ ሰፊ የመሆን፣ የመጽናናትና የመቻል አቅም ተሰጥቶታል። አንዳንዴ ሐዘናችን ትልቅ የሚመስለን የልባችንን ጥልቅ አቅም ስለምንዘነጋ ወይም እይታችንን #በችግሩ ላይ ብቻ ስለምናተኩር ነው። ችግሮች እኮ ፈጣሪ አይደሉም፤ ፍጥረት ናቸው። ችግሮቻችን በፍጥነት እንዲነሱልን እጅ ዘርገተን ምላሹ የረቀቀ ሊኾነ ይችላል። ልክ እንደ ቀድሞ ነብያት የአንድ ሰው እድሜ ያህል ትዕግስት ሊያስፈልግ ይችላል። ብዙው የሰው ልጅ እርሱ በእርሱ እንዲጠቃቀም በማድረግ የሚመልስልን ብዙ መልስ አልለ። በዚህ ውስጥ የማንነቃቸውና የማናስተውላቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ዱዓ አብዝቶ መለመንን የተለገሰ ሰው ጣዕሙን ያውቀው የለ?! ከሐጃው በላይ እርሱ የሰራውን መመረጥና ሪዷ (ውዴታ) ላይ ያደርሰዋል። እርሱ የወደደልንን መውደድ መቻል ደግሞ የባርነት ጥግ ነው እርሱ የመረጠልንን መቃወም ወይም እርሱ ያስቀመጠውን ሰበቦች ችላ ማለት ደግሞ ሰኽጥ ሊያስከትል ይችላል። አላህ ይዘንልን ብዙ ጊዜ የሚገጥመን ወስዋስ ይኽ ሁለተኛው ነው። አይን ማየት የማይችለው የሚመስለውን ያየ፤ ልብ መሸከም የማይችለው የለም ሰፊ ነውና! ያ አላህ በእዝነት ይኹን፤ አስረዳን ♥

Open in Telegram
Views406+42%vs avg
Forwards—
Reactions8
Comments—
#2531Text
Views437+53%vs avg
Forwards—
Reactions24
Comments—