Кабинет
የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

የካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

Юзернейм
@stgeorge_gibi_gubae
Категория
Религия
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики1 479
Просмотров на пост, 7 дн.142за 7 дней
ERR9,60 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
5 нояб. 2026 г.476
11 нояб. 2026 г.373
13 нояб. 2026 г.334
25 нояб. 2026 г.142

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01
    Просмотры476
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02
    Просмотры373
    Пересылки—
    Реакции3
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры334
    Пересылки—
    Реакции2
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры154
    Пересылки—
    Реакции2
    Комментарии—

Новые посты

#5167Фото
Просмотры130−56%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#5166Фото
Просмотры154−48%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5165Фото
Просмотры334+14%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5164Фото
Просмотры373+27%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#5162Фото
Просмотры476+62%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5161Фото
Просмотры509+73%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5160Фото
Просмотры416+42%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#5159Фото
Просмотры396+35%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
#5157Превью ссылки
Просмотры493+68%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#5156Текст

እንኳን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" እና ለቅዱስ "ሐናንያ ሐዋርያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው አልፈዋልና:: 2ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው ንጉሥ ታዜር / አይዛና / ሠይፈ አርዕድ እና ንግሥት አሕየዋ / ሶፍያ ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት 2 ዕንቁዎችን አስረከባቸው:: ንግስት አሕየዋ (ሶፍያም) መጋቢት 29 ቀን በ311 ዓ/ም ጸንሳ: ታሕሳስ 29 ቀን በ312 ዓ/ም 2ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ 2 ፍሬዎች በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን ጠንቅቀው ተምረዋል:: ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ12 ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ 2ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች:: ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም "የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: 2ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው:: ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ19 ዓመታቸው: 2ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና" አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ:: በወቅቱ ፍሬምናጦስ (የሁዋላው አቡነ ሰላማ) በቤተ መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል: ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ? በርግጥ ምሥጢሩ ንገረን" አሉት:: እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ300 ዓመታት በፊት አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው:: "አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት:: ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ:: ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ154 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ:: በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና 12 ቤተ መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል:: ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ10 ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ:: ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ:: ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ52 ዓመቱ: በ364 ዓ/ም ጥቅምት 4 ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ15 ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ379 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ67 ዓመቱ በክብር ዐርፏል:: ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ30 ቀናት የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ: በሕገ ኦሪት አድጐ: ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው:: ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ: ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር:: ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነው የነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል:: ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: 2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው: ፈወሰው: አጠመቀው: በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19) ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን:: =>ጥቅምት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ 2.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ባኮስ ሰማዕት 5.ቅዱሳን ባባ እና ማማ 6.ቅዱስ ዮሐንስ ሕጽው =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Открыть в Telegram
Просмотры438+49%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—

Все посты

Связи