በስመ አብ ወወልድ መንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚊ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ 👣 ወደ፦ ቦሌ አራብሳ በኩር ዋሻ ደብረፀሐይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህዳር | 20 | እሑድ | 2018 💰የጉዞዋጋ መስተንገዶን ጨምሮ 500 ብር 💒 መነሻ ቦታ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን 🕰መነሻ ሰዓት 12:30 መመለሻ ሰዓት 12:00 ለመክፈል እነዚህን አማራጮች መጠቀም ትችላላችሁ Commercial bank 1000604911908 Arsema mulugeta Abyssinia 265799396 Yididiya getnet Telebirr 0974038864 elias muligeta ማሳሰቢያ ፩.ክርስትያናዊ አለባበስ እንዳይዘነጋ ፪.በሞባይል ባንኪንግ ወይም በባንክ ከከፈላችሁ በኋላ ደረሰኙን screenshot አርጋችሁ ከታች ባለው አካውንት መላክ እንዳትረሱ @ELIA122334 ለበለጠ መረጃ 0976138312 ❗️ለጉዞው ይረዳን ዘንድ ሁላችንም እስከ ህዳር 18 ድረስ ክፍያችንን እንፈፅም❗️ ኑ! አብረን ወደ ቤተክርስቲያን እንሒድ አንድነታችንን መሰባሰባችንን አንተው !
Open in Telegramየካቴድራል፣ ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 5, 2026 | 476 |
| Nov 11, 2026 | 373 |
| Nov 13, 2026 | 334 |
| Nov 25, 2026 | 142 |
Most viewed this month
- 01Views476Forwards—Reactions—Comments—
- 02Views373Forwards—Reactions3Comments—
- 03Views334Forwards—Reactions2Comments—
- 04Views154Forwards—Reactions2Comments—
Latest posts
++++++++++++++++++++++ የአቻ ግፊት ++++++++++++++++++++++ "እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ" መፅሀፈ ነገስት ቀዳማዊ 12:8 📅ቀን አርብ ህዳር 18/2019 📍 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ⌚️ 10:30-11:30 ሁላችንም ጓደኞቻችንን ይዘን በጊዜ እንገኝ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈ ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ share & join 📲@StGeorge_Gibi_Gubae
Open in Telegram💎💎የአገልጋዮች ስልጠና💎💎 📅ቀን ቅዳሜ ኅዳር /5/2019 ሰንበት ኅዳር /6/2019 📍 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ⌚️ 8:00 - 10፡00 ሁላችንም በጊዜ እንገኝ❗️ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ share & join 📲@StGeorge_Gibi_Gubae
Open in Telegram✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ነገረ ማርያም ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 'ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተገጎናፅፋ ጨረቃከእግሮቿ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአስራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች'' ዮሐንስ ራእይ 12:1 📅ቀን አርብ ኀዳር /4/2019 📍 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ⌚️ 10:30-11:30 ሁላችንም ጓደኞቻችንን ይዘን በጊዜ እንገኝ❗️ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ share & join 📲@StGeorge_Gibi_Gubae
Open in Telegram🕯 ዝክረ ቅዱስ ጊዮርጊስ 🎯 ቅዳሜ ጥቅምት 28 2018ዓ.ም. 🕰 ከ 7:30 - 9:00 🏤 በሰንበት ት/ቤቱ ሕንጻ ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር እንድንገኝ ስንል በአክብሮት በአክብሮት እንጠይቃለን። "ፍቅር ያጌብረኒ ከመእንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል። ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ማኅበራችንን አንተው! @StGeorge_Gibi_Gubae በሰዓታችን እንገኝ!
Open in Telegram✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ባልንጀራ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ''ባልንጀራህንም ብትከዳው በእግዚአብሄርም ስም በሐሰት ብትምል እንደ ስራህ ፍዳህን ተቀበላለህና'' 📅ቀን አርብ ጥቅምት 20|2019 📍 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ⌚️ 10:30-11:30 ሁላችንም ጓደኞቻችንን ይዘን በጊዜ እንገኝ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈ ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ share & join 📲@StGeorge_Gibi_Gubae
Open in TelegramForwarded from የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 🌹 ልዩ የቅበላ መርኃግብር 🌹 ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 122፥1 በአ.አ.ዩ ኮሜርስ ካምፓስ የተመደባችሁ የ1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች እናንተን እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት ሐሙስ ጥቅምት 12 ልዩ የቅበላ መርኃግብር አዘጋጅተንላችኋል። ላልሰሙት በመንገር በዕለቱ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን እንድትገኙልን በእግዚአብሔር ስም እንጋብዛለን። 📅 ሐሙስ ጥቅምት 12/2019 ⏰ 7:30-10:30 📍በማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን 🚌 ቦታውን ለማታውቁት ትራንስፖርት አዘጋጅተናል!! በካፌው በኩል ባለው መውጫ በር አስተባባሪዎችን ታገኛላችሁ። ለበለጠ መረጃ +251942004349 +251961346165 +251991184116 ይደውሉ የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube
Open in Telegram✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ የእግዚአብሔር መቅደስ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ''ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ'' 📅ቀን አርብ ጥቅምት13|2019 📍 በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ⌚️ 10:30-11:30 ሁላችንም ጓደኞቻችንን ይዘን በጊዜ እንገኝ የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ ◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈◎◈ ያወቅነውን በማሳወቅ የበኩላችንን እንወጣ share & join 📲@StGeorge_Gibi_Gubae
Open in Telegramበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! የካቴድራል፣ቅድስት ማርያም እና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ በግቢ ጉባኤ ውስጥ ባሉት አገልግሎቶች መሳተፍ የምትፈልጉ አህቶች ወንድሞች!!! https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScUmgr3CUrKdtIUQgSk_ZIiy5yNQ5JS74aCaQbZjWoZr2ut-Q/viewform?usp=publish-editor
Open in Telegramእንኳን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" እና ለቅዱስ "ሐናንያ ሐዋርያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ††† ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው አልፈዋልና:: 2ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው ንጉሥ ታዜር / አይዛና / ሠይፈ አርዕድ እና ንግሥት አሕየዋ / ሶፍያ ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት 2 ዕንቁዎችን አስረከባቸው:: ንግስት አሕየዋ (ሶፍያም) መጋቢት 29 ቀን በ311 ዓ/ም ጸንሳ: ታሕሳስ 29 ቀን በ312 ዓ/ም 2ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ 2 ፍሬዎች በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን ጠንቅቀው ተምረዋል:: ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ12 ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ 2ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች:: ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም "የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: 2ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው:: ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ19 ዓመታቸው: 2ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና" አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ:: በወቅቱ ፍሬምናጦስ (የሁዋላው አቡነ ሰላማ) በቤተ መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል: ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ? በርግጥ ምሥጢሩ ንገረን" አሉት:: እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ300 ዓመታት በፊት አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው:: "አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት:: ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ:: ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ154 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ:: በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና 12 ቤተ መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል:: ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ10 ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ:: ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ:: ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ52 ዓመቱ: በ364 ዓ/ም ጥቅምት 4 ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ15 ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ379 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ67 ዓመቱ በክብር ዐርፏል:: ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ30 ቀናት የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ: በሕገ ኦሪት አድጐ: ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው:: ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ: ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል:: በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር:: ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነው የነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል:: ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: 2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው: ፈወሰው: አጠመቀው: በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19) ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን:: =>ጥቅምት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ 2.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ባኮስ ሰማዕት 5.ቅዱሳን ባባ እና ማማ 6.ቅዱስ ዮሐንስ ሕጽው =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Open in TelegramConnections
Similar channels
Wolkite University muslim student jema@wkumuslimsReligion1.48K
ዜና ቤተክርስቲያን@zenatewahedo16Religion1.47K
ሔብሮን ቤተክርስቲያን Hebron Church@hebronchurchReligion1.5K
GCME-SLM@slmethiopiaReligion1.5K
ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ@wweotcReligion1.51K- AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ@aljueddaawaReligion1.43K
🕋GAADDISA ISLAAMAA♥️ظلال الإسلام✍@gaaddisaislaamaaReligion1.53K
ÃL~Fãlâh Dãwã grøúp@alfalahdawagrpReligion1.54K