ግብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦ " ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለበት ሀገር አስር ሺህ የማይሞላ ሰው ግብር የሚከፍልበት ሀገር የአስር ሺህ ሰው ግብር የ100 ሚሊዮን ሰው ፍላጎት እንዴት ሊያሟላ እንደሚችል መገመት ለናተ ከባድ አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብር የሚከፍሉ ኃይሎች በጣም ጥቂት ናቸው። የግብር ቤዝ ማስፋት ያስፈልጋል ሲባል ሰው ከሰራው ስራ ውስጥ በየደረጃው መጠነኛ የሆነ ግብር መክፈል ካልቻለ መሰረተ ልማት ማምጣት አይቻልም። የግብርና ሴክተር እያደገ ነው አርሶ አደር ላይ ለውጥ እያመጣነው ቢባልም አርሶ አደሮቻችን እስካሁን በቂ የሚባል ግብር አይከፍሉም። ማዳበሪያ ድጎማ ይጠብቃሉ፣ ማዳበሪያ በጊዜው በነሱ ማሳ አካባቢ እንዲደርስ ይጠብቃሉ ነገር ግን ያን መሰረተልማት ለመገንባት የሚያስችል ግብር ካልመጣ መንግሥት የሚጠበቅበትን ነገር በበቂ ለመከወን ይቸገራል። ስራ የሚሰሩ ግብር የሚከፍሉ ሰዎች በአንድ በኩል ግብር መክፈል ኩራት መሆኑን ማወቅ አለባቸው ለሌላ በኩል ስራ በሰራን ቁጥር በዚያው ልክ የምናጋራው የሃብት ልክ እንዳለ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነጋዴዎች ግብር መክፈል ላይ ነው የሚቸገሩት እንጂ በተለያየ መንገድ ደግፉ ቢባሉ መንግሥት አካውንት በማያደርጋቸው መንገዶች በጣም በርካታ ብር ያወጣሉ ፤ ግብር የመክፈል ፍላጎቱ ከመንግሥት ሰራተኞች አንጻር ሲታይ ታማኝ ግብር ከፋይ በጣም ውስን ነው። አስበው የሚከፍሉ በጣም ጥቂት እንዳሉ ይታወቃል። አብዛኛው ግን በግብር ስወራ ላይ ነው ጊዜ የሚያባክነው። ይሄን በአሰራር ማሻሻል መቆጣጠር ያስፈልጋል። "
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 6 030 |
| 3 ч | 14 000 |
- Через 1 час6 030
- Всего сейчас14 000








