ግብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፦ " ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባለበት ሀገር አስር ሺህ የማይሞላ ሰው ግብር የሚከፍልበት ሀገር የአስር ሺህ ሰው ግብር የ100 ሚሊዮን ሰው ፍላጎት እንዴት ሊያሟላ እንደሚችል መገመት ለናተ ከባድ አይሆንም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግብር የሚከፍሉ ኃይሎች በጣም ጥቂት ናቸው። የግብር ቤዝ ማስፋት ያስፈልጋል ሲባል ሰው ከሰራው ስራ ውስጥ በየደረጃው መጠነኛ የሆነ ግብር መክፈል ካልቻለ መሰረተ ልማት ማምጣት አይቻልም። የግብርና ሴክተር እያደገ ነው አርሶ አደር ላይ ለውጥ እያመጣነው ቢባልም አርሶ አደሮቻችን እስካሁን በቂ የሚባል ግብር አይከፍሉም። ማዳበሪያ ድጎማ ይጠብቃሉ፣ ማዳበሪያ በጊዜው በነሱ ማሳ አካባቢ እንዲደርስ ይጠብቃሉ ነገር ግን ያን መሰረተልማት ለመገንባት የሚያስችል ግብር ካልመጣ መንግሥት የሚጠበቅበትን ነገር በበቂ ለመከወን ይቸገራል። ስራ የሚሰሩ ግብር የሚከፍሉ ሰዎች በአንድ በኩል ግብር መክፈል ኩራት መሆኑን ማወቅ አለባቸው ለሌላ በኩል ስራ በሰራን ቁጥር በዚያው ልክ የምናጋራው የሃብት ልክ እንዳለ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ነጋዴዎች ግብር መክፈል ላይ ነው የሚቸገሩት እንጂ በተለያየ መንገድ ደግፉ ቢባሉ መንግሥት አካውንት በማያደርጋቸው መንገዶች በጣም በርካታ ብር ያወጣሉ ፤ ግብር የመክፈል ፍላጎቱ ከመንግሥት ሰራተኞች አንጻር ሲታይ ታማኝ ግብር ከፋይ በጣም ውስን ነው። አስበው የሚከፍሉ በጣም ጥቂት እንዳሉ ይታወቃል። አብዛኛው ግን በግብር ስወራ ላይ ነው ጊዜ የሚያባክነው። ይሄን በአሰራር ማሻሻል መቆጣጠር ያስፈልጋል። "
Открыть в TelegramПосты канала Natnael Mekonnen
🚨 በካዛንችስ በካሬ 80,500 birr ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ቤቶችን ለ1ሳምንት ብቻ በተዘጋጀ ቅናሽ በ9ዙር ቀስ ብለው በ2 አመት ከ6ወር እየከፈሉ መግዛት ለሚፈልጉ በካሬ 115,000ሺ ብር በ15% ቅድመ ክፍያ ብቻ!!! 🏢ባለ አንድ መኝታ (92kare) = 10.5 Million Birr 🗞 15% ቅ.ክፍያ = 1.5 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 7.4 Million Birr 🏢ባለ ሁለት መኝታ (123 kare) = 14.1Million Birr 🗞15% ቅ.ክፍያ = 2.1 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 9.9 Million ብር 🏢ባለ ሦስት መኝታ (163 kare) = 18.7 Million Birr 🗞15% ቅ.ክፍያ = 2.8 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 13.1 Million ብር 🚨ያስተውሉ ፡ ቤቶን እስኪረከቡ ድረስ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አይኖረንም ይህም መልካም ዜና ነው!!! በዚህ መንደር 👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሰፋፊ ሊፍቶች 👉ምቹ እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች 👉ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ 👉አውቶማቲክ ጀነሬተር የተገጠመለት 👉የከርሰ ምድር ውሃ እና 👉ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሰገነት አካቷል ለበለጠ መረጃ : 09-18-31-47-21| Sales Consultatnt ይደዉሉልን!
Открыть в Telegramበቅርቡ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከእስር ተለቆ (ፍርዱን ሳይጨርስ ወጥቶ) በአንድ ወር ውስጥ 5 ሴቶችን የገደለው ተጠርጣሪ ! • ግለሰቡ አሁን በእስር ላይ ይገኛል። ከቀናት በፊት በትግራይ እንዳስላሰ ሸረ ከተማ በስራ ቦታዋ ላይ እያለች የሶስት ልጆች እናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለና አስክሬኗ ላይ ጾታዊ ጥቃት የፈጸመ ተስፋይ ዮሐንስ የተባለ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። ግለሰቡ እሷን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሴቶችንም መግደሉን ከሞቱ በኋላ ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል። የሰሜን ምዕራብ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ በዚህ ጉዳይ ላይ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ምን አሉ ? ግለሰቡ 54 ዓመቱ እንደሆነና በ2015 ዓ/ም አንዲትን ሴት ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጥላት በማታለል ወስዶ ገድሏት የ22 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር። አሁን በቅርቡ ጦርነት ሲቀሰቀስ ከእስር ከወጣ በኋላ አምስት ሴቶችን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመግደል መጠርጠሩን ኮማንደሩ ተናግረዋል። እንደ ፖሊስ ገለጻ፣ ግለሰቡ አምስቱንም ሴቶች ከገደለ በኋላ ፆታዊ ጥቃት ፈጽሟል። ከአምስቱ መካከል የአንዲትን ሟች የአምስት ዓመት ልጅንም ማገቱን ፖሊስ አስረድቷል። ተጠርጣሪው 5ቱን ሴቶች የገደላቸው ከጥቅምት 19 እስከ ኅዳር 8/2019 ዓ.ም ባሉት 20 ቀናት ውስጥ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል። - መጀመሪያ የተገደለችው ዮርዳኖስ ሓጎስ ስትባል ጥቅምት 19 ተገድላለች። - የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሟች የሻለም ዘነበ ጥቅምት 25 ተገድላለች። - ሦስተኛዋ ሟች ገነት ደጀን ጥቅምት 30 ተገድላለች። - አራተኛ ሟች ሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ኅዳር 7 ተገድላለች። - አምስተኛዋ ሟች ወሰንየለሽ መኮንን ኅዳር 8 ተገድላለች። ተጠርጣሪው በሴቶቹ ላይ ግድያውን ለመፈጸም ቢላዋ፣ መጥረቢያ እና ድንጋይ እንደተጠቀመ ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከተገደላቸው በኋላ ጾታዊ ጥቃት እንደፈጸመባቸው ተመላክቷል። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ወንጀሉን እንደፈጸመ ያመነ ሲሆን፣ ወንጀሉን የፈጸመበትን ምክንያት ሲያስረዳ " በተፈጥሮዬ ችግር ስላለብኝ ነው " የሚል ምላሽ እንደሰጠ ፖሊስ አመልክቷል። ኮማንደር ገብረሥላሴ እንዳብራሩት፣ ግድያ መፈጸሙ ለተጠርጣሪው የኩራት እና የእርካታ ስሜት የሚሰጠው እንደሚመስል በምርመራው ተረድተዋል። በተጠርጣሪው ተገድለዋል ከተባሉት መካከል አንዷ የሆነችው የየሻለም ዘነበ የአምስት ዓመት ልጅም የት እንዳለች እስካሁን አልታወቀም። ምርመራው እንደሚያሳየው፤ ተጠርጣሪው ልጅቷን ካገተ በኋላ እናቷን 40 ሺህ ብር እንድትሰጠው በመጠየቅ፣ ልጇን እንደሚመልስላት ነግሯት ነበር። የሻለምም ራቅ ወዳለ ወዳለ ቦታ በመምጣት ልጇን እንደምትረከብ ነግሯት ከደረሰች በኋላ እንደገደላት ፖሊስ ገልጿል። ነገር ግን ልጅቷ ያለችበት ቦታ እስካሁን አልታወቀም፤ ጉዳዩም በምርመራ ላይ ይገኛል። ከሟቾቹ መካከል የሆነችው ገነት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበረች ያለው ፖሊስ፣ እሷን ጨምሮ ሁሉም ሟቾች በሻይ ቡና እና በአልኮል መጠጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው ነበር። የምርመራው መነሻ የሆነው በኅዳር 7/2019 ዓ.ም የተገደለችው የሚሊዮን ገብረእግዚአብሔር ግድያ ነው። ከሟቿ ጋር ትሠራ የነበረች ሴት፣ ሚሊየን በጠዋት ስልክ ደውላላት፣ ተስፋይ የሚባል ሰው ቡና በርካሽ ዋጋ እንደሚያቀርብላት ነግሯት ወደ ሥራ ቦታዋ እንድትመጣ እንደጠራት አሳውቃት ነበር። አብራት የምትሠራዋ ወደ ሥራ ቦታው ባቀናችበት ወቅት ግን ሚሊየን ሻይ ቡና የምትሠራበት ቦታ በሩ ተዘግቶ ነበር የጠበቃት። በዚህም ምክንያት ጓደኛዋን ፈልጋ ስላጣቻት ቁልፍ አፈላልጋ በሩን ከፍታ ስትገባ አስክሬኗን እንዳገኘች የፖሊስ ምርመራ አመልክቷል። ፖሊስ ከጓደኛዋ በተገኘው መረጃ መሠረት ምርመራ ሲያካሂድ ተስፋይ የሚባል ግለሰብ ከሟቿ ጋር በስልክ ተደዋውሎ እንደነበር ማወቁን ኮማንደር ገብረሥላሴ ገልጸዋል። ከዚያም የተጠርጣሪውን ማንነት፣ አካላዊ ገጽታ እና ልዩ መለያ በማጣራት ወደ ተጠርጣሪው መድረሳቸውን ተናግረዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በሠራው ወንጀል ከተፈረደበት እስር ማምለጡም ፖሊስ ምርመራውን ተስፋይ ላይ እንዲደረግ አስችሏል ሲሉ ኮማንደሩ ይገልጻሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላም የወንጀሉን እውነተኛ ሁኔታ ለማረጋገጥ ግድያዎቹ ወደ ተፈጸሙባቸው ቦታዎች እንዲመራቸው እንደጠየቁት፣ እሱም እየመራ አምስት የወንጀል ቦታዎችን እንዳሳየ ኮማንደሩ አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከል የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ገነት ደጀን ከተገደለች በኋላ የት እንዳለች ሳይታወቅ እንደቆየች እና ቤተሰቦቿም በዚያን ጊዜ ስለመገደሏ እንዳላወቁ ተገልጿል። ተጠርጣሪው ከከተማ ራቅ ወዳለ ቦታ ወስዶ አስክሬኗ የሚገኝበትን ቦታ የጠቆመ ሲሆን፣ የሟቿ መሆናቸውን የሚያመለክቱ የግል ንብረቶች እና የአካል ቅሪቶች እንዳገኙ ኮማንደሩ ገልጸዋል። የሌሎቹ አስክሬን ቀደም ብሎ የተገኘ ቢሆንም በማን እና በምን ምክንያት እንደተገደሉ ለመመርመር በወቅቱ የነበረው የፀጥታ ሁኔታ እንዳላስቻለ ኮማንደሩ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል የሻለም ዘነበ እና ገነት ደጀን ከቤት ውጪ ሲገደሉ ቀሪዎቹ በቤታቸው መገደላቸውን ፖሊስ አመልክቷል። ይሁንና ምርመራው ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም። በተለይ የአምስት ዓመቷ ሕፃን ያለችበትን ቦታ ለማወቅ እና ሌሎች ተጨማሪ የወንጀል ጥቆማዎች ካሉ ለማጣራት ምርመራው እየቀጠለ እንደሆነ ኮማንደር ገብረሥላሴ አማረ ለቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ገልጸዋል።
Открыть в Telegram🚨 በካዛንችስ በካሬ 80,500 birr ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ቤቶችን ለ1ሳምንት ብቻ በተዘጋጀ ቅናሽ በ9ዙር ቀስ ብለው በ2 አመት ከ6ወር እየከፈሉ መግዛት ለሚፈልጉ በካሬ 115,000ሺ ብር በ15% ቅድመ ክፍያ ብቻ!!! 🏢ባለ አንድ መኝታ (92kare) = 10.5 Million Birr 🗞 15% ቅ.ክፍያ = 1.5 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 7.4 Million Birr 🏢ባለ ሁለት መኝታ (123 kare) = 14.1Million Birr 🗞15% ቅ.ክፍያ = 2.1 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 9.9 Million ብር 🏢ባለ ሦስት መኝታ (163 kare) = 18.7 Million Birr 🗞15% ቅ.ክፍያ = 2.8 Million Birr ✨Cash ለሚከፍሉ 30% ቅናሽ = 13.1 Million ብር 🚨ያስተውሉ ፡ ቤቶን እስኪረከቡ ድረስ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አይኖረንም ይህም መልካም ዜና ነው!!! በዚህ መንደር 👉ደረጃቸውን የጠበቁ ሰፋፊ ሊፍቶች 👉ምቹ እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች 👉ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ 👉አውቶማቲክ ጀነሬተር የተገጠመለት 👉የከርሰ ምድር ውሃ እና 👉ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሰገነት አካቷል ለበለጠ መረጃ : 09-18-31-47-21| Sales Consultatnt ይደዉሉልን!
Открыть в Telegramጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በነገው ዕለት ለምክር ቤቱ አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት በነገው ዕለት ያካሂዳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ምክር ቤቱ ነገ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤው ላይ የመንግሥትን አቋም ካዳመጠ በኋላ የድጋፍ ሞሽን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ።
Открыть в Telegram✨አንጋፋው ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት 🏠 በተግባር ከተረጋገጠ ታማኝነት፣ ከበፊቱ በበለጠ ኃይል፣ በአዲስ ራዕይ እና ዘመናዊነትን በጠበቀ አቅም በጎተራ ፕሮጀክት ዳግም ተመልሷል። ✨ከዚህ በፊት ሁለት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ አስረክቧል :: 🫵የኑሮ ደረጃዎን በጎተራ ያሳድጉ – ዘነበ ፍረው ሪል እስቴት🫵 ✨እንደ Addis tomorrow ልዩ የEconomy zone, Mehamedian village ባሉ ቦታዎች የተከበበ ከ10 % ቅድመ ክፍያ ጀምሮ፤ 👉በካሬ ከ105,500 ብር ጀምሮ 👉በ3 አመት የሚረከቧቸው አማራጮች 👉የንግድ ሱቆች ከ 16 ካሬ -300 ካሬ በ net Area እየሸጥን እንገኛለን ✨ስቱዲዮ (66 ካሬ ): ✨1 መኝታ(83 ካሬ): ✨2 መኝታ(122 ካሬ): ✨3 መኝታ(168 ካሬ) ✨ምርጥ የከተማዋን እይታ ያላቸውን ክፍሎች ቅድሚያ በመምረጥ ቤትዎን አሁኑኑ ያስይዙ! ✨ለበለጠ መረጃ፣ ለቢሮ ቀጠሮ፣ ሳይት ለመጎብኘት ይደውሉ ☎️0912355631
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ አየር ኃይል፤ የሰማያችን አለኝታ፣ የሉዓላዊነታችን መከታ፦ "በድልና በመስዋዕትነት የደመቀ የኢትዮጵያ ሰማይ አለኝታ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ኃይል 91ኛ ዓመት ምስረታውን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል። ከዘጠኝ አስርት ዓመታት በላይ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የአየር ክልል በጀግንነት እና በመስዋዕትነት ሲጠብቅ የቆየው ይህ ታሪካዊ ተቋም፣ 91ኛ ዓመት ምስረታውን ሕዳር 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም ያከብራል። ይህ ታላቅ መታሰቢያ የ91 ዓመታትን የጽናት፣ የሀገር ፍቅር ጉዞ ከመዘከር ባሻገር፣ የተቋሙን የወደፊት ራዕይና የእድገት አቅጣጫ የሚያመላክት ልዩ አጋጣሚ ነው። የኢፌዴሪ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ 91ኛ ዓመት ምስረታ በቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄደው የ10ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የተቋሙን ወቅታዊ አቅም፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሰው ኃይሉን ዝግጁነት አንስተዋል። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዘመኑን የዋጁ ትጥቆች በመታጠቅና የሰው ኃይል በማብቃት በሀገራችን ላይ የሚቃጡ ጥቃቶችን በማክሸፍ ታሪክ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዘጠና ዓመታት በፊት በአነስተኛ የአቪዬሽን አቅም የተጀመረው የአየር ኃይሉ ጉዞ፣ ዛሬ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን፣ የተራቀቁ የአየር ውጊያና የአየር መከላከያ አቅሞችን እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ብቃትን የተላበሰ ጠንካራ ተቋም እንዲገነባ አስችሎታል። ይህ ለውጥ የትውልዶች የብቃት፣ የተሞክሮና የመስዋዕትነት ቅብብሎሽ ውጤት ሲሆን፣ ለዛሬው ቁመናና ለነገው የላቀ አቅም ጠንካራ መሠረት ሆኗል። ከበዓሉ ዋነኛ ዝግጅቶች መካከል በተቋሙ ታሪካዊ መነሻ በሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ እሁድ ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም የሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር አለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ ይገኝበታል። "አየር ኃይላችን መመኪያችን!" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ይህ ሁለተኛ ዙር አለም አቀፍ 10ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ዓለም አቀፍ አትሌቶችንና የሩጫ አፍቃሪዎችን የሚያሳትፍ ታላቅ ስፖርታዊ ኩነት ሲሆን ለመሮጫ የተዘጋጀው ቲሸርትም በሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በይፋ ተመርቋል። የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በተቋሙና በሕዝቡ መካከል የመተማመንና የመተባበር ግንኙነት ማጠናከር፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ውድ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ክብር መስጠት፣ እንዲሁም ዛሬም የሀገርን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቁ ላሉ የአየር ኃይል አባላት አጋርነት ማሳየት የዝግጅቱ ዋነኛ ዓላማዎች ናቸው። የአየር ኃይል 91 ዓመታት የታሪክ፣ የጀግንነትና የትውልዱ የተሳትፎ ውጤት ናቸው። ይህንኑ ታሪካዊ ሂደት በማክበር፣ የዛሬውን አቅም በማጠናከርና ለነገው ስኬት በመዘጋጀት የተቋሙ ልህቀት ጉዞ ተጠናክሮ ቀጥላል። በመሆኑም ሁሉም የስፖርት አፍቃሪዎች፣ የአየር ኃይል ደጋፊዎችና መላው ሕዝብ ሕዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ በመሳተፍ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ዘብ ለቆመው ተቋም ያላችሁን አክብሮት፣ ፍቅርና ድጋፍ በተግባር የምትገልፁበት መድረክ ተሳታፊ እንደድትሆኑ አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጥሪ አቅርቧል።
Открыть в Telegram📍ሲምሲ(CMC) /አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር/ አጠገብ 🔥🔥35%እና 30%ልዩ ቅናሽ 🔥🔥 (የ3አመት ሳይት) 👉ባለ1መኝታ 73*105,000=7,665,000 ቅድመ ክፍያ 20%=1,533,000 👉ባለ2መኝታ 112*105,000=11,760,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,352,000 👉ባለ3መኝታ 125*105,000=13,125,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,625,000 👉👉👉ለምሳሌ 100%ስትከፍሉ(አንዴ ስትከፍሉ) ባለ1መኝታ 7,665,000ብር የነበረው 5,365,500 ብር ይሆናል 📍አዋሬ ቁጥር 2 40/60አከፋፈል 🔥ስቱዲዮ 42 እና 46 ካሬ 👉42 ካሬ 3.3 ሚሊየን 👉46 ካሬ 3.7 ሚሊየን 👉🏾 👉ባለ 1 መኝታ 80 እና 75 ካሬ 💥የ80ካሬ ➣ ሙሉ ክፍያ 9,200,000 ➣ 100% ክፍያ ለሚከፍል 30% ቅናሽ ሲደረግ ጠቅላላ ክፍያው 6.4 ሚሊዮን ብር ይሆናል። 📍ቡልጋሪያ 🔥ስቲድዮ=40ካሬ 👉ሙሉ ዋጋ=4,600,000 👉ቅድመ ክፍያ 20%=920,000 👉ከዛ የክፍያ አማራጭ በየ ወሩ1%እየከፈሉ 46,000ብር ለ36ወር 👉👉100%ለከፈለ ሙሉዋጋ =3,220,000ይሆናል 🔥1መኝታ=62ካሬ 👉ሙሉ ክፍያ=6,820,000 👉20%ቅድመ ክፍያ=1,364,000 👉1%በየወሩ=68,200(36ወር) 👉100%ለከፈለ ሙሉዋጋ=4,774,000ይሆናል 👉2መኝታ=110&113ካሬ 👉3መኝታ=152ካሬ ለበለጠ መረጃ 09-78-79-13-42 ይደውሉ:: ቴምር ሪል እስቴት የህልምዎ ማረፊያ!
Открыть в Telegramሱዳን ሰላም ይገባታል፤ ሕዝቧ ሕይወትና ክብር ይገባዋል፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም በገዛ ልጆቿ መገንባት አለበት። ኢትዮጵያ እንደ መንግሥትም እንደ ሕዝብም፣ የሱዳንን ደኅንነት፣ መረጋጋትና አንድነት ለመመለስ፣ ውይይትን የሰላም ድልድይ፣ ወንድማማችነትንም የጋራ የወደፊት ዕጣ ፈንታ መሠረት ለማድረግ ከሚደረግ እያንዳንዱ ቅን ጥረት ጎን ትቆማለች። ዐቢይ አሕመድ ዐሊ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኅዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 23፣ 2026
Открыть в Telegramለሁሉም የሱዳን ወገኖች ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመጡ የቀረበ ግልጽ ጥሪ ዐቢይ አሕመድ ዐሊ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያና ሱዳን ከመልክዓ ምድራዊና ፖለቲካዊ ድንበሮች የዘለለ፣ በሰብዓዊ ወንድማማችነት፣ በማኅበራዊና ባህላዊ ትስስር እንዲሁም በተከታታይ ትውልዶች መካከል በተፈጠረ መስተጋብር ላይ የተመሠረተ ጥልቅና ሥር የሰደደ ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። ይህ ግንኙነት በመልካም ፈቃድ፣ በመግባባት፣ በመተባበርና በጋራ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የተገነባ ሲሆን፣ ቀጣናው ያስተናገዳቸውን የተለያዩ ለውጦችና ፈተናዎች ተቋቁሞ ጸንቶ ቆይቷል። ከዚህ ታሪካዊ ቅርስ በመነሣት፣ ኢትዮጵያ እንደ መንግሥትም እንደ ሕዝብም ሱዳንን እንደ ተራ ጎረቤት ሀገር ብቻ ሳይሆን፣ ጥልቅ የፍቅር፣ የታሪክና የአብሮነት ትስስር ያላት ወንድም ሀገርና የተወደደ ሕዝብ አድርጋ ትመለከታለች። በመሆኑም፣ በሱዳን እየተከሰተ ያለው ጦርነት፣ ውድመትና ሰብዓዊ ስቃይ በጎረቤት ሀገር የተፈጠረ ፖለቲካዊ ወይም የጸጥታ ክስተት ብቻ ተደርጎ ሊታይ አይችልም። ይልቁንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕሊና የሚነካ ቁስል ሲሆን፣ በወንድማማችነት፣ በመተባበርና ለሱዳን ሰላም፣ ደኅንነት፣ አንድነትና መረጋጋት ባለን ቅን ቁርጠኝነት ላይ የተመሠረተ ኃላፊነት የተሞላበት አቋም እንድንወስድ የሚጠይቀን ነው። ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትሰጠው ትኩረት ከደኅንነትና ከጋራ ጥቅም ብቻ የሚመነጭ አይደለም። በዋናነት በታሪካዊ የወንድማማችነት ትስስርና የሱዳን ሕዝብ በደኅንነት፣ በሰላምና በክብር የመኖር እንዲሁም የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በነፃነት የመወሰን መብት እንዳለው ባላት ጽኑ እምነት ላይ የተመሠረተ ነው። እ ኤ.አ. ሚያዝያ 15 ቀን 2023 ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንሥቶ፣ ኢትዮጵያ የቀውሱን ሂደት በቅርበት ስትከታተል የቆየች ሲሆን፣ ጦርነቱን ለማስቆምና የሱዳንን አንድነት፣ የግዛት አንድነትና መረጋጋት በሚደግፈው ታሪካዊ አቋሟ መሠረት ለፖለቲካዊ መፍትሔ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ተከታታይ ጥረቶችን አድርጋለች። ይህ አቋም የአሁኑ ጊዜ ውጤት ሳይሆን፣ የሱዳን መረጋጋት ለመላው ቀጣና መረጋጋት የማዕዘን ድንጋይ ነው ብሎ የሚያምነው የኢትዮጵያ አካሄድ ቀጣይነት ነው። ይህ አካሄድ እ.ኤ.አ. በ2019 በግልጽ ታይቷል። ከታኅሣሥ አብዮት በኋላ በሱዳን የሽግግር ወቅት በተፈጠረው ውጥረትና የፖለቲካ መግባባት አለመኖር መካከል፣ ኢትዮጵያ የሲቪልና የወታደራዊ ወገኖችን አቋም ለማቀራረብ ቀዳሚ ተነሣሽነት በመውሰድ ንቁ ሚና ተጫውታለች። በቀጣናዊ ድጋፍና በዓለም አቀፍ ዕውቅና የታገዘው የኢትዮጵያ ጥረት፣ በሽግግር ወታደራዊ ምክር ቤትና በወቅቱ በነፃነትና ለውጥ ኃይሎች በተወከሉት የሲቪል ኃይሎች መካከል ስምምነት እንዲደረስ መንገድ ጠርጓል። ይህም የሱዳን ሕዝብ የሲቪል አስተዳደር እንዲኖረውና በሰላም፣ በፍትሕና በመረጋጋት የተገነባ ሀገር የመመሥረት ሕጋዊ ምኞቱን ለመደገፍ ነበር። የሱዳን ሕዝብ በልጆቹ ሕይወት፣ በደኅንነቱና በመረጋጋቱ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። ሀገሪቱ ሰፊ መፈናቀልና ስደት አስተናግዳለች። መሠረተ ልማቶች፣ የመንግሥት ተቋማትና የሕይወት መሠረቶች ለውድመት ተዳርገዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያንም ስቃያቸውን የሚያስቆምና በደኅንነትና በክብር የመኖር ተፈጥሯዊ መብታቸውን የሚመልስ የተስፋ ጭላንጭል እየጠበቁ ነው። ከዚህ አንጻርና በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅንና እውነተኛ ተነሣሽነት፣ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ሲቪል ኃይሎችን ጨምሮ ሁሉም የሱዳን ወገኖች ኢትዮጵያ በምታዘጋጀውና በምትደግፈው ሁሉን አካታችና ግልጽ የሱዳናውያን ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ያቀርባል። የዚህ ጥሪ ዓላማ ለቁም ነገር ውይይት ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ጦርነቱን ማስቆም፣ ግጭትንና መከፋፈልን ማስወገድ፣ እንዲሁም ለዘላቂና ሁሉን አቀፍ ሰላም መሠረት የሚሆን ሀገራዊ መግባባት ላይ መድረስ ነው። ኢትዮጵያ ይህ ተነሣሽነት ከተለየ ፖለቲካዊ አጀንዳ የመነጨ ወይም በማንኛውም የሱዳን ወገን ጉዳት ላይ የተመሠረተ ጥቅም ለማግኘት የታሰበ እንዳልሆነ አጽንዖት ትሰጣለች። ይልቁንም ለሱዳን ምድርና ሕዝብ ካላት እውነተኛ አሳቢነት፣ የጦርነቱ መቀጠል ማንንም እንደማይጠቅምና እውነተኛው አሸናፊ ሱዳንና ሕዝቧ መሆን እንዳለባቸው ካላት ጽኑ እምነት የመነጨ ነው። ግጭቱ ከቀጠለ ትልቁን ኪሳራ የሚሸከመው የሱዳን ሀገር፣ ተቋማቷ፣ ታሪኳ፣ ብዝኃነቷና የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ ነው። ኢትዮጵያ ይህንን ተነሣሽነት ስታቀርብ፣ ሁሉንም ወገኖች በእኩልነት ለማስተናገድና በግልጽነት፣ በቁም ነገርና በጋራ መከባበር ላይ የተመሠረተ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ታረጋግጣለች። ከውጭ የሚጫኑ መፍትሔዎች ዘላቂ ሰላም ሊያሰፍኑ እንደማይችሉ ባላት እምነት፣ ኢትዮጵያ የሱዳን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሱዳናውያን ብቻ መወሰን እንዳለበት አጽንዖት ትሰጣለች። የሱዳናውያን ውይይት ቀውሱን ለማስወገድና የሕዝቡን ክብር፣ የሀገሪቱን አንድነትና ብዝኃነት የሚጠብቅ፣ የሀገርን ጥቅም ከሁሉም በላይ የሚያስቀምጥ አዲስ ሀገራዊ ቃል ኪዳን ለመቅረጽ የሚያስችል ዋነኛ መንገድ ነው። ዓላማው አንዱ ወገን ሌላውን ማሸነፉ ሳይሆን፣ ሱዳን ማሸነፏ፣ መንግሥታዊ ሥርዓቷ መልሶ መቋቋሙ፣ ደም መፋሰሱ ማቆሙና ሁሉንም ልጆቿን ለሚያቅፍ የወደፊት ዘመን መንገድ መክፈት ነው። በዚህ አውድ፣ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ ወንድምና ወዳጅ ሀገራት፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ለሰላም ያለውን ሕጋዊ ምኞት እንዲደግፉ፣ የተጎጂዎችን፣ የተፈናቃዮችንና የስደተኞችን ስቃይ ለማቃለል ሰብዓዊ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ታቀርባለች። እንዲሁም የግጭቱን ዕድሜ ሊያራዝሙ ከሚችሉ ጠባብ የጥቅም ስሌቶች በመራቅ፣ ጦርነቱን ለማስቆምና ቀውሱን ለማስወገድ የሚደረጉ ቁም ነገር ያላቸውን ጥረቶች ሁሉ እንዲደግፉ ትጠይቃለች። ኢትዮጵያ ለዚህ ተነሣሽነት ስኬት ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶቿን፣ ዲፕሎማሲያዊ አቅሟንና ከሚመለከታቸው አጋሮች ጋር ያላትን ትብብር ለመጠቀም ዝግጁ መሆኗን ታረጋግጣለች። የሱዳን ወገኖች በድርድር ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው የሱዳንንና የሕዝቧን ጥቅም የሚያስጠብቅ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግም ዝግጁ ናት። የሱዳን ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም ነው፤ የሱዳን ደኅንነት የኢትዮጵያ ደኅንነት ነው፤ የሱዳን መረጋጋትም የአፍሪካ ቀንድና የአካባቢው ቀጣና መረጋጋት የማዕዘን ድንጋይ ነው። በመሆኑም፣ ይህ ጥሪ ፖለቲካዊ ተነሣሽነት ብቻ ሳይሆን፣ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ጥልቅ ትስስር የሚያንጸባርቅ ቅን የወንድማማችነትና ሰብዓዊነት ጥሪ ነው። ኢትዮጵያ በፈተና ወቅት ከሱዳናውያን ወንድሞቿ ጎን መቆሟንና ሁለቱን ሕዝቦች የሚያስተሳስራቸው ነገር ከሚለያያቸው እንደሚበልጥ ያላትን እምነት የሚገልጽ ነው። እውነተኛ ጉርብትናም የሚገለጠው ከደስታ ጊዜ በፊት በችግር ወቅት ነው። ሁሉም የሱዳን ወገኖች በሀገራዊ ኃላፊነት ስሜትና የሱዳንን የበላይ ጥቅም በማስቀደም ለዚህ ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ እንጠብቃለን። ቅን ፍላጎቶች በሚገናኙበት ጊዜ ሱዳናውያን ልዩነቶቻቸውን ማሸነፍ እንደሚችሉ እናምናለን። ወደ ሰላም የሚወስዱት መንገዶች ምንም ያህል የተወሳሰቡ ቢሆኑ፣ የሀገር ጥቅም ከግጭት በላይ ቅድሚያ ሲሰጠው ሰላም ማስፈን ይቻላል።
Открыть в Telegramየኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል “በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ የኢትዮጵያ ሰማይ አለኝታ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል - ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ 🇪🇹✈️ በዓሉ ህዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም ዓለም አቀፍ አትሌቶች በሚሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ እንደሚከበር፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ 91ኛውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። 👉 ሁሉም ኢትዮጵያውያን በቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ እና በሌሎች ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
Открыть в Telegram📍ሲምሲ(CMC) /አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር/ አጠገብ 🔥🔥35%እና 30%ልዩ ቅናሽ 🔥🔥 (የ3አመት ሳይት) 👉ባለ1መኝታ 73*105,000=7,665,000 ቅድመ ክፍያ 20%=1,533,000 👉ባለ2መኝታ 112*105,000=11,760,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,352,000 👉ባለ3መኝታ 125*105,000=13,125,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,625,000 👉👉👉ለምሳሌ 100%ስትከፍሉ(አንዴ ስትከፍሉ) ባለ1መኝታ 7,665,000ብር የነበረው 5,365,500 ብር ይሆናል 📍አዋሬ ቁጥር 2 40/60አከፋፈል 🔥ስቱዲዮ 42 እና 46 ካሬ 👉42 ካሬ 3.3 ሚሊየን 👉46 ካሬ 3.7 ሚሊየን 👉🏾 👉ባለ 1 መኝታ 80 እና 75 ካሬ 💥የ80ካሬ ➣ ሙሉ ክፍያ 9,200,000 ➣ 100% ክፍያ ለሚከፍል 30% ቅናሽ ሲደረግ ጠቅላላ ክፍያው 6.4 ሚሊዮን ብር ይሆናል። 📍ቡልጋሪያ 🔥ስቲድዮ=40ካሬ 👉ሙሉ ዋጋ=4,600,000 👉ቅድመ ክፍያ 20%=920,000 👉ከዛ የክፍያ አማራጭ በየ ወሩ1%እየከፈሉ 46,000ብር ለ36ወር 👉👉100%ለከፈለ ሙሉዋጋ =3,220,000ይሆናል 🔥1መኝታ=62ካሬ 👉ሙሉ ክፍያ=6,820,000 👉20%ቅድመ ክፍያ=1,364,000 👉1%በየወሩ=68,200(36ወር) 👉100%ለከፈለ ሙሉዋጋ=4,774,000ይሆናል 👉2መኝታ=110&113ካሬ 👉3መኝታ=152ካሬ ለበለጠ መረጃ 09-78-79-13-42 ይደውሉ:: ቴምር ሪል እስቴት የህልምዎ ማረፊያ!
Открыть в Telegramበመቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች መካከል 12ቱ ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደረገ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ከሚገኙ 15 የነዳጅ ማደያዎች መካከል 12ቱ ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጋቸውን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋይ ግርማይ ገልጸዋል። በመቐለ ከተማ 750 የሕዝብ ታክሲዎች እንዳሉ የገለጹት ኃላፊው፣ ታክሲዎቹ ቅድሚያ የነዳጅ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉን ጠቁመዋል። የተደረጉት እርምጃዎች በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት እና የነዳጅ ሥርጭት አገልግሎት እንዲቀጥል ያለመ መሆኑን አመላክተዋል። የነዳጅ ሽያጩ በቴሌ ብር ዲጂታል ግብይት ብቻ እንዲደረግ መመሪያ ወርዶ ተፈፃሚ እየሆነ ሲሆን፣ ይህም የመጣው ነዳጅ በትክክል ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋሉን ለማወቅና ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ተገልጿል። በቀጣይም የነዳጅ አቅርቦት ላይ መቆራረጥና እጥረት እንዳይከሰት ከፌዴራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል።
Открыть в Telegram✨አንጋፋው ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት 🏠 በተግባር ከተረጋገጠ ታማኝነት፣ ከበፊቱ በበለጠ ኃይል፣ በአዲስ ራዕይ እና ዘመናዊነትን በጠበቀ አቅም በጎተራ ፕሮጀክት ዳግም ተመልሷል። ✨ከዚህ በፊት ሁለት ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ አስረክቧል :: 🫵የኑሮ ደረጃዎን በጎተራ ያሳድጉ – ዘነበ ፍረው ሪል እስቴት🫵 ✨እንደ Addis tomorrow ልዩ የEconomy zone, Mehamedian village ባሉ ቦታዎች የተከበበ ከ10 % ቅድመ ክፍያ ጀምሮ፤ 👉በካሬ ከ105,500 ብር ጀምሮ 👉በ3 አመት የሚረከቧቸው አማራጮች 👉የንግድ ሱቆች ከ 16 ካሬ -300 ካሬ በ net Area እየሸጥን እንገኛለን ✨ስቱዲዮ (66 ካሬ ): ✨1 መኝታ(83 ካሬ): ✨2 መኝታ(122 ካሬ): ✨3 መኝታ(168 ካሬ) ✨ምርጥ የከተማዋን እይታ ያላቸውን ክፍሎች ቅድሚያ በመምረጥ ቤትዎን አሁኑኑ ያስይዙ! ✨ለበለጠ መረጃ፣ ለቢሮ ቀጠሮ፣ ሳይት ለመጎብኘት ይደውሉ ☎️0912355631
Открыть в Telegramየአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ በመቅሰም የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በልማት ዘርፎች ማስፋፋት አለባቸው፡- የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ***************** ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ዕድገትና የቴክኖሎጂውን በተግባር ላይ የማዋል ጥረት እንዳስደነቃቸው የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄሲካ አሉፖ ገለጹ። ምክትል ፕሬዚዳንቷ ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል። በኢንስቲትዩቱ የተመለከቷቸው የሰው ሠራሽ አስተውሎት አተገባበር ፕሮግራሞች እጅግ እንዳስደነቋቸው ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂውን በትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም በተግባራዊ አገልግሎቶች ላይ በፍጥነት እያስፋፋች መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ ተሞክሮ በመቅሰም የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በትምህርት ተቋማት እና በተግባራዊ የልማት ዘርፎች ማስፋፋት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዩጋንዳ በአሁኑ ወቅት የሰው ሠራሽ አስተውሎትን ለመተግበር የሚያስችል ፖሊሲና ሕጋዊ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ መሆኗን ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያ ተሞክሮ በግብርና፣ በጤና፣ በሳይንስና በመንግሥት አገልግሎት ዘርፎች ቴክኖሎጂውን ለመተግበር ያላቸውን ጥረት እንደሚያፋጥን ተናግረዋል። አፍሪካውያን ተሞክሮዎቻቸውን፣ ፈጠራዎቻቸውን እና የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን መጋራት እንዳለባቸው ያስገነዘቡት ምክትል ፕሬዚዳንቷ፣ ሌሎች ሀገራትም ወደ ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ቡድኖቻቸውን በመላክ ከባለሙያዎቹ ጋር እንዲማሩና ተሞክሮውን ወደየሀገራቸው እንዲያሸጋግሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሰው ኃይልን በመደገፍ ለሕዝብ ያሉ ችግሮችን በፍጥነትና በብቃት ለመፍታት ወሳኝ መሣሪያ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
Открыть в Telegram