የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶችን በጀርሞች መላመድ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ⚫ "ከ20 እና 30 ዓመታት በኋላ ለልጅ ልጆቻችን መድኃኒት ላናገኝ እንችላለን" የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶችን በጀርሞች መላመድ በፍጥነት እየተስፋፋና አዳዲስ መድኃኒቶችን የማምረት ሂደት በሚፈለገው ልክ እያደገ ባለመሆኑ፣ የወደፊቱ ትውልድ ቀላል የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን እንኳን የሚያድን መድኃኒት ሊያጣ እንደሚችል ተጠቆመ። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የክሊኒካል ፋርማሲ ረዳት ፕሮፌሰር አበበ ዘለቀ እንደሚሉት፣ አሁን ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉ ፈዋሽ መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ ምክንያት ከገበያ ውጪ እየሆኑ መጥተዋል። ከ10 እስከ 15 ዓመታት በፊት ለባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች በስፋት ይውል የነበረው 'ቴትራሳይክሊን' አሁን በሽታዎችን ማከም ባለመቻሉ ከገበያ ውጪ መሆኑን ያስታወሱት ባለሙያው፣ የአሁኖቹ መድኃኒቶችም በተመሳሳይ ጊዜ ከገበያ ውጪ እንደሚሆኑ ያስረዳሉ። ችግሩ በሰው ሕክምና ብቻ የተገደበ ሳይሆን በእንስሳት እርባታና በንጽህና ጉድለትም ይባባሳል ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር አበበ ያስረዳሉ። "ዶሮ አርቢዎች የዶሮ መድኃኒት ሲጠፋባቸው የሰውን መድኃኒት ይጠቀማሉ። አሁን ዶክሲሳይክሊን (Doxycycline) የሚባል መድኃኒት አለ፤ እኛ አሁን በህክምና እየተጠቀምነው ያለ ነው። እነሱ ያንን መድኃኒት ለዶሮዎቹ ይሰጣሉ። ስለዚህ በዶሮው ውስጥ ያለው ባክቴሪያ መድኃኒቱን ይለማመደዋል፤ ከዚያም ያ የተለማመደ ባክቴሪያ ከዶሮው ወደ ሰው ሊመጣ ይችላል ማለት ነው" ብለዋል። በጤና ሚኒስቴር የመድኃኒትና የአቅርቦት ሰንሰለት ልዩ አማካሪ ዶክተር ዱመሳ ዳሳ በበኩላቸው፣ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የፀረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶችን የሚሸጡ ፋርማሲዎች እንደ ጥፋታቸው ደረጃ ድርጅታቸውን ለተወሰነ ጊዜ ከማሸግ አንስቶ እስከ ፈቃድ መሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚጠብቃቸው አመላክተዋል። በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በኩል የሚከለክል መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ቢሆንም፣ በሰው ኃይል፣ በፋይናንስና በአቅም ውስንነት ምክንያት የቁጥጥር ሥራው በሁሉም ቦታ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ አለመሆኑን ጠቁመዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም ከዚህ ቀደም በነበረው የጤና ፖሊሲ ላይ ያልነበረውን የፀረ-ተህዋሲያን መላመድ መከላከል ጉዳይ ያካተተ አዲስ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡንና የመጨረሻ የማጽደቅ (Final Endorsement) ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በገጠር አካባቢዎች ወደ ስምንት በመቶ የሚሆነው ማህበረሰብ መድኃኒቶችን ከትንንሽ ሱቆች እና መደበኛ ካልሆኑ ገበያዎች እንደሚገዛ የጠቆሙት ዶክተር ዱመሳ፣ በእነዚህ ሱቆች የሚሸጡት መድኃኒቶች ጊዜያቸው ያለፈባቸውና መጠናቸው አነስተኛ በመሆኑ ጀርሙን ከመግደል ይልቅ መድኃኒቱን እንዲላመደው በማድረግ ድርብ ጫና እንደሚያሳድሩ አብራርተዋል። በግል ክሊኒኮች ያለው የላቦራቶሪ ምርመራ እጥረት፣ በግምት ጠንካራ መድኃኒቶችን የማዘዝ ልማድ፣ የሕክምና ጊዜ ሳይጨርሱ ማቋረጥና ኮንትሮባንድ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውም ተነስቷል። እ.ኤ.አ. በ2021 በወጣ ዓለም አቀፍ ጥናት መሠረት በየዓመቱ ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከፀረ-ተህዋሲያን መላመድ ጋር በተያያዘ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ በኢትዮጵያም በየዓመቱ ወደ 85 ሺህ 300 የሚጠጉ ሰዎች በዚሁ ችግር ይሞታሉ። ሆኖም አሁን ባለው የላቦራቶሪ መሠረተ ልማት እጥረት ምክንያት በሀገሪቱ «ንቁ የቅኝት ሥራ» ስለማይከናወን ትክክለኛው የሞት ቁጥር ከዚህ በእጅጉ ሊበልጥ እንደሚችል ዶክተር ዱመሳ አስጠንቅቀዋል። ያደጉ ሀገራት ከኢንፌክሽን ጫና መውጣታቸውንና በኢትዮጵያ ግን ተላላፊ በሽታዎች አሁንም ዋነኛ ገዳዮች መሆናቸውን ጠቁመው፣ የመድኃኒት መላመድ ሲታከልበት ጫናው ይበልጥ ከባድ ይሆናል። ችግሩ ካልተገታ እ.ኤ.አ. እስከ 2050 ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ 39 ሚሊዮን ሰዎችን ለሞት ሊዳርግና የጤና ወጪን በአንድ ትሪሊዮን ዶላር ሊያሳድግ እንደሚችል ይጠበቃል። ኢትዮጵያም ይህንን ስጋት ለመቀልበስ ከ2026 እስከ 2030 የሚቆይ አራተኛ ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ቀርጻ እየሰራች ሲሆን፣ በሰው ጤና ዘርፍ 42 እንዲሁም በእንስሳት ጤና 41 የቅኝት ጣቢያዎችን አቋቁማ ወደ ሥራ ገብታለች ተብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Открыть в Telegram
TIKVAH-MAGAZINE
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። በ +251913134524 ላይ ያግኙን። ለማስታወቂያ @tikvahmagbot ላይ መረጃ ይጠይቁ።
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 17 нояб. 2026 г. | 25 200 |
| 23 нояб. 2026 г. | 15 400 |
| 24 нояб. 2026 г. | 12 100 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры36,2 тыс.Пересылки—Реакции131Комментарии—
- 02Просмотры28,5 тыс.Пересылки—Реакции61Комментарии—
- 03Просмотры18,3 тыс.Пересылки—Реакции17Комментарии—
- 04Просмотры17,8 тыс.Пересылки—Реакции12Комментарии—
Новые посты
የአላቂ ዕቃዎች እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኗል! ⚫"በሚያሳዝን ይሄታ ህጻናት ወረፋቸው ደርሶ ለህክምና ይምጡ ስንል ሕይወታቸው አልፏል የሚባልበት ሁኔታዎች አሉ" - ዶ/ር ዳዊት እሸቱ በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል በአሁኑ ወቅት ከ8 ሺህ በላይ የሚሆኑ የልብ ሕሙማን ሕፃናት የቀዶ ጥገና ሕክምና ወረፋ እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ማዕከሉ አስታወቀ። ማዕከሉ በዓመት እስከ 1 ሺህ 500 ታካሚዎችን የማስተናገድ አቅም ቢኖረውም፣ በገጠመው የአላቂ ዕቃዎች እጥረት ምክንያት በዓመት 700 የቀዶ ጥገና ሕክምናዎችን ብቻ እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል። የማዕከሉ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ዳዊት እሸቱ እንደገለጹት፣ ለሕክምናው የሚያስፈልጉ እስከ 80 በመቶ የሚሆኑ አላቂ ዕቃዎች በሀገር ውስጥ ስለማይገኙ በግዢ ከውጭ የሚመጡ ናቸው። "የእነዚህ አላቂ ዕቃዎች እጥረት ትልቅ ፈተና ሆኖብን ነው ያለው" ያሉት ዶክተር ዳዊት፣ የወረፋው መብዛት በታካሚዎች ሕይወት ላይ ከባድ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አስረድተዋል። "በሚያሳዝን ሁኔታ ሕፃናት ወረፋቸው ደርሶ ለሕክምና ይምጡ ስንል ሕይወታቸው አልፏል የሚባልበት ሁኔታዎች አሉ፤ ይህ የሚያሳየው የችግሩን ደረጃ እና ፈተናው ምን ያህል እንደሆነ ነው" ሲሉ ነው የገለጹት። ይህንን ጫና ለመቀነስም ከዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ለሕፃናት ስፔሻሊስቶች የልብ አልትራሳውንድ ስልጠና በመስጠት ሕመሙን ቀድሞ የመለየት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። የማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኅሩይ ዓሊ በበኩላቸው፣ በቀላል ሕክምና መዳን የሚችሉ ሕፃናት በግንዛቤ እጥረት ምክንያት ለከፋ ጉዳት እየተዳረጉ መሆኑን አንስተዋል። ችግሩን በዘላቂነት ለመቀነስም በከተሞችና በገጠር ክሊኒኮች የጤና አጠባበቅ ትምህርት ቢሰራጭና ወላጆች ሕፃናቱ መውሰድ ያለባቸውን መድኃኒት እንዲያውቁ ቢደረግ ወረፋ የሚጠባበቁት ሕፃናት ቁጥር እየቀነሰ እንደሚሄድ ነው የገለጹት። ማዕከሉ ለታካሚ ሕፃናት የሚሰጠው የቀዶ ጥገና አገልግሎት አንድም ሳንቲም ሳይጠየቅ ሙሉ በሙሉ በነፃ የሚከናወን መሆኑን ያስታወቁት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ "በአማካይ ለአንድ የልብ ሕሙማን ሕፃን እስከ ስድስት መቶ ሺህ ብር ድረስ ያስፈልጋል፣ የቀዶ ጥገናውን ወጪ ጭምር፤ ይህን ሁሉ ወጪ ሙሉ በሙሉ በነፃ ነው የምንሰራው" ብለዋል። በዓመት 1 ሺህ 500 ሕፃናት ሲታከሙ የሚወጣው ወጪ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ ኅሩይ፣ በሀገር ውስጥ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ብቃት አስተማማኝ ደረጃ ላይ በመድረሱ "የውጭ ባለሙያ አያስፈልገንም፣ የሀገራችን ባለሙያ ጠንክሯል ብለን እናስባለን" ሲሉ አረጋግጠዋል። በቅርቡ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ቢያንስ 25 ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና እንዲያገኙ የሚያስችሉ የሕክምና ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጓ ተገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Открыть в Telegramየጥንት የጠዋቱ ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት በአዲስ መልክ ጎተራ ላይ ከ Addis Tomorrow economic zone ኘሮጀክት ፊትለፊት በ 7000 ካሬ ላይ የሚገነባ G+25 የሆነ ኘሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል! ይህ ኘሮጀክት በውስጡ ቤቶች ከስቱዲዮ እስከ ባለ 3 መኝታ ያካተተ ሲሆን :- ስቱዲዮ 66 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 6,303,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 630,300 ብር 100% ለሚከፍል - 4,727,250 ብር ባለ 1 መኝታ 83 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 7,926,500 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 792,650 ብር 100% ለሚከፍል - 5,944,875 ብር ባለ 2 መኝታ 122 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 11,651,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 1,165,100 ብር 100% ለሚከፍል - 8,738,250 ብር ባለ 3 መኝታ 168 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 16,044,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 1,604,400 ብር 100% ለሚከፍል - 12,033,000 ብር ፕሮጀክቱ ለኑሮ ምቹ የሆነ በርከት ያሉ መገልገያዎች የያዙ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ እና በአካል ለመጎብኘት በ 0906926956 ይደውሉልን! ቴሌግራም:- @Realeastateaddis
Открыть в Telegramየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጸጥታ ስጋት ለተፈተኑ ነጋዴዎች የሐይቅ ላይ ትራንስፖርትን እንደ አማራጭ እንዲመለከቱ እየሰራሁ ነው አለ። በጸጥታ ስጋት ምክንያት በመንገድ መዘጋጋት ለተፈተኑት የቡርጂና አማሮ ማህበረሰብ ነጋዴዎች፣ የሐይቅ ላይ የጭነት ጀልባ ትራንስፖርት እንደ አማራጭ መፍትሄ እንዲመለከቱት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ምክር ቤቱ ከኤምሬትስ ሆሊዴይስ ጋር ዓለም አቀፍ የንግድና ቱሪዝም ትብብር የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረመበት ወቅት ነው። በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው የጸጥታና የመንገድ መዘጋጋት ችግር በንግዱ እንቅስቃሴ ላይ እያሳደረ ስላለው ተጽዕኖ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ቦጋለ ቢታኔ፣ በቡርጂና አማሮ አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ አውጥተው መሸጥ ተስኗቸው ረጅም አቋራጭ መንገዶችን ለመጠቀም መገደዳቸውን አንስተዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍም በሐይቅ ላይ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት እንደ አማራጭ መፍትሄ እንዲጠቀሙ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ፕረዚዳንቱ፥ በቅርቡ በአርባ ምንጭ አካባቢ የጋሞ ልማት ማህበር ጀልባ ማስገባቱን አንስተዋል። ኢንጂነር ቦጋለ፣ ሌሎች ነጋዴዎችም ተደራጅተው የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ጀልባዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የንግዱን ማህበረሰብ ችግር እንዲፈቱ ምክር ቤቱ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። አክለውም የጸጥታውን ችግር ነጋዴው ብቻውን ሊፈታው ስለማይችል ከመንግሥትና ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ችግሩን ለመቅረፍ በየመዋቅሩ የሚገኙ የንግድ ምክር ቤቶች በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ከኤምሬትስ ሆሊዴይስ ጋር የተፈራረመው ስምምነት ከ128 ሺህ በላይ የሚሆኑ የምክር ቤቱ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለውን የንግድና የቱሪዝም ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው። ስምምነቱ በዱባይና በኤምሬትስ አየር መንገድ መዳረሻዎች ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖችንና ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት የክልሉን ምርቶች ለማስተዋወቅ እንዲሁም ነጋዴዎች ወደ ውጭ ለሚያደርጉት ጉዞ ልዩ የዋጋ ቅናሽ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ክልሉ ቅመማ ቅመም፣ የቁም እንስሳት፣ ሰሊጥና ቡናን ጨምሮ በርካታ ምርቶችን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቢልክም በክልሉ ነጋዴዎች በኩል በቀጥታ የሚላከው አነስተኛ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ በአካባቢው የሚታየውን የአስመጪ እጥረትና የደረሰኝ አሰጣጥ ችግር ለመፍታት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ስምምነቱ ደላላን በማስቀረት የክልሉን ላኪዎች ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ እንደሚያገናኝና ባለሀብቶች ከአዲስ አበባ በቀጥታ ወደ አርባ ምንጭ እንዲመጡ እንደሚያስችልም ተመላክቷል። የኤምሬትስ ሆሊዴይስ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ማናጀር ማይታ አልቡቴሂ በበኩላቸው፣ አጋርነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የቱሪዝምና የንግድ ልውውጥ ለማስፋት ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸው፣ ኩባንያቸው ባሉት የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አማካኝነት የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለዓለም ለማስተዋወቅ አስቀድሞ ስምምነት መፈጸሙን አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ ከተመሠረተ ሁለት ዓመት ቢሆነውም ወደ ኢንዶኔዥያ፣ ቱርክ፣ ቻይና እና ቤልጂየም የንግድ ልዑካንን በመላክ ስምንት የክልሉ ነጋዴዎች የአስመጪና ላኪነት ፈቃድ እንዲያወጡና የሞሪንጋ ምርቶችን ወደ ቱርክ በብቸኝነት የሚያቀርብ ወኪል እንዲፈጠር ማስቻሉ ተገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Открыть в Telegramብሪቲሽ-ጋናዊው ድምፃዊ ፊውዝ ኦዲጂ (Fuse ODG) በኢትዮጵያ ቆይታው ዩኒቲ ፓርክን ጎበኘ በመድረክ ስሙ «ፊውዝ ኦዲጂ» (Fuse ODG) በመባል የሚታወቀው ብሪቲሽ-ጋናዊ ድምፃዊ እና የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ናና ሪቻርድ አቢዮና፣ በኢትዮጵያ እያደረገ ባለው ጉብኝት የዩኒቲ ፓርክን ጎብኝቷል። ድምፃዊው በፓርኩ በነበረው ቆይታ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች፣ ባህላዊ እሴቶች እና የቀድሞ ነገሥታትን ታሪክ የሚያሳዩ ክፍሎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። ድምፃዊው ከሙዚቃ ሥራዎቹ ባሻገር በጠንካራ የፓን-አፍሪካኒዝም አቋሙ የሚታወቅ ሲሆን፣ «ዚስ ኢዝ ኒው አፍሪካ» (This Is New Africa - TINA) የተሰኘውን ንቅናቄ በማጉላት አፍሪካ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በድህነት እና በችግር ብቻ የምትሳልበትን ትርክት ለመቀየር የተለያዩ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። #VisitEthiopia #Pan_Africanism #Ethiopia
Открыть в Telegramቢፒኦ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአዲስ አበባ ለሚገነባው ግዙፍ የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ (ቢፒኦ) ማዕከል ዋና ኦፕሬተር እንዲሆን ከሲሲአይ ግሎባል (CCI Global) ጋር ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል። ለመሆኑ ቢፒኦ (BPO) ምንድን ነው? ቢፒኦ (Business Process Outsourcing) አንድ ኩባንያ የራሱን የሥራ ክፍል ወይም አገልግሎት ለሌላ ድርጅት በውል የሚሰጥበት ዓለም አቀፍ የንግድ አሠራር ነው። ቀላሉ ምሳሌ የደንበኛ አገልግሎት ሲሆን፣ አንድ የውጭ ኩባንያ ደንበኞቹ የሚደውሉለትን የጥያቄና የቅሬታ መስመር በራሱ ሀገር ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ከሚያስተናግድ ይልቅ አዲስ አበባ ላለ ድርጅት በውል ይሰጣል። አዲስ አበባ ያሉ ሠራተኞች ደንበኞችን በስልክ፣ በውይይት መስኮት ወይም በኢሜይል ሲያስተናግዱ የውጭው ኩባንያ ለአገልግሎቱ ክፍያ ይፈጽማል። ይህ አሠራር ለውጭ ኩባንያዎች የሥራ ማስኬጃ ወጪን ሲቀንስ፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ገቢንና ለወጣት ምሩቃን ሰፊ የሥራ ዕድል ያስገኛል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢፒኦ በደንበኞች አገልግሎት፤ በአስተዳደር ሥራ ወይም በዲጂታል መሰረተ ልማት ላይ ያተኮረ ነው። ይህ አሠራር በኢትዮጵያ ገና በጅምር ደረጃ ላይ ቢሆንም፣ አንዳንድ ሀገር በቀል ኩባንያዎች በተለያየ መንገድ በዚህ ሥራ ተሳታፊ ሆነው ቆይተዋል። በዚህም በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ለሌለው ማክዶናልድስ እንዲሁም ለሃይኔከንና ጊሊያድ የደንበኛ አገልግሎት ጥሪዎችን በማስተናገድ የሚሰሩ የግል ተቋማት በኢትዮጵያ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ኢትዮጵያ በ26 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት እየገነባችው ያለው ዘመናዊ ህንጻ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል። ይህንን ግንባታው ያልተጠናቀቀ ህንጻ CCI Global ለ10 ዓመታት ለመከራየት መስማማቱ፣ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና በመንግሥት ድጋፍ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። አዲሱ ኦፕሬተር ሲሲአይ ግሎባል በደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በስፋት የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከ80 በላይ ከሚሆኑ ዓለም አቀፍ ትላልቅ ተቋማት ጋር የሚሰራ ድርጅት ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ አውትሶርሲንግ ማኅበር መረጃ እንደሚያሳየው በሀገሪቱ በዘርፉ የተመዘገቡ 25 ኩባንያዎች የሚገኙ ሲሆን፣ እንደ አፕዎርክ (Upwork) ባሉ መድረኮች በርቀት የሚሠሩ ፍሪላንሰሮችን ጨምሮ ዘርፉ ወደ 15,000 ሠራተኞች ያስተዳድራል፤ ገቢውም በ2025 ወደ 50 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል። አዲሱ ማዕከል ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የዘርፉን የሰው ኃይል በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ቢታመንም፣ ኢትዮጵያ ከሌሎች የዘርፉ ተዋናይ ሀገራት አንጻር ገና በጅምር ደረጃ ላይ ትገኛለች። ለአብነት ያህል ኬንያ በዓመት ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር፣ ግብጽ 5.2 ቢሊዮን ዶላር፣ ፊሊፒንስ 40 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ሕንድ በቢፒኦ ዘርፍ ብቻ 59 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ያገኛሉ። ኢትዮጵያ ወደዚህ ገበያ በስፋት እየገባች ያለችው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፉ የቢፒኦ ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ባለበት ወቅት ነው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Открыть в Telegram"በቅርቡ በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተገኘውን የፖሊዮ ቫይረስ ምላሽ ለመስጠት የተቀናጀ የክትባት ዘመቻ ተዘጋጅቷል" - ዶ/ር ክንፉ መንዙራ ⚫ ከ11 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል። በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የፖሊዮ ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ፣ በአምስት አካባቢዎች የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታወቀ። በኢንስቲትዩቱ የጤና ባለሙያና የመስክ ኤፒዲሚዮሎጂስት ዶ/ር ክንፉ መንዙራ እንደተናገሩት፥ በዘመቻው እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህጻናት ክትባቱን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። ቫይረሱ በቅኝት ሥራዎች አማካኝነት መገኘቱን የገለጹት ዶክተር ክንፉ፣ ዘመቻው የተዘጋጀው ለዚህ ምላሽ ለመስጠት መሆኑን አስረድተዋል። "የቅኝት ሥራዎች ይሰራሉ፤ እሱን መሠረት በማድረግ የፖሊዮ ቫይረስ ተገኝቷል ማለት ነው" ያሉት ዶክተር ክንፉ፣ "በቅርቡ እነዚህ የተገኙት የፖሊዮ ቫይረስ በተለይ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል ውስጥ የተገኙትን ምላሽ ለመስጠት የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ተዘጋጅቷል" ብለዋል። ቫይረሱ የት እና ስንት ኬዞች ተገኙ? በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል በክትባት የምንከላከላቸው በሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ባለሙያ አቶ መስፍን ከፋ፣ በቅርቡ በተደረገ የቅኝትና የላቦራቶሪ ምርመራ በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በድምሩ ሦስት የፖሊዮ ኬዞች ተገኝተዋል ብለዋል። 📍 በኦሮሚያ ክልል፦ በቀድሞው ምዕራብ ሸዋ ዞን በአሁኑ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን አምቦ አካባቢ አንድ ኬዝ ተገኝቷል። 📍 በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፦ በጋርዱላ ዞን አንድ እንዲሁም በጎፋ ዞን አንድ፤ በድምሩ ሁለት ኬዞች ተገኝተዋል። በአጠቃላይ በዓመቱ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘጠኝ የፖሊዮ ኬዞች መመዝገባቸውን የጠቆሙት አቶ መስፍን፣ ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ክልል እና በምዕራብ ኦሮሚያ (ወለጋ) አካባቢዎች ተገኝተው ለነበሩ ኬዞች የክትባት ምላሽ መሰጠቱን አስታውሰዋል። "ኬዝ ካልተገኘ ምንም አይነት ካምፔን (ዘመቻ) አናደርግም፤ መደበኛ ክትባቱ ይቀጥላል። ኬዝ ሲኖር ግን ማጠናከሪያ ክትባቱን ለልጆች መስጠት ስለሚያስፈልግ ለዛ ነው ይህንን ዘመቻ ያስፈለገው" ሲሉ አቶ መስፍን አስረድተዋል። በሽታው ምን ያህል አደገኛ ነው? ፖሊዮ በቀላሉ የሚተላለፍ እና የማይመለስ የአካል ጉዳት የሚያስከትል አደገኛ በሽታ መሆኑን አቶ መስፍን አስረድተዋል። "መጀመሪያ ላይ ልክ እንደ ጉንፋን አይነት መሰል ምልክት ይኖረዋል፤ ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ መሰል ነገር ይኖረውና እጅን እና እግርን ለቋሚ የአካል ጉዳት የሚያደርገው በሰዓታት ውስጥ ነው፤ በሦስት ቀን ውስጥ አንድ ልጅ ሙሉ ሽባ ይሆናል" ያሉት አቶ መስፍን፣ "ምንም አይነት ሕክምና ብንሰጥ አንመልሰውም" ሲሉ የበሽታውን አስከፊነት ገልጸዋል። ቫይረሱ በሰገራ አማካኝነት ውሃንና አካባቢን በመበከል ከአንድ ልጅ ወደ ሌላ ልጅ በፍጥነት እንደሚተላለፍ የጠቆሙት ባለሙያው፣ ከተያዙ 200 ህጻናት መካከል አንዱ ለቋሚ የአካል ጉዳት እንደሚዳረግ ተናግረዋል። ክትባቱ የት እና ለእነማን ይሰጣል? በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች እስካሁን የተረጋገጠ ኬዝ ባይኖርም፣ ቫይረሱ ከተገኘባቸው አካባቢዎች ጋር ባላቸው ቅርበትና የሕዝብ እንቅስቃሴ ምክንያት በሽታው እንዳይዛመት ለመከላከል በዘመቻው እንዲካተቱ መደረጉን አቶ መስፍን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት የተቀናጀው የክትባት ዘመቻ የሚካሄደው በአምስት አካባቢዎች ላይ ነው። እነሱም፦ 🟢 አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ 🟢 ኦሮሚያ ክልል (ቀደም ሲል ዘመቻ ከተካሄደባቸው ከወለጋ ዞኖች በስተቀር)፤ 🟢 ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፤ 🟢 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ናቸው። በሁሉም አካባቢዎች እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ክትባቱን የሚወስዱ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋና አምቦ አካባቢዎች ግን በተለየ ሁኔታ እስከ 10 ዓመት እድሜ ያሉ ህጻናት እንደሚከተቡ አቶ መስፍን ገልጸዋል። በመደበኛ የክትባት መርሃ ግብር ክትባታቸውን የወሰዱ ህጻናትም ቢሆኑ፣ ወረርሽኝ ሲከሰት የመከላከል አቅማቸውን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ በዘመቻው ላይ ተጨማሪ ክትባት መውሰድ እንዳለባቸው አቶ መስፍን አስገንዝበዋል። አሰጣጡ እንዴት ይከናወናል? ክትባቱ የሚሰጠው #ቤት_ለቤት በመሄድ ሲሆን፣ በሁለት ዙር ተከፍሎ ይካሄዳል። "የመጀመሪያው ዙር አራት ቀን ይቆያል፤ ከዚያ ከአንድ ወር በኋላ ሁለተኛው ዙር በሚታወጀው ቀን የሚካሄድ ይሆናል" ሲሉ ዶክተር ክንፉ የአሰጣጥ ሂደቱን አብራርተዋል። ከዚህ ቀደም በዘመቻ ወቅት ይሰጥ የነበረው ሁለት ጠብታ ብቻ እንደነበር ያስታወሱት አቶ መስፍን፣ አሁን ግን ሦስቱንም የፖሊዮ ቫይረስ ዝርያዎች ሙሉ በሙሉ ለመከላከል ሲባል ከሁለት የተለያዩ ክትባቶች ሁለት ሁለት ጠብታ (በድምሩ አራት ጠብታ) እንደሚሰጥ አብራርተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ህጻናት በግራ እጃቸው ትንሿ ጣት ጥፍር ላይ ምልክት (Finger mark) የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ቤቶችም ላይ ምልክት ይደረጋል። የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት፣ ከዓለም አቀፍ የፖሊዮ ማጥፋት ፕሮግራም እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። እስካሁን ክትባቶችን እና የክትባቱን ቅዝቃዜ ጠብቀው የሚያቆዩ ቁሳቁሶችን (Cold chain) ወደ ክልሎችና ዞኖች የማሰራጨት ሥራ ተሠርቷል። በተጨማሪም ክትባቱን ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል። ወደ ሀገር ውስጥ የገባው ክትባት በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (EFDA) ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ መሆኑን እና በህጻናት ላይ ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያስከትል ባለሙያው አረጋግጠዋል። የክትባት ባለሙያዎች ቤት ለቤት ስለሚመጡ ወላጆች ህጻናትን ቤት ውስጥ በማቆየት እንዲያስከትቡ አቶ መስፍን አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም @TikvahethMagazine
Открыть в Telegramየጥንት የጠዋቱ ዘነበ ፍሬው ሪል እስቴት በአዲስ መልክ ጎተራ ላይ ከ Addis Tomorrow economic zone ኘሮጀክት ፊትለፊት በ 7000 ካሬ ላይ የሚገነባ G+25 የሆነ ኘሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል! ይህ ኘሮጀክት በውስጡ ቤቶች ከስቱዲዮ እስከ ባለ 3 መኝታ ያካተተ ሲሆን :- ስቱዲዮ 66 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 6,303,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 630,300 ብር 100% ለሚከፍል - 4,727,250 ብር ባለ 1 መኝታ 83 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 7,926,500 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 792,650 ብር 100% ለሚከፍል - 5,944,875 ብር ባለ 2 መኝታ 122 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 11,651,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 1,165,100 ብር 100% ለሚከፍል - 8,738,250 ብር ባለ 3 መኝታ 168 ካሬ ሙሉ ዋጋ - 16,044,000 ብር ቅድመ ክፍያ (10%) - 1,604,400 ብር 100% ለሚከፍል - 12,033,000 ብር ፕሮጀክቱ ለኑሮ ምቹ የሆነ በርከት ያሉ መገልገያዎች የያዙ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ እና በአካል ለመጎብኘት በ 0906926956 ይደውሉልን! ቴሌግራም:- @Realeastateaddis
Открыть в Telegram🌅 በ1%ወርሃዊ ክፍያ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ! 🌴🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ🌴🌴 የንግድ ሱቅ ከታዋቂው ቴምር ሪል እስቴት 👉ገንብተን ማስረከብ ጥያቄ አይሆንብንም ከ10 በላይ አፓርትመንት እና ሱቆችን ጥንቅቅ አርገን አስረክበናል!! 👉አሁን ደግሞ ሳር ቤት አደባባዩ ፊት ለፊት እና አፍሪካ ህብረት በ ቡልጋሪያ ላይ ሱቆችን አውጥተናል። ▪️ግራውንድ ፍሎር –10 ሜ² 3,200,000 ብር ▪️ 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 3,568,000 ብር ▪️ 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 2,625,000 ብር ▪️ 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²፡ 2,635,000 ብር ▪️ 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²፡ 2,660,000 ብር ▪️ 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²፡ 2,600,000 ብር ** አከፋፈል 👉ቅድመ ክፍያ 25% 👉ለ2 አመት ለ24 ወር በየወሩ 1%=24% 👉ስትራክቸር ሲያልቅ 10% 👉ሴራሚክ ስራ ሲያልቅ 10% 👉አልሙኒየም ስራ ሲያልቅ 10% 👉ሱቁን ሲረከቡ 21% *100% ለሚከፍሉ የ 30% ቅናሽ - ግራውንድ ወለል – 10 ሜ²: 2,240,000 ብር - 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 2,497,600 ብር - 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 1,837,500 ብር - 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²: 1,844,500 ብር - 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²: 1,862,000 ብር - 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²: 1,820,000 ብር እንዲሁም ከተጠቀሱት ካሬ አማራጮች ውጪ ካሬ አማራጮች አሉን ይደውሉልን። +251980782850 ቴምር ሪል እስቴት
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
TIKVAH-ETHIOPIA@tikvahethiopiaНовости и СМИ1,62 млн
Fana Media Corporation S.C (FMC)@fanatelevisionНовости и СМИ203 тыс.
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®@esat_tv1Новости и СМИ204 тыс.
Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ@ayuzehabeshanewsНовости и СМИ259 тыс.
YeneTube@yenetubeНовости и СМИ143 тыс.
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ@sputnik_ethiopiaНовости и СМИ50,8 тыс.
4-3-3 World News@ethionews433Новости и СМИ49,7 тыс.
ቀዳሚ ዜና@kedami_newsНовости и СМИ28,4 тыс.
Кто упоминает
TIKVAH-ETHIOPIA@tikvahethiopia2 упоминанияПоследний пост